Ethiopia



ግጭት እና ብጥብጥ ለብዙኀን መገናኛ ላይ ፈተና ደቅነዋል

በቅርብ ሳምንታት ጋዛ እና ሄይቲ ውስጥ በጋዜጠኞች ላይ የተፈጸሙት ግድያዎች ብዙኀን መገናኛ ላይ የተደቀኑትን አደጋዎች አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው። እንደ አው

“የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው የኑሮ ጫናውን ያከብደዋል” የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

በኢትዮጵያ፣ ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በሥራ ላይ የዋለው አዲሱ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ፣ አሁን እየታየ ያለውን የኑሮ ጫና ያባብሰዋል ሲሉ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ
የአሜሪካ ድምፅ

“የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው የኑሮ ጫናውን ያከብደዋል” የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

በኢትዮጵያ፣ ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በሥራ ላይ የዋለው አዲሱ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ፣ አሁን እየታየ ያለውን የኑሮ ጫና ያባብሰዋል ሲሉ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እና የታክሲ አሽከርካሪዎች ስጋታቸውን ገለጹ፡፡ ነዋሪዎቹ፣ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ዙርያ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ፣ የትራንስፖርት ወጪን ያንራል፣ በአገልግሎቶችና ሸቀጦች ዋጋ ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ብለዋል፡፡ አስተያየት ሰጭዎቹ፣ መንግሥት የኅብረተሰቡን የኑሮ ኹኔታ የሚያረጋጉ ርምጃዎችን እንዲወስድም ጠይቀዋል፡፡ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪውና ርምጃው በፈጠረው ስጋት ዙርያ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ በተያያዘ ዜና፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በዛሬ ውሎው የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ስርዐትን ለመደንገግ የወጣ ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል፡፡

አሜሪካ በቲክቶክ ላይ የጣለችው እገዳ ተፈፃሚ ሊሆን ቀናቶች ብቻ ቀርተውታል

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድቤት፣ የማኅበራዊ ሚዲያን በብሔራዊ ደኅንነት ምክንያት ማገድ የሚያስችለው አዲስ ሕግ በመጠቀም፣ የቲክ ቶክ ባለቤት የሆነው ባ
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካ በቲክቶክ ላይ የጣለችው እገዳ ተፈፃሚ ሊሆን ቀናቶች ብቻ ቀርተውታል

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድቤት፣ የማኅበራዊ ሚዲያን በብሔራዊ ደኅንነት ምክንያት ማገድ የሚያስችለው አዲስ ሕግ በመጠቀም፣ የቲክ ቶክ ባለቤት የሆነው ባይትዳንስ የቻይና ኩባንያ የሚያደርገው የቃል ክርክር በፍጥነት እንዲጠናቀቅ እያደረገ ነው። የአሜሪካ ድምፁ ስቲቭ ኸርማን በዚህ ዙሪያ ያደረሰንን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በስፋት እየተዛመተ ላለው የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት በሺሕዎች የተቆጠሩ አካባቢያቸውን እንዲለቁ ታዘዙ

የእሳት አደጋ ሠራተኞች ብርቱ ትንቅንቅ እያደረጉ ላሉበት አደገኛ የሰድድ እሳት ቃጠሎ፣ ከ130 ሺሕ በላይ የሎስ አንጀለስ አካባቢ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እን
የአሜሪካ ድምፅ

በስፋት እየተዛመተ ላለው የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት በሺሕዎች የተቆጠሩ አካባቢያቸውን እንዲለቁ ታዘዙ

የእሳት አደጋ ሠራተኞች ብርቱ ትንቅንቅ እያደረጉ ላሉበት አደገኛ የሰድድ እሳት ቃጠሎ፣ ከ130 ሺሕ በላይ የሎስ አንጀለስ አካባቢ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል። እስካሁን ቢያንስ አምስት ሰዎች በአደጋው ሕይወታቸውን ማጣታቸው እና ከ1 ሺሕ በላይ ሕንፃዎች መውደማቸው ታውቋል። ትላንት ከቀትር በኋላ ላይ አዲስ የተቀሰቀሰው እና በጥድፊያ እየተዛመተ ያለው ቃጠሎ ‘ሆሊውድ ሂልስ’ በመባል የሚታወቀው ማዕከላዊ ሎስ አንጀለስ የሚገኝ የመኖሪያ መንደር ነዋሪዎች ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ቤታቸውን ጥለው እንዲሸሹ በማስገደድ የቅርብ ጊዜው ነው። ለሰደድ እሳቱ መዛመት አመች ያደረገው፡ በአካባቢው ያለው ደረቅ የአየር ጠባይ እና ኃይለኛ ነፋስ ተቀላቅለው እስከ ነገ አርብ ድረስ አሁን በያዘው ፍጥነት እንደሚቀጥል የሚቲዎሮሎጂ ባለሞያዎች ጠቁመዋል። በአንጻሩ የእሳቱን መዛመት ለመከላከል የተሰማሩትን አውሮፕላኖች ሥራ አስተጓጉሎ የነበረው ኃይለኛ ንፋስ ከትላንት ረቡዕ አንስቶ ሥራቸውን መልሰው እንዲቀጥሉ በሚያስችል ሁኔታ መቀነሱም ተጠቁሟል። «ዛሬ ማምሻው ላይ ያለው ቀለል ያለ የንፋስ ሁኔታ የሰደድ እሳቱን መዛመት ለመከላከል የሚያግዙ አውሮፕላኖች እና ብዛት ያላቸው ተጨማሪ መከላከያዎች ወደ እሳቱ ለማቅረብ አስችሎናል” ያሉት የፓሳዴና የእሳት አደጋ ዋና አዛዥ ቻድ አውጉስቲን “ይህም አደጋውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ስለመቻላችን ተስፋ ሰጥቶናል” ብለዋል።   የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የሰደድ እሳቱን መዛመት ለመዋጋት ለሚያስፈልገው ሥራ የሚውል የገንዘብ እና ሌሎች እርዳታዎች ለካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት ለመልቀቅ የሚያስችል የፌደራል የአደጋ ጊዜ አዋጅ አጽድቀዋል። ዋይት ሀውስ ትላንት ረቡዕ ማምሻው ላይ እንዳስታወቀው ባይደን “በቀጣዩ ቀናት ውስጥ ሙሉ ትኩረታቸውን የፌዴራል መንግስቱ ለሚሰጠው ጠቅላላ ምላሽ አመራር ለመስጠት” ወደ ጣሊያን ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ ሰርዘዋል። »ሰደድ እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር፣ አካባቢውን መልሶ የመገንባቱ ጥረት መስመሩን እና ብሎም ወደ ቀድሞው የተረጋጋ ሁኔታ መመለሱን እስክናረጋገጥ ድረስ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ተዘጋጅተናል። ብዙ ጊዜ መውሰዱ የማይቀር ነው” ያሉት ባይደን፣ “ያለጥርጥርም ረዥም ጉዞ የሚጠይቅ ነው” ሲሉ አክለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚንስቴርም “ተጨማሪ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን እና እገዛዎችን” ወደ ግዛቱ ለመላክ ቃል ገብቷል። የአደጋ ጊዜ ባለሥልጣናት መሰንበቻውን የታየውን ደረቅ የዓየር ሁኔታ ተንተርሰው በሎስ አንጀለስ አካባቢ የሰደድ እሳት ሊቀሰቀስ እንደሚችል ቢያስጠነቅቁም፣ የሰደድ እሳቱ መዛመት ግን ከተጠበቀውም የከፋ መሆኑ ተዘግቧል። «የሎስ አንጀለስ አውራጃ የእሳት አደጋ መከላከያ ለአንድ ወይም ለሁለት ዋና ዋና የሚሰኙ የቃጠሎ አደጋዎች መዘጋጀቱን ጠቁመው፣ የነፋሱ ማየል እና በአካባቢው ያለው ዝቅተኛ እርጥበት ተደማምረው ለደረሱት አራት ከፍተኛ ቃጠለዎች መዘጋጀቱን አዳጋች አድርገውታል» ሲሉ የአውራጃው የእሳት አደጋ መከላከያ አዛዥ አንተኒ ማሮን ትላንት ረቡዕ ተናግረዋል። ከሆሊዉድ እና አካባቢው በተጨማሪ በፓሲፊክ ፓሊሴድስ፣ አልታዴና፣ ፓሳዴና እና ሲልማር የተባሉት መንደሮች ቃጠሎው ከበረታባቸው አካባቢዎች ውስጥ ናቸው። በእስካሁኑ ቃጠሎ በርካታ ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የነበረ ሃብት የወደመ ሲሆን፤ እሳቱ አሁንም መዛመቱን አላቆመም። ማሮን ይህንን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት “እሳቱን ማጥፋት የተቻለበትን ሥፍራ መጠን የሚያረጋግጥ ስሌት እስካሁን የለንም” ብለዋል። የአካባቢውን የእሳት አደጋ ሰራተኞች ለመርዳት ቁጥራቸው ሁለት ሺህ የሚጠጋ የብሄራዊው ጥበቃ አባላት መሰማራታቸውም ታውቋል። በአውሎ ንፋስ እየተገፋ ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው የተዛመተው እሳት ከፍተኛ ጉዳት ባደረሰበት የፓሲፊክ ፓሊሴድስ አካባቢ የአደጋ ሰራተኞች እሳቱን ለማጥፋት ይጠቀሙባቸው የነበሩትን ውሃ ማጠራቀሚያዎች ማራቆቱም ተመልክቷል።  በፓስፊክ ፓሊሴድስ የደረሰው ቃጠሎ በሎስ አንጀለስ ታሪክ እስከዛሬ ከታዩት ሁሉ በአውዳሚነቱ የከፋው ሲሆን፤ እስካሁን በተረጋገጠው ከ1 ሺሕ በላይ ሕንፃዎች ተቃጥለዋል። የፓሊሴድሱ ቃጠሎ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2008 ከደረሰው እና ‘የሳየሬ እሳት’ የሚል ስያሜ ከተሰጠው በከተማይቱ ሰሜናዊ ዳርቻ የሚገኙ 604 ሕንፃዎችን ካወደመውም ታሪካዊው የእሳት አደጋም የከፋ ነው።

