23 December 2024   19:16:13
Ethiopia



የጫት ገበያ የተዳከመባቸው የምስራቅ ኢትዮጵያ አርሶ አደሮች

የምስራቅ ኢትዮጵያ የጫት አምራቾች፣ የጫት ዋጋ በመውረዱ ምክኒያት ለችግር መዳረጋቸውን ገለጹ። የአካባቢው ጫት ላኪዎች በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ የጫት ምርት �

የአልቤኒያ መንግሥት ቲክ ቶክን ለአንድ ዓመት እንደሚዘጋው አስታወቀ

የአልቤኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከማኅበራዊ ትስስር ገጾች አንዱ የኾነው ቲክቶክ፣ ግጭት ቀስቃሽ እና በተለይ ሕፃናትን የሚያሸማቅቁ ቪዲዮች የሚሰራጭበት በመኾ�
የአሜሪካ ድምፅ

የአልቤኒያ መንግሥት ቲክ ቶክን ለአንድ ዓመት እንደሚዘጋው አስታወቀ

የአልቤኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከማኅበራዊ ትስስር ገጾች አንዱ የኾነው ቲክቶክ፣ ግጭት ቀስቃሽ እና በተለይ ሕፃናትን የሚያሸማቅቁ ቪዲዮች የሚሰራጭበት በመኾኑ መንግሥታቸው ለአንድ ዓመት እንደሚዘጋው ትላንት ቅዳሜ ታኅሣሥ፣ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አስታወቁ። በቲክቶክ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ኅዳር ወር አጋማሽ ላይ አንድ አዳጊ፣ በሌላ አዳጊ በስለት መገደሉን ተከትሎ የአልቤኒያ ባለሥልጣናት ከ1 ሺሕ 300 መምሕራንና ወላጆች ጋራ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ላይ የተናገሩት የአልቤኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤዲ ራማ፣ ቲክቶክ በአልቤኒያ ሪፐብሊክ ውስጥ እንደማይኖርና ሙሉ በሙሉ እንደሚዘጋ ተናግረዋል። የመዝጋቱ ሂደትም በመጪው ዓመት እንደሚጀምር አስታውቀዋል። ቲክቶክ አልባኒያ ውስጥ ወኪል እንዳለው አልታወቀም። በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት የተጠየቀው ቲክቶክ ቅዳሜ ዕለት በሰጠው የኢሜል ምላሽ፣ በስለት ተወግቶ ስለተገደለው አዳጊ የአልቤኒያ መንግሥት በአስቸኳይ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠይቋል። ድርጊቱን ፈጽሟል የተባለውም ኾነ፣ ድርጊቱ የተፈጸመበት ተጎጂ አዳጊ የቲክቶክ ገጽ እንደነበራቸው የሚያሳይ አንድም መረጃ እንደሌለ በኢሜል ያስታወቀ ድርጅቱ ፣ «እንደውም ብዙ ሪፖርቶች እንዳረጋገጡት ወደ አደጋው እንዲያመራ ምክኒያት የኾነው ቪዲዮ የተሰራጨው በሌላ የትስስር ገጽ ላይ እንጂ በቲክቶክ አይደለም» ብሏል። አልቤኒያ ውስጥ ከቲክቶክ ተጠቃሚዎች ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሕፃናት መኾናቸውን የሀገር ውስጥ ጉዳዮችን የሚያጠኑ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ልጆች ቲክቶክ ላይ በሚያዩዋቸው ግጭት ቀስቃሽ ቪዲዮዎችና የሚፈጠሩ አለመግባባቶች ወደ ትምሕርት ቤት በሚሄዱበት ጊዜ እንደ ቢለዋ ያሉ ስለት ነገሮችና ሌሎች ቁሳቁሶችን እየያዙ መሄድ በመጀመራቸው ወላጆችን ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል። ቲክቶክ በተመሰረተበት ቻይና «በተሻለ ሁኔታ እንዴት ማጥናት እንደሚቻል፣ ተፈጥሮን እንዴት መንከባከብ እንደሚቻል እና የመሳሰሉትን በጎና የተለዩ መልዕክቶች ናቸው የሚተላለፉት» ሲሉ የአልቤኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራማ ተናግረዋል። ራማ ቲክቶክ እንዲዘጋ ያሳለፉትን ውሳኔ በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች አልተቀበሉትም።

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአዲሰ አበባ ጉብኝት

ቅዳሜ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚኽ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያና በሶማሊ
የአሜሪካ ድምፅ

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአዲሰ አበባ ጉብኝት

ቅዳሜ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚኽ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል በቱርክ ለተፈረመው የአንካራ ስምምነት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።ፕሬዝደንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ በመኾን በሰጡት የጋራ መግለጫ የሁሉንም ሉዓላዊነት ከማክበር ጋራ የተያያዘው ስምምነት ሊደገፍ የሚገባው ነው ብለዋል።

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአዲሰ አበባ ጉብኝት 

ቅዳሜ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚኽ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያና በሶማ�
የአሜሪካ ድምፅ

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአዲሰ አበባ ጉብኝት 

ቅዳሜ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚኽ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል በቱርክ ለተፈረመው የአንካራ ስምምነት ድጋፋቸውን ገልጸዋል ። ፕሬዝደንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ በመኾን በሰጡት የጋራ መግለጫ የሁሉንም ሉዓላዊነት ከማክበር ጋራ የተያያዘው ስምምነት ሊደገፍ የሚገባው ነው ብለዋል። በቱርክ ፕሬዝደንት ረሽፕ ታይፕ ኤርዶዋን ሸምጋይነት የተካሄደውን ሦስተኛ ዙር ድርድር ተከትሎ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሐሙድ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግባቸውን ለመፍታትና አንዳቸው የሌላውን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ መስማማታቸው ይታወሳል ። ሁለቱ አገራት በመጭው የካቲት ወር በዝርዝር ጉዳይ ላይ ውይይት እንደሚጀምሩም ይጠበቃል። የሁለቱን ሀገራት ስምምነት ያደነቁት ፕሬዝደንት ማክሮን፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ እንዲሳካ ፈረንሳይ ባላት አቅም የበኩሏን ሚና መጫወት እንደምትፈልግ ጠቅሰዋል። በንግግር፣ በውይይት፣ ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ፣ ዓለምአቀፍ ሕጎችን እና ጎረቤት ሀገሮችን ባከበረ መልኩ መሠራት የሚችልበትን መንገድ ሀገራቸው ለማመቻቸት እንደምትፈልግ አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር ለማግኘት ያላትን ፍላጎት በተመለከተ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ጋራ በዝርዝር መወያየታቸውን ተናግረዋል። ከዚህ አንጻር ማክሮንን ድጋፍ መጠየቃቸውና ፣ ፕሬዝደንቱም ጥያቄውን መቀበላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።  «መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ከፈረንሳይ እና ከፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚህ ረገድ የሚጨበጥ ውጤት የሚጠብቅ መኾኑን ከወዲሁ ልገልጽ እፈልጋለሁ» በማለትም ተናግረዋል ። በኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል በፕሪቶሪያ የተፈረመው ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት  በሁለቱ መሪዎች ውይይት ከተነሱት ነጥቦች አንዱ መኾኑን የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ገልጸዋል። ሀገራቸው ከዚህ ስምምነት አተገባበር አንጻር ድጋፍ ማድረግ እንደምትፈልግም ተናግረዋል። ሀገራቸው በሽግግር ፍትህ አማካኝነት የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንደምትፈልግም አመልክተዋል። ፕሬዝዳንት ማክሮን በዛሬው የአዲስ አበባ ቆይታቸው፣ በመንግሥታቸው የገንዘብ ድጋፍ የታደሰውንና በአዲስ አበባ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ወይም ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ጎብኝተዋል። ፈረንሳይ ለብሔራዊ ቤተመንግሥቱ እድሳት የ25 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጓንም ተናግረዋል። ቤተመንግሥቱ የቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ የብር ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ በ1948 ዓ.ም. የተገነባ ነው።

