ቀጣይ በጀቱን ለመወሰን ጥቂት ሰዓታት የቀሩት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክርቤት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል
newsare.net
ዴሞክራቶች እና አንዳንድ ሪፐብሊካኖች የዕዳ ጣሪያውን እስከ አውሮፓውያኑ 2027 ድረስ ለማራዘም ያቀረቡትን ጥያቄ ከተቃወሙ በኋላ ሐሙስ ዕለት በHግ መወሰኛ ምክርቀጣይ በጀቱን ለመወሰን ጥቂት ሰዓታት የቀሩት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክርቤት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል
ዴሞክራቶች እና አንዳንድ ሪፐብሊካኖች የዕዳ ጣሪያውን እስከ አውሮፓውያኑ 2027 ድረስ ለማራዘም ያቀረቡትን ጥያቄ ከተቃወሙ በኋላ ሐሙስ ዕለት በHግ መወሰኛ ምክርቤቱ በችኮላ የተደረገው ድርድር ከሽፏል። ለውጡ የመጣው ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ኤሎን መስክ መንግሥትን እስከ መጭው መጋቢት ድረስ በገንዘብ ለመደገፍ የተጠየቀውን የሁለትዮሽ ስምምነት ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው። የአሜሪካ ድምጽ የኮንግረስ ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን እና አሶሽየትድ ፕሬስን ዘገባዎች ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more