የጂሚ ካርተ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

በ100 ዓመታቸው ባለፈው እሑድ  ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አስከሬን ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ብሔራዊ ካቴድራል ዛሬ
የአሜሪካ ድምፅ

የጂሚ ካርተ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

በ100 ዓመታቸው ባለፈው እሑድ  ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አስከሬን ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ብሔራዊ ካቴድራል ዛሬ የአሸኛኘት ሥነ ሥርዓት ተደርጎለታል። ከብሔራዊ ካቴድራሉ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት በኋላ 39ኛው ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር በትውልድ ከተማቸው ፕሌይንስ፣ ጆርጂያ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ቅጥር ጊቢ ውስጥ ባለፈው ዓመት በሞት ከተለዩትና የ77 ዓመታት የትዳር አጋራቸው ሮዘሊን ካርተር ጎን እንደሚቀበሩም ታውቋል። በብሔራዊ ካቴድራል በተደረገው ሥነ ሥርዓት የአሜሪካ  የቀድሞ ፕሬዝደንቶችና ምክትል ፕሬዝደንቶች የተገኙ ሲሆን፣ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የውዳሴ ንግግር አድርገዋል። ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሚፈጸመው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የቤተሰብ ዓባላትና ጓደኞች እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ብቻ እንደሚገኙ ታውቋል። ጂሚ ካርተር ፕሌይንስ በተሰነች የጆርጂያ ከተማ በእ.አ.አ 1924 ተወለዱ። ከአሜሪካው የባሕር ኃይል ማሰልጠኛ በ1946 ተመረቁ። የአባታቸውን ሞት ተከትሎ የቤተሰቡን የግብርና ሥራ ለማስተዳደር በ1953 ወደ ትውልድ ከተማቸው ፕሌይንስ እስኪመለሱ ድረስ በባሕር ኃይሉ በሰብመሪን ኦፊሰርነት አገልግለዋል። በ1971 ብዙም ያልታወቁትና በደቡብ የሃገሪቱ ክፍል የጆርጂያ አገረ ገዥ የነበሩት ካርተር፣ በ1976 ሪፐብሊካኑን ጀራልድ ፎርድ በጠባብ ውጤት በማሸነፍ ፕሬዝደንት 39ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነዋል። ካርተር በሰብአዊ መስክ ላደረጉት አስተዋጽኦ በእ.አ.አ 2002 የኖቤል የሰላም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ጂሚ ካርተር ከአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ሁሉ ረጅም ዕድሜ የኖሩ ናቸው። ከባለቤታቸው ራዝሊን ጋራ የቆዩበት የትዳር ዘመንም እንደ አሜሪካ ፕሬዝደንት እና ቀዳማዊ እመቤት ረጅሙ ነው።

የሞዛምቢኩ ተቃዋሚ መሪ ከስደት ተመለሱ

ባለፈው መስከረም መጨረሻ በሞዛምቢክ በተካሄደው ምርጫ አሸናፊ እንደሆኑ የሚገልጹት የተቃዋሚ መሪው ቬናንሲዮ ሞንድላኔ ዛሬ ከስደት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል
የአሜሪካ ድምፅ

የሞዛምቢኩ ተቃዋሚ መሪ ከስደት ተመለሱ

ባለፈው መስከረም መጨረሻ በሞዛምቢክ በተካሄደው ምርጫ አሸናፊ እንደሆኑ የሚገልጹት የተቃዋሚ መሪው ቬናንሲዮ ሞንድላኔ ዛሬ ከስደት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ሞንድላኔ አጨቃጫቂውን የምርጫ ውጤትና የጠበቃቸውን መገደል ተከትሎ ሀገር ጥለው ወጥተው ነበር። የሀገሪቱ የሕገ መንግሥት ም/ቤት ገዢው ፓርቲ ምርጫውን እንዳነሸነፈ ማወጁን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ታዛቢዎች ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ እንዳልሆነ ሲያስታውቁ ቆይተዋል። ሞንድላኔ ማፑቶ እንደደረሱ ደጋፊዎቻቸው ቢያጅቧቸውም የፀጥታ ኃይሎች በአስለቃሽ ጭስ በትነዋቸዋል። ወደ ሃገራቸው መመለሳቸው የፖለቲካ ስምምነት መደረጉን የሚያመለክት ሳይሆን፣ በሞዛምቢክ ለመኖር በግል መወሰናቸውን እንደሆነ ሞንድላኔ ተናግረዋል። ፈርተው ከሃገር እንዳልወጡም የተቃዋሚው መሪ አስታውቀዋል። የሞንድላኔ ወደ ሃገር መመለስ ተቃውሞውን እንዳያባብስ ተሰግቷል። በምርጫው አሸናፊ እንደሆኑ የተነገረው የፍሪሊሞ ፓርቲው ዳንኤል ቻፖ በመጪው ሳምንት ቃለ መሃላ እንደሚፈጽሙ ፕሮግራም ተይዟል። ፓርቲው ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሃገሪቱን ሲመራ ቆይቷል።

የግብጽ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ፍልስጤማውያን በአንድነት እንዲቆሙ ጠየቁ

ከፍልስጤም የነፃነት ድርጅት (ፒ ኤል ኦ) ተወካዮች ጋራ ዛሬ የተገናኙት የግብጹ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር የፍልስጤማውያን ራስ ገዝ አስተዳደር እንዲጠናከርና ፍልስ
የአሜሪካ ድምፅ

የግብጽ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ፍልስጤማውያን በአንድነት እንዲቆሙ ጠየቁ

