Ethiopia



የሴቶች ውክልና እና ሴቶችን ማብቃት በኢትዮጵያ

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የላቀ ብዛት ያላቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የሚኒስትር ቦታዎች እና የፍትህ አ

የአቶ ክርስቲያን እና የአቶ ዮሐንስ የእስር ቤት አያያዝ እንደሚያሳስባቸው ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገለፁ

በቅርቡ የቀዶ ሕክምና የተደረገላቸው የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ወደ ሌላ እስር ቤት መዛወራቸውን ቤተሰቦቻቸው እ
የአሜሪካ ድምፅ

የአቶ ክርስቲያን እና የአቶ ዮሐንስ የእስር ቤት አያያዝ እንደሚያሳስባቸው ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገለፁ

በቅርቡ የቀዶ ሕክምና የተደረገላቸው የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ወደ ሌላ እስር ቤት መዛወራቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገልፀዋል፡፡ ሁለቱ ታሳሪዎች “ከፍተኛ ሕመም እየተሰማቸው ነው ወደ ቂሊንጦ የተዛወሩት” ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ በተለይ አቶ ዮሐንስ የሚገኙበት ማቆያ ሥፍራ ለጤንነታቸው የሚያሰጋቸው እንደኾነ ተናግረዋል፡፡ ይህ ሁኔታ እንዲቀየር ለፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልፀዋል፡፡ የቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ዳይሬክተር ኮማንደር ዓለምሰገድ፣ ውንጀላውን አስተባብለዋል፡፡

በሞዛምቢክ ተቃውሞው ቀጥሎ ተጨማሪ 21 ሰዎች ሞቱ  

በሞዛምቢክ የሕገ መንግሥቱ ም/ቤት ገዢው ፓርቲ ባለፈው መስከረም መጨረሻ ላይ የተደረገውን ምርጫ እንዳነሸነፈ ማወጁን ተከትሎ ባለፉት 24 ሠዓታት ውስጥ በተደረ
የአሜሪካ ድምፅ

በሞዛምቢክ ተቃውሞው ቀጥሎ ተጨማሪ 21 ሰዎች ሞቱ  

በሞዛምቢክ የሕገ መንግሥቱ ም/ቤት ገዢው ፓርቲ ባለፈው መስከረም መጨረሻ ላይ የተደረገውን ምርጫ እንዳነሸነፈ ማወጁን ተከትሎ ባለፉት 24 ሠዓታት ውስጥ በተደረገ ተቃውሞ ሁለት ፖሊሶችን ጨምሮ ቢያንስ 21 ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። አጨቃጫቂውን የምርጫ ውጤት ተከትሎ የሃገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ም/ቤት ገዢው ፍሬሊሞ ፓርቲ ማሸነፉን እንዳስታወቀ የተቃዋሚው መሪ ቬናሲዮ ሞንድላኔ ተቃውሞ እንዲደረግ ትላንት ጥሪ አድርገው ነበር። ከእአአ 1975 ጀምሮ ላለፉት አምሳ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው የፍሬሊሞ ፓርቲ ባለፈው መስከረም መጀመሪያ ላይ በተደረገው ምርጫ አሸናፊ መሆኑ ከታወጀ ወዲህ በሃገሪቱ ለሳምንታት በርካታ ሕይወት የቀጠፈ ተቃውሞ ተደርጓል። እስከ አሁን 150 ሰዎች ከምርጫው ጋራ በተያያዘ ሁከት ህይወታቸው አልፏል። የገዢው ፓርቲ እጩ ዳንኤል ቻፖ አሸናፊ እንደሆኑ ቢነገርም፣ በአብዛኛው ወጣቶች የሆኑ የተቃዋሚው ቬናሲዮ ሞንድላኔ ደጋፊዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ አድርገዋል። በውጤቱ ቻፖ 65 በመቶውን ድምጽ እንዳገኙ ሲነገር፣ ሞንድላኔ ደግሞ 24 በመቶ እንዳገኙ ታውቋል። ባለፉት 24 ሰዓታት 236 የሚሆኑ ጥቃቶች ተፈፅመው ሁለት ፖሊሶችን ጨምሮ የ21 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 13 ሲቪሎችና 12 ፖሊሶች ደግሞ መጎዳታቸውን የሃገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል። በመዲናዋ ማፑቶ ሱቆች ሲዘረፉና ሲቃጠሉ የሚያሳዩ ምስሎች በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ታይተዋል፡፡

ሩሲያ በገና ዕለት የዩክሬንን የኃይል መሠረተ ልማቶች መታች

ሩሲያ በዩክሬን የነዳጅ እና ሌሎችም የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ተከታታይ የሚሳዬል ጥቃት መፈጸሟንና በርካቶች በዛሬው ገና ዕለት ካለ ኤሌክቲሪክ ኅይል መቅረ
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ በገና ዕለት የዩክሬንን የኃይል መሠረተ ልማቶች መታች

ሩሲያ በዩክሬን የነዳጅ እና ሌሎችም የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ተከታታይ የሚሳዬል ጥቃት መፈጸሟንና በርካቶች በዛሬው ገና ዕለት ካለ ኤሌክቲሪክ ኅይል መቅረታቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በጥቃቱ 78 የአየር እና የምድር ተወንጫፊ ሚሳዬሎች እንዲሁም 106 ሻሂድ እና ሌሎች ዓይነት ድሮኖች ጥቅም ላይ መዋላቸው ታውቋል። በርካታ ዩክሬናውን በገና ዕለት በምድር ውስጥ የባቡር ጣቢያዎች ለመጠለል ተገደዋል። በጥቃቱ ቢያንስ አንድ ሰው ሳይሞት እንዳልቅረ ተነግሯል። በተለይም በካርኪቭ ክልል በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በቀዝቃዛው ወቅት ሙቀት ማግኘት እንዳልቻሉም ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በሌላ በኩል ሩሲያ ውስጥ አንድ ድሮን በአየር ላይ ተመቶ ፍርስራሹ ሲወድቅ የአንዲት ሴትን ሕይወት ሲያጠፋ ሦስት ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል። “ፑቲን ሆን ብለው በገና ዕለት ጥቃቱን ፈጽመዋል። ከዚህ በላይ ኢሰብአዊነት አለን?” ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። “ሩሲያ በመላው ዩክሬን ኅይል እንዲቋረጥ በማጥቃት ላይ ነች” ሲሉም አክለዋል። አንድ ሚሳዬል የሞልዶቫንና የሮማንያን የአየር ክልል አልፎ እንደመጣ የዩክሬኑ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር አንድሪል ሲቢሃ አስታውቀዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጥቃት የጀመረችው ከሁለት ዓመታት በፊት በገና ዋዜማ መሆኑ ይታወሳል።

የየመን አማፂያን ሚሳዬል ወደ ቴል አቪቭ አስወነጨፉ

የየመን አማፂያን ወደ ቴል አቪቭ፣ እስራኤል ዛሬ ረቡዕ ሚሳዬል ማስወንጨፋቸውን አስታውቀዋል። ጥቃቱ የአደጋ ማስጠንቀቂያ እንዲደወል ሲያደርግ፣ ጉዳት ግን አ
የአሜሪካ ድምፅ

የየመን አማፂያን ሚሳዬል ወደ ቴል አቪቭ አስወነጨፉ

የየመን አማፂያን ወደ ቴል አቪቭ፣ እስራኤል ዛሬ ረቡዕ ሚሳዬል ማስወንጨፋቸውን አስታውቀዋል። ጥቃቱ የአደጋ ማስጠንቀቂያ እንዲደወል ሲያደርግ፣ ጉዳት ግን አላደረሰም ተብሏል። የእስራኤል ሠራዊት በበኩሉ ሚሳዬሉ ድንበር ከማቋረጡ በፊት መመታቱን አስታውቋል። ሁቲዎች ሚሳዬል ሲያስወነጭፉ በሁለት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። በጋዝ ሰርጥ እስራኤል በምታካሂደው ጦርነት ከፍልስጤማውያን ጋራ ያላቸውን አንድነት ለማሳየት እንደሆነ የሁቲ አማጺያን አስታውቀዋል። በእስራኤል ላይ ሚሳዬል ከማስወንጨፍ በተጨማሪ፣ ሁቲዎች በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ በሚተላለፉ መርከቦች ላይ ጥቃት በመፈጸማቸው ቁልፍ የሆነው የንግድ መርከቦች መተላለፊያ ተስተጓጉሏል። የእስራኤል ባለሥልጣናት በበኩላቸው በኢራን በሚደገፉት ሁቲዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ በመዛት ላይ ናቸው። በሌላ በኩል የእስራኤል ሠራዊት ባደረገው ምርመራ፣ ሠራዊቱ በጋዛ በመገኘቱ ምክንያት ባለፈው ነሐሴ ስድስት ታጋቾች መሞታቸውን ትላንት አስታውቋል። እንደ ምርመራው ውጤት ከሆነ፣ ሠራዊቱ መግባቱን ተከትሎ፣ ሐማስ አንድ ትውልደ እስራኤል የሆነ አሜሪካዊን ጨምሮ ስድስት ታጋቾችን ለ330 ቀናት ከያዙ በኋላ ገድለዋል። እስራኤል በጋዛ በምታካሂደው ጦርነት እስከ አሁን 45 ሺሕ ሰዎች እንደተገደሉ የፍልስጤማውያኑ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያስታውቃል።

