Ethiopia



ለ”ሔር ኢሴ” የተሰጠውን እውቅና የኢሳ ጎሳዎች ኡጋዝ በድሬደዋ ተረከቡ

በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ውስጥ የሰፈረው፣ “ሔር ኢሴ” የተሰኘው በኢት

በወራ ጃርሶ ወረዳ ቡና ለመጠጣት የተሰባሰቡ ሰዎች በፍንዳታ መጎዳታቸውን ቤተሰቦች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወራ ጃርሶ ወረዳ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል ተባብሶ በቀጠለው ግጭትና የተኩስ ል
የአሜሪካ ድምፅ

በወራ ጃርሶ ወረዳ ቡና ለመጠጣት የተሰባሰቡ ሰዎች በፍንዳታ መጎዳታቸውን ቤተሰቦች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወራ ጃርሶ ወረዳ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል ተባብሶ በቀጠለው ግጭትና የተኩስ ልውውጥ ምክኒያት፣ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን የተጎጂ ቤተሰብ እና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። የተጎጂ ቤተሰብ አባል መኾናቸውን የገለጹ ግለሰብ ፣ ከቤታቸው ደጃፋ በሚገኝ ዛፍ ጥላ ስር ኾነው ቡና በመጠጣት ላይ የነበሩ ሰዎች እና ሕፃናት ጭምር ከርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ ፍንጣሪ መገደላቸውን ተናግረዋል። በወረዳው ደረሰ በተባለው ጉዳት ዙሪያ ከክልሉ ባለሥልጣናት ጀምሮ እስከ ወረዳው ድረስ የሚመለከታቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ለማነጋገር የአሜሪካ ድምፅ ያደረገው ጥረት ባለ ሥልጣናቱ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ምክንያት ሊሳካ አልቻለም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በአማራ ክልል በመንግሥት አስተባባሪነት የተጠራ ነው የተባለ ሰልፍ ተካሄደ

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች በክልሉ መንግሥት ቀስቃሽነት የተዘጋጀ ነው የተባለ፣ ሰላምን የሚጠይቅ ሰልፍ ተካሄደ። ደሴ ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ያገኘና
የአሜሪካ ድምፅ

በአማራ ክልል በመንግሥት አስተባባሪነት የተጠራ ነው የተባለ ሰልፍ ተካሄደ

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች በክልሉ መንግሥት ቀስቃሽነት የተዘጋጀ ነው የተባለ፣ ሰላምን የሚጠይቅ ሰልፍ ተካሄደ። ደሴ ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ያገኘናቸው ተሳታፊዎች፣ ክልሉ ከግጭት እንዲወጣና ሰላም እንዲመጣ የሚጠይቅ ሐሳብ በሰልፉ ላይ ማንፀባረቃቸውን ተናግረዋል። በሌላ በኩል ሰልፍ የወጡት በአስገዳጅነት መኾኑን የተናገሩ አንድ የወልድያ ከተማ ነዋሪ፣ “መንግሥት ነዋሪዎች በፈቃዳቸው ሰልፍ እንዲወጡ ቢፈቅድና ትክክለኛውን የሕዝብ ስሜት ቢያዳምጥ ተገቢ ይኾን ነበር” ብለዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሞዛምቢክ ጋዜጠኞች ሐሰተኛ መረጃን ለመዋጋት ጥረታቸውን አጠናቅረው ቀጥለዋል

በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሐሰተኛ መረጃ መስፋፋቱን ተከትሎ፣ በሞዛምቢክ  የሚገኙ ጋዜጠኞች ኾን ተብለውም ሆነ ባለማወቅ የሚጋሩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመዋጋት ግን
የአሜሪካ ድምፅ

በሞዛምቢክ ጋዜጠኞች ሐሰተኛ መረጃን ለመዋጋት ጥረታቸውን አጠናቅረው ቀጥለዋል

በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሐሰተኛ መረጃ መስፋፋቱን ተከትሎ፣ በሞዛምቢክ  የሚገኙ ጋዜጠኞች ኾን ተብለውም ሆነ ባለማወቅ የሚጋሩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመዋጋት ግንባር ቀደም ኾዋል። አማሪሊስ ጉሌ በዚህ ዙሪያ ከማፑቶ ያደረሰንን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ትላልቆቹ የኒው ዮርክ መደብሮች ምዕተ ዓመት ያስቆጠረውን የበዓል ገበያተኛ መሳቢያ ዘዴ ያልተውት ስለምን ይኾን?

ከአንድ መቶ ዓመት በላይ ባስቆጠረው ገበያተኛ መሳቢያ መንገድ ዝነኞቹ የኒው ዮርክ ከተማ መደብሮች በየዓመቱ፣ መስኮቶቻቸውን ከበዓሉ ጋራ በተያያዙ ነገሮች አ
የአሜሪካ ድምፅ

ትላልቆቹ የኒው ዮርክ መደብሮች ምዕተ ዓመት ያስቆጠረውን የበዓል ገበያተኛ መሳቢያ ዘዴ ያልተውት ስለምን ይኾን?

ከአንድ መቶ ዓመት በላይ ባስቆጠረው ገበያተኛ መሳቢያ መንገድ ዝነኞቹ የኒው ዮርክ ከተማ መደብሮች በየዓመቱ፣ መስኮቶቻቸውን ከበዓሉ ጋራ በተያያዙ ነገሮች አስውበው ለአላፊ አግዳሚው እይታ ያቀርባሉ። የቪኦኤ ዘጋቢ ዶራ መህኩዋር ይኽ የቆየ የገበያተኛ መጥሪያ ስልት እስከ አኹን እንደዘለቀ ቃኝታ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ቅዳሜ ታኅሣስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሀገሪቱ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች አስታውቀዋል።
የአሜሪካ ድምፅ

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ቅዳሜ ታኅሣስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሀገሪቱ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች አስታውቀዋል። ፕሬዝደንቱ በዋነኛነት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ በመኾን፣ በሀገራቸው መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ የታደሰውንና አዲስ አበባ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ወይም ኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት መርቀው እንደሚከፍቱም ጠቅሰዋል። የፈረንሳዩ መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያካሂዱም እነዚሁ ምንጮች አመልክተዋል። ምንጮቹ እንደጠቀሱት፣ ሁለቱ መሪዎች በቅድሚያ የሚወያዩት፣ በዚኽ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል በቱርክ በተፈረመው የአንካራ ስምምነት ላይ ነው። ፕሬዝደንት ማክሮን ስምምነቱን እንደሚቀበሉት በመግለጽ፣ ድጋፋቸውን እንደሚያሳዩም ዲፕሎማሲያዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል። ፕሬዝደንቱ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በተመለከተ እንደሚነጋገሩና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከሚታዩ ግጭቶች አንጻርም ተመሳሳይ የሰላም መፍትሔዎችን እንደሚያበረታቱ ምንጮቹ አስረድተዋል። ፈረንሳይ ቅዳሜ እንደሚመረቅ ለሚጠበቀው የብሔራዊ ቤተ መንግሥት እድሳት የ25 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጓን የፈረንሳይ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች ተናግረዋል።  ቤተ መንግሥቱ የቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ የብር ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ በ1948 ዓ.ም. የተገነባ ነው።

በሞዛምቢክ አውሎ ነፋስ የሞቱት ቁጥር ወደ 45 አሻቀበ

በሞዛምቢክ በተከሰተው ከፍተኛ አውሎ ነፋስና ዝናብ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 45 ማሻቀቡ ተነግሯል። ባለፈው እሑድ የሰሜን ሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ ክፍለ ግዛትን በ
የአሜሪካ ድምፅ