የአሜሪካ ሴኔት ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታደገውን በጀት አጸደቀ

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የአሜሪካ መንግሥትን እስከ መጋቢት የሚያቆየውን በጀት አጸደቀ። በሪፐብሊካን ተመራጮች ብዙኅን ድምፅ ስር �
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ ሴኔት ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታደገውን በጀት አጸደቀ

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የአሜሪካ መንግሥትን እስከ መጋቢት የሚያቆየውን በጀት አጸደቀ። በሪፐብሊካን ተመራጮች ብዙኅን ድምፅ ስር ያለው የሕግ መምሪያ ምክር ቤት እና በዲሞክራት አብላጫ ቁጥጥር ስር ያለው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት፣ ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታገደውን በጀት ትላንት እኩለ ሌሊት ላይ አጽድቀዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የበጀት ረቂቁን እንደሚደግፉና ሕግ እንዲኾን እንደሚፈርሙ ትላንት ዐርብ ተናግረው ነበር። የጸደቀው በጀት ሕግ ኾኖ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ፣ መንግሥቱን እስከ መጪው መጋቢት የሚያቆየው በጀት ይኾናል። 100 ቢሊዮን ዶላር ለአደጋዎችና ለርዳታ፣ 10 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ለግብርና ሥራ ድጋፍ በበጀቱ ተይዟል። የጸደቀው በጀት የፌደራል መንግሥቱን የዕዳ ጣሪያ ከፍ እንዲል አያደርግም።

ቀጣይ በጀቱን ለመወሰን ጥቂት ሰዓታት የቀሩት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክርቤት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል

ዴሞክራቶች እና አንዳንድ ሪፐብሊካኖች የዕዳ ጣሪያውን እስከ አውሮፓውያኑ 2027 ድረስ ለማራዘም ያቀረቡትን ጥያቄ ከተቃወሙ በኋላ ሐሙስ ዕለት በHግ መወሰኛ ምክር�
የአሜሪካ ድምፅ

ቀጣይ በጀቱን ለመወሰን ጥቂት ሰዓታት የቀሩት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክርቤት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል

ዴሞክራቶች እና አንዳንድ ሪፐብሊካኖች የዕዳ ጣሪያውን እስከ አውሮፓውያኑ 2027 ድረስ ለማራዘም ያቀረቡትን ጥያቄ ከተቃወሙ በኋላ ሐሙስ ዕለት በHግ መወሰኛ ምክርቤቱ በችኮላ የተደረገው ድርድር ከሽፏል። ለውጡ የመጣው ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ኤሎን መስክ መንግሥትን እስከ መጭው መጋቢት ድረስ በገንዘብ ለመደገፍ የተጠየቀውን የሁለትዮሽ ስምምነት ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው። የአሜሪካ ድምጽ የኮንግረስ ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን እና አሶሽየትድ ፕሬስን ዘገባዎች ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።    

የቱርክ እና ኢራን መሪዎች ካይሮ ላይ ተገናኙ

የቱርክ እና ኢራን መሪዎች የሶሪያው ፕሬዝደነት ባሻር አል አሳድ ሥልጣን ካከተመ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ካይሮ ላይ በመካሄድ ላይ ባለውና በአብዛኛው የእስልም�
የአሜሪካ ድምፅ

የቱርክ እና ኢራን መሪዎች ካይሮ ላይ ተገናኙ

የቱርክ እና ኢራን መሪዎች የሶሪያው ፕሬዝደነት ባሻር አል አሳድ ሥልጣን ካከተመ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ካይሮ ላይ በመካሄድ ላይ ባለውና በአብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ የስምንት ሀገራት ጉባኤ ላይ ተገናኝተዋል። በሶሪያው ጦርነት ሁለቱ ሀገራት በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው የነበረ ሲሆን፣ ቱርክ የአሳድ ተቃዋሚዎችን ስትደግፍ ኢራን ደግሞ የአሳድን አገዛዝ ደግፋለች። በሶሪያ መረጋጋትና ሰላም እንዲሰፍን፣ ሽብርተኝነት እንዲጠፋ እንዲሁም የተረጋጋችና ፀጥታ የሰፈነባትን ሶሪያ ማየት እንደሚሹ የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሽፕ ታይፕ ኤርዶዋን በውይይታቸው ወቅት ማስታወቃቸውን የቱርክ ፕሬዝደንታዊ ጽሕፈት ቤት በአወጣው መግለጫ ላይ ተመልክቷል። የሶሪያን የግዛት ሉአላዊነት እና የሀገሪቱን አንድነት መጠበቅ አስፈላጊ እንደኾነም ኤርዶዋን መናገራቸውን ጽሕፈት ቤቱ አመልክቷል። ከኢራኑ ፕሬዝደንት ማሱድ ፐዘሽካን ቢሮ የወጣው መግለጫ በበኩሉ፣ የሶሪያ ድንበር ሳይደፈር ተጠብቆ የመቆየቱ አስፍላጊነት ላይ ፕሬዝደንቱ አጽንኦት መስጠታቸውን አመልክቷል። እስራኤል በቀጠናው ፈጽማዋለች ያሉትንና “ወንጀል” ሲሉ ለገለጹት ድርጊት ሙስሊም ሀገራት ኃላፊነት ባለው መንገድ ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው ፕሬዝደንቱ ማሳሰባቸውም ተጠቁሟል። “ግጭት በሚካሄድባቸው ሥፍራዎች የሚገኙ ሰዎች ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስባቸው መከላከል ሃይማኖታዊ፣ ሕጋዊ እና ሰብአዊ ግዴታችን ነው” ሲሉም ማሱድ ፐዘሽካን ማከላቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል። ‘ዲ 8’ በሚል የሚጠራው የስምንት ሃገራት የኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ በካይሮ በመካሄድ ላይ ያለው፣ በጋዛ ጦርነት በሚካሄድበት፣ በሌባኖስ በጽኑ ያልተከበረ የተኩስ ማቆም ስምምነት ባለበት፣ ሶሪያ ባልተረጋጋችበትና ቀጠናው በአጠቃላይ በግጭት በሚተራመስበት ወቅት ነው።

አሜሪካ በፈፀመችው የአየር ጥቃት በሶሪያ የአይሲስ መሪ ተገደለ

የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ዛሬ ዓርብ በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ እንዳስታወቀው፣ መሪውን አቡ ዮሱፍን ጨምሮ ሁለት የአይሲስ አባላት ሶሪያ ውስጥ በተፈጸመ
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካ በፈፀመችው የአየር ጥቃት በሶሪያ የአይሲስ መሪ ተገደለ

የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ዛሬ ዓርብ በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ እንዳስታወቀው፣ መሪውን አቡ ዮሱፍን ጨምሮ ሁለት የአይሲስ አባላት ሶሪያ ውስጥ በተፈጸመ አየር ጥቃት ተገድለዋል። የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት ሐሙስ መሆኑን ያስታወቅቁት የዕዙ መሪ ጀኔራል ማይክል ኩሪላ፣ የአይሲስ መሪዎችና ዓባላት ዒላማ መደረጋቸው እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። አሜሪካ አይሲስ በሶሪያ የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም ሊያንሰራራ ይችልላ የሚል ሥጋት እንዳላት ማስታወቋን የጠቆመው የሮይትረስ ዘገባ፣ በሀገሪቱ ሰሜን ምሥራቅ በቱርክ በሚደገፉት አማጺያን እና ከአሜሪካ ጋራ ባበሩት የኩርድ ሚሊሺያዎች መካከል ግጭት እንዳይኖር እንደምትሻ አመልክቷል። ምዕራባውያን መንግስታት ‘ሃያት ታህሪር አል-ሻም’ ወይም በምጻሩ ‘ኤች ቲ ኤስ’ በመባል የሚታወቀውንና በሶሪያ የቀድሞ አል ቃይዳ ቅርንጫፍ ቡድን ጋራ ንግግር ለመክፈት እንደሚሹና በሽብርተኝነት መፈረጁን ለማንሳት ክርክር መጀመራቸውንም የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

