የሶሪያ ሚኒስትሮች የአሜሪካ ማዕቀብ እንዲነሳ ጠየቁ
newsare.net
የሶሪያ የሽግግር መንግስት ሚኒስትሮች ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድን ከስልጣን ካነሱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኳታር ባደረጉት ጉብኝት ዩናይትድ ስቴትስ በደማስየሶሪያ ሚኒስትሮች የአሜሪካ ማዕቀብ እንዲነሳ ጠየቁ
የሶሪያ የሽግግር መንግስት ሚኒስትሮች ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድን ከስልጣን ካነሱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኳታር ባደረጉት ጉብኝት ዩናይትድ ስቴትስ በደማስቆ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እንድታነሳ አሳስበዋል፡፡ የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች ከሶሪያ ጊዜያዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ አል-ሻይባኒ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ሙርሃፍ አቡ ቃስራ እና ከአዲሱ የስለላ ሃላፊ አናስ ኻታብ ጋር መነጋገራቸውን አስታውቋል። ኳታር እንደሌሎች አረብ ሀገራት ሶርያ በአሳድ አስተዳደር ስር እያለች የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ወደነበረበት አልመለሰችም። ከኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ቢን አብዱላዚዝ አልኩላይፊ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ የሶሪያ ጊዜያዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ አል-ሻይባኒ አሜሪካ በሶሪያ ላይ የጣለችው ማዕቀብ እንዲነሳ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል። ጊዜያዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እርምጃዎቹን ለሃገራቸው ፈጣን ማገገም እንቅፋት ነው ሲሉ መንግስታቸው “ዩናይትድ ስቴትስ እነዚህን ማዕቀቦች እንድታነሳ በድጋሜ ይጠይቃል” ሲሉ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። በታህሳስ ወር መጨረሻ ላይ ኳታር በሶሪያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ በፍጥነት እንዲነሳላት ጥሪ አቅርባ እንደነበረም ዘገባው አስታውሷል፡፡ Read more