በሞዛምቢክ አውሎ ነፋስ የሞቱት ቁጥር ወደ 45 አሻቀበ

በሞዛምቢክ በተከሰተው ከፍተኛ አውሎ ነፋስና ዝናብ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 45 ማሻቀቡ ተነግሯል። ባለፈው እሑድ የሰሜን ሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ ክፍለ ግዛትን በመታው አውሎ ነፋስ እና ዝናም ሠላሳ አራት ሰዎች መሞታቸውን ትላንት ማክሰኞ የወጣው የመጀመሪያው አሃዝ አሳይቶ ነበር፡፡  በአውሎ ነፋሱ 500 የሚኾኑ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ አደጋ መከላከል ባለሥልጣን አስታውቋል። 36 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች መሉ በሙሉ አሊያም  በከፊል ፈርሰዋል። 181 ሺሕ ሰዎች በከፍተኛው አውሎ ነፋሱ ተጠቂ ኾነዋል። የአደጋ መከላከል ማዕከሉ በአወጣው በኋለኛው አሃዝ መሠረት ካቦ ዴልጋዶ ውስጥ  38 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ናምፑላ ክፍለ ሀገር ውስጥ ደግሞ አራት ሰዎች ሞተዋል፡፡ ወደ መሃል ሀገር ገባ ብላ በትምገኘው ኒያሳ ውስጥ ደግሞ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል፡፡  የደረሰበት ያልታወቀ አንድ ሰው መኖሩንም መረጃው አመልክቷል፡፡ በሰዓት 260 ኪ.ሜ. ፍጥነት የነበረው ነፋስና ከፍተኛ ዝናም ቀድሞውንም ግጭትና ደካማ መሠረተ ልማት የነበረውን የሞዛምቢክን ሰሜናዊ ክፍል አጥቅቷል። አውሎ ነፋሱ በሕንድ ውቅያኖስ የምትገኘውን የፈረንሣይ ደሴት ማዮትን ከመታ በኋላ ነበር ወደ ሞዛምቢክ ያቀናው። በማዮት ቢያንስ በመቶ ወይም በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሳይገድል እንዳልቀረ ተሰግቷል።

VOA60 Africa - Ghana: Supreme Court rejects legal challenges to anti-LGBT legislation

Ghana: The Supreme Court Wednesday rejected two separate legal challenges to Africa's most restrictive anti-LGBT legislation, paving the way for President Nana Akufo-Addo to sign it into law. He had delayed doing so pending the court’s decision.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Ghana: Supreme Court rejects legal challenges to anti-LGBT legislation

Ghana: The Supreme Court Wednesday rejected two separate legal challenges to Africa's most restrictive anti-LGBT legislation, paving the way for President Nana Akufo-Addo to sign it into law. He had delayed doing so pending the court’s decision.

VOA60 America - Return to Earth for 2 stuck NASA astronauts delayed until March

NASA's two astronauts stuck at the International Space Station, Butch Wilmore and Suni Williams, will not return until the end of March or even April because of a delay in launching their replacements, according to NASA.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Return to Earth for 2 stuck NASA astronauts delayed until March

NASA's two astronauts stuck at the International Space Station, Butch Wilmore and Suni Williams, will not return until the end of March or even April because of a delay in launching their replacements, according to NASA.

VOA60 World - Relief operations intensified on French territory of Mayotte following deadly cyclone

Mayotte: Relief operations intensified on Wednesday, as 120 tons of food arrived at the airport for distribution following Cyclone Chido, the worst storm to hit the French overseas territory in 90 years. The death toll remains unclear, with only 22 fatalitie
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Relief operations intensified on French territory of Mayotte following deadly cyclone

Mayotte: Relief operations intensified on Wednesday, as 120 tons of food arrived at the airport for distribution following Cyclone Chido, the worst storm to hit the French overseas territory in 90 years. The death toll remains unclear, with only 22 fatalities confirmed in hospitals so far.

የጋና ጋዜጠኞች የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እየሠሩ ነው

በጋና ሆን ተብለውም ኾነ ባለማወቅ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች በከፍተኛ መጠን ጨምረዋል። በመኾኑም አንዳንድ ጋዜጠኞች ትክክለኛ ዘገባዎችን በመሥራት ሐሰተኛ
የአሜሪካ ድምፅ

የጋና ጋዜጠኞች የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እየሠሩ ነው

በጋና ሆን ተብለውም ኾነ ባለማወቅ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች በከፍተኛ መጠን ጨምረዋል። በመኾኑም አንዳንድ ጋዜጠኞች ትክክለኛ ዘገባዎችን በመሥራት ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመዋጋት ተስፋ ያደርጋሉ። አይዛክ ካልዲዚ ከጋና ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የውጭ ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ዐዋጅ ጸደቀ

የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው “የባንክ ሥራ ረቂቅ ዐዋጅ” በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል። ውሳኔው የሀገር ውስጥ ባ
የአሜሪካ ድምፅ

የውጭ ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ዐዋጅ ጸደቀ

የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው “የባንክ ሥራ ረቂቅ ዐዋጅ” በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል። ውሳኔው የሀገር ውስጥ ባንኮችን ከውድድር ውጭ በማድረግ ከዘርፉ ሊያስወጣቸው እንደሚችል የምክር ቤቱ አባላት ስጋታቸውን አንፀባርቀዋል። የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በሰጡት ምላሽ፣ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ እንዲሠሩ መፈቀዱ የሀገር ውስጥ ባንኮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አይኖረውም ብለዋል፡፡ የምጣኔ ሀብት  ጉዳዮች ተንታኝ ዶ/ር አብዱል መናን መሐመድም፣ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረግ፣ ለሀገር ውስጥ ባንኮች ስጋት አይኾንም ይላሉ፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ካሳ እና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው መኖሪያ ቤታቸው እየፈረሰ መኾኑን የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ

በአዲስ አበባ፣ የካ ክፍለ ከተማ የሚኖሩና ቤታቸው እየፈረሰባቸው እንደሚገኝ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩ ነዋሪዎች፣ ቤታቸው ከመፍረሱ በፊት፣ መንግሥት ቃል ገብ
የአሜሪካ ድምፅ

ካሳ እና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው መኖሪያ ቤታቸው እየፈረሰ መኾኑን የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ

በአዲስ አበባ፣ የካ ክፍለ ከተማ የሚኖሩና ቤታቸው እየፈረሰባቸው እንደሚገኝ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩ ነዋሪዎች፣ ቤታቸው ከመፍረሱ በፊት፣ መንግሥት ቃል ገብቶላቸው የነበረው የሁለት ዓመት የቤት ኪራይ ክፍያ እንዳልተፈፀመላቸው፣ ምትክ ቦታም እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል። በወንዝ ዳር ልማት ምክንያት፣ ቤታቸው እየፈረሰ እንደሚገኝ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ወደየ ዘመዶቻቸው እንዲጠጉ አሊያም ተከራይተው እንዲኖሩ መፍትሔ ከጠየቋቸው ኃላፊዎች እንደተነገራቸው ተናግረዋል። “ከተማችን እንድትቀየር እንፈልጋለን፣ ልማቱንም እንደግፋለን” በማለት የተናገሩት አስተያየት ሰጭዎቹ፣ ኾኖም መንግሥት ቅድሚያ ማረፊያ እንዲያዘጋጅላቸው፣ ጊዜም እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ስለ ጉዳዩ ምላሽ የሰጠው ክፍለ ከተማው በበኩሉ፣ ለልማት ተነሺዎቹ ምትክ ቦታ መስጠቱን እና የካሳ ክፍያ ለመፈፀምም እየሠራ መኾኑን ገልጿል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሂዩማን ራይትስ ዋች የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኅይሎችን ሴቶችን በመድፈር ወንጀል ከሰሰ

የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ተዋጊዎች እና ተባባሪ ታጣቂዎች፣ ደቡባዊ ኮርዶፋን ክፍለ ግዛት ውስጥ አዋቂ ሴቶች እና ልጃገረዶችን ደፍረዋል፣ ሌሎችም ወሲባዊ
የአሜሪካ ድምፅ

ሂዩማን ራይትስ ዋች የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኅይሎችን ሴቶችን በመድፈር ወንጀል ከሰሰ

የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ተዋጊዎች እና ተባባሪ ታጣቂዎች፣ ደቡባዊ ኮርዶፋን ክፍለ ግዛት ውስጥ አዋቂ ሴቶች እና ልጃገረዶችን ደፍረዋል፣ ሌሎችም ወሲባዊ ጥቃቶችን ፈጽመዋል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች ከሰሰ። በታጣቂዎቹ የተፈጸመው ጥቃት የጦር ወንጀል መኾኑን አመልክቷል። የሰብአዊ መብት ቡድኑ በማያያዝ አድራጎቱ የሱዳንን ሲቪሎች ከጥቃት የሚጠብቅ እና ሰለባዎቹም ፍትሕ እንዲያገኙ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ርምጃ በአስቸኳይ መወሰድ እንዳለበት አጥብቆ የሚያሳስብ መኾኑን አመልክቷል። መሐመድ ዩሱፍ ለቪኦኤ ከናይሮቢ ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

ዩክሬይን ሞስኮ ውስጥ የሩስያን ጄኔራል ለገደለው የቦምብ ፍንዳታ ኃላፊነት ወሰደች

የሩስያ የኑክሌር ባዮሎጅካዊ እና ኬሚካል መከላከያ ኃይል ዘርፍ አዛዥ የነበሩት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ዛሬ ማክሰኞ ሞስኮ ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ተገድለ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩክሬይን ሞስኮ ውስጥ የሩስያን ጄኔራል ለገደለው የቦምብ ፍንዳታ ኃላፊነት ወሰደች

የሩስያ የኑክሌር ባዮሎጅካዊ እና ኬሚካል መከላከያ ኃይል ዘርፍ አዛዥ የነበሩት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ዛሬ ማክሰኞ ሞስኮ ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ተገድለዋል፡፡ ዩክሬን ጄኔራሉን በሚኖሩበት ሕንጻ ደጃፍ መንገድ ላይ በቆመ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ (ስኩተር) ላይ እንዳይታይ ተደርጎ በተጠመደ ቦምብ መግደሏን አስታውቃለች፡፡ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ እና ረዳታቸው የተገደሉት በደቡብ ምስራቅ ሞስኮ ከሚገኘው መኖሪያቸው ወደ ሥራ ለመሄድ እየወጡ በነበረበት ወቅት መሆኑን የሩሲያ የምርመራ ቡድን አስታውቋል፡፡ ፍንዳታው ከተፈፀመበት ቦታ የወጣው ቪዲዮ የተቃጠለ የህንጻው የፊት ለፊት ገጽታ፣ የተሰባበሩ ጡቦች እና መስኮቶችን ያሳያል። የቦምብ ጥቃቱ የደረሰው ኪሪሎቭን ለሦስት አመታት በዘለቀው ጦርነት የሩስያ ሃይሎች በዩክሬን ላይ ተጠቅመውታል በተባለው የኬሚካል ጦር መሣሪያ እጃቸው አለበት በሚል የዩክሬን አቃቤ ሕግ ክስ ከመሰረተባቸው ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑ ነው። ብሪታንያን እና ካናዳን ጨምሮ በርካታ ሀገሮች ኪሪሎቭን በጦርነቱ ከነበራቸው ሚና ጋራ በተያያዘ ባለፈው ጥቅምት ማዕቀብ ጥለውባቸው ነበር፡፡ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የዩክሬን የደኅንነት አገልግሎት ባለሥልጣን ከጥቃቱ ጀርባ ኤጀንሲው እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ ባለሥልጣኑ ኪሪሎቭን “የጦር ወንጀለኛው ሙሉ በሙሉ ሕጋዊ ኢላማ” ነበር ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የሩሲያ የዜና ማሰራጫዎች ቦምቡ በርቀት መቆጣጠሪያ እንደፈነዳ ዘግበዋል፡፡ ዋናው የሩሲያ መንግሥት የምርመራ ተቋም በበኩሉ የጄኔራል ኪሪሎቭን ሞት የሽብርተኝነት ምርመራ የከፈተበት መሆኑን አስታውቋል፡፡ የሩሲያ ባለሥልጣናት «ዩክሬንን እንቀጣታለን» ሲሉ ዝተዋል፡፡

ተመድ ለሦሪያውያን የሚደረገው የሰብአዊ ርዳታ እንደሚጨምር ተስፋ አድርጓል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሦሪያውያን ሰብአዊ ርዳታ ለማስገባት ተስፋ እንዳለው የድርጅቱ ባለሥልጣናት ዛሬ ማክሰኞ ተናግረዋል፡፡ የአውሮፓ ሀገራት በ
የአሜሪካ ድምፅ

ተመድ ለሦሪያውያን የሚደረገው የሰብአዊ ርዳታ እንደሚጨምር ተስፋ አድርጓል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሦሪያውያን ሰብአዊ ርዳታ ለማስገባት ተስፋ እንዳለው የድርጅቱ ባለሥልጣናት ዛሬ ማክሰኞ ተናግረዋል፡፡ የአውሮፓ ሀገራት በበኩላቸው ለበርካታ ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆዩትን ፕረዝደንት ባሻር አል አሳድን ካስወገዱት አማጺያን ጋራ የሚያደርጉትን ንግግር ቀጥለዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ኃላፊ ቶም ፍሌቸር ከአማፂያኑ መሪ አህመድ አል ሻራ ጋራ “ገንቢ ውይይት” ማድረጋቸውን ገልጸው ይህም “ወሳኝ የኾኑ የሰብአዊ ድጋፎችን መጠን ለማሳደግ የሚያመቻች መሠረት ይሆናል” ብለዋል ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴረዥ፣ በበኩላቸው በሦሪያ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ባሻር የሚመራው መንግሥት የሰብአዊ ረድኤት ሠራተኞችን ለመጠበቅ፣ የሰብአዊ ርዳታ አገልግሎቶች በሁሉም ድንበሮች በኩል እንዲገቡ ለማስቻል እና ለሰብአዊ ረድኤት ሠራተኞች ፈቃድ እና ቪዛ ለማፋጠን የገባውን ቃል በደስታ መቀበላቸውን ተናግረዋል። በሦሪያ የፈረንሳይ ልዩ መልዕክተኛ ዣን ፍራንሲስ ጊላሜ ዛሬ ማክሰኞ ሦሪያን በጎበኙበት ወቅት «ፈረንሳይ በሽግግራቸው ወቅት ከሶሪያውያን ጋራ ለመኾን በዝግጅት ላይ ነች» ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የፈረንሳዩ ልዩ መልዕክተኛ ሽግግሩን ከሚመሩት ጋራ ለመወያየት በቅርቡ ወደ ሦሪያ ከሄዱት ልዑካን መካከል አንዱ ናቸው። የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ዲፕሎማቶቹ በደማስቆ ከአማፂያን መሪዎች ጋራ ዛሬ የመጀመሪያውን ውይይት እንደሚያደርጉ ገልጿል። የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ካያ ካላስ በበኩላቸው ኅብረቱ ለሶሪያ የሚያደርገውን ሰብአዊ ርዳታ እያጠናከረ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ የሦሪያን «የዲሞክራሲ ምኞት» እንዴት እንደሚደግፍ ኅብረቱ እያጤነ መኾኑንም የውጭ ፖሊሲ ኃላፊዋ ተናግረዋል።