የእህል ርዳታ ወደ ቡግና ወረዳ መጓጓዝ መጀመሩን ባለሥልጣናት አስታወቁ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በረኅብ ለተጎዱ ሰዎች የርዳታ እህል ወደ ወረዳው እንዲገባ ከመንግሥትና ከፋ�
የአሜሪካ ድምፅ

የእህል ርዳታ ወደ ቡግና ወረዳ መጓጓዝ መጀመሩን ባለሥልጣናት አስታወቁ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በረኅብ ለተጎዱ ሰዎች የርዳታ እህል ወደ ወረዳው እንዲገባ ከመንግሥትና ከፋኖ ታጣቂዎች ጋራ ስምምነት ማድረጋቸውን አስታወቁ። በስምምነቱ መሰረትም የርዳታ እህሉ እየገባ መኾኑን አንድ የኃይማኖት አባት ተናግረዋል። የሰሜን ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል፣ አካባቢው በፋኖ ታጣቂዎች ስር በመኾኑ ለተከሰተው የምግብ እጥረት መንግሥት በቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻለም ብለዋል። የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በአደረጉት ጥረትም ከ110 ሺሕ በላይ ለሆኑ ሰዎች ከ16 ሺሕ ኩንታል በላይ የርዳታ እህል ወደ ስፍራው እየተጓጓዘ መኾኑን አስታውቀዋል። የወረዳው ነዋሪ ያለበትን የምግብና የጤና ችግር ለፋኖ ታጣቂዎችና ለመንግሥት አካላት ለማስረዳት ከተመረጡት 18 ግለሰቦች መካከል “አንዱ ነበርኩ” ያሉት ቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዝናቤ ይርዳው በአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረሰው ስምምነት መድኃኒቶችንና አልሚ ምግቦች ወደ ወረዳው መግባት መቻላቸውን ተናግረዋል። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ሁለት የአይና ቡግና ወረዳ ነዋሪ እናቶች፣ ለሕፃን ልጆቻቸው አልሚ ምግቦችን ከጤና ተቋማት ተቀብለው ወደ ቤታቸው እየሄዱ እንደሆነ ተናግረዋል። በሌላ በኩል አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ዛሬ ታኅሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በፌስ ቡክ ገጹ በአወጣው መግለጫ በቡግና ወረዳ የምግብ እጥረት ቀውስ ሰለመኖሩ የወጡ ሪፖርቶችን እየተከታተለ መኾኑን አመልክቷል። «ሁኔታውን መከታተላችንን እና መገምገማችንን እንቀጥላለን» ያለው መግለጫው ቀውሱ መወገዱን ለማረጋገጥ እንደሚሠራም ጠቅሷል። ኤምባሲው በመግለጫው ቀውሱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን አላካተተም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመደገፍ ፣ አጋሮቹ በአኹኑ ሰዓት በችግሩ በተጠቁት አብዛኞቹ ስፍራዎች የምግብ እና አልሚ ንጥረ ምግቦች ስርጭትን ያጠናከሩ መሆናቸውንም አክሏል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

“የትግራይ ሰራዊት በዲዲአር ስም እንዲበተን እየተደረገ ነው” - በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት

በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራ የህወሓት ቡድን ዛሬ መቐለ ከተማ በሰጡት መግለጫ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች፣ ታጣቂዎችን ትጥ�
የአሜሪካ ድምፅ

“የትግራይ ሰራዊት በዲዲአር ስም እንዲበተን እየተደረገ ነው” - በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት

በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራ የህወሓት ቡድን ዛሬ መቐለ ከተማ በሰጡት መግለጫ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች፣ ታጣቂዎችን ትጥቅ በማስፈታት እና በመልሶ ማዋሃድ ሥራ ስም፣ የትግራይ መሰረታዊ ጥያቄ ሳይመለስ የቀድሞ ተዋጊዎች እንዲበተኑ እየተደረገ ነው ሲል ክስ አሰማ። የህወሓት አንዱ ክፋይ በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ፣ “የእምቢታ ዘመቻ” ብሎ የጠራው ስብሰባ ሲያጠናቅቅ፣ “ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲፈፅም የተሰጠው ሥራ ሙሉ በሙሉ ወድቋል” በማለትም ገልጿል። በሌላ በኩል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለሦስት ቀናት ያካሔደውን ስብሰባ አስመልክቶ በአወጣው መግለጫ፣ “ክልሉን ወደ ግርግር እና የአመፅ ተግባር ለማስገባት የሚንቀሳቀሱ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አይታገስም” ብሏል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ገቡ የተባሉ 44 ደቡብ ሱዳናውያን አርብቶ አደሮች መታሰራቸውን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በመግባት ከብት ዘርፈዋል የተባሉ 44 የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮችን ማሰሩን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ከ200 በላይ ከብቶችን ማስመለሱ�
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ገቡ የተባሉ 44 ደቡብ ሱዳናውያን አርብቶ አደሮች መታሰራቸውን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በመግባት ከብት ዘርፈዋል የተባሉ 44 የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮችን ማሰሩን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ከ200 በላይ ከብቶችን ማስመለሱንና ለባለቤቶቹ ማስረከቡንም ፖሊስ ገልጿል። ባለፈው ዐርብ ታኅሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ተጠርጣሪዎቹ ተይዘውበት ከነበረው ሱርማ ወረዳ ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕከል መዘዋወራቸውንም የኮሚሽኑ ሚዲያ እና ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጄላን አብዲ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

በዋግ ኽምራ ዞን ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ከ2016 ዓ.ም የመኸር ወቅት ጀምሮ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ምክኒያት ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ �
የአሜሪካ ድምፅ

በዋግ ኽምራ ዞን ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ከ2016 ዓ.ም የመኸር ወቅት ጀምሮ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ምክኒያት ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ምሕረት መላከ፣ ባለፈው ክረምት በዞኑ ደጋማ አካባቢዎች የደረሰውን የተፈጥሮ አደጋ ተከትሎ ከ14 በላይ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች በአደረጉት ግምገማ 44 ሰዎች መሞታቸውን ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሰብአዊ መብቶችን በኪነ-ጥበብ

በኢትዮጵያ ይስተዋላሉ የሚባሉ የመብት ጥሰቶችን የሚዳስስ፣ በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብትን የሚያስተምርና ሴቶች በሕይወት የመኖር መብት እንዳላቸው የሚያ�
የአሜሪካ ድምፅ

ሰብአዊ መብቶችን በኪነ-ጥበብ

በኢትዮጵያ ይስተዋላሉ የሚባሉ የመብት ጥሰቶችን የሚዳስስ፣ በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብትን የሚያስተምርና ሴቶች በሕይወት የመኖር መብት እንዳላቸው የሚያስታውስ ፣ ተውኔት፣ የፎቶ ግራፍ አውደ ርእይና ስዕል አዲስ አበባ ከተማ ላይ ለእይታ በቃ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ፣ በሰብአዊ መብቶች ላይ ትኩረት ያደረገ የፊልም ፌስቲቫል በኢትዮጵያ ከተሞች በማካሄድ ላይ መኾኑን አስታውቋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት የሕፃናትን የኢንተርኔት ደኅንነት ሕግ እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀረበ

በዚህ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሥራ ዘመን ሕፃናትን ከማኅበራዊ ሚዲያ ጠንቆች ለመከላከል በሁለቱም ፓርቲዎች ትብብር የተያዘው ጥረት ጊዜው እያለቀበት ነ
የአሜሪካ ድምፅ

የዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት የሕፃናትን የኢንተርኔት ደኅንነት ሕግ እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀረበ

በዚህ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሥራ ዘመን ሕፃናትን ከማኅበራዊ ሚዲያ ጠንቆች ለመከላከል በሁለቱም ፓርቲዎች ትብብር የተያዘው ጥረት ጊዜው እያለቀበት ነው። የሕፃናት የኢንተርኔት ደኅንነት ሕግ ከጸደቀ፣ በኢንተርኔት ላይ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን ለሚመለከቱ የግል መረጃዎች ጥበቃዎችን ይደነግጋል። ለመናገር ነፃነት ተሟጋቾች እና አንዳንድ ሪፐብሊካኖች ግን፣ ሕጉ ወደ ሳንሱር ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። የቪኦኤ የምክር ቤት ዘጋቢ ካትሪን ጊብሰን ተጨማሪ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የካሜሩን ጋዜጠኞች ከመጪው ምርጫ በፊት የተሳሳተ መረጃን ለመዋጋት ተስፋ ያደርጋሉ

ካሜሩናውያን ሀገሪቱን ለሰባት ዓመታት በፕሬዝደንትነት የሚመራውን ፕሬዝደንት ለመምረጥ በመጪው ዓመት ወደ ምርጫ ጣቢያ ያመራሉ። በማዕከላዊ የአፍሪካ አህጉ�
የአሜሪካ ድምፅ

የካሜሩን ጋዜጠኞች ከመጪው ምርጫ በፊት የተሳሳተ መረጃን ለመዋጋት ተስፋ ያደርጋሉ

ካሜሩናውያን ሀገሪቱን ለሰባት ዓመታት በፕሬዝደንትነት የሚመራውን ፕሬዝደንት ለመምረጥ በመጪው ዓመት ወደ ምርጫ ጣቢያ ያመራሉ። በማዕከላዊ የአፍሪካ አህጉር በምትገኘው ካሜሩን ከዚህ በፊት በተደረጉ ምርጫዎች ወቅት የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ጭቅጭቅ ፈጥረዋል። በመጪው ምርጫ ይህ እንዳይደገም፣ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ባለሙያዎች ቀድሞ ለመከላከል ርምጃ በመውሰድ ላይ ናቸው። ጆድዘካ ዳንሃቱ ከካሜሩን የላከውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዶናልድ ትረምፕና ኢላን መስክ በምክር ቤት የቀረበውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅ ቀረ

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና ባለ ሀብቱ ኢላን መስክ በአሜሪካ ምክር ቤት በሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነት ቀርቦ የነበረውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅ �
የአሜሪካ ድምፅ

ዶናልድ ትረምፕና ኢላን መስክ በምክር ቤት የቀረበውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅ ቀረ

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና ባለ ሀብቱ ኢላን መስክ በአሜሪካ ምክር ቤት በሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነት ቀርቦ የነበረውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅ ቀርቷል። የወቅቱ የበጀት ዓመት ነገ ዐርብ ሌሊት ስለሚጠናቀቅ፣ ከዚያ በፊት በምክር ቤቱ በጀት የማይጸድቅ ከኾነ በርካታ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሥራ ሊያቆሙ ወይም ‘አስፈላጊ’ ተብለው ከተመደቡ የመንግሥት ሠራተኞች ውጪ የሆኑት ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ሥራ ላይገቡ ይችላሉ። ሥራቸውን የሚቀጥሉትም ቢሆኑ በጀቱ እስከሚለቀቅ ካለ ደመወዝ ሊሠሩ እንደሚችሉ ታውቋል። ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና ተመራጩ ምክትል ፕሬዝደንት ጄ ዲ ቫንስ ትላንት በጋራ ባወጡት መግለጫ የቀረበው የበጀት ረቂቅ «ወደዲሞክራቶቹ ፍላጎት ያጋደለ ነው» በሚል ተቃውመዋል። በመጪው የትረምፕ አስተዳደር የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ብዛት፣ ፕሮግራሞች እና ሠራተኞች ለመቀነስ የተቋቋመውን ቡድን ከሚመሩት አንዱ የሆኑት ባለ ሀብቱ ኢላን መስክ “እጅግ የበዛ ወጪ የሚያስከትል” ብለው የበጀት ሐሳቡን ውድቅ አድርገዋል። በጀቱን የሚደግፉ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባላት ከሁለት ዓመት በኋላ በሚደረገው ምርጫ መራጮች በድምጻቸው ሊቀጧቸው እንደሚችሉ ኢላን መስክ ዝተዋል። ሪፐብሊካን የም/ቤት ዓባላት በበጀቱ ላይ እንደገና እንዲደራደርሩ ጥሪ ያደረጉት ትረምፕ፣ ያንን የማያደርጉ ከሆነ “ሀገርን እንደመክዳት ይቆጠራል” ብለዋል። የፕሬዝደንት ጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን ከመጠናቀቁ በፊትም የሀገሪቱ የዕዳ ጣሪያ ከፍ እንዲል ትረምፕ ጠይቀዋል። የባይደን አስተዳደር የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የመዝጋቱን ሐሳብ ነቅፏል።  

የአማዞን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ

በሰባት የአማዞን መጋዘኖች የሚገኙ ሠራተኞች ከዛሬ ሐሙስ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ መትተዋል። ሠራተኞቹ አድማውን የጠሩት አማዞን ባለፈው እሑድ ቀጠሮ ተይዞለ�
የአሜሪካ ድምፅ

የአማዞን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ

በሰባት የአማዞን መጋዘኖች የሚገኙ ሠራተኞች ከዛሬ ሐሙስ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ መትተዋል። ሠራተኞቹ አድማውን የጠሩት አማዞን ባለፈው እሑድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረውን የአሠሪ እና ሠራተኛ ውል ድርድር ችላ ብሏል በሚል ነው። በአድማው የሚሳተፉት በኒው ዮርክ፣ ካሊፎርኒያ፣ ኢሊኖይ እና ጆርጂያ በሚገኙ የአማዞን የሸቀጥ ማከማቻና ማደራጃ መጋዘኖች የሚሠሩ ሠራተኞች መኾናቸው ታውቋል። አማዞን በበኩሉ አድማው በሥራው ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ብሎ እንደማይጠብቅ አስታውቋል። የሠራተኛ ማኅበሩ በአሥር የአማዞን መጋዘኖች የሚገኙ 10 ሺሕ ሠራተኞችን እንደሚወክል አስታውቋል። አማዞን በአጠቃላይ በዋና ዋና ቢሮዎችና መጋዘኖች የሚሠሩ 1.5 ሚሊዮን ሠራተኞች አሉት፡፡ ዛሬ አድማ የመቱት በሳን ፍራንሲስኮ፣ ካሊፎርኒያ መጋዘን ውስጥ የሚሠሩ እንዲሁም በሌሎች አራት ግዛቶች ውስጥ የሚገኙና ሸቀጥ ለሥርጭት በሚያዘጋጁ ጣቢያዎች ውስጥ የሚሠሩ መኾናቸው ታውቋል። በሌሎች ሥፍራዎች የሚገኙ የአማዞን ሠራተኞችም አድማውን ለመቀላቀል ዝግጁ መሆናቸውን የሠራተኛ ማኅበሩ አስታውቋል። ሸቀጡን የሚያጓጉዙ ሾፌሮች የኩባንያው ተቀጣሪዎች ሳይሆኑ፣ ለሦስተኛ ወገን የሚሠሩ መሆናቸውን አማዞን ይገልጻል። የአክሲዮን ገበያ ዛሬ ማለዳ በተከፈተበት ወቅት የአማዞን ድርሻ በአንድ በመቶ ከፍ ብሏል።