ከፍልስጤም የነፃነት ድርጅት (ፒ ኤል ኦ) ተወካዮች ጋራ ዛሬ የተገናኙት የግብጹ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር የፍልስጤማውያን ራስ ገዝ አስተዳደር እንዲጠናከርና ፍልስጤማውያን በአንድነት እንዲቆሙ ጥሪ አድርገዋል። በውይይቱ ወቅት የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ባድር አብደላቲ ለፍልስጤማውያን ራስ ገዝ አስተዳደር  ሃገራቸው ያላትን ድጋፍ እንደገለጹ ከቢሯቸው የወጣው መግለጫ አመልክቷል። በተጨማሪም ፍልስጤማውያንን ከመሬታቸው ላይ ለማፈናቀል ያለም ማንኛውም ዕቅድ ግብጽ እንደምትቃወም ማስታወቃቸው ተመልክቷል። ግብጽ ባለፈው ወር ፋታህ እና ሐማስ በተሰኙት ፍልስጤማውያን ቡድኖች መካከል ጋዛ ከጦርነቱ በኋላ በፍልስጤማውያን ራስ ገዝ አስተዳደር ቁጥጥር ሥር በሚሆንበት ሁኔታ ላይ ውይይት አስተናግዳ ነበር። በእስራኤል በተያዘው ዌስት ባንክ የተወሰነውን ክፍል የሚያስተዳድረው ፋታህ፣ በፍልስጤማውያን ራስ ገዝ አስተዳደርም ሆነ ፍልስጤማውያንን እንደሚወክል ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው ፒ ኤል ኦ ላይ ተጽእኖ እንዳለው ይነገራል። ሐማስ በእ.አ.አ 2007 ጋዛን ከተቆጣጠረ ወዲህ ፋታህ ከጋዛ እንዲገለል ተደርጓል።

በቻድ ፕሬዝደንታዊ ቤተ መንግሥት ላይ የተሰነዘረው ጥቃት መክሸፉን መንግሥት አስታወቀ

የጦር መሣሪያና ምሳር የያዙ፣ ሁለት ደርዘን የሚሆኑና የኮማዶ አባላት ናቸው የተባሉ፣ በቻድ የፕሬዝደንቱ ቤተ መንግሥት ላይ ትላንት ምሽት ጥቃት መሰንዘራቸው
የአሜሪካ ድምፅ

በቻድ ፕሬዝደንታዊ ቤተ መንግሥት ላይ የተሰነዘረው ጥቃት መክሸፉን መንግሥት አስታወቀ

የጦር መሣሪያና ምሳር የያዙ፣ ሁለት ደርዘን የሚሆኑና የኮማዶ አባላት ናቸው የተባሉ፣ በቻድ የፕሬዝደንቱ ቤተ መንግሥት ላይ ትላንት ምሽት ጥቃት መሰንዘራቸው ሲነገር፣ መንግሥት በበኩሉ ማክሸፉን አስታውቋል። ተቃዋሚው ፓርቲ ደግሞ የመንግሥትን መግለጫ እንደሚጠራጠር ገልጿል። የመንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት አብደራማን ኩላማላህ፣ ሃያ አራት የሚሆኑ የኮማንዶ ዓባላት በቤተ መንግሥቱን ጠባቂዎች ላይ ጥቃት ቢሠነዝሩም ወዲያውኑ ሊገቱ ችለዋል ብለዋል። ሁኔታዎችን በቁጥጥር ሥር ማድረግ መቻላቸውንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። በክስተቱ 19 ሰዎች እንደተገደሉ ተመልክቷል። አብዛኞቹ ጥቃት አድራሾቹ ናቸው ተብሏል። ኢንጃሚና ትላንት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ በፕሬዝደንቱ ቤት መንግሥት አቅራቢያ ከፍተኛ ተኩስ የተሰማ ሲሆን፣ ወደ ቤተ መንግሥቱ የሚያመሩት መንገዶች ሲዘጉ፣ ታንኮችን በመንድ ላይ ማየቱን በሥፍራው የነበረው የኤኤፍፒ ዜና ወኪል በዘገባው አመልክቷል። በጥቃቱ ወቅት ፕሬዝደንት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ኢንቶ በቤተ መንግሥት ውስጥ እንደነበሩ ተነግሯል። የጥቃት አድራሾ ዓላማ ምን እንደሆነ አለመታወቁን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

ቻይናዊያን ጎብኚዎች እና ነጋዴዎች ወደሲሼልስ እየጎረፉ ነው

አፍሪካ ምሥራቃዊ ጠረፍ ላይ የምትገኘው የደሴቶች ሀገር ሲሼልስ ሰፊ የባሕል ስብጥር ያላቸው ሰዎች አብረው የሚኖሩባት ሀገር ነች። በዘር ሐረግ ቻይናዊያን የሆ
የአሜሪካ ድምፅ

ቻይናዊያን ጎብኚዎች እና ነጋዴዎች ወደሲሼልስ እየጎረፉ ነው

አፍሪካ ምሥራቃዊ ጠረፍ ላይ የምትገኘው የደሴቶች ሀገር ሲሼልስ ሰፊ የባሕል ስብጥር ያላቸው ሰዎች አብረው የሚኖሩባት ሀገር ነች። በዘር ሐረግ ቻይናዊያን የሆኑ ለረጅም ጊዜ ሲሼልስ የሚኖሩ ሰዎች አሉ። አሁን ደግሞ ቻይናዊን ሀገራቸው በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ ቁልፍ በኾነችው ሀገር መዋዕለ ነዋይ በመመደብ በምታደርገው እንቅስቃሴ ተስበው የንግድ ሥራ ለመጀመር ሲሼልስ በብዛት በመግባት ላይ ናቸው። ኬት ባርትሌት ከትልቋ የሲሼልስ ደሴት ከተማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ትረምፕ ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ ዳኛው የቅጣት ውሳኔ እንዳይሰጡ እንዲታገድላቸው ጠየቁ

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ጥፋተኛ በተባሉበት የአፍ ማሳዢያ ክፍያ  ክስ ጉዳይ  ዳኛው የቅጣት ውሳኔያቸውን እንዳያሰሙ እንዲታገድ ጠበቆቻቸው ጠቅላይ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ ዳኛው የቅጣት ውሳኔ እንዳይሰጡ እንዲታገድላቸው ጠየቁ

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ጥፋተኛ በተባሉበት የአፍ ማሳዢያ ክፍያ  ክስ ጉዳይ  ዳኛው የቅጣት ውሳኔያቸውን እንዳያሰሙ እንዲታገድ ጠበቆቻቸው ጠቅላይ ፍ/ቤቱን ጠይቀዋል። ዳኛዋን መርቻን ፣ ትረምፕ ባለፈው ሐምሌ የንግድ ሰነዶችን በማጭበርበር በ34 ክሶች ጥፋተኛ ኾነው በመገኘታቸው የቅጣት ውሳኔያቸውን ከነገ በስቲያ ዐርብ ሊሰጡ  ቀጠሮ ይዘዋል። የቅጣት ውሳኔው መሰማቱ በፕሬዝደንታዊ ተቋሙና በፌዴራል መንግሥቱ ሥራ ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ ተጽዕኖ እና ጉዳት ያደርሳል በሚል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንዲያግድ የትረምፕ ጠበቆች ጠይቀዋል። ዳኛው በትረምፕ ላይ የእሥርም ኾነ የገንዘብ ቅጣት ወይም   ወይም የአመክሮ ገደብ ያለው ትዕዛዝ እንደማያስተላልፉባቸው አመላክተዋል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛው እስከ ነገ ሐሙስ ድረስ መልስ እንዲሰጡ ጠይቋል። የትረምፕ ጠበቆች ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ከዚህ በፊት ሰጥቷቸው የነበረውን ያለመከሰስ መብት በመጥቀስ ዐርብ ሊሰማ ቀጠሮ የተያዘለትን የቅጣት ውሳኔ እንዳይከናወን ጠይቀዋል። የትረምፕ ጠበቆች በተጨማሪም ከክሱ ጋራ ተያይዘው የቀረቡ አንዳንዶቹ ማስረጃዎች በፕሬዝደንታዊ ያለመከሰስ መብት መሠረት ይፋ መውጣት እንደሌለባቸው ቢጠይቁም፣ ዳኛው እንደማይስማሙ አስታውቀዋል።

