የጂሚ ካርተር መንግሥታዊ የአስክሬን ሽኝት ሥነ ሥርዐት ዛሬ ጀመረ
newsare.net
በ100 ዓመታቸው እሑድ ታኅሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር፣ ስድስት ቀናት የሚቆየው የቀብር እና የሽኝየጂሚ ካርተር መንግሥታዊ የአስክሬን ሽኝት ሥነ ሥርዐት ዛሬ ጀመረ
በ100 ዓመታቸው እሑድ ታኅሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር፣ ስድስት ቀናት የሚቆየው የቀብር እና የሽኝት ሥነ ሥርዐት ዛሬ ጀመረ። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ጥር 1 ቀን 2017 ዓ/ም እንደሚፈፀም ታውቋል። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለጂሚ ካርተር ብሔራዊ የሐዘን ቀን ባወጁበት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ/ም፣ የቀብራቸውም ሥነ ሥርዓት በዛው ዕለት እንዲፈፀም ፕሮግራም እንዲያዝ አድርገዋል። በተጨማሪም የመንግሥት ሕንፃዎች ሰንደቅ ዓላማቸውን ለ30 ቀናት ዝቅ አድርገው እንዲሰቅሉ መመሪያ አስተላልፈዋል። የጂሚ ካርተር ሕይወት ወደ ኋላ ሲቃኝ ጂሚ ካርተር ፕሬዝደንት ከመሆናቸው በፊት፣ የለውዝ ገበሬ እንዲሁም የጆርጂያ ግዛት አገረ ገዥ ነበሩ። በእ.አ.አ ጥር 20 ቀን 1977 ዓ.ም ቃለ መሃላ በመፈጸም ሥልጣን ሲረክከቡ፣ 39ኛው የአሜሪከ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር “እንደ ሕዝቡ መልካም የኾነ” ያሉትን መንግሥት እንደሚያቋቁሙ ቃል ገብተው ነበር። “በዚህ አዲስ ምዕራፍ በምንከፍትበት ዕለት፣ ፍትህና ሰላም የሰፈነበት ዓለምን ከመቅረጽ የበለጠ የተከበረና ከባድ ተግባር የለም፣” ሲሉ በቃለ መሃላ ሥነ ሥርዐታቸው አከባበር ላይ ተናግረዋል። ይህን ቃላቸውን ከአንድ የሥልጣን ዘመን በኋላም በነበራቸው ሕይወት ቀጥለውት ነበር። የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ከመሆናቸው በተጨማሪ በስማቸው የተሰየመውንና ለትርፍ ያልተቋቋመውን ዓለም አቀፍ ድርጅት፣ የካርተር ማዕከልን መርተዋል። “ሠላምን ማስፈን፣ በሽታን ማጥፋት እና ተስፋን ማለምለም” የማዕከሉ ተልዕኮዎች ናቸው። “የካርተር ማዕከልን ሥራ የምመለከተው ፕሬዝደንት በነበርኩበት ወቅት ለመሥራት የሞከርኩት ተቀጽላ እንደሆነ አድርጌ ነው” ብለዋል ካርተር። ጂሚ ካርተር ፕሌይንስ በተሰነች የጆርጂያ ከተማ በእ.አ.አ 1924 ተወለዱ። ከአሜሪካው የባሕር ኃይል ማሰልጠኛ በ1946 ተመረቁ። የአባታቸውን ሞት ተከትሎ የቤተሰቡን የግብርና ሥራ ለማስተዳደር በ1953 ወደ ትውልድ ከተማቸው ፕሌይንስ እስኪመለሱ ድረስ በባሕር ኃይሉ በሰብመሪን ኦፊሰርነት አገልግለዋል። ካርተር ወደ ፖለቲካው ዓለም የገቡት በ1960ዎቹ የሰብአዊ መብት ንቅናቄዎች በሚካሄዱበት ወቅት ነበር። በጆርጅያ ግዛት ምክር ቤት ለሁለት የሥራ ዘመን አገልግለው ከዛም በ1971 የግዛቲቱ አገረ ገዥ ለመሆን በቅተዋል። በወቅቱ ስለነበረውና በዘር መድልኦ ላይ የሚደረገውን ትግል በተመለከተ ሲናገሩም፣ “በግልጽ የምነግራችሁ ቢኖር የዘር መድልኦ ዘመን አብቅቷል” ብለው ነበር። በ1971 ብዙም ያልታወቁትና በደቡብ የሃገሪቱ ክፍል አገረ ገዥ የነበሩት ካርተር፣ በ1976 ሪፐብሊካኑን ጀራልድ ፎርድ በጠባብ ውጤት በማሸነፍ ፕሬዝደንት ሆኑ። በሶስተኛው ዓመት፣ 1979 “የካምፕ ዴቪድ ስምምነት” ተብሎ የሚጠራውን፣ በግብጽ እና በእስራኤል መካከል የሰላም ስምምነት እንዲፈጸም አስቻሉ። ይህም የፕሬዝደንትነት ዘመናቸው ዋና ስኬት ተደርጎ ይታያል። “ወደ ፕሬዝደንትነት