የሞዛምቢኩ ተቃዋሚ መሪ ከስደት ተመለሱ
newsare.net
ባለፈው መስከረም መጨረሻ በሞዛምቢክ በተካሄደው ምርጫ አሸናፊ እንደሆኑ የሚገልጹት የተቃዋሚ መሪው ቬናንሲዮ ሞንድላኔ ዛሬ ከስደት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋልየሞዛምቢኩ ተቃዋሚ መሪ ከስደት ተመለሱ
ባለፈው መስከረም መጨረሻ በሞዛምቢክ በተካሄደው ምርጫ አሸናፊ እንደሆኑ የሚገልጹት የተቃዋሚ መሪው ቬናንሲዮ ሞንድላኔ ዛሬ ከስደት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ሞንድላኔ አጨቃጫቂውን የምርጫ ውጤትና የጠበቃቸውን መገደል ተከትሎ ሀገር ጥለው ወጥተው ነበር። የሀገሪቱ የሕገ መንግሥት ም/ቤት ገዢው ፓርቲ ምርጫውን እንዳነሸነፈ ማወጁን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ታዛቢዎች ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ እንዳልሆነ ሲያስታውቁ ቆይተዋል። ሞንድላኔ ማፑቶ እንደደረሱ ደጋፊዎቻቸው ቢያጅቧቸውም የፀጥታ ኃይሎች በአስለቃሽ ጭስ በትነዋቸዋል። ወደ ሃገራቸው መመለሳቸው የፖለቲካ ስምምነት መደረጉን የሚያመለክት ሳይሆን፣ በሞዛምቢክ ለመኖር በግል መወሰናቸውን እንደሆነ ሞንድላኔ ተናግረዋል። ፈርተው ከሃገር እንዳልወጡም የተቃዋሚው መሪ አስታውቀዋል። የሞንድላኔ ወደ ሃገር መመለስ ተቃውሞውን እንዳያባብስ ተሰግቷል። በምርጫው አሸናፊ እንደሆኑ የተነገረው የፍሪሊሞ ፓርቲው ዳንኤል ቻፖ በመጪው ሳምንት ቃለ መሃላ እንደሚፈጽሙ ፕሮግራም ተይዟል። ፓርቲው ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሃገሪቱን ሲመራ ቆይቷል። Read more