የሶማሊያው ፕሬዝደንት አሥመራ ገቡ

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል አንካራ ላይ ሥምምነት ከተፈፀመ ወዲህ የሶማሊያው ፕሬዝደንት በቀጠናው ጉብኝት ሲያደርጉ የመጀመሪያው ነው። ሃሳን ሼክ ሞሃ
የአሜሪካ ድምፅ

የሶማሊያው ፕሬዝደንት አሥመራ ገቡ

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል አንካራ ላይ ሥምምነት ከተፈፀመ ወዲህ የሶማሊያው ፕሬዝደንት በቀጠናው ጉብኝት ሲያደርጉ የመጀመሪያው ነው። ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ አሥመራ ሲደርሱ በኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በሚያሳድጉበትና በዓለም አቀፍና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ የኤርትራው የማስታወቂያ ምኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በX ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል። የፕሬዝደንት ሃሳን ጉብኝት የመጣው ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ በመካከላቸው ያለውን ውጥረት ለማርገብ ከሁለት ሳምንታት በፊት አንካራ ላይ ሥምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ ነው። ሁለቱ ሀገራት አንዱ የሌላውን ሉአላዊነት፣ እንዲሁም የግዛት አንድነት እንደሚያከብር በፈጸሙት ሥምምነት አስታውቀዋል። ሁለቱ ወገኖች በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለንግድ ጠቀሜታ የባሕር አቅርቦት እንዲኖራት ውይይት እንደሚያደርጉ ተስማምተዋል። አሥመራ ባለፈው ጥቅምት የግብጽ እና የሶማሊያን መሪዎች ለሦስትዮሽ ውይይት ጋብዛ አስተናግዳለች። በውይይቱ የሦስቱ ሃገራት መሪዎች የሶማሊያን ተቋማት ለማጠናከርና ከውስጥና ከውጪ የገጠሟትን ተግዳሮቶች ለመጋፈጥ ተስማምተዋል። በተጨማሪም የሶማሊያ ፌዴራል ሠራዊት ሽብርን እንዲጋፈጥና የሃገሪቱን ሉአላዊ ግዛት እንዲከላከል ለማስቻል ተስማምተዋል። የሶማሊያው ፕሬዝደንት ከሁለት ዓመታት በፊት ከተመረጡ ወዲህ አሥመራን ሲጎበኙ ለስምንተኛ ጊዜ ነው። ኤርትራ በርካታ የሶማሊያ ጦር ዓባላትን በማሠልጠን ላይ ስትሆን፣ የተወሰኑት ሥልጠናቸውን አጠናቀው ተመልሰዋል። ሶማሊያ፣ ግብጽ በአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ውስጥ ተሳትፎ ለማድረግ መወሰኗን በመልካም እንደምትቀበል አስታውቃለች፡፡

የወንዶች ስንፈተ ወሲብ መንስኤ እና መፍትሄ

የዩናይትድ ስቴትስ የጆንስ ሆፕኪንስ ማዕከል የጤና ባለሞያዎች 'የወንዶች ስንፈተ ወሲብ' በአብዛኛው ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ እንደሚከሰት ጠቁመዋል። የስኳ
የአሜሪካ ድምፅ

የወንዶች ስንፈተ ወሲብ መንስኤ እና መፍትሄ

የዩናይትድ ስቴትስ የጆንስ ሆፕኪንስ ማዕከል የጤና ባለሞያዎች 'የወንዶች ስንፈተ ወሲብ' በአብዛኛው ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ እንደሚከሰት ጠቁመዋል። የስኳር በሽታ፣ የልብ ህመም እና ቅጥ ያጣ እና ከመጠን ያለፈ  ውፍረት መንስኤ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። /የዚህ ሳምንት ኑሮ በጤንነት ችግሩን እና መፍትሄዎቹን ይቃኛል/

ምርታቸውን በከፍተኛ ዋጋ የሸጡ የቡና ገበሬዎች

ቡናቸውን በቀጥታ ለዓለም አቀፍ ገበያ ያቀረቡ የሲዳማ አርሶ አደሮች የቡና ምርታቸውን በከፍተኛ ዋጋ መሸጣቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። በዓለም አቀፍ ደረጃ
የአሜሪካ ድምፅ

ምርታቸውን በከፍተኛ ዋጋ የሸጡ የቡና ገበሬዎች

ቡናቸውን በቀጥታ ለዓለም አቀፍ ገበያ ያቀረቡ የሲዳማ አርሶ አደሮች የቡና ምርታቸውን በከፍተኛ ዋጋ መሸጣቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። በዓለም አቀፍ ደረጃ የልዩ ጣዕም ቡና ባለቤቶችን በየዓመቱ እያወዳደረ የሚሸልመው ካፕ ኦፍ ኤክሰሌንሲ (COE) የተባለ ዓለም አቀፍ ድርጀት የኢትዮጵያ ፕሮጀከት ማናጀር አቶ እንዳለ አስፋው ከኢትዮጵያ የ600 አርሶ አደሮች ቡና ተወዳድሮ የ40ዎቹ ቡና አሸናፊ መኾኑን አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዲሬክተር ዶ.ር አዱኛ ደበላ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም በከፍተኛ ዋጋ መሸጡን ተናግረዋል። የCOE ዕውቅና መርኃ ግብር የአርሶ አደሮች በጥራት እንዲያመርቱ አነሳስቷቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ሁለተኛው የትረምፕ የስልጣን ዘመን እና ሰሜን ኮሪያ

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው በሰሜን ኮሪያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን በማጥበቅ የኒውክሊየር የጦር
የአሜሪካ ድምፅ

ሁለተኛው የትረምፕ የስልጣን ዘመን እና ሰሜን ኮሪያ

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው በሰሜን ኮሪያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን በማጥበቅ የኒውክሊየር የጦር መሣሪያ መርሃ ግብሯን እንድትሰርዝ ሊያስገድዷት ሞክረው ነበር። በሁለተኛው የአስተዳደር ዘመናቸው ትረምፕ ከሰሜን ኮሪያ ምን መጠበቅ እንደሚኖርባቸው የሚቃኝ ዘገባ የአሜሪካ ድምጹ ያንግ ጋዮ ኪም አጠናቅሯል። ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡    

ኬንያ በሴቶች ላይ ያነጣጠሩ ከ7ሺህ በላይ ጾታዊ ጥቃቶች መመዝገቧን አስታወቀች

የኬንያ መንግሥት ካለፈው ዓመት መስከረም ወር አንስቶ ባለው ጊዜ ከ7 ሺህ በላይ ወሲባዊ እና ጾታዊ ጥቃት መመዝገቡን አስታውቋል። ከነዚህ ውስጥ 100 የሚሆኑት ጥቃ
የአሜሪካ ድምፅ

ኬንያ በሴቶች ላይ ያነጣጠሩ ከ7ሺህ በላይ ጾታዊ ጥቃቶች መመዝገቧን አስታወቀች

የኬንያ መንግሥት ካለፈው ዓመት መስከረም ወር አንስቶ ባለው ጊዜ ከ7 ሺህ በላይ ወሲባዊ እና ጾታዊ ጥቃት መመዝገቡን አስታውቋል። ከነዚህ ውስጥ 100 የሚሆኑት ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች እና ልጃገረዶች የተመዘገቡት ደግሞ በዚህ ዓመት፣ ከነሐሴ ወር ወዲህ ባለው ጊዜ ነው። ይህን ተከትሎ የኬንያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የሴቶችን እና ልጃገረዶችን ጥቃት የሚከላከል ልዩ የጸጥታ ቡድን ማቋቋሙን አስታውቋል። መሐመድ ዩሱፍ በዚህ ዙሪያ ያደረሰንን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች።    