እስራኤል ከጦርነቱ በኋላ የጋዛን ጸጥታ ለመቆጣጠር ሐሳብ እንዳላት አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር፣ «እስራኤል ካትዝ  ሃገራቸው ከሃማስ ጋራ የምታካሂደውን ጦርነት ካጠናቀቀች በኋላም የአካባቢውን ደኅንነት ትቆጣጠራለች&raqu
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል ከጦርነቱ በኋላ የጋዛን ጸጥታ ለመቆጣጠር ሐሳብ እንዳላት አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር፣ «እስራኤል ካትዝ  ሃገራቸው ከሃማስ ጋራ የምታካሂደውን ጦርነት ካጠናቀቀች በኋላም የአካባቢውን ደኅንነት ትቆጣጠራለች» ብለዋል፡፡ የመከላከያ ሚንስትሩ ዛሬ ማክሰኞ በX ማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባወጡት ጹሑፍ  «የሃማስን ወታደራዊ እና የመንግሥት አቅም  ካስወገደች በኋላ እስራኤል ጋዛ ላይ የፀጥታ ቁጥጥር ለማድረግ ሙሉ በሙሉ የመንቀሳቀስ ነፃነት ታገኛለች» ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ጋዛን በሚመለከት ያላቸውን ሐሳብ  በዌስት ባንክ ይዞታዎቿ ወታደሮቿ  የሽብርተኞችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር  ከሚያደርጉት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጋራ አመሳስለውታል፡፡ ይህ የእስራኤል ጋዛን የመቆጣጠር ፍላጎት ግን ከጦርነት በኋላ ሊኖር በሚገባው ሁኔታ ላይ አሜሪካና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ ሌሎች ካላቸው ምልከታ ጋራ ይጻረራል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በጥቅምት ወር ሲናገሩ የጋዛ ጦርነት መቆም «ሀማስ እንደሚወጣ  እስራኤልም እንደማትቆይ በሚያረጋግጥ መንገድ» መኾን እንዳለበት አሳስበዋል፡ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ በበኩላቸው    ድርጅታቸው አንዳንድ የዌስት ባንክን አካባቢዎች የሚያስተዳድረው የፍልስጤም አስተዳደር ጋዛንም ይቆጣጠራል ብለው እንደሚገምት ባለፈው መስከረም ተናግረዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋዛ የጤና ኃላፊዎች እስራኤል ዛሬ ባደረሰችው ጥቃት ዐስር ሰዎች መገደላቸውን አስታውቀዋል፡፡ የእስራኤል ጦር በበኩሉ በደቡባዊ ጋዛ ባካሄደው ወታደራዊ ጥቃት ላይ ሁለት ወታደሮቹ መገደላቸውን አስታውቋል፡፡

በጋምቤላ አንድ ባለሀብት እና አሽከርካሪያቸው በሙርሌ ታጣቂዎች መገደላቸውን ክልሉ አስታወቀ

በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ገዱ በተባለ ቀበሌ፣ በወርቅ ማዕድን ሥራ ላይ ለመሰማራት ቦታ መረጣ ላይ የነበሩ አቶ ሰለሞን ጋሻው የተባሉ ባለሀብት ከእነ ሾፌራቸው
የአሜሪካ ድምፅ

በጋምቤላ አንድ ባለሀብት እና አሽከርካሪያቸው በሙርሌ ታጣቂዎች መገደላቸውን ክልሉ አስታወቀ

በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ገዱ በተባለ ቀበሌ፣ በወርቅ ማዕድን ሥራ ላይ ለመሰማራት ቦታ መረጣ ላይ የነበሩ አቶ ሰለሞን ጋሻው የተባሉ ባለሀብት ከእነ ሾፌራቸውን መገደላቸውን፣ በወረዳው የውሀ እና ማዕድን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አጁሉ ሉት ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል። ስለ ጉዳዩ ከቪኦኤ የተጠየቁት በደቡብ ሱዳን ታላቁ ፒቦር አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ጎላ ቦዮኢ ስለ ጉዳዩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለና በማያውቁት ጉዳይ ላይም መረጃ መስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

ፍርድ ቤት በሽብር ተከሳሾች ላይ ምስክርነት መስማት ጀመረ

በእነዶር. ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ፣ የሽብር ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች፣ ላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸው ሦስት ምስክሮች ቃል በፍርድ ቤት ተሰማ። ዐቃቤ ሕግ
የአሜሪካ ድምፅ

ፍርድ ቤት በሽብር ተከሳሾች ላይ ምስክርነት መስማት ጀመረ

በእነዶር. ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ፣ የሽብር ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች፣ ላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸው ሦስት ምስክሮች ቃል በፍርድ ቤት ተሰማ። ዐቃቤ ሕግ አሉኝ ካላቸው 96 ምስክሮች ውስጥ አምስቱን አቅርቦ፣ ከ51 ተከሳሾች ውስጥ በሦስቱ ላይ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። በሌላ ዜና፣ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለው ዛሬ በቀጠሮአቸው መሰረት ሆስፒታል ሔደው ተጨማሪ ምርመራ እንደተደረገላቸው ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

አዲሱ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር መጠነ ሰፊ ፈተናዎች ይጠብቋቸዋል

አዲሱ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍራንሷ ባይሩ ሀገራቸው በአያሌ ችግሮች እየተፈተነች ባለችበት በዚህ ወቅት  ሥራቸውን ጀምረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በዚ
የአሜሪካ ድምፅ

አዲሱ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር መጠነ ሰፊ ፈተናዎች ይጠብቋቸዋል

አዲሱ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍራንሷ ባይሩ ሀገራቸው በአያሌ ችግሮች እየተፈተነች ባለችበት በዚህ ወቅት  ሥራቸውን ጀምረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በዚህ ሳምንት አዲሱን ካቢኔያቸውን ያቋቁማሉ፡፡የሽግግር በጀት እንዲመደብ የቀረበው ረቂቅ ህግ እንዲጸድቅ ግፊት ያደርጋሉ፡፡ ሀገሪቱን ከገባችበትን የበጀት አረንቋ  ለማውጣት የሚያግዝ የረዥም ጊዜ በጀት ለሚመድበው ሕግ ድጋፍ ለማሰባሰብ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ከሳቸው በፊት ለነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ውድቀት ምክንያት ይህ እንደመሆኑ  ፈታኝ እንደሚሆንባቸው ተመልክቷል፡፡ የ73 ዓመቱ አንጋፋ ፖለቲከኛ በደቡብ ምዕራብ ፓው ከተማ የረዥም ጊዜ ከንቲባ የነበሩ እና  ለዘብተኛ አቋም ያላቸው ሲሆኑ በርካታ ሥራዎች እና ፈተናዎች ይጠብቋቸዋል፡፡ ባለፈው ዓርብ ፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮን  የሾሟቸው ፍራንሷ ባይሩ በዚህ ዓመት የተሾሙ  አራተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው ፡፡ ባይሩ  እጅግ የተከፋፈለ በሆነው የሕግ መምሪያው ምክር ቤት የኃይለኞቹ  ግራ እና ቀኝ ዘመም ጎራዎች ከባድ  ጭቅጭቅ ይጠብቃቸዋል፡፡ ባለፉት ወራት  ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የግብርና ምርቶች፣ በሠራተኛ ጉዳዮች እና  በሌሎችም ችግሮች  ቅሬታ ለማሰማት አርሶ አደሮች፣ መምህራን፣ የሆስፒታል እና የባቡር ሠራተኞች ጨምሮ  በሺዎች የሚቆጠሩ  ሰዎች አደባባይ ወጥተዋል። የፈረንሳይ አለመረጋጋት አስቀድሞም  ሩስያ ዩክሬን ውስጥ  እያስመዘገበችው ባለው ድል እንዲሁም ከመጭው የትረምፕ አስተዳደር ጋር ተያይዞ በአትላንቲክ ተሻጋሪው ግንኙነት ላይ ሊከሰት በሚችለው መፈረካከስ ስጋት ላይ ያለውን የአውሮፓ ሕብረትን አሳስቦታል፡፡ ታዋቂው የፈረንሳይ ለ ሞንድ ጋዜጣ አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ባይሩ “ከሌሎቹ ለረዘመ ጊዜ እንደሚቆዩ  ወይም የተሻለ ስኬት እንደሚያገኙ የሚጠቁም ምንም ነገር የለም” ሲል በርዕሰ አንቀጹ አስነብቧል፡፡