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያሰበችውን ግብ እያሳካች መኾኑን ፑቲን ተናገሩ

ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ ኅይሎች በዩክሬን ጦርነት ዋና ግባቸውን ለመምታት እየተቃረቡ መኾኑን በዓመታዊ ጋዜጣዊ  መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል። በጦ�
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያሰበችውን ግብ እያሳካች መኾኑን ፑቲን ተናገሩ

ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ ኅይሎች በዩክሬን ጦርነት ዋና ግባቸውን ለመምታት እየተቃረቡ መኾኑን በዓመታዊ ጋዜጣዊ  መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል። በጦር ሜዳው እንዳገኙ ለሚገልጹት የበላይነት አዲሶቹ የሩሲያ  ሱፐርሶኒክ ሚሳዬሎች አስተዋጽኦ እንዳደረጉ አመልክተዋል። በመንግሥት ቴሌቭዥን ቀርበው ከሩሲያውያን ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ የሰጡት ፑቲን፣ የሀገራቸው ኅይሎች በሁሉም ግንባሮች ግሥጋሤ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። ፑቲን ፣ “ሁኔታዎች እየተቀያየሩ ነው። በየቀኑ በሁሉም ግንባሮች ግሥጋሤ አለ” ሲሉ አስታውቀዋል።  ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን እ.አ.አ ከ2022 ወዲህ በፍጥነት እየገሠገሠችና በርካታ ሥፍራዎችን በመቆጣጠር ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ወዳላቸው ከተሞች በመቃረብ ላይ መኾኗን ምዕራባውያንና የሩሲያ ወታደራዊ ተንታኞች በመግለጽ ላይ ናቸው። ዩክሬን የሩሲያን ኩርስክ ክልል ይዛ መቆየቷን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፣ የዩክሬን ኅይሎች “በእርግጠኝነት እንዲወጡ የደረጋል” ሲሉ ተደምጠዋል። የሩሲያ አዲስ ሱፐርሶኒክ ‘ኦረሽኒክ’ ሚሳዬሎች ከእይታ ውጪ ስለኾኑ መትቶ ለመጣል እንደማይቻል ፑቲን ተናግረዋል። ሩሲያ የሠራቻቸውን እነዚህ ሚሳዬሎች የዩክሬን ወታደራዊ ፋብሪካዎችን በመምታት ሞክራቸዋለች፡፡ በእነዚህ ሚሳዬሎች ተጨማሪ ድብደባዎችን እንደሚያደርጉና የምዕራባውያን የመከላከያ መሣሪያዎች መትተው ይጥሏቸው እንደሁ የሚታይ ይሆናል ብለዋል ፑቲን። 

ህወሓት አዲስ ሰላማዊ የፖለቲካዊ ትግል ለማካሔድ መወሰኑ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገለጹ

ለሁለት ከተከፈሉት የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች፣ በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ዛሬ መቐለ ከተማ ላይ ከፓርቲው ከ
የአሜሪካ ድምፅ

ህወሓት አዲስ ሰላማዊ የፖለቲካዊ ትግል ለማካሔድ መወሰኑ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገለጹ

ለሁለት ከተከፈሉት የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች፣ በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ዛሬ መቐለ ከተማ ላይ ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋራ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል። “እምቢ የማለት ዘመቻ” የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ ውይይት መክፈቻ ላይ የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ በትግራይ ክልል በአሁኑ ጊዜ ልዩ ትግል እና መደጋገፍ እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል። በሌላ በኩል፣ ሦስት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች በአራት የትግራይ ዞኖች ዳሰሳ ማካሔዳቸውን ገልጸው በሰጡት መግለጫ፣ ህወሓትን ትጥቅ በማስታጠቅ ከሰዋል። በዶክተር ደብረ ጽዮን የሚመራው የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የኾኑት፣ ዶክተር ፍሰኻ ሀብተ ጽዮን፣ “እኛ ፓርቲ ነን ማስታጠቅም መመልመልም አንችልም፣ ትግላችንም ሰላማዊ ነው” ብለዋል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በወራ ጃርሶ ወረዳ ቡና ለመጠጣት የተሰባሰቡ ሰዎች በፍንዳታ መጎዳታቸውን ቤተሰቦች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወራ ጃርሶ ወረዳ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል ተባብሶ በቀጠለው ግጭትና የተኩስ ል�
የአሜሪካ ድምፅ

በወራ ጃርሶ ወረዳ ቡና ለመጠጣት የተሰባሰቡ ሰዎች በፍንዳታ መጎዳታቸውን ቤተሰቦች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወራ ጃርሶ ወረዳ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል ተባብሶ በቀጠለው ግጭትና የተኩስ ልውውጥ ምክኒያት፣ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን የተጎጂ ቤተሰብ እና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። የተጎጂ ቤተሰብ አባል መኾናቸውን የገለጹ ግለሰብ ፣ ከቤታቸው ደጃፋ በሚገኝ ዛፍ ጥላ ስር ኾነው ቡና በመጠጣት ላይ የነበሩ ሰዎች እና ሕፃናት ጭምር ከርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ ፍንጣሪ መገደላቸውን ተናግረዋል። በወረዳው ደረሰ በተባለው ጉዳት ዙሪያ ከክልሉ ባለሥልጣናት ጀምሮ እስከ ወረዳው ድረስ የሚመለከታቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ለማነጋገር የአሜሪካ ድምፅ ያደረገው ጥረት ባለ ሥልጣናቱ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ምክንያት ሊሳካ አልቻለም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በአማራ ክልል በመንግሥት አስተባባሪነት የተጠራ ነው የተባለ ሰልፍ ተካሄደ

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች በክልሉ መንግሥት ቀስቃሽነት የተዘጋጀ ነው የተባለ፣ ሰላምን የሚጠይቅ ሰልፍ ተካሄደ። ደሴ ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ያገኘና
የአሜሪካ ድምፅ

በአማራ ክልል በመንግሥት አስተባባሪነት የተጠራ ነው የተባለ ሰልፍ ተካሄደ

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች በክልሉ መንግሥት ቀስቃሽነት የተዘጋጀ ነው የተባለ፣ ሰላምን የሚጠይቅ ሰልፍ ተካሄደ። ደሴ ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ያገኘናቸው ተሳታፊዎች፣ ክልሉ ከግጭት እንዲወጣና ሰላም እንዲመጣ የሚጠይቅ ሐሳብ በሰልፉ ላይ ማንፀባረቃቸውን ተናግረዋል። በሌላ በኩል ሰልፍ የወጡት በአስገዳጅነት መኾኑን የተናገሩ አንድ የወልድያ ከተማ ነዋሪ፣ “መንግሥት ነዋሪዎች በፈቃዳቸው ሰልፍ እንዲወጡ ቢፈቅድና ትክክለኛውን የሕዝብ ስሜት ቢያዳምጥ ተገቢ ይኾን ነበር” ብለዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሞዛምቢክ ጋዜጠኞች ሐሰተኛ መረጃን ለመዋጋት ጥረታቸውን አጠናቅረው ቀጥለዋል

በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሐሰተኛ መረጃ መስፋፋቱን ተከትሎ፣ በሞዛምቢክ  የሚገኙ ጋዜጠኞች ኾን ተብለውም ሆነ ባለማወቅ የሚጋሩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመዋጋት ግን�
የአሜሪካ ድምፅ

