በአሜሪካ በተነሳ አውሎ ነፋስ አራት ሰዎች ሞቱ
newsare.net
በደቡባዊ የዩናይትድ ስቴትስ ክፍል በሚገኙ ግዛቶች በተነሳ አውሎንፋስ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ባለሥልጣናት አስታወቁ። የደረሰው የጉዳት መጠን ላይ ምርበአሜሪካ በተነሳ አውሎ ነፋስ አራት ሰዎች ሞቱ
በደቡባዊ የዩናይትድ ስቴትስ ክፍል በሚገኙ ግዛቶች በተነሳ አውሎንፋስ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ባለሥልጣናት አስታወቁ። የደረሰው የጉዳት መጠን ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል። በቴክሳስ፣ ሉዊዚያና፣ ሚሲሲፒ፣ አላባማ እና ጆርጂያ ውስጥ በአውሎንፋስ ምክንያት የደረሱ ቢያንስ 45 ጉዳቶች ሪፖርት መደረጋቸውን፣ በብሔራዊ አየር ሁኔታ አገልግሎት የአየር ትንበያ ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ ባለሞያዎች አስታውቀዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ለበዓል በሚጓጓዙበት ወቅት የተነሳው አውሎነፋስ በአየር ማርፊያዎች መዘግየት እና የመንገድ መዘጋጋት የፈጠረ ሲሆን፣ በደቡባዊ ጆርጂያ ግዛት በሚገኘው የአትላንታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ብቻ ከ600 በላይ በረራዎች ላይ መዘግየት እንደፈጠረ አንድ የበረራ መከታተያ ተቋም አመልክቷል። የኤሌክትሪክ አገልግሎት መከታተያ ድህረ ገጽ በበኩሉ በሚሲሲፒ፣ ቴክሳስ፣ አላባማ፣ ሰሜን ካሮላይና እና ጆርጂያ የሚኖሩ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደተቋረጠባቸው አመልክቷል። Read more