በ84 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ፣ 84 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመማር ማስተማር ሥራው እንዳይቀጥሉ እንደተወሰነባቸው የሀገሪቱ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ።
የአሜሪካ ድምፅ

በ84 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ፣ 84 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመማር ማስተማር ሥራው እንዳይቀጥሉ እንደተወሰነባቸው የሀገሪቱ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ። ርምጃው የተወሰደው፣ ተቋማቱ ዳግም እንዲመዘገቡ የወጣውን መመሪያ ባለማክበራቸው እንደሆነ የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ቃለአቀባይ ማርታ አድማሱ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡፡ አስተያየት የሰጡን፣ የዘርፉ ተዋናዮች ደግሞ ለዳግመ ምዝገባው የተሰጠው ጊዜ አጭር ነው፣ የምዝገባ መመሪያውም ውይይት ያልተደረገበትና የማያሠራ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

የአሜሪካ ጦር የሁቲ ዒላማዎችን መደብደቡን አስታወቀ

የየመን አማፂያን በአሜሪካ የጦር መርከቦች እና የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን መደብደቡን የአሜሪካ ጦ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ ጦር የሁቲ ዒላማዎችን መደብደቡን አስታወቀ

የየመን አማፂያን በአሜሪካ የጦር መርከቦች እና የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን መደብደቡን የአሜሪካ ጦር አስታውቋል። በርካታ ድብደባዎች መደረጋቸውንና በአሜሪካ የጦር ኃይል ዓባላትም ሆነ መሣሪያዎች ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል።  የዕዙ መግለጫ ድብደባው የተፈፀመበትን የመሣሪያ ማከማቻ ሥፍራ አላሳወቀም። ድብደባዎቹ በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማፂያን በቀጠናው በሚገኙ አጋሮች፣ በወታደራዊ እና የንግድ መርከቦች ላይ የደቀኑትን ስጋት ለመቀነስ የተፈፀሙ መሆናቸውንም ዕዙ አስታውቋል። በሰሜን ምዕራብ አምራን ግዛትና መዲናዋ ሰነአ በምትገኝበት የሰነአ ግዛት ድብደባ መፈፀሙን አል ማሲራ የተሰኘው የሁቲ ቴሌቪዥን ጣቢያ አስታውቋል። የሁቲ አማፂያን ከፍልስጤማውያን ጋራ ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት በሚል ከአንድ ዓመት በላይ በእስራኤልና በቀይ ባሕር እንዲሁም በኤደን ባሕረ ሰላጤ በሚመላለሱ መርከቦች ላይ ሚሳዬሎችን ሲተኩሱ ቆይተዋል።

ትላልቆቹ ኃያላን የሚፎካከሩባት ትንሿ የደሴቶች ሀገር ሲሼልስ

በአፍሪካ ምሥራቃዊ የውቅያኖስ ጠረፍ ላይ የምትገኘው ትንሿ የደሴት ሀገር ሲሼልስ ሳትጠበቅ ትላልቅ ኃያላን ፉክክር ቦታ ሆናለች፡፡ ቻይና ከሲሼልስ ጋራ ለዓመታ
የአሜሪካ ድምፅ

ትላልቆቹ ኃያላን የሚፎካከሩባት ትንሿ የደሴቶች ሀገር ሲሼልስ

በአፍሪካ ምሥራቃዊ የውቅያኖስ ጠረፍ ላይ የምትገኘው ትንሿ የደሴት ሀገር ሲሼልስ ሳትጠበቅ ትላልቅ ኃያላን ፉክክር ቦታ ሆናለች፡፡ ቻይና ከሲሼልስ ጋራ ለዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ስትገነባ ቆይታለች፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ግን ወሳኝ ወደ ሆነቸው የህንድ ውቅያኖስ ደሴት የተመለሰችው በቅርቡ ነው። ኬት ባርትሌት ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ የደሴቲቱን ነዋሪዎች ልብ ለመማረክ ምን እያደረጉ እንደሆነ ለመመልከት ወደሲሸልስ ማሄ ደሴት ተጉዛለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በኬኒያ እየጨመረ ያለው የሴቶች  ጥቃት

ኬኒያ ውስጥ ካለፈው 2024 ዓመተ ምሕረት መስከረም ወር ወዲህ ባለሥልጣናት የመዘገቧቸው በሴቶች ላይ የተፈጸሙ ወሲባዊ እና ሊሎችም ጾታዊ ጥቃቶች ቁጥር ከሰባት ሺ
የአሜሪካ ድምፅ

በኬኒያ እየጨመረ ያለው የሴቶች  ጥቃት

ኬኒያ ውስጥ ካለፈው 2024 ዓመተ ምሕረት መስከረም ወር ወዲህ ባለሥልጣናት የመዘገቧቸው በሴቶች ላይ የተፈጸሙ ወሲባዊ እና ሊሎችም ጾታዊ ጥቃቶች ቁጥር ከሰባት ሺህ አንድ መቶ መብለጡ ተነግሯል። የሀገሪቱ የደኅንነት ሚኒስቴር እየተባባሰ ላለው በሴቶች እና በልጃገረዶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት መፍትሔ የሚፈልግ ልዩ ቡድን አቋቁሟል። መሐመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ገና በላሊበላ

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት - ገና በዓል በልዩ ኹኔታ ከሚከበርባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች በቀዳሚነት የምትጠቀሰው፣ በዐማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ የ
የአሜሪካ ድምፅ