በሞዛምቢክ ጋዜጠኞች ሐሰተኛ መረጃን ለመዋጋት ጥረታቸውን አጠናቅረው ቀጥለዋል

በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሐሰተኛ መረጃ መስፋፋቱን ተከትሎ፣ በሞዛምቢክ  የሚገኙ ጋዜጠኞች ኾን ተብለውም ሆነ ባለማወቅ የሚጋሩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመዋጋት ግንባር ቀደም ኾዋል። አማሪሊስ ጉሌ በዚህ ዙሪያ ከማፑቶ ያደረሰንን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ለ”ሔር ኢሴ” የተሰጠውን እውቅና የኢሳ ጎሳዎች ኡጋዝ በድሬደዋ ተረከቡ

በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ውስጥ የሰፈረው፣ “ሔር ኢሴ” የተሰኘው በኢት�
የአሜሪካ ድምፅ

ለ”ሔር ኢሴ” የተሰጠውን እውቅና የኢሳ ጎሳዎች ኡጋዝ በድሬደዋ ተረከቡ

በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ውስጥ የሰፈረው፣ “ሔር ኢሴ” የተሰኘው በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ የሚገኙት የሶማሌ ኢሳ ማኅበረሰብ የፍትህ ሥርዐት፣ ሌሎች የተደበቁ ኢትዮጵያዊ ባህሎችም እውቅና እንዲያገኙ የሚያነሳሳ መኾኑ ተገለጸ። ለባህላዊ ሥርዐቱ ከፓራጓይ የተሰጠውን ዕውቅና የተቀበሉት የልዑካን ቡድኖች ምስክር ወረቀቱን፣ ድሬደዋ ላይ ለኢሳ ጎሳዎች ኡጋዝ ወይም መሪ አስረክበዋል።  ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ትላልቆቹ የኒው ዮርክ መደብሮች ምዕተ ዓመት ያስቆጠረውን የበዓል ገበያተኛ መሳቢያ ዘዴ ያልተውት ስለምን ይኾን?

ከአንድ መቶ ዓመት በላይ ባስቆጠረው ገበያተኛ መሳቢያ መንገድ ዝነኞቹ የኒው ዮርክ ከተማ መደብሮች በየዓመቱ፣ መስኮቶቻቸውን ከበዓሉ ጋራ በተያያዙ ነገሮች አ�
የአሜሪካ ድምፅ

ትላልቆቹ የኒው ዮርክ መደብሮች ምዕተ ዓመት ያስቆጠረውን የበዓል ገበያተኛ መሳቢያ ዘዴ ያልተውት ስለምን ይኾን?

ከአንድ መቶ ዓመት በላይ ባስቆጠረው ገበያተኛ መሳቢያ መንገድ ዝነኞቹ የኒው ዮርክ ከተማ መደብሮች በየዓመቱ፣ መስኮቶቻቸውን ከበዓሉ ጋራ በተያያዙ ነገሮች አስውበው ለአላፊ አግዳሚው እይታ ያቀርባሉ። የቪኦኤ ዘጋቢ ዶራ መህኩዋር ይኽ የቆየ የገበያተኛ መጥሪያ ስልት እስከ አኹን እንደዘለቀ ቃኝታ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ቅዳሜ ታኅሣስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሀገሪቱ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች አስታውቀዋል። �
የአሜሪካ ድምፅ

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ቅዳሜ ታኅሣስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሀገሪቱ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች አስታውቀዋል። ፕሬዝደንቱ በዋነኛነት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ በመኾን፣ በሀገራቸው መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ የታደሰውንና አዲስ አበባ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ወይም ኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት መርቀው እንደሚከፍቱም ጠቅሰዋል። የፈረንሳዩ መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያካሂዱም እነዚሁ ምንጮች አመልክተዋል። ምንጮቹ እንደጠቀሱት፣ ሁለቱ መሪዎች በቅድሚያ የሚወያዩት፣ በዚኽ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል በቱርክ በተፈረመው የአንካራ ስምምነት ላይ ነው። ፕሬዝደንት ማክሮን ስምምነቱን እንደሚቀበሉት በመግለጽ፣ ድጋፋቸውን እንደሚያሳዩም ዲፕሎማሲያዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል። ፕሬዝደንቱ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በተመለከተ እንደሚነጋገሩና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከሚታዩ ግጭቶች አንጻርም ተመሳሳይ የሰላም መፍትሔዎችን እንደሚያበረታቱ ምንጮቹ አስረድተዋል። ፈረንሳይ ቅዳሜ እንደሚመረቅ ለሚጠበቀው የብሔራዊ ቤተ መንግሥት እድሳት የ25 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጓን የፈረንሳይ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች ተናግረዋል።  ቤተ መንግሥቱ የቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ የብር ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ በ1948 ዓ.ም. የተገነባ ነው።

በሞዛምቢክ አውሎ ነፋስ የሞቱት ቁጥር ወደ 45 አሻቀበ

በሞዛምቢክ በተከሰተው ከፍተኛ አውሎ ነፋስና ዝናብ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 45 ማሻቀቡ ተነግሯል። ባለፈው እሑድ የሰሜን ሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ ክፍለ ግዛትን በ
የአሜሪካ ድምፅ

በሞዛምቢክ አውሎ ነፋስ የሞቱት ቁጥር ወደ 45 አሻቀበ

በሞዛምቢክ በተከሰተው ከፍተኛ አውሎ ነፋስና ዝናብ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 45 ማሻቀቡ ተነግሯል። ባለፈው እሑድ የሰሜን ሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ ክፍለ ግዛትን በመታው አውሎ ነፋስ እና ዝናም ሠላሳ አራት ሰዎች መሞታቸውን ትላንት ማክሰኞ የወጣው የመጀመሪያው አሃዝ አሳይቶ ነበር፡፡  በአውሎ ነፋሱ 500 የሚኾኑ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ አደጋ መከላከል ባለሥልጣን አስታውቋል። 36 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች መሉ በሙሉ አሊያም  በከፊል ፈርሰዋል። 181 ሺሕ ሰዎች በከፍተኛው አውሎ ነፋሱ ተጠቂ ኾነዋል። የአደጋ መከላከል ማዕከሉ በአወጣው በኋለኛው አሃዝ መሠረት ካቦ ዴልጋዶ ውስጥ  38 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ናምፑላ ክፍለ ሀገር ውስጥ ደግሞ አራት ሰዎች ሞተዋል፡፡ ወደ መሃል ሀገር ገባ ብላ በትምገኘው ኒያሳ ውስጥ ደግሞ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል፡፡  የደረሰበት ያልታወቀ አንድ ሰው መኖሩንም መረጃው አመልክቷል፡፡ በሰዓት 260 ኪ.ሜ. ፍጥነት የነበረው ነፋስና ከፍተኛ ዝናም ቀድሞውንም ግጭትና ደካማ መሠረተ ልማት የነበረውን የሞዛምቢክን ሰሜናዊ ክፍል አጥቅቷል። አውሎ ነፋሱ በሕንድ ውቅያኖስ የምትገኘውን የፈረንሣይ ደሴት ማዮትን ከመታ በኋላ ነበር ወደ ሞዛምቢክ ያቀናው። በማዮት ቢያንስ በመቶ ወይም በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሳይገድል እንዳልቀረ ተሰግቷል።

VOA60 Africa - Ghana: Supreme Court rejects legal challenges to anti-LGBT legislation

Ghana: The Supreme Court Wednesday rejected two separate legal challenges to Africa's most restrictive anti-LGBT legislation, paving the way for President Nana Akufo-Addo to sign it into law. He had delayed doing so pending the court’s decision.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Ghana: Supreme Court rejects legal challenges to anti-LGBT legislation

Ghana: The Supreme Court Wednesday rejected two separate legal challenges to Africa's most restrictive anti-LGBT legislation, paving the way for President Nana Akufo-Addo to sign it into law. He had delayed doing so pending the court’s decision.

