የአሜሪካ ጦር የሁቲ ዒላማዎችን መደብደቡን አስታወቀ
newsare.net
የየመን አማፂያን በአሜሪካ የጦር መርከቦች እና የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን መደብደቡን የአሜሪካ ጦየአሜሪካ ጦር የሁቲ ዒላማዎችን መደብደቡን አስታወቀ
የየመን አማፂያን በአሜሪካ የጦር መርከቦች እና የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን መደብደቡን የአሜሪካ ጦር አስታውቋል። በርካታ ድብደባዎች መደረጋቸውንና በአሜሪካ የጦር ኃይል ዓባላትም ሆነ መሣሪያዎች ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል። የዕዙ መግለጫ ድብደባው የተፈፀመበትን የመሣሪያ ማከማቻ ሥፍራ አላሳወቀም። ድብደባዎቹ በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማፂያን በቀጠናው በሚገኙ አጋሮች፣ በወታደራዊ እና የንግድ መርከቦች ላይ የደቀኑትን ስጋት ለመቀነስ የተፈፀሙ መሆናቸውንም ዕዙ አስታውቋል። በሰሜን ምዕራብ አምራን ግዛትና መዲናዋ ሰነአ በምትገኝበት የሰነአ ግዛት ድብደባ መፈፀሙን አል ማሲራ የተሰኘው የሁቲ ቴሌቪዥን ጣቢያ አስታውቋል። የሁቲ አማፂያን ከፍልስጤማውያን ጋራ ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት በሚል ከአንድ ዓመት በላይ በእስራኤልና በቀይ ባሕር እንዲሁም በኤደን ባሕረ ሰላጤ በሚመላለሱ መርከቦች ላይ ሚሳዬሎችን ሲተኩሱ ቆይተዋል። Read more