ትረምፕ የዋጋ ንረቱን ለመቀነስ እና ተጨማሪ ነዳጅ ለማውጣት ቃል ገቡ

በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራጮች ትልቅ ቦታ ከሰጧቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ኢኮኖሚው ነበር። የዶናልድ ትረምፕን ወደ ሥልጣን መመለስ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ የዋጋ ንረቱን ለመቀነስ እና ተጨማሪ ነዳጅ ለማውጣት ቃል ገቡ

በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራጮች ትልቅ ቦታ ከሰጧቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ኢኮኖሚው ነበር። የዶናልድ ትረምፕን ወደ ሥልጣን መመለስ የሚጠባበቁ ብዙ አሜሪካዊያን ተመራጩ ፕሬዝደንት ቅድሚያ ከሚሰጧቸው ክንዋኔዎች አንዱ ኢኮኖሚውን ማሻሻል ይሆናል ብለው እንደሚጠብቁ ይናገራሉ። የቪኦኤው ስካት ስተርንስ ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

አዲሱ የፌዴራል ኮሚኒኬሽ ኮሚሽን እጩ ግዙፍ ኩባንያዎችን የሚነቅፉና የቻይና ተጽእኖ የሚያሳስባቸው ናቸው

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የፌዴራል ኮሚኒኬሽ ኮሚሽንን (FCC) እንዲመሩ ብረንዳን ካርን አጭተዋል። ብረንዳን ካር በአሜሪካ ማንኛውንም ኮሚኒኬሽን በሚቆ
የአሜሪካ ድምፅ

አዲሱ የፌዴራል ኮሚኒኬሽ ኮሚሽን እጩ ግዙፍ ኩባንያዎችን የሚነቅፉና የቻይና ተጽእኖ የሚያሳስባቸው ናቸው

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የፌዴራል ኮሚኒኬሽ ኮሚሽንን (FCC) እንዲመሩ ብረንዳን ካርን አጭተዋል። ብረንዳን ካር በአሜሪካ ማንኛውንም ኮሚኒኬሽን በሚቆጣጠረው ኤፍሲሲ ውስጥ ከእ.አ.አ 2017 ጀምሮ በኮሚሽነርነት አገልግለዋል። በቆይታቸውም ከከፍተኛ የቴክኖሎጂ ተቋማት እንዲሁም ከቻይና ተጋርጧል ያሉትን አሉታዊ ተጽእኖ ሲጋፈጡ ቆይተዋል። የቪኦኤዋ ዶራ መክዋር የላከችው ዘገባ ነው። ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

VOA60 World- Hundreds and possibly thousands are feared dead in the French territory of Mayotte after it was hit by Cyclone Chido

French rescue teams, medical personnel and tons of supplies have been sent. The official death toll on Monday morning stood at 14.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World- Hundreds and possibly thousands are feared dead in the French territory of Mayotte after it was hit by Cyclone Chido

French rescue teams, medical personnel and tons of supplies have been sent. The official death toll on Monday morning stood at 14.

በጋዛ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ45 ሺሕ ማለፉን የሀገሩ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

እስራኤል በፍልስጤም ግዛት በሀማስ ታጣቂዎች ላይ ባካሄደችው ጥቃት ከ45 ሺሕ በላይ ሰዎችን ገድላለች ሲል የጋዛ ጤና ሚንስቴር ዛሬ ሰኞ በአወጣው መግለጫ አስታወ
የአሜሪካ ድምፅ

በጋዛ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ45 ሺሕ ማለፉን የሀገሩ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

እስራኤል በፍልስጤም ግዛት በሀማስ ታጣቂዎች ላይ ባካሄደችው ጥቃት ከ45 ሺሕ በላይ ሰዎችን ገድላለች ሲል የጋዛ ጤና ሚንስቴር ዛሬ ሰኞ በአወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ በግጭቱ ወደ 107 ሺሕ የሚጠጉ ሰዎች መቁሰላቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል። አሃዙ ሲቪሎችና እና ተዋጊዎችን ለይቶ አላስቀመጠም። ነገር ግን ቀደም ሲል ሚንስቴሩ በአወጣቸው መግለጫዎች ከተገደሉት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚኾኑት ሴቶች እና ህጻናት መኾናቸውን አስታውቋል፡፡ የጋዛ ጤና ሚንስቴር በዕለታዊ መግለጫው ባለፉት ቀናት 52 ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። የጋዛ የሲቪል መከላከያ እና የሆስፒታል ባለሥልጣናት የትላንቱ ደም አፋሳሽ ጥቃት በሰሜናዊ ጋዛ ከተማ እና በደቡባዊ ጋዛ ካን ዮኒስ እንዲሁም በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው የኑሴራት የስደተኞች ካምፕ የደረሱትን ጥቃቶች እንደሚያካትት አመልክተዋል፡፡ የእስራኤል የጦር ኃይል ትላንት እሁድ በኑሴራት የሀማስን የዕዝ እና ቁጥጥር ማዕከል መምታቱን ተናግሯል። እስራኤል “የሀማስ ታጣቂዎች ፍልስጤማዊያን ሲቪሎች ባሉባቸው አካባቢዎች ይንቀሳቀሳሉ” በማለት በተደጋጋሚ የምትወነጅል  ሲሆን ፍልስጤማውያን እና የመብት ተሟጋቾች በበኩላቸው “የእስራኤል ጦር የሲቪሎችን ሞት ለመከላከል በቂ ሥራ እየሠራ አይደለም” በማለት ይከሳሉ።

ሂዩማን ራይትስ ዋች የሱዳን ታጣቂዎች የጅምላ ጾታዊ ጥቃት ፈጽመዋል ሲል ከሰሰ

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ቡድኖች እና አጋር ሚሊሻዎች 20 ወራት ባለፉት የሱዳን ጦርነት፤ በደቡብ ሱዳን ሴቶች ላይ የጅምላ ጾታዊ ጥቃት ፈጽመዋል ሲል ዓለም አቀፉ የሰብ
የአሜሪካ ድምፅ

ሂዩማን ራይትስ ዋች የሱዳን ታጣቂዎች የጅምላ ጾታዊ ጥቃት ፈጽመዋል ሲል ከሰሰ

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ቡድኖች እና አጋር ሚሊሻዎች 20 ወራት ባለፉት የሱዳን ጦርነት፤ በደቡብ ሱዳን ሴቶች ላይ የጅምላ ጾታዊ ጥቃት ፈጽመዋል ሲል ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ዛሬ ሰኞ በአወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡  የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ቡድን በዐዲሱ ሪፖርቱ ከጎርጎርሳዊያኑ መስከረም 2023 አንስቶ በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት በቡድን መድፈር እና በጾታዊ ባርነት መያዝን ጨምሮ ጾታዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ከሰባት እስከ 50 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ያሉ በርካታ ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ መመዝገቡን አስታውቋል፡፡ ኒውርክ የሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ፣ ባለፈው ሳምንት በአወጣው ሌላ ሪፖርቱ፣ በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት ከጎርጎርሳውያኑ ታኅሣሥ 2023 እስከ መጋቢት 2024 ድረስ ባለው ጊዜ፤ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እና አጋር የአረብ ሚሊሻዎች በተለይም በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት ኑባ ሲቪሎች ላይ ብዙ ጥቃቶችን መፈጸማቸውን በስፋት ዘርዝሯል፡፡ «ጥቃቶቹ በስፋት ያልተዘገቡ» ናቸው ያለው መግለጫው «የጦርነት ወንጀሎች» ናቸው ብሏል፡፡ ባለፈው ጥቅምት የመንግሥታቱ ድርጅት ገለልተኛ ዓለም አቀፍ የሱዳን የሀቅ አጣሪ ተልዕኮ፤ ሁለቱም ወገኖች እንግልትና እና ጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ በርካታ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ገልጿል። «በሱዳን የመዘገብነው ጾታዊ ጥቃት መጠን እጅግ አስደንጋጭ ነው” ሲሉ የመርማሪ ቡድኑ ሰብሳቢ መሀመድ ቻንዴ ኦትማን ተናግረዋል። የፈጥኖ ደራሽ ቡድኑ የተባበሩት መንግሥታት ክትትል ውጤቱን »የማኅበራዊ ሚዲያ ፕሮፓጋንዳ« ሲል ውድቅ አድርጎታል፡፡ በቅርቡም የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ኃላፊ ቶም ፍሌቸር፣ ሱዳን ውስጥ በወረርሽኝ መልክ በስፋት መፈጸሙን የገለጹት ጾታዊ  ጥቃት በሴቶች ላይ ስለደረሰው ጾታዊ ጥቃት ወረርሽኝ ዓለም »የተሻለ ማድረግ አለባት" በማለት ሁኔታው አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቀዋል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዋች ባለፈው ሳምንት ባወጣው የመጀመሪያ ሪፖርቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት “ሱዳን ውስጥ የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት የሚጠብቅ ተልዕኮ በአስቸኳይ እንዲያሰማሩ” አሳስቧል።

