የአቶ ክርስቲያን እና የአቶ ዮሐንስ የእስር ቤት አያያዝ እንደሚያሳስባቸው ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገለፁ
newsare.net
በቅርቡ የቀዶ ሕክምና የተደረገላቸው የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ወደ ሌላ እስር ቤት መዛወራቸውን ቤተሰቦቻቸው እየአቶ ክርስቲያን እና የአቶ ዮሐንስ የእስር ቤት አያያዝ እንደሚያሳስባቸው ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገለፁ
በቅርቡ የቀዶ ሕክምና የተደረገላቸው የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ወደ ሌላ እስር ቤት መዛወራቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገልፀዋል፡፡ ሁለቱ ታሳሪዎች “ከፍተኛ ሕመም እየተሰማቸው ነው ወደ ቂሊንጦ የተዛወሩት” ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ በተለይ አቶ ዮሐንስ የሚገኙበት ማቆያ ሥፍራ ለጤንነታቸው የሚያሰጋቸው እንደኾነ ተናግረዋል፡፡ ይህ ሁኔታ እንዲቀየር ለፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልፀዋል፡፡ የቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ዳይሬክተር ኮማንደር ዓለምሰገድ፣ ውንጀላውን አስተባብለዋል፡፡ Read more