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ተደጋግሞ በሚደርሰው ርዕደ መሬት ነዋሪዎች ስጋታቸውን ገለጹ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ተደጋግሞ በሚደርሰው ርዕደ መሬት ምክንያት ሥጋት ውስጥ መውደቃቸውን የአካባቢው ኗሪዎች አስታወቁ፡፡ ትናንት እና ከትና
የአሜሪካ ድምፅ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ተደጋግሞ በሚደርሰው ርዕደ መሬት ነዋሪዎች ስጋታቸውን ገለጹ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ተደጋግሞ በሚደርሰው ርዕደ መሬት ምክንያት ሥጋት ውስጥ መውደቃቸውን የአካባቢው ኗሪዎች አስታወቁ፡፡ ትናንት እና ከትናንት በስቲያ ምሽት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ተፈጠረ በተባለው ርዕደ መሬት የፈንታሌ ተራራ አናት ላይ የጭስ ምልክት ታይቷል፣ የከባድ ፍንዳታ ድምጽ ተሰምቷል፣ የድንጋይ ናዳም ተስተውሏል ሲሉ ኗሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ ርዕደ መሬቱ የተፈጠረበት በአፋር ክልል ዞን ሦስት አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ወሃና ፍሳሽ አገልግሎት የመሬት መንቀጥቀጡንና ንዝረቱን ተከትሎ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ የአርብቶ አደሮች ፍየሎችና ግመሎች በድንጋጤ በርግገው መጥፋታቸውን ጠቁሟል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊሲክስ ህዋ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም በበኩሉ ላለፉት ስድስት ቀናት የመሬት መንቀጥቀጡ መከሰቱን አረጋግጦ የትናንቱ በሬክተር ስኬል 4.9 እንደሚለካ አመልክቷል፡፡

በሱዳን ረሃብ እየተስፋፋ ነው ተባለ

በጦርነት ትርምስ ውስጥ ባለችው ሱዳን ረሃብ በአምስት አካባቢዎች መስፋፋቱና ወደ ሌሎች ተጨማሪ አምስት አካባቢዎችም ሊስፋፋ እንደሚችል አንድ በዓለም ደረጃ ረ
የአሜሪካ ድምፅ

በሱዳን ረሃብ እየተስፋፋ ነው ተባለ

በጦርነት ትርምስ ውስጥ ባለችው ሱዳን ረሃብ በአምስት አካባቢዎች መስፋፋቱና ወደ ሌሎች ተጨማሪ አምስት አካባቢዎችም ሊስፋፋ እንደሚችል አንድ በዓለም ደረጃ ረሃብን የሚከታተል ተቋም አስታውቋል። በጦርነቱ የሚሳተፉ ወገኖች፣ በዓለም ትልቁ የረሃብ ቀውስ እንደሆነ ለሚነገረው የሱዳን ቸነፈር ተጠቂዎች ሰብአዊ ርዳታን ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ማስተጓጎል መቀጠላቸውን ተቋሙ ጨምሮ አስታውቋል። ‘የረሃብ ክትትል ኮሚቴ’ በሚል የሚታወቀው ተቋም ጨምሮ እንደገልጸው፣ ከበባ ውስጥ ባለችው የሰሜን ዳርፉር መዲና አል ፋሽር ውስጥ በሚገኙ ሁለት መጠለያዎች፣  እንዲሁም በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት በሚገኙ ሌሎች ሁለት አካባቢዎች ረሃብ ተስፋፍቷል። ባለፈው ነሐሴ በሰሜን ዳርፉር ዛምዛም መጠለያ የተከሰተው ረሃብ መቀጠሉንም ኮሚቴው አስታውቋል። የረሃብን ሁኔታ የሚያረጋግጠውና ደረጃ የሚያወጣው ተቋም እንዳስታወቀው፣ በሰሜን ዳርፉር ባሉ ሌሎች አምስት አካባቢዎችም ረሃቡ እንደሚስፋፋ ግምቱን አስቀምጧል። በመላ ሱዳን የሚገኙ አስራ ሰባት አካባቢዎች ደግሞ ለረሃብ ተጋላጭ መሆናቸውም ታውቋል። በሱዳን 24፡6 ሚሊዮን የሚሆነው ወይም ከአጠቃላይ ሕዝቡ ግማሽ የሚሆነው እስከሚቀጥለው ወር ድረስ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚሻ ኮሚቴው አስታውቋል። ኮሚቴው በሱዳን የሚያደርገውን የምግብ ዋስትና ጥናት መንግስት እያስተጓጎለበት እንደሆነ ገልጿል። የሱዳን መንግሥትም የኮሚቲው ሪፖርት “ተአማኒ አይደለም” በሚል በጥናቱ መሳተፉን እንዳቆመ አስውቋል።

የቀድሞው ፕሬዝደንት ቢል ክሊንተን ሆስፒታል ገቡ

የቀድሞው ፕሬዝደንት ቢል ክሊንተን ትኩሳት ስለገጠማቸው ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሜድስታር ጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ገብተዋል። የ78 ዓመቱ የቀድሞ ፕ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞው ፕሬዝደንት ቢል ክሊንተን ሆስፒታል ገቡ

የቀድሞው ፕሬዝደንት ቢል ክሊንተን ትኩሳት ስለገጠማቸው ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሜድስታር ጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ገብተዋል። የ78 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝደንት ለምርመራ ትላንት ከሰዓት በኋላ ሆስፒታል መግባታቸውንና በጥሩ ሁኔታ መሆናቸውን እንዲሁም ለሚሰጣቸው ክብካቤ ማመስገናቸውን የክሊንተን ጽ/ቤት ምክትል ኅላፊ ኤንጀል ኡሬና ተናግረዋል። እአአ ከ1993 እስከ 2001 የአሜሪካ ፕሬዝደንት የነበሩት ክሊንተን፣ በዚህ ዓመት በተካሄደው ምርጫ በዲሞክራቲክ ፓርቲው ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሄሪስ ለፕሬዝደንትነት ባደረጉት ዘመቻም ቅስቀሳ በማድረግ ተሳትፈዋል። ክሊንተን ሥልጣን ከለቀቁ ወዲህ የጤና እክል ሲደጋግማቸው ቆይቷል። እአአ በ2004 የደረት ውጋትና የትንፋሽ ማጠር ህመም ከገጠማቸው በኋላ ከፍተኛ የልብ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸዋል። በዓመቱ፣ 2005 ሳንባቸው በከፊል እክል ገጥሞት ነበር። እአአ 2010 ደግሞ የደም መዘዋወሪያ ሥር (ኮሮናሪ አርተሪ) መተላለፊያ ቱቦ ገብቶላቸዋል። ክሊንተን ሥጋ መመገብ አቁመው አትክልት መመገብን በማዘውተራቸው ክብደታቸውን በጣም ለመቀነስ ችለዋል። የኮቪድ ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በነበረበት 2021 ለስድስት ቀናት ካሊፎርኒያ የሚገኝ ሆስፒታል ገብተው የነበረ ሲሆን፣ ህመማቸው ከኮቪድ ጋራ የተገናኘ ሳይሆን በሽንት መተላለፊያ ላይ ባጋጠመ ማመርቀዝ ምክንያት ነበር።

ሶማሊያ “የኢትዮጵያ ኅይሎች አጥቅተውኛል” ስትል ክስ አሰማች

ሶማሊያ የኢትዮጵያ ኅይሎች “ሳይነኩና ባልተጠበቀ” ባለችው ሁኔታ በሁለቱ ሀገራት ድንበር መካከል  በሶማሊያ በኩል ባለችው ዶሎው ከተማ ላይ በሚገኝ ሠራዊቷ ላ
የአሜሪካ ድምፅ