የቴክኒክ ችግር ያጋጠመው አውሮፕላን በሰላም ማረፉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ

ወደ ዱባይ ሊጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ ብዙም ሳይቆይ በአጋጠመው የቴክኒክ ችግር ፣ ወደ አዲስ አበባ አየር ማረፊያ መመለ
የአሜሪካ ድምፅ

የቴክኒክ ችግር ያጋጠመው አውሮፕላን በሰላም ማረፉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ

ወደ ዱባይ ሊጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ ብዙም ሳይቆይ በአጋጠመው የቴክኒክ ችግር ፣ ወደ አዲስ አበባ አየር ማረፊያ መመለሱን አየር መንገዱ አስታወቀ። አየር መንገዱ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ በአወጣው አጭር መግለጫ፣ የበረራ ቁጥሩ ET 612 የኾነ አውሮፕላን ታኅሣሥ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ወደ ዱባይ ለሚያደርገው በረራ ከአዲስ አበባ ከተነሳ ከ30 ደቂቃ በኋላ፣ በአጋጠመው የቴክኒክ ችግር፣ አዲስ አበባ ተመልሶ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሰላም ማረፉን አስታውቋል። መንገደኞች እና የበረራ ሠራተኞች ለጥንቃቄ ሲባል በአስቸኳይ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ መደረጉን አስታውቋል። በአፍሪካ ግዙፍ የኾነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በተፈጠረው የቴክኒክ ችግር ምክኒያት መንገደኞቹ ለደረሰባቸው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል። አውሮፕላኑ ስላጋጠመው የቴክኒክ ችግር ጉዳይ እና በአውሮፕላኑ ላይ ተሳፍረው የነበሩት መንገደኞቹ ቁጥር በአየር መንገዱ መግለጫ ላይ በዝርዝር አልሠፈረም።

ባይደን በዩክሬን እና ሶሪያ ጉዳይ ከቡድን 7 ሀገራት ጋር ተነጋገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን  ኪየቭ  ከሩሲያ ጋር እያደረገች ላለችው ውጊያ የሚሆን ድጋፍን ለማረጋገጥ ያለመ የርቀት መገናኛ ስብሰባ ከቡድን 7 መሪ
የአሜሪካ ድምፅ

ባይደን በዩክሬን እና ሶሪያ ጉዳይ ከቡድን 7 ሀገራት ጋር ተነጋገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን  ኪየቭ  ከሩሲያ ጋር እያደረገች ላለችው ውጊያ የሚሆን ድጋፍን ለማረጋገጥ ያለመ የርቀት መገናኛ ስብሰባ ከቡድን 7 መሪዎች ጋር በትናንትናው ዕለት አከናውነዋል። የአሁኑ ስብሰባ የተደረገው ለዩክሬን በሚሰጠው ድጋፍ ዙሪያ ትችት የሚያሰሙት ተመራጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ፣ ስልጣን ሊረከቡ ስድስት ሳምንታት ብቻ በቀሩበት ወቅት ነው።  የአሁኑ ንግግር የዓለም ባንክ የዩክሬንን ኢኮኖሚ ለመደጎም ለዘረጋው መርሀ ግብር የሚሆን 20 ቢሊየን ዶላር  ዩናይትድ ስቴትስ ከሰጠች በኃላ የተከናወነ ነው።ገንዘቡ ከቡድን 7 ዲሞክራሲያዊ አገሮች የተገኘ አዲስ ለኪየቭ የሚሰጠው  50 ቢሊዮን ዶላር ብድር አካል ነው ። ገንዘቡ በቡድን ሰባት ሀገራት ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ  ሩሲያ ሉዓላዊ ንብረቶች ከሚገኝ  የወለድ ገቢ የሚከፈል ነው። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ባይደን  ለኪየቭ ተጨማሪ የአየር መከላከያ ፣መድፍ ፣ድሮኖች እና የጦር ተሽከርካሪዎችን የሚሆን  አዲስ የደህንነት ድጋፍ አፅድቀዋል።ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች ወዲህ ዋሺንግተን ይፋ ያደረገችው 72ኛ  ጥቅል ድጋፍ ነው ። በአውሮፓዊያኑ ጥር 20 ባይደን  የአሜሪካ ቀረጥ ከፋዮች ገንዘብ ኪቭን ለመርዳት ውሏል በሚል ወቀሳ ሲያሰሙ ለሰነበቱት ትራምፕ ስልጣን ያስረክባሉ ።ስለ ዕቀዳቸው በዝርዝር ባያስረዱም ፣ ትራምፕ በፍጥነት ጦርነቱን አስቆማለሁ እያሉ ሲናገሩ ተሰምተዋል ።ይህ ንግግራቸው ዩክሬን እጅ እንድትሰጥ የማስገደድ ትርጉም አለው በሚል ብዙ አውሮፓዊያን  ያሰጋሉ።   የቡድን 7 ሀገራት መሪዎች የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን ከስልጣን መውረድ ተከትሎ በሶሪያ ከተካሄደው ወሳኝ የስልጣን ሽግግር ጋር በተያያዙ ፈጣን ሽግግሮች  ላይም ትኩረት አድርገዋል። ሐሙስ ዕለት መሪዎቹ በሶሪያ ውስጥ "ተዓማኒነት ያለው፣ አካታች እና ወደ አንድ ኃይማኖት ወይንም ፖለቲካ እሳቤ ብቻ ያላደላ አስተዳደርን የሚያሰፍን  የሽግግር ሂደትን  ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን በጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች የጆርጂያ ፕሬዚደንት ሆኖ መመረጥ ለአውሮፓ ህብረት ዓላሚዎች ጉዳት ሆኗል

የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ሚኬይል ካቬላሽቪሊ  የጆርጂያ ፕሬዝደንት ሆነው መመረጣቸው  በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል ።ዜናው የተሰማው ተቃዋሚዎች  ሀገሪቱ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች የጆርጂያ ፕሬዚደንት ሆኖ መመረጥ ለአውሮፓ ህብረት ዓላሚዎች ጉዳት ሆኗል

የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ሚኬይል ካቬላሽቪሊ  የጆርጂያ ፕሬዝደንት ሆነው መመረጣቸው  በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል ።ዜናው የተሰማው ተቃዋሚዎች  ሀገሪቱ የአውሮፓ ህብረትን ለመቀላቀል ያላትን ፍላጎት መና የሚያስቀር ፣ ለቀድሞዋ የሀገሪቱ ንጉሳዊ አስተዳደር ገዢ ሩሲያ ድል የሚያቀናጅ ሲሉ የጠሩት የገዥው ፓርቲ እርምጃ እየበረታ በመጣበት ወቅት ነው። የ53 አመቱ ካቬላሽቪሊ  ፣2017ቱን ቀጥተኛ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በተካው ሰርዓት መሰረት ለጆርጂያ ህልም ፓርቲ  የተሰጡ  300 የመራጭ ወኪል መቀመጫዎችን  በመቆጣጠር በቀላል ድምጽ አሸንፈዋል። በደቡባዊ ካውካሷ ሀገር ፣ የጆርጂያ ህልም ፓርቲ ጥቅት 26 በተደረገው ምርጫ ፓርላማውን መቆጣጠር የቻለው  በሞስኮ ድጋፍ ምርጫውን በማጭበርበር ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች ይከሳሉ። የጆርጂያ ተሰናባች ፕሬዝዳንት እና ዋና ዋና አፍቃሪ ምዕራብ ፓርቲዎች ፣ በፓርላማ ስብሰባዎች ላይ አድማ በመምታት ዳግመኛ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀርበዋል።  የጆርጂያ ህልም ፓርቲ የአውሮፓ ህብረትን ለመቀላቀል ግፊት እንደሚያደርግ ፣ አብሮም ከሩሲያ ጋር ያለውን ግንኙነት እንደሚያድስ ቃል ገብቷል። በአውሮፓዊያኑ  2008 ሩሲያ ከጆርጂያ ጋር አጭር ጦርነት ውስጥ ገብታ የነበረ ሲሆን ፣  ይህም ሞስኮ ሁለት ተገንጣይ ክልሎችን እንደ ገለልተኛ ሀገራት እውቅና እንድተሰጣቸው መርቷታል። በደቡብ ኦሴቲያ እና በአብካዚያ የሩሲያ ጦር ኃይል ስምሪት እንዲጨምርም አድርጓል ። ባይደዚና አይቫንሽቪሊ በተባለ  ፣ ሩሲያ ውስጥ ሀብቱን ባፈራ ቢሊየነር ፣ የተመሰረተው የጆርጂያ ህልም ፓርቲ  ከቀን ተቀን አምባገነን እየሆነና እና ወደ ሩሲያ እያጋዳለ ስለመሆኑ ትችት ይቀርብበታል ።ገዥው ፓርቲ ግን ክሱን አይቀበልም ።  ፓርቲው በቅርቡ ክሬምሊን የመናገር ነፃነትን እና የኤልጂቢቲኪው+ መብቶችን ለመግታት የሚጠቀምባቸውን ዓይነት  ህጎችን አውጥቷል። አፍቃሪ ምዕራብ የሆኑት  ሰሎሜ ዙራቢችቪሊ ከ2018 ጀምሮ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ፣  የስድስት አመት የስልጣን ዘመናቸው ሰኞ ዕለት ያበቃል ። እራሳቸውን ብቸኛ ህጋዊ መሪ ሲሉ የሚገልጹት ፕሬዚደንቷ አዲስ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ  በስልጣናቸው እንደሚቆዩ ተናግረዋል። የጆርጂያ ህልም ባለፈው ወር ፣ ሀገሪቱ  ወደ አውሮፓ ህብረት ለመቀላቀል የምታደርገውን ድርድር ለማቆም መወሰኑ  የተቃዋሚዎችን ቁጣና ተቃውሞ አባብሶታል። የእንግሊዙ ማንቺስተር ሲቲ ክለብ እና በስዊዝ ሱፐር ሊግ ውስጥ በሚገኙ ክለቦች የቀድሞ ተጫዎች የነበሩት  ፣ለፕሬዚደንትነት በጆርጂያ ህልም ፓርቲ የተመረጡት ካቪላሽቪሊ ባላቸው ዝቅተኛ ትምህርት ደረጃ ተቃዋሚዎች ሲሳለቁባቸው ቆይተዋል ።  በ2016 የአውሮፓዊያኑ ዘመን በጆርጂያ ህልምን ፓርቲ በመወከል የፓርላማ ተመራጭ ከሆኑ በኃላ የህዝቦች ኃይል ፖለቲካዊ ንቅናቄ የተሰኘ ፓርቲ በአውሮፓዊያኑ 2022 መስርተዋል። ይህ ፓርቲ የጆርጂያ ህልም ፓርቲ አጋር ሲሆን በጠንካራ ጸረ ምዕራባዊያን አቋሙ ይበልጡኑ ዕውቅና አግኝቷል።

የደቡብ ኮሪያ ፓርላማ ወታደራዊ ህግ ያወጁት ፕሬዚደንት ከስልጣን እንዲነሱ ድምጽ ሰጠ

የደቡብ ኮሪያ ህግ አውጭዎች  ፣ ሀገሪቱን  በወታደራዊ አመራር ውስጥ ለማድረግ በሞከሩት ፕሬዚደንት ዩን ሱክ ዮል ላይ ስልጣናቸውን ሊገፍ የሚችል ክስ መስርቶባ
የአሜሪካ ድምፅ

የደቡብ ኮሪያ ፓርላማ ወታደራዊ ህግ ያወጁት ፕሬዚደንት ከስልጣን እንዲነሱ ድምጽ ሰጠ

የደቡብ ኮሪያ ህግ አውጭዎች  ፣ ሀገሪቱን  በወታደራዊ አመራር ውስጥ ለማድረግ በሞከሩት ፕሬዚደንት ዩን ሱክ ዮል ላይ ስልጣናቸውን ሊገፍ የሚችል ክስ መስርቶባቸዋል። ይህ ከፍተኛ እርምጃ ተፈጸሚ ይሆን ዘንድ  በዳኞች መጽደቅ አለበት። በዛሬው ዕለት በነበረው ድምጽ አሰጣጥ ስነ ስርዓት ላይ ፣ 12 ወግ አጥባቂ ህግ አውጭዎች ተቃዋሚ ኃይሎችን  በመቀላቀል ፣ በአምስት አመት የስልጣን ዘመናቸው አጋማሽ ላይ በሚገኙት ዮን ላይ ስልጣናቸውን የሚገፍ ክስ እንዲመሰረት ወስነዋል ። ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቱ በይፋ  ከስልጣን መነሳት እንዳለባቸው  እስኪወስን ድረስ የአሁኑ እርምጃ  የዮንን ሥልጣን በጊዜያዊነት ያግዳል። በጊዜያዊነት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀን ደክ ሱ የተጠባባቂ ፕሬዚደንትነት ኃላፊነቱን ይረከባሉ። የድምጽ አሰጣጥ ስነ ስርዓቱ ከመጀመሩ  ከደቂቃዎች በፊት ፣ ዩን የመጡነት ገዥው ህዝባዊ ጉልበት ፓርቲ ሂደቱን የተቃወመ ቢሆንም ፣  ካለፈው ሳምንቱ የሂደቱ ላይ አድማ በተጻራሪ  አባላቱ በነጻነት ድምጻቸውን እንዲሰጡ ግን ፈቅዷል። በሚስጢር ከተሰጠው ድምጽ ጋር ተዳምሮ የውሳኔው ሚዛን  ከዩን ተቃራኒ እንዲያጋድል አድርጓል። 204 ህግ አውጪዎች ህጉን  በመደገፍ 85ቱ ደግሞ በመቃወም ድምጻቸውን እንደሰጡ የመጨረሻው ድምጽ አሰጣጥ ውጤት ያሳያል። ከብሔራዊ ምክር ቤቱ ውጭ የተገኘ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር  ሕዝብ ደስታውን ሲገልጽ ታይቷል።  ዩን ደቡብ ኮሪያ በ1980ዎቹ ዴሞክራሲያዊት ሀገር ከሆነች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓዊያኑ ጥር 3 ላይ በሀገሪቱ ወታደራዊ አስተዳደርን ተግባራዊ ለማድረግ ያወጁ የመጀመሪያ ሰው ሆነዋል። ይሁንና ህግ አውጪዎች አዋጁን በሰዓታት ውስጥ ቀልብሰውታል።  ዩን ስልጣናቸውን ለመግፈፍ ስለቀረባባቸው ክስ እስካሁን መልስ አልሰጡም።  