ገና በላሊበላ

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት - ገና በዓል በልዩ ኹኔታ ከሚከበርባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች በቀዳሚነት የምትጠቀሰው፣ በዐማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ የምትገኘው የላሊበላ ከተማ ናት። በዩኔስኮ የሰው ልጆች ቅርስ ኾኖ የተመዘገቡት የ11 ውቅር አብያተ መቅደሶች መገኛዋ ላሊበላ፣ በገና በዓል ሰሞን፣ ዐያሌ የአገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎችንና ተሳላሚ ምእመናንን በሞቀ አቀባበል ታስተናግዳለች። በዐማራ ክልል የቀጠለው በትጥቅ የተደገፈ ግጭት ከመቀስቀሱና ከመስፋፋቱ በፊት፣ ለክብረ በዓሉ ከተለያዩ ስፍራዎች ወደ ላሊበላ ከተማ የሚጎርፉት ጎብኚዎች ብዛት በሚሊዮኖች የሚቆጠር እንደነበር፣ የከተማዋ አስተዳደር መረጃ ያመለክታል። የከተማዋ ነዋሪዎች፣ «ከወትሮው የተቀዛቀዘ ነው፤» ብለዋል። የሰሜን ወሎ ዞን ባህል እና ቱሪዝም መምሪያ ሓላፊ ገነት ሙሉጌታ ደግሞ፣ በዓሉ በተለመደው መልኩ እንዲከበር አስቀድመው ጥሪ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸው፣ «በዓሉን የሚያከብሩ ሰዎች ወደ ከተማ እየገቡ ነው፤» ብለዋል። በተጨማሪም፣ የበዓሉን ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ይዘት የሚያስረዱ ባለሞያዎች በፕሮግራሙ ላይ መካተታቸውን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የባሕረ ሐሳብ ሊቃውንት፣ «ተረፍ/ተውሳክ» እያሉ የሚጠሯት ጳጉሜን የምትጨምረውን የቀናት ቁጥር ተከትሎ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት - ገና፣ በየአራት ዓመቱ ታኅሣሥ 28 ቀን ከዚያ በቀር ግን ታኅሣሥ 29 ላይ ይውላል። ዘንድሮም፣ ነገ ታኅሣሥ 29 ቀን ይከበራል። በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩት በዓላት፣ ገና በደማቅነቱ ይወሳል፡፡ ስያሜው፣ «ጌና» ከሚለው የግሪክ ቃል የተወረሰ ሲኾን፣ ትርጉሙም ልደት ማለት ነው። ቃሉ የአረብኛም መሠረት እንዳለውና ምስጋና፣ ብልጥግና የሚል ትርጉምም እንዳለው ሊቃውንቱ ያስረዳሉ። በቤተ ልሔም የክርስቶስ መወለድ የተበሠረበት፣ መላእክት እና እረኞች በአንድነት ያመሰገኑበት፣ ሦስቱ የጥበብ ሰዎች እጅ መንሻ ያቀረቡበት ገናናው ገና፣ ከመንፈሳዊ ይዘቱ ባሻገር ያለው ማኅበራዊ እና ባህላዊ ክንዋኔው በብዙኀኑ ዘንድ ተናፋቂ እንደሚያደርገው ሊቃውንቱ ያስረዳሉ። ከወጥ አለት የተፈለፈሉትን ዐሥራ አንዱን ውቅር አብያተ መቅደስ እንዳነፃቸው የሚታመነውና ከ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የዛጉዌ ነገሥታት አንዱ የነበረው የቅዱስ ላሊበላም ልደት፣ ታኅሣሥ 29 ቀን እንደሚከበር፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዛግብት በሰሜን ወሎ አገረ ስብከት የደብረ ሮሃ የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ ዲያቆን ተስፋ ውቤ ገና ያስረዳሉ። በላሊበላ የበዓለ ገና አከባበር፣ «ቤዛ ኩሉ» ተብሎ የሚጠራው በጠዋቱ የሚደረገው የሊቃውንቱ ዝማሬ፣ ልዩ እና ታላቅ የክብረ በዓሉ ትዕይንት ነው። የሚከናወነውም ከጸሎተ ቅዳሴው በኋላ ቤተ ማርያም በተባለው ቤተ መቅደስ ሲኾን፣ ከታች ባለነጭ ካባ ካህናት፣ ከላይ ደግሞ ባለጥቁር ካባ ካህናት በቅዱስ ያሬድ ዜማ «ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ» ማለትም «የዓለም ኹሉ መድኃኒት ዛሬ ተወለደ» እያሉ ይዘምራሉ። በጥቅሉ፣ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ቅዱስ መካን በኾነችውና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ደግሞ የቅርስ ማእከል ኾና በተመዘገበችው ላሊበላ፣ ገና የገነነ ስፍራ አለው፡፡ አማኞች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ወድ ሥፍራው በመሔድ ያከብራሉ። ኾኖም “የዘንድሮውን ገና በጸጥታ መደፍረስና በኑሮ ውድነት ምክንያት በቀድሞ ድምቀቱ ለማክበር ይቸግራል፤” ይላሉ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ምእመናን፡፡ የዐማራ ክልል መንግሥት ደግሞ “በዓሉን አብረን እናክብር” የሚል መልእክት ሲያስተላልፍ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን በመጥቀስ ነው፡፡ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

“የህወሓት አመራሮችን ልዩነት በድርድር ለመፍታት የተደረገው አልተሳካም” ጄነራል ታደሰ ወረደ

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት በድርድር ለመፍታት፣ በክልሉ የጸጥታ አመራር አካላት ለወራት የተካሔደው ጥረት እንዳልተሳካ የክልሉ ምክትል ፕ
የአሜሪካ ድምፅ

“የህወሓት አመራሮችን ልዩነት በድርድር ለመፍታት የተደረገው አልተሳካም” ጄነራል ታደሰ ወረደ

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት በድርድር ለመፍታት፣ በክልሉ የጸጥታ አመራር አካላት ለወራት የተካሔደው ጥረት እንዳልተሳካ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ሌተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ገለጹ። የተከፋፈሉት የህወሓት አመራሮች፣ ሁለቱም አሸናፊ የሚኾኑበትን መንገድ ከመምረጥ ይልቅ አንደኛው አንደኛውን ለማጥፋት በመፈለጋቸው ድርድሩ ሊሳካ አልቻለምም ብለዋል። ከሁለቱም ወገን ምላሽ ለማግነት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ከፓርቲያቸው መሪነት ለቀቁ

የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ ከለዘብተኛው ፓርቲ መሪነት ራሳቸውን ማግለላቸውን ዛሬ አስታውቀዋል። በአመራራቸው ላይ ተቃውሞ የበረታባቸው ትሩዶ
የአሜሪካ ድምፅ

የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ከፓርቲያቸው መሪነት ለቀቁ

የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ ከለዘብተኛው ፓርቲ መሪነት ራሳቸውን ማግለላቸውን ዛሬ አስታውቀዋል። በአመራራቸው ላይ ተቃውሞ የበረታባቸው ትሩዶ  በተለይም የገንዘብ ሚንስትራቸው ከሥልጣናቸው መልቀቃቸው በመንግሥታቸው ውስጥ ያለው ችግር የበረታ መሆኑን አመላክቶ ነበር። በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው መፋተግ የሚያመለክተው በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ እርሳቸው ጥሩ አማራጭ አለመሆናቸውን እንደሆነ ትሩዶ ተናግረዋል። ፓርቲው አዲስ መሪ እስከሚመርጥም በጠቅላይ ሚንስትርነት እንደሚቆዩ ትሩዶ አስታውቀዋል። ከሃያ ቀናት በኋላ ሥራውን መልሶ እንደሚጀምር ይጠበቅ የነበረው ፓርላማም እስከ መጋቢት አጋማሽ ድረስ እንደማይመለስ ተነግሯል። ባለው ጊዜም ለዘብተኛ ፓርቲው መሪውን እንደሚመርጥ ይጠበቃል። በካናዳ ሦስቱም ዋና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ፓርላማው በሚከፈትበት ወቅት ለዘብተኛ ፓርቲውን የትምምን ድምጽ ነፍገው ከሥልጣን እንደሚያስወግዱ አስታውቀው ነበር። ጀስቲን ትሩዶ ወደ ሥልጣን የመጡት ከአስር ዓመታት በፊት እ፡አ፡አ በ2015 ነበር። ይህም ለ10 ዓመታት የወግ አጥባቂ ፓርቲው ሃገሪቱ ከመራ በኋላ መሆኑ ነው። የምግብ ሸቀጥ ዋጋ እና የመኖሪያ ቤት መወደድ እንዲሁም የስደተኞች ቁጥር መጨመር ድምጽ ሰጪዎች በትሩዶ ላይ እንዲያማርሩ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።

አስር የአልሻባብ አባላት በአየር ጥቃት ተገደሉ

የአሜሪካ ጦር በፈጸመው የአየር ጥቃት 10 የአል ሻባብ አባላት መገደላቸውን የሶማሊያ መንግሥት አስታውቋል። የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በመግለጫው እንዳ
የአሜሪካ ድምፅ