ሶማሊያ “የኢትዮጵያ ኅይሎች አጥቅተውኛል” ስትል ክስ አሰማች

ሶማሊያ የኢትዮጵያ ኅይሎች “ሳይነኩና ባልተጠበቀ” ባለችው ሁኔታ በሁለቱ ሀገራት ድንበር መካከል  በሶማሊያ በኩል ባለችው ዶሎው ከተማ ላይ በሚገኝ ሠራዊቷ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ስትል ከሳለች፡፡ የሶማሊያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በአወጣው  መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ኅይሎች ዛሬ ጠዋት አራት  ሠዓት ላይ በከተማዋ በሶማሊያ መንግሥት ኅይሎች ሥር በነበሩ ሶስት ይዞታዎች ላይ የኢትዮጵያ ኅይሎች ጥቃት ፈጽመዋል ብሏል። ድርጊቱ የአንካራውን ስምምነት የጣሰ ነው ስትልም ሶማሊያ አስታውቃለች፡፡ ከኢትዮጵያ ጋራ በምትዋሰነው የሶማሊያዋ ዶሎው ከተማ በጁባላንድ ኅይሎች እና በሶማሊያ የመንግሥት ወታደሮች መካከል ዛሬ ግጭት መከሰቱ ቀደም ብሎ ተነግሮ ነበር። በከተማይቱ በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች ይገኛሉ። ከተማዋ በአብዛኛው ሞሃመድ ሁሴን አብዲ ላፌ በተባሉ ኮሚሽነር ሥር የምትደዳር ሲሆን፣ ኮሚሽነሩ ከኢትዮጵያ ኅይሎች ጋራ የቅርብ ግንኙነት እንዳላቸው ታውቋል። አንድ የከተማዋ ነዋሪ የኢትዮጵያ ኅይሎች ለኮሚሽነሩ ኅይሎች “ወግነዋል” ሲል ተናግሯል። ተፈጥሯል የተባለውን ክስተት በተመለከተ ከኢትዮጵያ ወገን ወዲያውኑ የተሰጠ ምላሽ የለም። ቪኦኤ በዛሬው ዶሎው ተከስቷል ስለተባለው ግጭት የኢትዮጵያ ኅይሎችን ሚና በገለልተኛ ወገን አላረጋገጠም። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶማሊያ መንግሥት ሁለት ባለሥልጣናትን ዛሬ ሰኞ ወደ ግብፅ እና ኢትዮጵያ መላኩ ታውቋል። የሶማሊያው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ ካይሮ ተገኝተው ከሀገሪቱ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ባድር አብደላቲ ጋራ እንደተነጋገሩ ሲታወቅ በሌላ በኩል ደግሞ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ዴታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ወደ አዲስ አበባ መጓዛቸው ታውቋል። የሶማሊያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በአወጣው መግለጫ ብፊቂ እና በአብደላቲ መካከል የተደረገው ውይይት ታሪካዊ ግንኙነታቸውን በማጠናከር፣ እንዲሁም በፀጥታ፣ ፖለቲካ፣ ትምህርት፣ እና የኢኮኖሚ ልማትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር አስታውቋል። ሁለቱ ምኒስትሮች “ውጤታማ ውይይት” አድርገዋል ሲሉ የግብጹ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ታሚም ካላፍ አስታውቀዋል። ሁለቱ ምኒስትሮች “ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩበት፣ በፀረ ሽብርተኝነት ላይ በሚደረግ ትብብር፣ እንዲሁም በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የማረጋጋትና ድጋፍ ልዑክ ምሥረታ በሚሳለጥበት መንገድ ላይ ተወያይተዋል” ሲሉ ቃል አቀባዩ በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ አመልክተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ዴታ አሊ ሞሃመድ ኦማር፣ የቱርክ መንግስት የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ አስመልክቶ አንካራ ላይ ስምምነት እንዲፈረም ባስቻለ በጥቂት ግዜያት ውስጥ ወደ አዲስ አበባ መጓዛቸው ታውቋል። የሶማሊያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ “ጉብኝቱ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋራ ለሚኖራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላትን የማያወላውል ቁርጠኝነት የሚያመለከት ነው” ብሏል። ”ጉብኝቱ በጋራ መከባበር፣ በጋራ ፍላጎትና ትብብር ላይ የተመሠረቱ ተሻጋሪ መልካም አጋጣሚዎች ላይ ያተኮረ ነው” ሲልም አክሏል።

በ2024 ረዥም ጊዜ የቆዩ አንዳንዶቹ ገዢ ፓርቲዎች ሲቀጥሉ፣ ሌሎች ከባድ ሽንፈት ገጥሟቸዋል

ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት በቀሩት የአውሮፓውያን 2024 ዓመት፣ አፍሪካዊያን መረጮች፣ አፍሪካ ውስጥ በተካሄዱ ፕሬዝዳንታዊ፣ የፓርላማ ወይም አካባቢያዊ ምርጫዎች የ
የአሜሪካ ድምፅ

በ2024 ረዥም ጊዜ የቆዩ አንዳንዶቹ ገዢ ፓርቲዎች ሲቀጥሉ፣ ሌሎች ከባድ ሽንፈት ገጥሟቸዋል

ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት በቀሩት የአውሮፓውያን 2024 ዓመት፣ አፍሪካዊያን መረጮች፣ አፍሪካ ውስጥ በተካሄዱ ፕሬዝዳንታዊ፣ የፓርላማ ወይም አካባቢያዊ ምርጫዎች የተጠመዱ ነበሩ፡፡ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት ረዥም ጊዜ ሥልጣን ላይ የቆዩ ገዥ ፓርቲዎች ወንበራቸውን አስጠብቀው ሲቆዩ፣  ሌሎቹ ከባድ ሽንፈት ደርሶባቸዋል። በርካታ ምርጫዎችን የዘገበችው የቪኦኤ የናይሮቢ ቢሮ ኃላፊ ሜሪያማ ዲያሎ በዚህ ዓመት በአህጉሪቱ ዴሞክራሲ ምን ያህል በአግባቡ ተግባራዊ እንደተደረገ ተመልክታለች፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ስንፈተ ወሲብ በአይቮሪ ኮስት ወንዶች ላይ ያመጣው አሣር ይላል ርእሱ

‘ኢሬክታይል ዲስፈንክሽን’ ወይም ስንፈተ ወሲብ በአይቮሪ ኮስት በርካታ ወንዶችን እያሳሰበ እየመጣና በችግሩ ምክንያትም ራሳቸውን ከማኅበረሰቡ እንዲያገሉ በ
የአሜሪካ ድምፅ

ስንፈተ ወሲብ በአይቮሪ ኮስት ወንዶች ላይ ያመጣው አሣር ይላል ርእሱ

‘ኢሬክታይል ዲስፈንክሽን’ ወይም ስንፈተ ወሲብ በአይቮሪ ኮስት በርካታ ወንዶችን እያሳሰበ እየመጣና በችግሩ ምክንያትም ራሳቸውን ከማኅበረሰቡ እንዲያገሉ በማድረግ ላይ ይገኛል። ለመገለሉ እና ለችግሩ መፍትሄ ፍለጋ በመደረግ ላይ ባለበት ወቅት፣ ሐኪሞችና የስነ ልቦና ባለሙያዎች በጋራ በመሆን ርዳታ ለመስጠት እየጣሩ ነው። ያሲን ሲያው ከአቢጃን፣ አይቮሪ ኮስት ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአልቤኒያ መንግሥት ቲክ ቶክን ለአንድ ዓመት እንደሚዘጋው አስታወቀ

የአልቤኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከማኅበራዊ ትስስር ገጾች አንዱ የኾነው ቲክቶክ፣ ግጭት ቀስቃሽ እና በተለይ ሕፃናትን የሚያሸማቅቁ ቪዲዮች የሚሰራጭበት በመኾ
የአሜሪካ ድምፅ