ቆይታ ከአዲሷ የአፍሪቃ ሥነ ጥበብ ሙዚየም ምክትል ድሬክተር ዶ/ር ሄራን ሰረቀ ብርሃን ጋር

በቅርቡ ነው በዩናይትድ ስቴትሱ የስሚትሶኒያን ብሔራዊ ሙዚየም ሥር ከሚገኙት 21 ሙዚየሞች አንዱ ለሆነው የዋሽንግተኑ የአፍሪቃ ሥነ ጥበብ ሙዚየም ምክትል ድሬክ
የአሜሪካ ድምፅ

ቆይታ ከአዲሷ የአፍሪቃ ሥነ ጥበብ ሙዚየም ምክትል ድሬክተር ዶ/ር ሄራን ሰረቀ ብርሃን ጋር

በቅርቡ ነው በዩናይትድ ስቴትሱ የስሚትሶኒያን ብሔራዊ ሙዚየም ሥር ከሚገኙት 21 ሙዚየሞች አንዱ ለሆነው የዋሽንግተኑ የአፍሪቃ ሥነ ጥበብ ሙዚየም ምክትል ድሬክተር ሆነው እንዲያገግሉ የተመረጡት። ሄራን ሰረቀ ብርሃን ይባላሉ። ‘ለአፍሪቃ ሥነ ጥበብ ሥራዎች መልካም ዕድል አለ’ ብለው እንደሚያምኑ የሚናገሩት ዶ/ር ሄራን፤ ሙዚየሙ የሚያዘጋጃቸውን አውደ ትዕይንቶች የሚያስተባብር በአሕጉሪቱ ተቀማጭ የሆነ ባለ ሞያ በቀጥታ የሚሳተፍበትን ሁኔታ ጠቅሰዋል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2003 እዚሁ ሙዚየም ውስጥ የታየውን በኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ ሥራዎች ላይ ያተኮረ አውደ ርዕይ ሃሳብ ያመነጩት ዶ/ር ሄራን፤ ለወራት በዘለቀው የጥበባት ትዕይንት የተለያዩ ኢትዮጵያ ነክ ሥራዎች በማስተባበርም ተሳትፈዋል። ከስነ ጥበብ ጋር ዝምድና ባላቸው በርካታ ሥራዎቻቸው የሚታወቁት የአፍሪቃ ታሪክ ተመራማሪ፣ በነገስታቱ ዘመን በተቀናቃኝ ወገኖች መሃከል ስለሚፈጸሙ ጋብቻዎች ለድሕረ ምረቃ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ፣ ቤተ መዘክሩን በሚመለከቱ እና ሌሎች የተዛመዱ ርዕሶች ዙሪያም ያወጋሉ።

ደሴ ላይ ይገነባል ለተባለው ሆስፒታል ከሕዝብ ተሰብስቦ ገቢ አልተደረገም የተባለ ገንዘብ ክርክር አስነሳ

ደሴ ከተማ ላይ ሊገነባ ለታቀደው፣ “ወሎ ተርሸሪ ኬር የልእለ ህክምናና ትምህርት ማዕከል” ግንባታ ከሕዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ በአግባቡ ገቢ እንዳልተደረገ የ
የአሜሪካ ድምፅ

ደሴ ላይ ይገነባል ለተባለው ሆስፒታል ከሕዝብ ተሰብስቦ ገቢ አልተደረገም የተባለ ገንዘብ ክርክር አስነሳ

ደሴ ከተማ ላይ ሊገነባ ለታቀደው፣ “ወሎ ተርሸሪ ኬር የልእለ ህክምናና ትምህርት ማዕከል” ግንባታ ከሕዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ በአግባቡ ገቢ እንዳልተደረገ የፌደራል ዋና ኦዲተር አስታወቀ። ኦዲተር መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት፣ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱን ተጠያቂ አድርጓል። የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው፣ ለፕሮጀክቱ ገቢ ማሰባሰቢያ እንዲኾን በሚል የርዳታ ገንዘብ ለማሰባሰቢያ የተበተኑት ኩፖኖችና የሎተሪ ትኬቶችን መልሶ ለመሰብሰብ የተለያዩ ችግሮች ስላጋጠሟቸው ገንዘቡን መሰብሰብ እንዳልቻሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። በውዝግቡ ዙሪያ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የኢትዮጵያና የሶማሊያ ስምምነት በተንታኞች እይታ

በያዝነው ሳምንት በሶማሊያና ኢትዮጵያ መሪዎች መካከል አንካራ ላይ የተፈጸመውን ስምምነት አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የአፍሪካ ኅብረት እንዲሁም ኢጋድ በመ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያና የሶማሊያ ስምምነት በተንታኞች እይታ

በያዝነው ሳምንት በሶማሊያና ኢትዮጵያ መሪዎች መካከል አንካራ ላይ የተፈጸመውን ስምምነት አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የአፍሪካ ኅብረት እንዲሁም ኢጋድ በመልካም ተቀብለውታል። በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ወገኖች አንዱ የሌላውን የግዛት አንድነት እና ሉዐላዊነት ያከብራል። በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኝት ጥያቄ በተመለከተ በጋራ እንደሚሠሩበት ተመልክቷል። በሌላ በኩል የአንካራው ስምምነት፣ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚኾን አላመላከተም። ሃሩን ማሩፍ ስምምነቱ በሁለቱም ሃገራት እንዲሁም ከሶማሊላንድ ጋራ በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ላይ የሚኖረውን አንድምታ በተመለከተ ሁለት ተንታኞችን አነጋግሯል። እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።

በትረምፕ አስተዳደር ለውጭ ርዳታ በሚመደብ ገንዘብ የኦዲት ቁጥጥር እንደሚኖር ተንታኞች ተነበዩ

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጥር 20 ቀን ሥልጣን በሚረከበው የተመራጩ ፕሬዝደንት ትረምፕ አስተዳደር የውጭ ርዳታን በሚመለከት የሚነሱ ሁለት ቁልፍ ጥያቄዎች አ
የአሜሪካ ድምፅ

በትረምፕ አስተዳደር ለውጭ ርዳታ በሚመደብ ገንዘብ የኦዲት ቁጥጥር እንደሚኖር ተንታኞች ተነበዩ

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጥር 20 ቀን ሥልጣን በሚረከበው የተመራጩ ፕሬዝደንት ትረምፕ አስተዳደር የውጭ ርዳታን በሚመለከት የሚነሱ ሁለት ቁልፍ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነሱም በአኹኑ ወቅት «ዩናይትድ ስቴትስ ምን ያህል ገንዘብ ለውጭ ርዳታ ታወጣለች? ርዳታው የሚሰጠው ለማን ነው? » የሚሉት ናቸው፡፡ የአሜሪካ ድምጿ ቬሮኒካ ኢግሊሲያስ ባልዴራስ የሚያገኙት ርዳታ እንደሚቀነስ የሚጠበቁትን እና የርዳታ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚችሉትን የሚያስቃኝ ዘገባ አጠናቅራለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነታቸው መሻከሩን የሚያመለክቱ ቃላትን መለዋወጥ ጀምረዋል

ከሰሞኑ የኤርትራው ፕሬዝደንት ስለ ኢትዮጵያ ያደረጉት ንግግር እና በኢትዮጵያ በኩል የተሰማው ምላሽ፣ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ የሻከረው የሁለቱ አገራት
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነታቸው መሻከሩን የሚያመለክቱ ቃላትን መለዋወጥ ጀምረዋል

ከሰሞኑ የኤርትራው ፕሬዝደንት ስለ ኢትዮጵያ ያደረጉት ንግግር እና በኢትዮጵያ በኩል የተሰማው ምላሽ፣ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ የሻከረው የሁለቱ አገራት ግንኙነት መቋረጡን የሚያመለክት ነው ሲሉ የቀጣናዊ ጉዳዮች ተንታኞች ተናግረዋል። በዚኽ ጉዳይ ላይ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Get more results via ClueGoal