በኒው ኦርሊየንስ የመኪና አደጋ 10 ሰዎች ሞቱ
newsare.net
የአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመት ከተበሰረ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በአሜሪካ፣ ሉዚያና ግዛት በምትገኘው ኒው ኦርሊየንስ ከተማ አንድ ተሽከርካሪ ሕዝብ በተሰበሰበት ቦበኒው ኦርሊየንስ የመኪና አደጋ 10 ሰዎች ሞቱ
የአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመት ከተበሰረ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በአሜሪካ፣ ሉዚያና ግዛት በምትገኘው ኒው ኦርሊየንስ ከተማ አንድ ተሽከርካሪ ሕዝብ በተሰበሰበት ቦታ ላይ በመውጣት የዐስር ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ 30 ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የከተማዋ ድንገተኛ አደጋ መከላከያ አስታውቋል። የኒው ኦርሊየንስ ፖሊስም የበርካታ ሰዎች ሕይወት ላለፈበት አደጋ ምላሽ እየሰጠ መኾኑን በመግለፅ፣ ሰዎች አደጋው ከደረሰበት አካባቢ እንዲርቁ መክሯል። አደጋው የደረሰው በኒው ኦርሊየንስ የተካሄደው የአዲስ ዓመት ክብረ በዓል ማብቂያ ላይ ሲሆን፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች 'ኦል ስቴት' ቦል ተብሎ የሚጠራውን የዩንቨርስቲዎች የእግርኳስ ጨዋታ የሩብ ፍፃሜ ውድድር ለመከታተል እየተዘጋጁ ባሉበት ሰዓት መሆኑ ተመልክቷል። Read more