የአልቤኒያ መንግሥት ቲክ ቶክን ለአንድ ዓመት እንደሚዘጋው አስታወቀ

የአልቤኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከማኅበራዊ ትስስር ገጾች አንዱ የኾነው ቲክቶክ፣ ግጭት ቀስቃሽ እና በተለይ ሕፃናትን የሚያሸማቅቁ ቪዲዮች የሚሰራጭበት በመኾኑ መንግሥታቸው ለአንድ ዓመት እንደሚዘጋው ትላንት ቅዳሜ ታኅሣሥ፣ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አስታወቁ። በቲክቶክ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ኅዳር ወር አጋማሽ ላይ አንድ አዳጊ፣ በሌላ አዳጊ በስለት መገደሉን ተከትሎ የአልቤኒያ ባለሥልጣናት ከ1 ሺሕ 300 መምሕራንና ወላጆች ጋራ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ላይ የተናገሩት የአልቤኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤዲ ራማ፣ ቲክቶክ በአልቤኒያ ሪፐብሊክ ውስጥ እንደማይኖርና ሙሉ በሙሉ እንደሚዘጋ ተናግረዋል። የመዝጋቱ ሂደትም በመጪው ዓመት እንደሚጀምር አስታውቀዋል። ቲክቶክ አልባኒያ ውስጥ ወኪል እንዳለው አልታወቀም። በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት የተጠየቀው ቲክቶክ ቅዳሜ ዕለት በሰጠው የኢሜል ምላሽ፣ በስለት ተወግቶ ስለተገደለው አዳጊ የአልቤኒያ መንግሥት በአስቸኳይ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠይቋል። ድርጊቱን ፈጽሟል የተባለውም ኾነ፣ ድርጊቱ የተፈጸመበት ተጎጂ አዳጊ የቲክቶክ ገጽ እንደነበራቸው የሚያሳይ አንድም መረጃ እንደሌለ በኢሜል ያስታወቀ ድርጅቱ ፣ «እንደውም ብዙ ሪፖርቶች እንዳረጋገጡት ወደ አደጋው እንዲያመራ ምክኒያት የኾነው ቪዲዮ የተሰራጨው በሌላ የትስስር ገጽ ላይ እንጂ በቲክቶክ አይደለም» ብሏል። አልቤኒያ ውስጥ ከቲክቶክ ተጠቃሚዎች ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሕፃናት መኾናቸውን የሀገር ውስጥ ጉዳዮችን የሚያጠኑ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ልጆች ቲክቶክ ላይ በሚያዩዋቸው ግጭት ቀስቃሽ ቪዲዮዎችና የሚፈጠሩ አለመግባባቶች ወደ ትምሕርት ቤት በሚሄዱበት ጊዜ እንደ ቢለዋ ያሉ ስለት ነገሮችና ሌሎች ቁሳቁሶችን እየያዙ መሄድ በመጀመራቸው ወላጆችን ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል። ቲክቶክ በተመሰረተበት ቻይና «በተሻለ ሁኔታ እንዴት ማጥናት እንደሚቻል፣ ተፈጥሮን እንዴት መንከባከብ እንደሚቻል እና የመሳሰሉትን በጎና የተለዩ መልዕክቶች ናቸው የሚተላለፉት» ሲሉ የአልቤኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራማ ተናግረዋል። ራማ ቲክቶክ እንዲዘጋ ያሳለፉትን ውሳኔ በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች አልተቀበሉትም።

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአዲሰ አበባ ጉብኝት

ቅዳሜ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚኽ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያና በሶማሊ
የአሜሪካ ድምፅ

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአዲሰ አበባ ጉብኝት

ቅዳሜ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚኽ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል በቱርክ ለተፈረመው የአንካራ ስምምነት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።ፕሬዝደንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ በመኾን በሰጡት የጋራ መግለጫ የሁሉንም ሉዓላዊነት ከማክበር ጋራ የተያያዘው ስምምነት ሊደገፍ የሚገባው ነው ብለዋል።

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአዲሰ አበባ ጉብኝት 

ቅዳሜ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚኽ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያና በሶማ
የአሜሪካ ድምፅ

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአዲሰ አበባ ጉብኝት 

ቅዳሜ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚኽ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል በቱርክ ለተፈረመው የአንካራ ስምምነት ድጋፋቸውን ገልጸዋል ። ፕሬዝደንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ በመኾን በሰጡት የጋራ መግለጫ የሁሉንም ሉዓላዊነት ከማክበር ጋራ የተያያዘው ስምምነት ሊደገፍ የሚገባው ነው ብለዋል። በቱርክ ፕሬዝደንት ረሽፕ ታይፕ ኤርዶዋን ሸምጋይነት የተካሄደውን ሦስተኛ ዙር ድርድር ተከትሎ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሐሙድ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግባቸውን ለመፍታትና አንዳቸው የሌላውን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ መስማማታቸው ይታወሳል ። ሁለቱ አገራት በመጭው የካቲት ወር በዝርዝር ጉዳይ ላይ ውይይት እንደሚጀምሩም ይጠበቃል። የሁለቱን ሀገራት ስምምነት ያደነቁት ፕሬዝደንት ማክሮን፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ እንዲሳካ ፈረንሳይ ባላት አቅም የበኩሏን ሚና መጫወት እንደምትፈልግ ጠቅሰዋል። በንግግር፣ በውይይት፣ ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ፣ ዓለምአቀፍ ሕጎችን እና ጎረቤት ሀገሮችን ባከበረ መልኩ መሠራት የሚችልበትን መንገድ ሀገራቸው ለማመቻቸት እንደምትፈልግ አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር ለማግኘት ያላትን ፍላጎት በተመለከተ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ጋራ በዝርዝር መወያየታቸውን ተናግረዋል። ከዚህ አንጻር ማክሮንን ድጋፍ መጠየቃቸውና ፣ ፕሬዝደንቱም ጥያቄውን መቀበላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።  «መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ከፈረንሳይ እና ከፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚህ ረገድ የሚጨበጥ ውጤት የሚጠብቅ መኾኑን ከወዲሁ ልገልጽ እፈልጋለሁ» በማለትም ተናግረዋል ። በኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል በፕሪቶሪያ የተፈረመው ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት  በሁለቱ መሪዎች ውይይት ከተነሱት ነጥቦች አንዱ መኾኑን የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ገልጸዋል። ሀገራቸው ከዚህ ስምምነት አተገባበር አንጻር ድጋፍ ማድረግ እንደምትፈልግም ተናግረዋል። ሀገራቸው በሽግግር ፍትህ አማካኝነት የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንደምትፈልግም አመልክተዋል። ፕሬዝዳንት ማክሮን በዛሬው የአዲስ አበባ ቆይታቸው፣ በመንግሥታቸው የገንዘብ ድጋፍ የታደሰውንና በአዲስ አበባ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ወይም ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ጎብኝተዋል። ፈረንሳይ ለብሔራዊ ቤተመንግሥቱ እድሳት የ25 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጓንም ተናግረዋል። ቤተመንግሥቱ የቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ የብር ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ በ1948 ዓ.ም. የተገነባ ነው።

የአሜሪካ ሴኔት ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታደገውን በጀት አጸደቀ

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የአሜሪካ መንግሥትን እስከ መጋቢት የሚያቆየውን በጀት አጸደቀ። በሪፐብሊካን ተመራጮች ብዙኅን ድምፅ ስር
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ ሴኔት ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታደገውን በጀት አጸደቀ

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የአሜሪካ መንግሥትን እስከ መጋቢት የሚያቆየውን በጀት አጸደቀ። በሪፐብሊካን ተመራጮች ብዙኅን ድምፅ ስር ያለው የሕግ መምሪያ ምክር ቤት እና በዲሞክራት አብላጫ ቁጥጥር ስር ያለው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት፣ ፌደራል መንግሥቱን ከመዘጋት የሚታገደውን በጀት ትላንት እኩለ ሌሊት ላይ አጽድቀዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የበጀት ረቂቁን እንደሚደግፉና ሕግ እንዲኾን እንደሚፈርሙ ትላንት ዐርብ ተናግረው ነበር። የጸደቀው በጀት ሕግ ኾኖ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ፣ መንግሥቱን እስከ መጪው መጋቢት የሚያቆየው በጀት ይኾናል። 100 ቢሊዮን ዶላር ለአደጋዎችና ለርዳታ፣ 10 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ለግብርና ሥራ ድጋፍ በበጀቱ ተይዟል። የጸደቀው በጀት የፌደራል መንግሥቱን የዕዳ ጣሪያ ከፍ እንዲል አያደርግም።

ቀጣይ በጀቱን ለመወሰን ጥቂት ሰዓታት የቀሩት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክርቤት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል

ዴሞክራቶች እና አንዳንድ ሪፐብሊካኖች የዕዳ ጣሪያውን እስከ አውሮፓውያኑ 2027 ድረስ ለማራዘም ያቀረቡትን ጥያቄ ከተቃወሙ በኋላ ሐሙስ ዕለት በHግ መወሰኛ ምክር
የአሜሪካ ድምፅ

ቀጣይ በጀቱን ለመወሰን ጥቂት ሰዓታት የቀሩት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክርቤት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል

ዴሞክራቶች እና አንዳንድ ሪፐብሊካኖች የዕዳ ጣሪያውን እስከ አውሮፓውያኑ 2027 ድረስ ለማራዘም ያቀረቡትን ጥያቄ ከተቃወሙ በኋላ ሐሙስ ዕለት በHግ መወሰኛ ምክርቤቱ በችኮላ የተደረገው ድርድር ከሽፏል። ለውጡ የመጣው ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ኤሎን መስክ መንግሥትን እስከ መጭው መጋቢት ድረስ በገንዘብ ለመደገፍ የተጠየቀውን የሁለትዮሽ ስምምነት ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው። የአሜሪካ ድምጽ የኮንግረስ ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን እና አሶሽየትድ ፕሬስን ዘገባዎች ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።    

