የአሜሪካ ሴኔት ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታደገውን በጀት አጸደቀ
newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የአሜሪካ መንግሥትን እስከ መጋቢት የሚያቆየውን በጀት አጸደቀ። በሪፐብሊካን ተመራጮች ብዙኅን ድምፅ ስርየአሜሪካ ሴኔት ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታደገውን በጀት አጸደቀ
የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የአሜሪካ መንግሥትን እስከ መጋቢት የሚያቆየውን በጀት አጸደቀ። በሪፐብሊካን ተመራጮች ብዙኅን ድምፅ ስር ያለው የሕግ መምሪያ ምክር ቤት እና በዲሞክራት አብላጫ ቁጥጥር ስር ያለው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት፣ ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታገደውን በጀት ትላንት እኩለ ሌሊት ላይ አጽድቀዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የበጀት ረቂቁን እንደሚደግፉና ሕግ እንዲኾን እንደሚፈርሙ ትላንት ዐርብ ተናግረው ነበር። የጸደቀው በጀት ሕግ ኾኖ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ፣ መንግሥቱን እስከ መጪው መጋቢት የሚያቆየው በጀት ይኾናል። 100 ቢሊዮን ዶላር ለአደጋዎችና ለርዳታ፣ 10 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ለግብርና ሥራ ድጋፍ በበጀቱ ተይዟል። የጸደቀው በጀት የፌደራል መንግሥቱን የዕዳ ጣሪያ ከፍ እንዲል አያደርግም። Read more