ዶናልድ ትረምፕና ኢላን መስክ በምክር ቤት የቀረበውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅ ቀረ
newsare.net
ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና ባለ ሀብቱ ኢላን መስክ በአሜሪካ ምክር ቤት በሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነት ቀርቦ የነበረውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅዶናልድ ትረምፕና ኢላን መስክ በምክር ቤት የቀረበውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅ ቀረ
ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና ባለ ሀብቱ ኢላን መስክ በአሜሪካ ምክር ቤት በሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነት ቀርቦ የነበረውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅ ቀርቷል። የወቅቱ የበጀት ዓመት ነገ ዐርብ ሌሊት ስለሚጠናቀቅ፣ ከዚያ በፊት በምክር ቤቱ በጀት የማይጸድቅ ከኾነ በርካታ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሥራ ሊያቆሙ ወይም ‘አስፈላጊ’ ተብለው ከተመደቡ የመንግሥት ሠራተኞች ውጪ የሆኑት ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ሥራ ላይገቡ ይችላሉ። ሥራቸውን የሚቀጥሉትም ቢሆኑ በጀቱ እስከሚለቀቅ ካለ ደመወዝ ሊሠሩ እንደሚችሉ ታውቋል። ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና ተመራጩ ምክትል ፕሬዝደንት ጄ ዲ ቫንስ ትላንት በጋራ ባወጡት መግለጫ የቀረበው የበጀት ረቂቅ «ወደዲሞክራቶቹ ፍላጎት ያጋደለ ነው» በሚል ተቃውመዋል። በመጪው የትረምፕ አስተዳደር የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ብዛት፣ ፕሮግራሞች እና ሠራተኞች ለመቀነስ የተቋቋመውን ቡድን ከሚመሩት አንዱ የሆኑት ባለ ሀብቱ ኢላን መስክ “እጅግ የበዛ ወጪ የሚያስከትል” ብለው የበጀት ሐሳቡን ውድቅ አድርገዋል። በጀቱን የሚደግፉ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባላት ከሁለት ዓመት በኋላ በሚደረገው ምርጫ መራጮች በድምጻቸው ሊቀጧቸው እንደሚችሉ ኢላን መስክ ዝተዋል። ሪፐብሊካን የም/ቤት ዓባላት በበጀቱ ላይ እንደገና እንዲደራደርሩ ጥሪ ያደረጉት ትረምፕ፣ ያንን የማያደርጉ ከሆነ “ሀገርን እንደመክዳት ይቆጠራል” ብለዋል። የፕሬዝደንት ጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን ከመጠናቀቁ በፊትም የሀገሪቱ የዕዳ ጣሪያ ከፍ እንዲል ትረምፕ ጠይቀዋል። የባይደን አስተዳደር የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የመዝጋቱን ሐሳብ ነቅፏል። Read more