የቱርክ እና ኢራን መሪዎች ካይሮ ላይ ተገናኙ

የቱርክ እና ኢራን መሪዎች የሶሪያው ፕሬዝደነት ባሻር አል አሳድ ሥልጣን ካከተመ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ካይሮ ላይ በመካሄድ ላይ ባለውና በአብዛኛው የእስልም
የአሜሪካ ድምፅ

የቱርክ እና ኢራን መሪዎች ካይሮ ላይ ተገናኙ

የቱርክ እና ኢራን መሪዎች የሶሪያው ፕሬዝደነት ባሻር አል አሳድ ሥልጣን ካከተመ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ካይሮ ላይ በመካሄድ ላይ ባለውና በአብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ የስምንት ሀገራት ጉባኤ ላይ ተገናኝተዋል። በሶሪያው ጦርነት ሁለቱ ሀገራት በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው የነበረ ሲሆን፣ ቱርክ የአሳድ ተቃዋሚዎችን ስትደግፍ ኢራን ደግሞ የአሳድን አገዛዝ ደግፋለች። በሶሪያ መረጋጋትና ሰላም እንዲሰፍን፣ ሽብርተኝነት እንዲጠፋ እንዲሁም የተረጋጋችና ፀጥታ የሰፈነባትን ሶሪያ ማየት እንደሚሹ የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሽፕ ታይፕ ኤርዶዋን በውይይታቸው ወቅት ማስታወቃቸውን የቱርክ ፕሬዝደንታዊ ጽሕፈት ቤት በአወጣው መግለጫ ላይ ተመልክቷል። የሶሪያን የግዛት ሉአላዊነት እና የሀገሪቱን አንድነት መጠበቅ አስፈላጊ እንደኾነም ኤርዶዋን መናገራቸውን ጽሕፈት ቤቱ አመልክቷል። ከኢራኑ ፕሬዝደንት ማሱድ ፐዘሽካን ቢሮ የወጣው መግለጫ በበኩሉ፣ የሶሪያ ድንበር ሳይደፈር ተጠብቆ የመቆየቱ አስፍላጊነት ላይ ፕሬዝደንቱ አጽንኦት መስጠታቸውን አመልክቷል። እስራኤል በቀጠናው ፈጽማዋለች ያሉትንና “ወንጀል” ሲሉ ለገለጹት ድርጊት ሙስሊም ሀገራት ኃላፊነት ባለው መንገድ ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው ፕሬዝደንቱ ማሳሰባቸውም ተጠቁሟል። “ግጭት በሚካሄድባቸው ሥፍራዎች የሚገኙ ሰዎች ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስባቸው መከላከል ሃይማኖታዊ፣ ሕጋዊ እና ሰብአዊ ግዴታችን ነው” ሲሉም ማሱድ ፐዘሽካን ማከላቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል። ‘ዲ 8’ በሚል የሚጠራው የስምንት ሃገራት የኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ በካይሮ በመካሄድ ላይ ያለው፣ በጋዛ ጦርነት በሚካሄድበት፣ በሌባኖስ በጽኑ ያልተከበረ የተኩስ ማቆም ስምምነት ባለበት፣ ሶሪያ ባልተረጋጋችበትና ቀጠናው በአጠቃላይ በግጭት በሚተራመስበት ወቅት ነው።

አሜሪካ በፈፀመችው የአየር ጥቃት በሶሪያ የአይሲስ መሪ ተገደለ

የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ዛሬ ዓርብ በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ እንዳስታወቀው፣ መሪውን አቡ ዮሱፍን ጨምሮ ሁለት የአይሲስ አባላት ሶሪያ ውስጥ በተፈጸመ
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካ በፈፀመችው የአየር ጥቃት በሶሪያ የአይሲስ መሪ ተገደለ

የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ዛሬ ዓርብ በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ እንዳስታወቀው፣ መሪውን አቡ ዮሱፍን ጨምሮ ሁለት የአይሲስ አባላት ሶሪያ ውስጥ በተፈጸመ አየር ጥቃት ተገድለዋል። የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት ሐሙስ መሆኑን ያስታወቅቁት የዕዙ መሪ ጀኔራል ማይክል ኩሪላ፣ የአይሲስ መሪዎችና ዓባላት ዒላማ መደረጋቸው እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። አሜሪካ አይሲስ በሶሪያ የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም ሊያንሰራራ ይችልላ የሚል ሥጋት እንዳላት ማስታወቋን የጠቆመው የሮይትረስ ዘገባ፣ በሀገሪቱ ሰሜን ምሥራቅ በቱርክ በሚደገፉት አማጺያን እና ከአሜሪካ ጋራ ባበሩት የኩርድ ሚሊሺያዎች መካከል ግጭት እንዳይኖር እንደምትሻ አመልክቷል። ምዕራባውያን መንግስታት ‘ሃያት ታህሪር አል-ሻም’ ወይም በምጻሩ ‘ኤች ቲ ኤስ’ በመባል የሚታወቀውንና በሶሪያ የቀድሞ አል ቃይዳ ቅርንጫፍ ቡድን ጋራ ንግግር ለመክፈት እንደሚሹና በሽብርተኝነት መፈረጁን ለማንሳት ክርክር መጀመራቸውንም የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

የእህል ርዳታ ወደ ቡግና ወረዳ መጓጓዝ መጀመሩን ባለሥልጣናት አስታወቁ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በረኅብ ለተጎዱ ሰዎች የርዳታ እህል ወደ ወረዳው እንዲገባ ከመንግሥትና ከፋ
የአሜሪካ ድምፅ

የእህል ርዳታ ወደ ቡግና ወረዳ መጓጓዝ መጀመሩን ባለሥልጣናት አስታወቁ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በረኅብ ለተጎዱ ሰዎች የርዳታ እህል ወደ ወረዳው እንዲገባ ከመንግሥትና ከፋኖ ታጣቂዎች ጋራ ስምምነት ማድረጋቸውን አስታወቁ። በስምምነቱ መሰረትም የርዳታ እህሉ እየገባ መኾኑን አንድ የኃይማኖት አባት ተናግረዋል። የሰሜን ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል፣ አካባቢው በፋኖ ታጣቂዎች ስር በመኾኑ ለተከሰተው የምግብ እጥረት መንግሥት በቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻለም ብለዋል። የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በአደረጉት ጥረትም ከ110 ሺሕ በላይ ለሆኑ ሰዎች ከ16 ሺሕ ኩንታል በላይ የርዳታ እህል ወደ ስፍራው እየተጓጓዘ መኾኑን አስታውቀዋል። የወረዳው ነዋሪ ያለበትን የምግብና የጤና ችግር ለፋኖ ታጣቂዎችና ለመንግሥት አካላት ለማስረዳት ከተመረጡት 18 ግለሰቦች መካከል “አንዱ ነበርኩ” ያሉት ቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዝናቤ ይርዳው በአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረሰው ስምምነት መድኃኒቶችንና አልሚ ምግቦች ወደ ወረዳው መግባት መቻላቸውን ተናግረዋል። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ሁለት የአይና ቡግና ወረዳ ነዋሪ እናቶች፣ ለሕፃን ልጆቻቸው አልሚ ምግቦችን ከጤና ተቋማት ተቀብለው ወደ ቤታቸው እየሄዱ እንደሆነ ተናግረዋል። በሌላ በኩል አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ዛሬ ታኅሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በፌስ ቡክ ገጹ በአወጣው መግለጫ በቡግና ወረዳ የምግብ እጥረት ቀውስ ሰለመኖሩ የወጡ ሪፖርቶችን እየተከታተለ መኾኑን አመልክቷል። «ሁኔታውን መከታተላችንን እና መገምገማችንን እንቀጥላለን» ያለው መግለጫው ቀውሱ መወገዱን ለማረጋገጥ እንደሚሠራም ጠቅሷል። ኤምባሲው በመግለጫው ቀውሱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን አላካተተም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመደገፍ ፣ አጋሮቹ በአኹኑ ሰዓት በችግሩ በተጠቁት አብዛኞቹ ስፍራዎች የምግብ እና አልሚ ንጥረ ምግቦች ስርጭትን ያጠናከሩ መሆናቸውንም አክሏል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

“የትግራይ ሰራዊት በዲዲአር ስም እንዲበተን እየተደረገ ነው” - በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት

በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራ የህወሓት ቡድን ዛሬ መቐለ ከተማ በሰጡት መግለጫ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች፣ ታጣቂዎችን ትጥ
የአሜሪካ ድምፅ