ከመምጣቴ በፊት በአረቦች እና በእስራኤል መካከል በ25 ዓመታት ውስጥ የተደረጉ አራት ጦርነቶች ነበሩ። በሶቪዬት ኅብረት የምትደገፈው ግብጽ በዚህ ውስጥ የመሪነት ሚና ነበራት፡፡ እነዚህ ሃገራት እስራኤልን በወታደራዊ መንገድ ሊገዳደሩ የሚችሉ ብቸኛ ሃገራት ነበሩ” ሲሉ ካርተር ተናግረዋል። ካርተር በተጨማሪም የፓናማ መተላለፊያ በፓናማ ቁጥጥር ሥር እንዲሆን እና ከቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ጋራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲመሠረት አድርገዋል። በ1979 በኢራን የተከሰተው የእስልምና አብዮት ግን የፕሬዝደንታዊ አስተዳደራቸውን አቅጣጫ እንዲቀይር አድርጓል። በሻይት የእስልምና መሪዎች የተመራው ተቃውሞ በአሜሪካ የሚደገፉትን ሻህ ወይም መሪ ከስልጣን ገርስሶ፣ ሻሁም ሃገር ጥለው እንዲወጡ አድርጓል። በ1979 ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ እስላማዊ ነውጠኞቹ ቴህራን ውስጥ የሚገኘውን የአሜሪካን ኤምባሲ ሰብረው በመግባት 66 አሜሪካውያንን አገቱ፡፡ ከአስር ቀናት በኋላ 13 የሚሆኑትን ቢለቁም የተቀሩትን ግን ለ 444 ቀናት አግተው ቆዩ። የቀሩትን ታጋቾች ለማስለቀቅ በሚያዚያ 1980 ካርተር ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ አዘዙ። ሙከራው ሳይሳካ ቀርቶ ስምንት የኤምባሲው ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ። ካርተር በሃገር ውስጥም ፈተና ገጠማቸው። የዋጋ ግሽበትና እየጨመረ የመጣው ሥራ አጥነት ኢኮኖሚውን አንገዳገደው። ይህም በ1980 በተደረገው ምርጫ በሪፕብሊካኑ ሮናልድ ሬገን እንዲረቱ አስተዋጽኦ አድርጓል። ሬገን ቃለ መሃላ በፍጸሙበት ዕለት፣ ኢራን አሜሪካውያን ታጋቾቹን ለቀቀች፡፡ ሽንፈቱ እና ድባቴ የተጫናቸው ካርተር፣ ፕሬዝደንታዊ ቤተ መጽሃፍት ለመገንባት ወደ ትውልድ ከተማቸው አቀኑ። ሐሳባቸው ከቤተ መጻሕፍት ግንባታም አልፎ ወደ ታወቀ ዓለም አቀፍ ትርፋማ ያልሆነ ድርጅትነት ተሸጋገረ። የካርተር ማዕከል ከመቶ በላይ ምርጫዎችን ታዘበ። ከሰሜን ኮሪያ ጋራ ከነበረውን የኑክሌር ፍጥጫ ከመሸምገል፣ በዩጋንዳ እና ሱዳን መካከል የሰላም ስምምነት እንዲፈረም እስከማድረግ ባሉ ተግባራት ሚና ተጫወተ። በጤና መስክ ደግሞ የጊኒ ዎርም በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶ ወደ መጥፋት ደረጃ እንዲደርስ አድርጓል። ካርተር በሰብአዊ መስክ ላደረጉት አስተዋጽኦ በእ.አ.አ 2002 የኖቤል የሰላም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የካርተር ማዕከል በእ.አ.አ 1989 በወቅቱ በኤርትራ የነበሩትን የአማጺያን መሪዎች በኢትዮጵያ ከነበሩት የደርግ መሪዎች ጋራ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ አትላንታ እና ኬንያ እንዲወያዩ አመቻችቷል። ማዕከሉ በኢትዮጵያም ሠላም እና ጤናን ለማስፈን፣ ግጭቶች እንዲቆሙ በማሸማገል፣ ምርጫን በመታዘብና የሰብአዊ መብትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ለረጅም ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል። ጂሚ ካርተር ከአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ሁሉ ረጅም ዕድሜ የኖሩ ናቸው። ከባለቤታቸው ራዝሊን ጋራ የቆዩበት የትዳር ዘመንም እንደ አሜሪካ ፕሬዝደንት እና ቀዳማዊ እመቤት ረጅሙ ነው። Read more