አስር የአልሻባብ አባላት በአየር ጥቃት ተገደሉ

የአሜሪካ ጦር በፈጸመው የአየር ጥቃት 10 የአል ሻባብ አባላት መገደላቸውን የሶማሊያ መንግሥት አስታውቋል። የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በመግለጫው እንዳለው፣ የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው ቢርሃኒ በተባለና ከኪሲማዮ ሰሜን ምዕራብ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ሥፍራ ነው። የሚኒስቴሩ መግለጫ የወጣው ትላንት እሑድ ሲኾን፣ የአየር ጥቃቱ መቼ እንደተፈጸመ ግን አላሳወቀም። የሶማሊያው የማስታወቂያ ሚኒስቴር። “ኻዋሪጅ (ወይም አፈንጋጮች) ጥቃት ለማድረስ በማቀድ ላይ ሳሉ  ተደምስሰዋል። በጥቃቱ ሲቪሎች ላይ ጉዳት አልደረሰም” ብሏል  “የሶማሊያ ኅይሎች አሜሪካ ዋናው አካል ከሆነው ዓለም አቀፍ አጋር ጋራ በመተባበር ኻዋሪጆችን ለማጥፋትና በሶማሊያ ሕዝብ ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ለመከላከል ቁርጠኞች ናቸው” ሲል አክሏል የማስታወቂያ ሚኒስቴሩ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶማሊያ ጦር የአፍሪካ ዕዝ ዛሬ እንዳስታወቀው ከሶማሊያ መንግሥት ጋራ በመተባበር ባደረገው የአየር ጥቃት ሞሃመድ ሚሬ ወይም አቡ አብዲራህማን በሚል ስም የሚታወቅ ከፍተኛ የአል ሻባብ አመራር ዓባል ከሁለት ሳምንታት በፊት በተፈጸመ የአየር ጥቃት መግደሉን አረጋግጧል። የሶማሊያ መንግሥት ሞሃመድ ሚሬ መገደሉን ከአንድ ሳምንት በፊት አስታውቆ ነበር። አፍሪኮም በአወጣው መግለጫ « ሚሬ በሌላ ስሙ አቡ አብዲራህማን  ባለፉት 15 ዓመታት  በአልሻባብ አገዛዝ ሥር ለዋሉት የሶማሊያ  አካባቢዎች ኃላፊው ነበር » ብሎታል። ሚሬ ለአያሌ ዓመታት ከቆዩ የአልሻባብ አባላት አንዱ እንደነበረ የጠቀሰው መግለጫው በቡድኑ  የሀገር አስተዳደር ሚኒስትርነት  እንዲሠራ እና በቡድኑ ስልታዊ ውሳኔዎች ቁልፍ ሚና እንደነበረው መግለጫው አውስቷል። በተወሰደው ጥቃት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት አለመድረሱን መግለጫው አክሎ አመልክቷል። የአሜሪካው የጦር ኃይል የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ማይክል ላንግሊ « በብሔራዊ ጸጥታ ስትራተጂያችን በዝርዝር እንደተመለከተው አሜሪካ የሚፈጠሩ የሽብርተኝነት ስጋቶችን በቁርጠኝነት መከላከሏን ትቀጥላለች» ማለታቸውን መግለጫው ጠቅሷል።  እ አ አ የ2024 የዓለም አቀፍ የሽብርተኝነት ሰንጠረዥ ሽብርተኛ ቡድኖች ከባድ ዓለም አቀፍ ስጋት መሆናቸው መቀጠሉን አጉልቶ አሳይቷል። ከእነዚህ ስጋቶች መካከል አንዱ አልሻባብ ነው« ያለው መግለጫው » በቀጣናው ከእኛ ጋራ ተመሳሳይ አመለካከት ካላቸው  አጋሮቻችን ጋራ ኾነን አልሻባብን እና ሌሎችንም አደገኛ አካላት እንዋጋቸዋለን« ብሏል። እነዚህን ድንበር ተሻጋሪ ስጋቶች በትብብር መታገል ለቀጠናው መረጋጋት እና ብልጽግና ይጠቅማል» ሲል  አውስቷል። አፍሪኮም  ስለተካሄደው ጥቃት ለጊዜው በዝርዝር ከመናገር ተቆጥቧል። 

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ኢትዮጵያዊው አንጋፋ ፖለቲከኛ እና የንግድ ሰው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በ94 ዓመታቸው ዛሬ ታኅሣሥ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታየቸውን የአሜሪካ ድምፅ ከ
የአሜሪካ ድምፅ

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ኢትዮጵያዊው አንጋፋ ፖለቲከኛ እና የንግድ ሰው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በ94 ዓመታቸው ዛሬ ታኅሣሥ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታየቸውን የአሜሪካ ድምፅ ከቤተሰባቸው መረዳት ችሏል። አቶ ቡልቻ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ በግንባር ቀደምትነት ከሚሳተፉ የፖለቲካ ሰዎች አንዱ ነበሩ። አቶ ቡልቻ የተቃዋሚው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ መስራቾች አንዱ ሲኾኑ፣ በአንድ ወቅት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልም ነበሩ። ከ1990ዎቹ ጀምሮ በሰላማዊ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ሲሳተፉ ቆይተዋል። አቶ ቡልቻ በ1967 ዓ.ም በፋይናንስ ምክትል ሚኒስትርነት፣ ሀገራቸውን ወክለውም በዓለም ባንክ ቦርድ አባልነት አገልግለዋል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ  በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አጋርተዋል። ጠቅላት ሚኒስትሩ አቶ ቡልቻ “በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ” ነበሩ ብለዋል። የአቶ ቡልቻ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ፕሮግራም ልጆቻቸው ከሚኖሩበት አሜሪካ ኢትዮጵያ ከደረሱ  በኋላ እንደሚወሰንም ከቤተሰብ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በጦርነት በታመሰችው ሱዳን 30 ሚሊዮን ሰዎች ርዳታ ይሻሉ

ጦርነት ባደቀቃት ሱዳን አብዛኞቹ ሕፃናት የኾኑ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ርዳታ እንደሚሹ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዛሬ አስታውቋል። 30.4 ሚሊዮን ከሚኾኑት
የአሜሪካ ድምፅ

በጦርነት በታመሰችው ሱዳን 30 ሚሊዮን ሰዎች ርዳታ ይሻሉ

ጦርነት ባደቀቃት ሱዳን አብዛኞቹ ሕፃናት የኾኑ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ርዳታ እንደሚሹ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዛሬ አስታውቋል። 30.4 ሚሊዮን ከሚኾኑት ውስጥ 20.9 ለሚሆኑት 4.2 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ርዳታ የጠየቀው ተመድ፣ በሱዳን ያለውን ሁኔታ “ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ሰብአዊ ቀውስ” ሲል ገልጾታል። ላለፉት 20 ወራት በሱዳን ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ሲካሄድ የቆየው ጦርነት ሕዝቡን ለቸነፈር አጋልጧል። በጦርነቱ በ10ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ፣ 8 ሚሊዮን የሚሆኑት በሃገር ውስጥ ተፈናቅለዋል። ከጦርነቱ ቀደም ብሎም 2.7 ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቅለው የነበረ ሲሆን፣ ይህም ሱዳንን በዓለም ትልቁ የሃገር ውስጥ ተፈናቃይ ያለባት ሃገር ያደርጋታል። ተጨማሪ 3.3 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ሃገር ጥለው ተሰደዋል። በመሆኑም ከጦርነቱ በፊት ይገመት ከነበረው 50 ሚሊዮን የሱዳን ሕዝብ ውስጥ አንድ አራተኛ የሚሆነው ተፈናቅሏል። በአምስት አካባቢዎች ረሃብ የታወጀ ሲሆን፣ እስከ መጪው ግንቦት ድረስ ተጨማሪ አምስት አካባቢዎች ለረሃብ እንደሚጋለጡ ይገመታል። 8.1 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በቅርቡ ረሃብ ሊገጥማቸው እንደሚችል ተነግሯል። በሱዳን ሠራዊት የሚደገፈው መንግሥት ረሃብ መግባቱን ሲያስተባብል፣ ረድኤት ድርጅቶች ደግሞ የቢሮክራሲ ማነቆ እና ሁከት ለተጎጂዎች እንዳይደርሱ ማድረጉን ይናገራሉ። የሱዳን ሠራዊት እና የፈጥኖ ደራሽ ኅይሉ ረሃብን እንደ ጦር መሣሪያ በመጠቀም ክስ ይቀርብባቸዋል። በሱዳን የሚካሂደው ጦርነት ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ቢሆንም፤ በመካከለኛው ምሥራቅና በዩክሬን በሚካሄዱት ጦርነቶች ምክንያት “የተረሳ ጦርነት” እንደሆነ ይነገራል።  

የቀድሞ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አስክሬን ሽኝት ሥነ ሥርዐቶች በጆርጂያ ክፍለ ግዛት ተጀምሯል

ባለፈው ሳምንት እሁድ በአንድ መቶ ዓመታቸው በሞት የተለዩት የ39ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አስክሬን ሽኝት መርሐ ግብሮች በኖሩበት በጆርጂ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አስክሬን ሽኝት ሥነ ሥርዐቶች በጆርጂያ ክፍለ ግዛት ተጀምሯል

