ሜሎኒ በፍሎሪዳ ድንገተኛ ጉብኝታቸው ከትራምፕ ጋር ያላቸውን ትብብር አሳደጉ
newsare.net
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ትላንት ቅዳሜ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመገናኘት ወደ ፍሎሪዳ ድንገተኛ ጉዞ አድርገዋል። የአውሮፓ መሪዎች እአአ ጥርሜሎኒ በፍሎሪዳ ድንገተኛ ጉብኝታቸው ከትራምፕ ጋር ያላቸውን ትብብር አሳደጉ
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ትላንት ቅዳሜ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመገናኘት ወደ ፍሎሪዳ ድንገተኛ ጉዞ አድርገዋል። የአውሮፓ መሪዎች እአአ ጥር 20 ከሚካሄደው በዓለ ሲመት በፊት ከትራምፕ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ለማጠናከር ይፈልጋሉ፡፡ የትራምፕ የማር-አ-ላጎ ሪዞርት አባላት ተመራጩ ፕሬዘዳንት ትራምፕ ሜሎኒን ሲያስተዋውቋቸው በጭብጨባ ሲቀበሏቸው የሚያሳዩ ቪድዮዎች በማህበራዊ ሚድያ ተጋርተዋል፡፡ «ይህ በጣም አስደሳች ነው፡፡ እኔ እዚህ ያለሁት የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆነች ድንቅ ሴት ጋር ነው» ሲሉ ትራምፕ ለማር-አ-ላጎ አባላት መናገራቸውንም ሚድያዎች ዘግበዋል፡፡ ሜሎኒ ከእአአ 2022 መገባደጃ ጀምሮ በጣልያን የቀኝ ክንፍ ጥምረትን በመምራት ያመጡትን መረጋጋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለትራምፕ ጠንካራ አጋር ተደርገው እየተቆጠሩ ነው። ትራምፕ በምርጫው እንዲያሸንፍ ከሩብ ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ ካደረገው ከቢሊየነር የቴክኖሎጂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሎን ማስክ ጋርም የቅርብ ግንኙነት መፍጠራቸው ይነገራል፡፡ የአውሮፓ ህብረት እና የክልል ጉዳዮች ሚኒስትር ቶማሶ ፎቲ ዛሬ እሁድ እንደተናገሩት ስብሰባው አስቀድሞ ያልተገለፀ ቢሆንም ጣሊያን «በሁለቱ ዓለማት በሆኑት የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ መካከል የዲፕሎማሲ ድልድይ » ልትሆን እንደምትችል ያሳያል ብለዋል። የሜሎኒ ጉዞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከመጭው ሃሙስ እስከ ጥር 12 ሮምን ለመጎብኘት ከያዙት ቀጠሮ አስቀድሞ የተደረገ ነው። ትራምፕ በህዳር ምርጫ ባይደንን አሸንፈው ወደ ኋይት ሀውስ ለመመለስ በዝግጅት ላይ ናቸው። ትራምፕና ሜሎኒ ስላደረጉት ውይይት ዝርዝር መረጃ ባይገለጽም ስለ ሩሲያ ዩክሬን ጦርነት፣ ንግድ ነክ ጉዳዮች፣ መካከለኛው ምስራቅ እና በቴህራን ስለታሰረው ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ ሁኔታ ለመነጋገር ሜሎኒ አስቀድመው እቅዱ እንደነበራቸው የጣሊያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። Read more