የጀርመኑ ፕሬዝደንት ፓርላማውን በትነው ምርጫ እንዲደረግ አዘዙ
newsare.net
የጀርመኑ ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ ዓርብ የሃገሪቱን ፓርላማ በትነው በሚቀጥለው ወር ምርጫ እንዲደረግ አዘዋል። ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ከየጀርመኑ ፕሬዝደንት ፓርላማውን በትነው ምርጫ እንዲደረግ አዘዙ
የጀርመኑ ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ ዓርብ የሃገሪቱን ፓርላማ በትነው በሚቀጥለው ወር ምርጫ እንዲደረግ አዘዋል። ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ከሳምንት በፊት መተማመኛ ድምጽ በማጣታቸውና ባለፈው ወር የገንዘብ ምኒስትራቸውን ማባረራቸውን ተከትሉ፣ በሶስት ፓርቲዎች ጥምር ያቋቋሙት መንግስት ፈርሷል። የዋና ዋና ፓርቲ መሪዎች እአአ በመጪው የካቲት 23 የፓርላማ ምርጫ እንዲደረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ምርጫው የሚካሄደው ቀድሞ ከታቀደው ሰባት ወራት ቀደም ብሉ ነው። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የወጣው የጀርመን ሕገ መንግሥት፣ ‘ቡንደስታግ’ ወይም የሃገሪቱ ሸንጎ ራሱን መበተን ስለማይችል፣ ውሳኔውን የመስጠት ሃላፊነቱ ፕሬዝደንቱ ላይ ወድቋል። በዚህም መሠረት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ፓርላማውን በትነው ምርጫ እንዲደረግ አዘዋል። የምርጫ ዘመቻው ግን ፓርላማው ከመበተኑ በፊትም በመካሄድ ላይ ነበር። በሕዝብ አስተያየት መለኪያ መሠረት ወግ አጥባቂው የተቃዋሚዎች ስብስብ በመምራት ላይ ሲሆን፣ የኦላፍ ሾልዝ ፓርቲ ደግሞ ይከተላል። በምርጫው ቁልፍ ጉዳዮች የሆኑት ፍልሰት፣ የተዳከመው ኢኮኖሚ እና ለዩክሬን የሚሰጥ ድጋፍ ናቸው። Read more