ባለፈው ሳምንት እሁድ በአንድ መቶ ዓመታቸው በሞት የተለዩት የ39ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አስክሬን ሽኝት መርሐ ግብሮች በኖሩበት በጆርጂያ ክፍለ ግዛት ትላንት ቅዳሜ ተጀምሯል። ለስድስት ቀናት በሚዘልቀው የሽኝት ሥነ ሥርዓት አስከሬናቸው ትላንት በትውልድ ከተማቸው በሚገኘው የቤተሰባቸው መኖሪያ እና እርሻ በኩል በክብር አጀብ አልፎ አትላንታ ከተማ ወደሚገኘው የካርተር ፕሬዝደንታዊ ማዕከል ለሐዘንተኞች እና አድናቂዎቻቸው ስንብት ተቀምጧል። በመቀጠል ወደ ዋሽንግተን ይሸኝ እና በተመሳሳይ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሕንጻ « ካፒቶል ሮተንዳ» አዳራሽ በክብር አርፎ ስንብት ይደረጋል። ሐሙስ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ በዋሽንግተን ብሔራዊ ካቴድራል የሽኝት መርሐ ግብር ይከናወናል። /የአሜሪካ ድምጹ ኬን ፋራቦ የኖቤል የሰላም ተሸላሚውን ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር ሕይወት እና የሕዝባዊ አገልግሎት ታሪክ በሚመለከት ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/  

ሜሎኒ በፍሎሪዳ ድንገተኛ ጉብኝታቸው ከትራምፕ ጋር ያላቸውን ትብብር አሳደጉ 

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ትላንት ቅዳሜ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመገናኘት ወደ ፍሎሪዳ ድንገተኛ ጉዞ አድርገዋል። የአውሮፓ መሪዎች እአአ ጥር
የአሜሪካ ድምፅ

ሜሎኒ በፍሎሪዳ ድንገተኛ ጉብኝታቸው ከትራምፕ ጋር ያላቸውን ትብብር አሳደጉ 

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ትላንት ቅዳሜ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመገናኘት ወደ ፍሎሪዳ ድንገተኛ ጉዞ አድርገዋል። የአውሮፓ መሪዎች እአአ ጥር 20 ከሚካሄደው በዓለ ሲመት በፊት ከትራምፕ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ለማጠናከር ይፈልጋሉ፡፡ የትራምፕ የማር-አ-ላጎ ሪዞርት አባላት ተመራጩ ፕሬዘዳንት ትራምፕ ሜሎኒን ሲያስተዋውቋቸው በጭብጨባ ሲቀበሏቸው የሚያሳዩ ቪድዮዎች በማህበራዊ ሚድያ ተጋርተዋል፡፡ «ይህ በጣም አስደሳች ነው፡፡ እኔ እዚህ ያለሁት የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆነች ድንቅ ሴት ጋር ነው» ሲሉ ትራምፕ ለማር-አ-ላጎ አባላት መናገራቸውንም ሚድያዎች ዘግበዋል፡፡ ሜሎኒ ከእአአ 2022 መገባደጃ ጀምሮ በጣልያን የቀኝ ክንፍ ጥምረትን በመምራት ያመጡትን መረጋጋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለትራምፕ ጠንካራ አጋር ተደርገው እየተቆጠሩ ነው። ትራምፕ በምርጫው እንዲያሸንፍ ከሩብ ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ ካደረገው ከቢሊየነር የቴክኖሎጂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሎን ማስክ ጋርም የቅርብ ግንኙነት መፍጠራቸው ይነገራል፡፡ የአውሮፓ ህብረት እና የክልል ጉዳዮች ሚኒስትር ቶማሶ ፎቲ ዛሬ እሁድ እንደተናገሩት ስብሰባው አስቀድሞ ያልተገለፀ ቢሆንም ጣሊያን «በሁለቱ ዓለማት በሆኑት የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ መካከል የዲፕሎማሲ ድልድይ » ልትሆን እንደምትችል ያሳያል ብለዋል። የሜሎኒ ጉዞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከመጭው ሃሙስ እስከ ጥር 12 ሮምን ለመጎብኘት ከያዙት ቀጠሮ አስቀድሞ የተደረገ ነው። ትራምፕ በህዳር ምርጫ ባይደንን አሸንፈው ወደ ኋይት ሀውስ ለመመለስ በዝግጅት ላይ ናቸው። ትራምፕና ሜሎኒ ስላደረጉት ውይይት ዝርዝር መረጃ ባይገለጽም ስለ ሩሲያ ዩክሬን ጦርነት፣ ንግድ ነክ ጉዳዮች፣ መካከለኛው ምስራቅ እና በቴህራን ስለታሰረው ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ ሁኔታ ለመነጋገር ሜሎኒ አስቀድመው እቅዱ እንደነበራቸው የጣሊያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።  

የሶሪያ ሚኒስትሮች የአሜሪካ ማዕቀብ እንዲነሳ ጠየቁ 

የሶሪያ የሽግግር መንግስት ሚኒስትሮች ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድን ከስልጣን ካነሱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኳታር ባደረጉት ጉብኝት ዩናይትድ ስቴትስ በደማስ
የአሜሪካ ድምፅ

የሶሪያ ሚኒስትሮች የአሜሪካ ማዕቀብ እንዲነሳ ጠየቁ 

የሶሪያ የሽግግር መንግስት ሚኒስትሮች ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድን ከስልጣን ካነሱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኳታር ባደረጉት ጉብኝት ዩናይትድ ስቴትስ በደማስቆ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እንድታነሳ አሳስበዋል፡፡  የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች ከሶሪያ ጊዜያዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ አል-ሻይባኒ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ሙርሃፍ አቡ ቃስራ እና ከአዲሱ የስለላ ሃላፊ አናስ ኻታብ ጋር መነጋገራቸውን አስታውቋል።  ኳታር እንደሌሎች አረብ ሀገራት ሶርያ በአሳድ አስተዳደር ስር እያለች የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ወደነበረበት አልመለሰችም።  ከኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ቢን አብዱላዚዝ አልኩላይፊ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ የሶሪያ ጊዜያዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ አል-ሻይባኒ አሜሪካ በሶሪያ ላይ የጣለችው ማዕቀብ እንዲነሳ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።  ጊዜያዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እርምጃዎቹን ለሃገራቸው ፈጣን ማገገም እንቅፋት ነው ሲሉ መንግስታቸው “ዩናይትድ ስቴትስ እነዚህን ማዕቀቦች እንድታነሳ በድጋሜ ይጠይቃል” ሲሉ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።   በታህሳስ ወር መጨረሻ ላይ ኳታር በሶሪያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ በፍጥነት እንዲነሳላት ጥሪ አቅርባ እንደነበረም ዘገባው አስታውሷል፡፡ 

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንታዊ የደህንነት ሃላፊ የዮንን እስር ተቃወሙ 

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል የጸጥታ ሃላፊ የፖለቲካ ቀውሱን ወደ ሌላ ከፍተኛ ግጭት ሊገፋው ይችላል ባሉት የተከሰሱትን መሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል
የአሜሪካ ድምፅ

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንታዊ የደህንነት ሃላፊ የዮንን እስር ተቃወሙ 