“የትግራይ ሰራዊት በዲዲአር ስም እንዲበተን እየተደረገ ነው” - በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት

በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራ የህወሓት ቡድን ዛሬ መቐለ ከተማ በሰጡት መግለጫ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች፣ ታጣቂዎችን ትጥቅ በማስፈታት እና በመልሶ ማዋሃድ ሥራ ስም፣ የትግራይ መሰረታዊ ጥያቄ ሳይመለስ የቀድሞ ተዋጊዎች እንዲበተኑ እየተደረገ ነው ሲል ክስ አሰማ። የህወሓት አንዱ ክፋይ በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ፣ “የእምቢታ ዘመቻ” ብሎ የጠራው ስብሰባ ሲያጠናቅቅ፣ “ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲፈፅም የተሰጠው ሥራ ሙሉ በሙሉ ወድቋል” በማለትም ገልጿል። በሌላ በኩል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለሦስት ቀናት ያካሔደውን ስብሰባ አስመልክቶ በአወጣው መግለጫ፣ “ክልሉን ወደ ግርግር እና የአመፅ ተግባር ለማስገባት የሚንቀሳቀሱ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አይታገስም” ብሏል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ገቡ የተባሉ 44 ደቡብ ሱዳናውያን አርብቶ አደሮች መታሰራቸውን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በመግባት ከብት ዘርፈዋል የተባሉ 44 የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮችን ማሰሩን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ከ200 በላይ ከብቶችን ማስመለሱ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ገቡ የተባሉ 44 ደቡብ ሱዳናውያን አርብቶ አደሮች መታሰራቸውን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በመግባት ከብት ዘርፈዋል የተባሉ 44 የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮችን ማሰሩን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ከ200 በላይ ከብቶችን ማስመለሱንና ለባለቤቶቹ ማስረከቡንም ፖሊስ ገልጿል። ባለፈው ዐርብ ታኅሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ተጠርጣሪዎቹ ተይዘውበት ከነበረው ሱርማ ወረዳ ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕከል መዘዋወራቸውንም የኮሚሽኑ ሚዲያ እና ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጄላን አብዲ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

በዋግ ኽምራ ዞን ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ከ2016 ዓ.ም የመኸር ወቅት ጀምሮ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ምክኒያት ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ
የአሜሪካ ድምፅ

በዋግ ኽምራ ዞን ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ከ2016 ዓ.ም የመኸር ወቅት ጀምሮ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ምክኒያት ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ምሕረት መላከ፣ ባለፈው ክረምት በዞኑ ደጋማ አካባቢዎች የደረሰውን የተፈጥሮ አደጋ ተከትሎ ከ14 በላይ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች በአደረጉት ግምገማ 44 ሰዎች መሞታቸውን ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሰብአዊ መብቶችን በኪነ-ጥበብ

በኢትዮጵያ ይስተዋላሉ የሚባሉ የመብት ጥሰቶችን የሚዳስስ፣ በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብትን የሚያስተምርና ሴቶች በሕይወት የመኖር መብት እንዳላቸው የሚያ
የአሜሪካ ድምፅ

ሰብአዊ መብቶችን በኪነ-ጥበብ

በኢትዮጵያ ይስተዋላሉ የሚባሉ የመብት ጥሰቶችን የሚዳስስ፣ በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብትን የሚያስተምርና ሴቶች በሕይወት የመኖር መብት እንዳላቸው የሚያስታውስ ፣ ተውኔት፣ የፎቶ ግራፍ አውደ ርእይና ስዕል አዲስ አበባ ከተማ ላይ ለእይታ በቃ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ፣ በሰብአዊ መብቶች ላይ ትኩረት ያደረገ የፊልም ፌስቲቫል በኢትዮጵያ ከተሞች በማካሄድ ላይ መኾኑን አስታውቋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት የሕፃናትን የኢንተርኔት ደኅንነት ሕግ እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀረበ

በዚህ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሥራ ዘመን ሕፃናትን ከማኅበራዊ ሚዲያ ጠንቆች ለመከላከል በሁለቱም ፓርቲዎች ትብብር የተያዘው ጥረት ጊዜው እያለቀበት ነ
የአሜሪካ ድምፅ

የዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት የሕፃናትን የኢንተርኔት ደኅንነት ሕግ እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀረበ

በዚህ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሥራ ዘመን ሕፃናትን ከማኅበራዊ ሚዲያ ጠንቆች ለመከላከል በሁለቱም ፓርቲዎች ትብብር የተያዘው ጥረት ጊዜው እያለቀበት ነው። የሕፃናት የኢንተርኔት ደኅንነት ሕግ ከጸደቀ፣ በኢንተርኔት ላይ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን ለሚመለከቱ የግል መረጃዎች ጥበቃዎችን ይደነግጋል። ለመናገር ነፃነት ተሟጋቾች እና አንዳንድ ሪፐብሊካኖች ግን፣ ሕጉ ወደ ሳንሱር ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። የቪኦኤ የምክር ቤት ዘጋቢ ካትሪን ጊብሰን ተጨማሪ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የካሜሩን ጋዜጠኞች ከመጪው ምርጫ በፊት የተሳሳተ መረጃን ለመዋጋት ተስፋ ያደርጋሉ

ካሜሩናውያን ሀገሪቱን ለሰባት ዓመታት በፕሬዝደንትነት የሚመራውን ፕሬዝደንት ለመምረጥ በመጪው ዓመት ወደ ምርጫ ጣቢያ ያመራሉ። በማዕከላዊ የአፍሪካ አህጉ
የአሜሪካ ድምፅ

የካሜሩን ጋዜጠኞች ከመጪው ምርጫ በፊት የተሳሳተ መረጃን ለመዋጋት ተስፋ ያደርጋሉ

ካሜሩናውያን ሀገሪቱን ለሰባት ዓመታት በፕሬዝደንትነት የሚመራውን ፕሬዝደንት ለመምረጥ በመጪው ዓመት ወደ ምርጫ ጣቢያ ያመራሉ። በማዕከላዊ የአፍሪካ አህጉር በምትገኘው ካሜሩን ከዚህ በፊት በተደረጉ ምርጫዎች ወቅት የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ጭቅጭቅ ፈጥረዋል። በመጪው ምርጫ ይህ እንዳይደገም፣ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ባለሙያዎች ቀድሞ ለመከላከል ርምጃ በመውሰድ ላይ ናቸው። ጆድዘካ ዳንሃቱ ከካሜሩን የላከውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዶናልድ ትረምፕና ኢላን መስክ በምክር ቤት የቀረበውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅ ቀረ

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና ባለ ሀብቱ ኢላን መስክ በአሜሪካ ምክር ቤት በሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነት ቀርቦ የነበረውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅ
የአሜሪካ ድምፅ

ዶናልድ ትረምፕና ኢላን መስክ በምክር ቤት የቀረበውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅ ቀረ

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና ባለ ሀብቱ ኢላን መስክ በአሜሪካ ምክር ቤት በሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነት ቀርቦ የነበረውን በጀት በመቃወማቸው ሳይጸድቅ ቀርቷል። የወቅቱ የበጀት ዓመት ነገ ዐርብ ሌሊት ስለሚጠናቀቅ፣ ከዚያ በፊት በምክር ቤቱ በጀት የማይጸድቅ ከኾነ በርካታ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሥራ ሊያቆሙ ወይም ‘አስፈላጊ’ ተብለው ከተመደቡ የመንግሥት ሠራተኞች ውጪ የሆኑት ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ሥራ ላይገቡ ይችላሉ። ሥራቸውን የሚቀጥሉትም ቢሆኑ በጀቱ እስከሚለቀቅ ካለ ደመወዝ ሊሠሩ እንደሚችሉ ታውቋል። ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና ተመራጩ ምክትል ፕሬዝደንት ጄ ዲ ቫንስ ትላንት በጋራ ባወጡት መግለጫ የቀረበው የበጀት ረቂቅ «ወደዲሞክራቶቹ ፍላጎት ያጋደለ ነው» በሚል ተቃውመዋል። በመጪው የትረምፕ አስተዳደር የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ብዛት፣ ፕሮግራሞች እና ሠራተኞች ለመቀነስ የተቋቋመውን ቡድን ከሚመሩት አንዱ የሆኑት ባለ ሀብቱ ኢላን መስክ “እጅግ የበዛ ወጪ የሚያስከትል” ብለው የበጀት ሐሳቡን ውድቅ አድርገዋል። በጀቱን የሚደግፉ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባላት ከሁለት ዓመት በኋላ በሚደረገው ምርጫ መራጮች በድምጻቸው ሊቀጧቸው እንደሚችሉ ኢላን መስክ ዝተዋል። ሪፐብሊካን የም/ቤት ዓባላት በበጀቱ ላይ እንደገና እንዲደራደርሩ ጥሪ ያደረጉት ትረምፕ፣ ያንን የማያደርጉ ከሆነ “ሀገርን እንደመክዳት ይቆጠራል” ብለዋል። የፕሬዝደንት ጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን ከመጠናቀቁ በፊትም የሀገሪቱ የዕዳ ጣሪያ ከፍ እንዲል ትረምፕ ጠይቀዋል። የባይደን አስተዳደር የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የመዝጋቱን ሐሳብ ነቅፏል።  