VOA60 America - Return to Earth for 2 stuck NASA astronauts delayed until March

NASA's two astronauts stuck at the International Space Station, Butch Wilmore and Suni Williams, will not return until the end of March or even April because of a delay in launching their replacements, according to NASA.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Return to Earth for 2 stuck NASA astronauts delayed until March

NASA's two astronauts stuck at the International Space Station, Butch Wilmore and Suni Williams, will not return until the end of March or even April because of a delay in launching their replacements, according to NASA.

VOA60 World - Relief operations intensified on French territory of Mayotte following deadly cyclone

Mayotte: Relief operations intensified on Wednesday, as 120 tons of food arrived at the airport for distribution following Cyclone Chido, the worst storm to hit the French overseas territory in 90 years. The death toll remains unclear, with only 22 fatalitie
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Relief operations intensified on French territory of Mayotte following deadly cyclone

Mayotte: Relief operations intensified on Wednesday, as 120 tons of food arrived at the airport for distribution following Cyclone Chido, the worst storm to hit the French overseas territory in 90 years. The death toll remains unclear, with only 22 fatalities confirmed in hospitals so far.

የጋና ጋዜጠኞች የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እየሠሩ ነው

በጋና ሆን ተብለውም ኾነ ባለማወቅ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች በከፍተኛ መጠን ጨምረዋል። በመኾኑም አንዳንድ ጋዜጠኞች ትክክለኛ ዘገባዎችን በመሥራት ሐሰተኛ �
የአሜሪካ ድምፅ

የጋና ጋዜጠኞች የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እየሠሩ ነው

በጋና ሆን ተብለውም ኾነ ባለማወቅ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች በከፍተኛ መጠን ጨምረዋል። በመኾኑም አንዳንድ ጋዜጠኞች ትክክለኛ ዘገባዎችን በመሥራት ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመዋጋት ተስፋ ያደርጋሉ። አይዛክ ካልዲዚ ከጋና ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የውጭ ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ዐዋጅ ጸደቀ

የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው “የባንክ ሥራ ረቂቅ ዐዋጅ” በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል። ውሳኔው የሀገር ውስጥ ባ
የአሜሪካ ድምፅ

የውጭ ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ዐዋጅ ጸደቀ

የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው “የባንክ ሥራ ረቂቅ ዐዋጅ” በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል። ውሳኔው የሀገር ውስጥ ባንኮችን ከውድድር ውጭ በማድረግ ከዘርፉ ሊያስወጣቸው እንደሚችል የምክር ቤቱ አባላት ስጋታቸውን አንፀባርቀዋል። የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በሰጡት ምላሽ፣ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ እንዲሠሩ መፈቀዱ የሀገር ውስጥ ባንኮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አይኖረውም ብለዋል፡፡ የምጣኔ ሀብት  ጉዳዮች ተንታኝ ዶ/ር አብዱል መናን መሐመድም፣ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረግ፣ ለሀገር ውስጥ ባንኮች ስጋት አይኾንም ይላሉ፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ካሳ እና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው መኖሪያ ቤታቸው እየፈረሰ መኾኑን የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ

በአዲስ አበባ፣ የካ ክፍለ ከተማ የሚኖሩና ቤታቸው እየፈረሰባቸው እንደሚገኝ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩ ነዋሪዎች፣ ቤታቸው ከመፍረሱ በፊት፣ መንግሥት ቃል ገብ�
የአሜሪካ ድምፅ

ካሳ እና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው መኖሪያ ቤታቸው እየፈረሰ መኾኑን የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ

በአዲስ አበባ፣ የካ ክፍለ ከተማ የሚኖሩና ቤታቸው እየፈረሰባቸው እንደሚገኝ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩ ነዋሪዎች፣ ቤታቸው ከመፍረሱ በፊት፣ መንግሥት ቃል ገብቶላቸው የነበረው የሁለት ዓመት የቤት ኪራይ ክፍያ እንዳልተፈፀመላቸው፣ ምትክ ቦታም እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል። በወንዝ ዳር ልማት ምክንያት፣ ቤታቸው እየፈረሰ እንደሚገኝ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ወደየ ዘመዶቻቸው እንዲጠጉ አሊያም ተከራይተው እንዲኖሩ መፍትሔ ከጠየቋቸው ኃላፊዎች እንደተነገራቸው ተናግረዋል። “ከተማችን እንድትቀየር እንፈልጋለን፣ ልማቱንም እንደግፋለን” በማለት የተናገሩት አስተያየት ሰጭዎቹ፣ ኾኖም መንግሥት ቅድሚያ ማረፊያ እንዲያዘጋጅላቸው፣ ጊዜም እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ስለ ጉዳዩ ምላሽ የሰጠው ክፍለ ከተማው በበኩሉ፣ ለልማት ተነሺዎቹ ምትክ ቦታ መስጠቱን እና የካሳ ክፍያ ለመፈፀምም እየሠራ መኾኑን ገልጿል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሂዩማን ራይትስ ዋች የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኅይሎችን ሴቶችን በመድፈር ወንጀል ከሰሰ

የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ተዋጊዎች እና ተባባሪ ታጣቂዎች፣ ደቡባዊ ኮርዶፋን ክፍለ ግዛት ውስጥ አዋቂ ሴቶች እና ልጃገረዶችን ደፍረዋል፣ ሌሎችም ወሲባዊ �
የአሜሪካ ድምፅ

ሂዩማን ራይትስ ዋች የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኅይሎችን ሴቶችን በመድፈር ወንጀል ከሰሰ

የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ተዋጊዎች እና ተባባሪ ታጣቂዎች፣ ደቡባዊ ኮርዶፋን ክፍለ ግዛት ውስጥ አዋቂ ሴቶች እና ልጃገረዶችን ደፍረዋል፣ ሌሎችም ወሲባዊ ጥቃቶችን ፈጽመዋል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች ከሰሰ። በታጣቂዎቹ የተፈጸመው ጥቃት የጦር ወንጀል መኾኑን አመልክቷል። የሰብአዊ መብት ቡድኑ በማያያዝ አድራጎቱ የሱዳንን ሲቪሎች ከጥቃት የሚጠብቅ እና ሰለባዎቹም ፍትሕ እንዲያገኙ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ርምጃ በአስቸኳይ መወሰድ እንዳለበት አጥብቆ የሚያሳስብ መኾኑን አመልክቷል። መሐመድ ዩሱፍ ለቪኦኤ ከናይሮቢ ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

ዩክሬይን ሞስኮ ውስጥ የሩስያን ጄኔራል ለገደለው የቦምብ ፍንዳታ ኃላፊነት ወሰደች

የሩስያ የኑክሌር ባዮሎጅካዊ እና ኬሚካል መከላከያ ኃይል ዘርፍ አዛዥ የነበሩት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ዛሬ ማክሰኞ ሞስኮ ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ተገድለ�
የአሜሪካ ድምፅ

