ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የመን ውስጥ ከተፈጸመ አየር ጥቃት መትረፋቸውን አስታወቁ
newsare.net
በየመን ሰነአ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰውን የአየር ጥቃት ተከትሎ፣ በወቅቱ በሥፍራው የነበሩት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዲሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የመን ውስጥ ከተፈጸመ አየር ጥቃት መትረፋቸውን አስታወቁ
በየመን ሰነአ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰውን የአየር ጥቃት ተከትሎ፣ በወቅቱ በሥፍራው የነበሩት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዲሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከጥቃቱ መትረፋቸውን አስታውቀዋል። ዶ/ር ቴድሮስ በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ በየመን የተገኙት በሃገሪቱ ታግተው የሚገኙ የተመድ ሠራተኞችን ለማስለቀቅ ድርድር ለማድረግ እንደነበር አመልክተዋል። “ሰነአ ላይ ወደ አውሮፕላን ልንገባ ስንል አየር ማረፊያው ላይ ድብደባ ደርሷል። አንድ የበረራ ባልደረባችን በጥቃቱ ተጎድቷል፣ እንዲሁም ሁለት ሰዎች እንደሞቱ ሪፖርት ተደርጓል” ሲሉ ዶ/ር ቴድሮስ በመልዕክታቸው አስታውቀዋል። “እኔም ሆንኩ የተመድ እና የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረቦቼ ተርፈናል” ሲሉም አክለዋል። በእስራኤልና በሁቲ አማጺያን መካለከል ውጥረት ማየሉን ተከትሉ በአየር ማረፊያውና አማጺያኑ በሚገኙባቸው አካባቢዎች ባሉ ወታደራዊ መሠረቶች እና የኃይል ማመንጫዎች ላይ የአየር ጥቃቶች በመደረግ ላይ ናቸው። የእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃሚን ኔታያሁ “ሥራው እሰከሚጠናቀቅ ድረስ ድብደባው ይቀጥላል” ብለዋል። የሁቲ አማጺያን ባለፉት ሁለት ቀናት ሁለት ጊዜ ወደ እስራኤል ሚሳኤል ተኩሰው እንደነበር ሲታወስ፣ ዛሬ በሰነአ የደረስውን የአየር ጥቃት “ጽዮናውያን በየመን ሕዝብ ላይ የፈጸሙት ወንጀል ነው” ሲሉ የሁቲ ቃል አቀባይ ሞሃመድ አብዱልሰላም ተናግረዋል። የእስራኤል ሠራዊት በበኩሉ“ ተዋጊ አውሮፕላኖቹ በሁቲ አማጺያን ሥር ባሉ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን አስታውቋል። በጋዛ ጦርነቱ ከፈነዳ ወዲህ የሁቲ አማጺያን ከፍልስጤማውያን ጋራ አጋራነታቸውን ለማሳየት በሚል በርካታ ሚሳዬሎችንና እና ድሮኖችን ወደ እስራኤል ሲያስወነጭፉ ቆይተዋል። Read more