የአማዞን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ

በሰባት የአማዞን መጋዘኖች የሚገኙ ሠራተኞች ከዛሬ ሐሙስ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ መትተዋል። ሠራተኞቹ አድማውን የጠሩት አማዞን ባለፈው እሑድ ቀጠሮ ተይዞለ
የአሜሪካ ድምፅ

የአማዞን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ

በሰባት የአማዞን መጋዘኖች የሚገኙ ሠራተኞች ከዛሬ ሐሙስ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ መትተዋል። ሠራተኞቹ አድማውን የጠሩት አማዞን ባለፈው እሑድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረውን የአሠሪ እና ሠራተኛ ውል ድርድር ችላ ብሏል በሚል ነው። በአድማው የሚሳተፉት በኒው ዮርክ፣ ካሊፎርኒያ፣ ኢሊኖይ እና ጆርጂያ በሚገኙ የአማዞን የሸቀጥ ማከማቻና ማደራጃ መጋዘኖች የሚሠሩ ሠራተኞች መኾናቸው ታውቋል። አማዞን በበኩሉ አድማው በሥራው ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ብሎ እንደማይጠብቅ አስታውቋል። የሠራተኛ ማኅበሩ በአሥር የአማዞን መጋዘኖች የሚገኙ 10 ሺሕ ሠራተኞችን እንደሚወክል አስታውቋል። አማዞን በአጠቃላይ በዋና ዋና ቢሮዎችና መጋዘኖች የሚሠሩ 1.5 ሚሊዮን ሠራተኞች አሉት፡፡ ዛሬ አድማ የመቱት በሳን ፍራንሲስኮ፣ ካሊፎርኒያ መጋዘን ውስጥ የሚሠሩ እንዲሁም በሌሎች አራት ግዛቶች ውስጥ የሚገኙና ሸቀጥ ለሥርጭት በሚያዘጋጁ ጣቢያዎች ውስጥ የሚሠሩ መኾናቸው ታውቋል። በሌሎች ሥፍራዎች የሚገኙ የአማዞን ሠራተኞችም አድማውን ለመቀላቀል ዝግጁ መሆናቸውን የሠራተኛ ማኅበሩ አስታውቋል። ሸቀጡን የሚያጓጉዙ ሾፌሮች የኩባንያው ተቀጣሪዎች ሳይሆኑ፣ ለሦስተኛ ወገን የሚሠሩ መሆናቸውን አማዞን ይገልጻል። የአክሲዮን ገበያ ዛሬ ማለዳ በተከፈተበት ወቅት የአማዞን ድርሻ በአንድ በመቶ ከፍ ብሏል።

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያሰበችውን ግብ እያሳካች መኾኑን ፑቲን ተናገሩ

ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ ኅይሎች በዩክሬን ጦርነት ዋና ግባቸውን ለመምታት እየተቃረቡ መኾኑን በዓመታዊ ጋዜጣዊ  መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል። በጦ
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያሰበችውን ግብ እያሳካች መኾኑን ፑቲን ተናገሩ

ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ ኅይሎች በዩክሬን ጦርነት ዋና ግባቸውን ለመምታት እየተቃረቡ መኾኑን በዓመታዊ ጋዜጣዊ  መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል። በጦር ሜዳው እንዳገኙ ለሚገልጹት የበላይነት አዲሶቹ የሩሲያ  ሱፐርሶኒክ ሚሳዬሎች አስተዋጽኦ እንዳደረጉ አመልክተዋል። በመንግሥት ቴሌቭዥን ቀርበው ከሩሲያውያን ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ የሰጡት ፑቲን፣ የሀገራቸው ኅይሎች በሁሉም ግንባሮች ግሥጋሤ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። ፑቲን ፣ “ሁኔታዎች እየተቀያየሩ ነው። በየቀኑ በሁሉም ግንባሮች ግሥጋሤ አለ” ሲሉ አስታውቀዋል።  ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን እ.አ.አ ከ2022 ወዲህ በፍጥነት እየገሠገሠችና በርካታ ሥፍራዎችን በመቆጣጠር ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ወዳላቸው ከተሞች በመቃረብ ላይ መኾኗን ምዕራባውያንና የሩሲያ ወታደራዊ ተንታኞች በመግለጽ ላይ ናቸው። ዩክሬን የሩሲያን ኩርስክ ክልል ይዛ መቆየቷን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፣ የዩክሬን ኅይሎች “በእርግጠኝነት እንዲወጡ የደረጋል” ሲሉ ተደምጠዋል። የሩሲያ አዲስ ሱፐርሶኒክ ‘ኦረሽኒክ’ ሚሳዬሎች ከእይታ ውጪ ስለኾኑ መትቶ ለመጣል እንደማይቻል ፑቲን ተናግረዋል። ሩሲያ የሠራቻቸውን እነዚህ ሚሳዬሎች የዩክሬን ወታደራዊ ፋብሪካዎችን በመምታት ሞክራቸዋለች፡፡ በእነዚህ ሚሳዬሎች ተጨማሪ ድብደባዎችን እንደሚያደርጉና የምዕራባውያን የመከላከያ መሣሪያዎች መትተው ይጥሏቸው እንደሁ የሚታይ ይሆናል ብለዋል ፑቲን። 

ህወሓት አዲስ ሰላማዊ የፖለቲካዊ ትግል ለማካሔድ መወሰኑ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገለጹ

ለሁለት ከተከፈሉት የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች፣ በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ዛሬ መቐለ ከተማ ላይ ከፓርቲው ከ
የአሜሪካ ድምፅ

ህወሓት አዲስ ሰላማዊ የፖለቲካዊ ትግል ለማካሔድ መወሰኑ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገለጹ

ለሁለት ከተከፈሉት የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች፣ በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ዛሬ መቐለ ከተማ ላይ ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋራ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል። “እምቢ የማለት ዘመቻ” የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ ውይይት መክፈቻ ላይ የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ በትግራይ ክልል በአሁኑ ጊዜ ልዩ ትግል እና መደጋገፍ እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል። በሌላ በኩል፣ ሦስት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች በአራት የትግራይ ዞኖች ዳሰሳ ማካሔዳቸውን ገልጸው በሰጡት መግለጫ፣ ህወሓትን ትጥቅ በማስታጠቅ ከሰዋል። በዶክተር ደብረ ጽዮን የሚመራው የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የኾኑት፣ ዶክተር ፍሰኻ ሀብተ ጽዮን፣ “እኛ ፓርቲ ነን ማስታጠቅም መመልመልም አንችልም፣ ትግላችንም ሰላማዊ ነው” ብለዋል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የጫት ገበያ የተዳከመባቸው የምስራቅ ኢትዮጵያ አርሶ አደሮች

የምስራቅ ኢትዮጵያ የጫት አምራቾች፣ የጫት ዋጋ በመውረዱ ምክኒያት ለችግር መዳረጋቸውን ገለጹ። የአካባቢው ጫት ላኪዎች በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ የጫት ምርት
የአሜሪካ ድምፅ

የጫት ገበያ የተዳከመባቸው የምስራቅ ኢትዮጵያ አርሶ አደሮች

የምስራቅ ኢትዮጵያ የጫት አምራቾች፣ የጫት ዋጋ በመውረዱ ምክኒያት ለችግር መዳረጋቸውን ገለጹ። የአካባቢው ጫት ላኪዎች በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ የጫት ምርት ትልቁ መዳረሻ የነበረው የሶማሊያ ገበያ በኬንያ ነጋዴዎች በመያዙ፣ የጫት ዋጋ መውረዱን እና ኹኔታው ሁሉንም የዘርፉን ተዋናዮች እየጎዳ እንደሚገኝ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥም አርሶ አደሮቹ እና ነጋዴዎቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Get more results via ClueGoal