ዩክሬይን ሞስኮ ውስጥ የሩስያን ጄኔራል ለገደለው የቦምብ ፍንዳታ ኃላፊነት ወሰደች

የሩስያ የኑክሌር ባዮሎጅካዊ እና ኬሚካል መከላከያ ኃይል ዘርፍ አዛዥ የነበሩት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ዛሬ ማክሰኞ ሞስኮ ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ተገድለዋል፡፡ ዩክሬን ጄኔራሉን በሚኖሩበት ሕንጻ ደጃፍ መንገድ ላይ በቆመ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ (ስኩተር) ላይ እንዳይታይ ተደርጎ በተጠመደ ቦምብ መግደሏን አስታውቃለች፡፡ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ እና ረዳታቸው የተገደሉት በደቡብ ምስራቅ ሞስኮ ከሚገኘው መኖሪያቸው ወደ ሥራ ለመሄድ እየወጡ በነበረበት ወቅት መሆኑን የሩሲያ የምርመራ ቡድን አስታውቋል፡፡ ፍንዳታው ከተፈፀመበት ቦታ የወጣው ቪዲዮ የተቃጠለ የህንጻው የፊት ለፊት ገጽታ፣ የተሰባበሩ ጡቦች እና መስኮቶችን ያሳያል። የቦምብ ጥቃቱ የደረሰው ኪሪሎቭን ለሦስት አመታት በዘለቀው ጦርነት የሩስያ ሃይሎች በዩክሬን ላይ ተጠቅመውታል በተባለው የኬሚካል ጦር መሣሪያ እጃቸው አለበት በሚል የዩክሬን አቃቤ ሕግ ክስ ከመሰረተባቸው ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑ ነው። ብሪታንያን እና ካናዳን ጨምሮ በርካታ ሀገሮች ኪሪሎቭን በጦርነቱ ከነበራቸው ሚና ጋራ በተያያዘ ባለፈው ጥቅምት ማዕቀብ ጥለውባቸው ነበር፡፡ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የዩክሬን የደኅንነት አገልግሎት ባለሥልጣን ከጥቃቱ ጀርባ ኤጀንሲው እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ ባለሥልጣኑ ኪሪሎቭን “የጦር ወንጀለኛው ሙሉ በሙሉ ሕጋዊ ኢላማ” ነበር ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የሩሲያ የዜና ማሰራጫዎች ቦምቡ በርቀት መቆጣጠሪያ እንደፈነዳ ዘግበዋል፡፡ ዋናው የሩሲያ መንግሥት የምርመራ ተቋም በበኩሉ የጄኔራል ኪሪሎቭን ሞት የሽብርተኝነት ምርመራ የከፈተበት መሆኑን አስታውቋል፡፡ የሩሲያ ባለሥልጣናት «ዩክሬንን እንቀጣታለን» ሲሉ ዝተዋል፡፡

ተመድ ለሦሪያውያን የሚደረገው የሰብአዊ ርዳታ እንደሚጨምር ተስፋ አድርጓል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሦሪያውያን ሰብአዊ ርዳታ ለማስገባት ተስፋ እንዳለው የድርጅቱ ባለሥልጣናት ዛሬ ማክሰኞ ተናግረዋል፡፡ የአውሮፓ ሀገራት በ�
የአሜሪካ ድምፅ

ተመድ ለሦሪያውያን የሚደረገው የሰብአዊ ርዳታ እንደሚጨምር ተስፋ አድርጓል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሦሪያውያን ሰብአዊ ርዳታ ለማስገባት ተስፋ እንዳለው የድርጅቱ ባለሥልጣናት ዛሬ ማክሰኞ ተናግረዋል፡፡ የአውሮፓ ሀገራት በበኩላቸው ለበርካታ ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆዩትን ፕረዝደንት ባሻር አል አሳድን ካስወገዱት አማጺያን ጋራ የሚያደርጉትን ንግግር ቀጥለዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ኃላፊ ቶም ፍሌቸር ከአማፂያኑ መሪ አህመድ አል ሻራ ጋራ “ገንቢ ውይይት” ማድረጋቸውን ገልጸው ይህም “ወሳኝ የኾኑ የሰብአዊ ድጋፎችን መጠን ለማሳደግ የሚያመቻች መሠረት ይሆናል” ብለዋል ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴረዥ፣ በበኩላቸው በሦሪያ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ባሻር የሚመራው መንግሥት የሰብአዊ ረድኤት ሠራተኞችን ለመጠበቅ፣ የሰብአዊ ርዳታ አገልግሎቶች በሁሉም ድንበሮች በኩል እንዲገቡ ለማስቻል እና ለሰብአዊ ረድኤት ሠራተኞች ፈቃድ እና ቪዛ ለማፋጠን የገባውን ቃል በደስታ መቀበላቸውን ተናግረዋል። በሦሪያ የፈረንሳይ ልዩ መልዕክተኛ ዣን ፍራንሲስ ጊላሜ ዛሬ ማክሰኞ ሦሪያን በጎበኙበት ወቅት «ፈረንሳይ በሽግግራቸው ወቅት ከሶሪያውያን ጋራ ለመኾን በዝግጅት ላይ ነች» ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የፈረንሳዩ ልዩ መልዕክተኛ ሽግግሩን ከሚመሩት ጋራ ለመወያየት በቅርቡ ወደ ሦሪያ ከሄዱት ልዑካን መካከል አንዱ ናቸው። የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ዲፕሎማቶቹ በደማስቆ ከአማፂያን መሪዎች ጋራ ዛሬ የመጀመሪያውን ውይይት እንደሚያደርጉ ገልጿል። የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ካያ ካላስ በበኩላቸው ኅብረቱ ለሶሪያ የሚያደርገውን ሰብአዊ ርዳታ እያጠናከረ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ የሦሪያን «የዲሞክራሲ ምኞት» እንዴት እንደሚደግፍ ኅብረቱ እያጤነ መኾኑንም የውጭ ፖሊሲ ኃላፊዋ ተናግረዋል።

እስራኤል ከጦርነቱ በኋላ የጋዛን ጸጥታ ለመቆጣጠር ሐሳብ እንዳላት አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር፣ «እስራኤል ካትዝ  ሃገራቸው ከሃማስ ጋራ የምታካሂደውን ጦርነት ካጠናቀቀች በኋላም የአካባቢውን ደኅንነት ትቆጣጠራለች&raqu
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል ከጦርነቱ በኋላ የጋዛን ጸጥታ ለመቆጣጠር ሐሳብ እንዳላት አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር፣ «እስራኤል ካትዝ  ሃገራቸው ከሃማስ ጋራ የምታካሂደውን ጦርነት ካጠናቀቀች በኋላም የአካባቢውን ደኅንነት ትቆጣጠራለች» ብለዋል፡፡ የመከላከያ ሚንስትሩ ዛሬ ማክሰኞ በX ማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባወጡት ጹሑፍ  «የሃማስን ወታደራዊ እና የመንግሥት አቅም  ካስወገደች በኋላ እስራኤል ጋዛ ላይ የፀጥታ ቁጥጥር ለማድረግ ሙሉ በሙሉ የመንቀሳቀስ ነፃነት ታገኛለች» ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ጋዛን በሚመለከት ያላቸውን ሐሳብ  በዌስት ባንክ ይዞታዎቿ ወታደሮቿ  የሽብርተኞችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር  ከሚያደርጉት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጋራ አመሳስለውታል፡፡ ይህ የእስራኤል ጋዛን የመቆጣጠር ፍላጎት ግን ከጦርነት በኋላ ሊኖር በሚገባው ሁኔታ ላይ አሜሪካና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ ሌሎች ካላቸው ምልከታ ጋራ ይጻረራል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በጥቅምት ወር ሲናገሩ የጋዛ ጦርነት መቆም «ሀማስ እንደሚወጣ  እስራኤልም እንደማትቆይ በሚያረጋግጥ መንገድ» መኾን እንዳለበት አሳስበዋል፡ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ በበኩላቸው    ድርጅታቸው አንዳንድ የዌስት ባንክን አካባቢዎች የሚያስተዳድረው የፍልስጤም አስተዳደር ጋዛንም ይቆጣጠራል ብለው እንደሚገምት ባለፈው መስከረም ተናግረዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋዛ የጤና ኃላፊዎች እስራኤል ዛሬ ባደረሰችው ጥቃት ዐስር ሰዎች መገደላቸውን አስታውቀዋል፡፡ የእስራኤል ጦር በበኩሉ በደቡባዊ ጋዛ ባካሄደው ወታደራዊ ጥቃት ላይ ሁለት ወታደሮቹ መገደላቸውን አስታውቋል፡፡

Get more results via ClueGoal