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል የጸጥታ ሃላፊ የፖለቲካ ቀውሱን ወደ ሌላ ከፍተኛ ግጭት ሊገፋው ይችላል ባሉት የተከሰሱትን መሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል ከሚደረገው ጥረት ጋር መተባበር እንደማይችሉ ዛሬ እሁድ ተናግረዋል፡፡  የእስር ትዕዛዙ ቀነ ገደብ ነገ ሰኞ እኩለ ሌሊት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን የጸጥታ ሃላፊው ፓርክ ቾንግ-ጁን በትብብር ማዘዣው ዙሪያ ያለውን የሕግ ክርክርም ላለመተባበራቸው ምክንያት አድርገው ጠቅሰዋል።  አስተያየቶቹ የተሰጡት የሴኡል ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣው ህገወጥ እና ልክ ያልሆነ ነው በማለት የፕሬዘዳንቱ ጠበቆች ያቀረቡትን ቅሬታ ውድቅ ካደረገ በኋላ ነው ሲሉ የደቡብ ኮርያ ሚድያዎች መዘገባቸውን የጠቀሰው ሮይተርስ ተጨማሪ አስተያየት ለመጠየቅ ወደ ፍርድ ቤት ያደረገው የስልክ ጥሪም ምላሽ እንዳላገኘም ገልጿል፡፡  ዮን እአአ ታህሳስ 3 ቀን ማርሻል ህግን ለማወጅ ባደረጉት ያልተሳካ ሙከራ ምክንያት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የእስር ትዕዛዝ የወጣባቸው የመጀመሪያው የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚደንት ሆነዋል፡፡ ይህም በእስያ ባለአራተኛዋ ትልቅ ኢኮኖሚዋና የአሜሪካ ቁልፍ አጋር በሆነችው ደቡብ ኮርያ የውስጥ የፖለቲካ ትርምስ ቀስቅሷል፡፡  የዩናትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር ዛሬ እሁድ ሴኡል ይደርሳሉ ተብሏል፡፡  ይህ በእንዲህ እንዳለ በዋና ከተማይቱ ሴኡል ከባድ በረዶ ባለበት በፕሬዘዳንት ዮን መኖሪያ አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ባደረጉት ሰልፍ የእስር ማዘዣው ውዝግብ ፈጥሯል፡፡  የተወሰኑ ሰልፈኞች ፕሬዘዳንቱ እንዲታሰሩ ሲጠይቁ ሌሎች ሰልፈኞች ደግሞ እስሩን ተቃውመው ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡   

የቀድሞ የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኮስታስ ሲሚቲስ አረፉ

የቀድሞ የግሪክ ጠቅላይ ሚንስትር እና ሀገራቸው ወደ አውሮፓ የጋራ መገበያያ ገንዘብ እንድትቀላቀል ያደረጉት ኮስታስ ሲሚቲስ በ88 አመታቸው መመሞታቸውን የሃገ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞ የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኮስታስ ሲሚቲስ አረፉ

የቀድሞ የግሪክ ጠቅላይ ሚንስትር እና ሀገራቸው ወደ አውሮፓ የጋራ መገበያያ ገንዘብ እንድትቀላቀል ያደረጉት ኮስታስ ሲሚቲስ በ88 አመታቸው መመሞታቸውን የሃገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡  በሙያቸው የስነህንጻ ባለሙያ የሆኑት ኮስታስ ሲሚቲስ የሶሻሊስት ፓሶክ ፓርቲ መስራችም ናቸው፡፡   ግሪክንም እአአ ከጥር 1996 እስከ 2004 ድረስ ለስምንት አመታት በጠቅላይሚንስትርነት መርተዋል፡፡ ይህም በሀገሪቱ ረዥሙ የስልጣን የቆይታ ጊዜ የነበራቸው መሪም አድርጓቸዋል፡፡  ግሪክ የአውሮፓ ህብረትን እአአ በ 2001 እንድትቀላቀል ከማድረጋቸው በተጨማሪ ትልቅ የመሰረተ ልማት ግንባታ መርሃ ግብር በማካሄድ ሃገራቸው እአአ በ2004 የተካሄደውን የኦሊምፒክ ውድድርን እንድታዘጋጅ በማስቻላቸው ይታወሳሉ ። ቆጵሮስ የአውሮፓ ህብረትን በዚሁ አመት እንድትቀላቀልም ድጋፍ ማድረጋቸውም ይነሳል፡፡ 

መንግሥት 80 ሺሕ ነዋሪዎችን ርዕደ መሬት ከተሰተባቸው አካባቢዎች እያራቀ መኾኑን አስታወቀ

በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ርዕደ መሬት በተከሰተበት ማዕከል አዋሳኝ ከሚገኙት አፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል አካባቢዎች 80 ሺሕ ነዋሪዎችን ማራቁን መንግሥት አስ
የአሜሪካ ድምፅ

መንግሥት 80 ሺሕ ነዋሪዎችን ርዕደ መሬት ከተሰተባቸው አካባቢዎች እያራቀ መኾኑን አስታወቀ

በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ርዕደ መሬት በተከሰተበት ማዕከል አዋሳኝ ከሚገኙት አፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል አካባቢዎች 80 ሺሕ ነዋሪዎችን ማራቁን መንግሥት አስታወቀ። በርዕደ መሬት መለኪያ እስከ 5.8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ መንቀጥቀጥ ዛሬ አርብ ታኅሣሥ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት መከሰቱን የኢትዮጵያ የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መሥሪያ ቤት አስታውቀዋል። መሥሪያ ቤቱ በአወጣው መረጃ፣ ቦታው ከኦሮሚያ ክልል አቦምሳ ከተማ 56 ኪሎ ሜትር እና ከአዳማ ከተማ 146 ኪሎ ሜትር ርቀት እንደሚገኝ የዕለት ሁኔታ በሚያወጣበት መረጃ አጋርቷል። ርዕደ መሬቱ በመጠን እና በድግግሞሽ እየጨመረ መምጣቱን የጠቆመው የኮምዩኒኬሽን መስሪያ ቤቱ መግለጫ፣ ዛሬ ቅዳሜ የተመዘገበው 5.8 ሬክተር ስኬል መጠን ከእስካኹኖቹ የጨመረ መኾኑን ያሳያል። ዛሬ ቅዳሜ ውድቅት ሌሊት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ከዚኽ ቀደሞቹ ጠንከር ብሎ አዲስ አበባ፣ አዳማ መተሃራ እና ሌሎች ከተሞች መሰማታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ንዝረቱ የተሰማበት መጠን እንደየ አካባቢዎች የተለያየ መኾኑን ከነዋሪዎቹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።   በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ርዕደ መሬቱ አፋር ውስጥ በምስራቅ ሸዋ ፈንታሌ አካባቢ ዶፈን በተባለ ተራራ መሀል ላይ መከሰቱን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። አክለውም “ርዕደ መሬቱ የተከሰተው እዛው ሰሞኑን ሲከሰትበት በነበረው አፋር ክልል ውስጥ አዋሽ ፈንታሌ እና ዶፈን ተራራ መሀል ነው። ሌሎቹ አካባቢዎች የተሰማው የርዕደ መሬቱ ንዝረት ነው” ብለዋል። የኢትዮጵያ ከርሰ ምድር ጥናት ተቋም ዛሬ የተከሰተው መጠኑ ከፍ ያለው 5.8 የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ 10 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍን ጠቁሟል። ከዛሬው ክስስተት በኋላ መግለጫ ያወጣው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ለችግሩ ተጋላጭ ናቸው የተባሉ አካባቢዎችን በመለየትም 12 ቀበሌዎች ላይ መንግሥት ከተለያዩ የሞያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሰሳ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። 80 ሺሕ  ነዋሪዎችን ርዕደ መሬት ከተሰተባቸው አካባቢዎች እያራቀ መኾኑን ገልጿል። በተያያዘም የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዛሬ ታኅሣሥ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በአወጣው መግለጫ፣ በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ ነዋሪዎች የርዕደ መሬቱ ክስተት ሊያደርሰው ለሚችል አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተብለው መለየታቸውን አስታውቋል።   ኮሚሽኑ በአፋር ክልል በአዋሽ ፈንታሌና ዱለቻ ወረዳዎች ውስጥ 35 ሺሕ የሚኾኑ ነዋሪዎች ለችግሩ ተጋላጭ መሆናቸውን አመልክቶ፣ በአዋሽ ፈንታሌ ስድስት ቀበሌዎች ውስጥ ከሚገኙ 15 ሺሕ ነዋሪዎች እስከ አሁን 7ሺሕ የሚሆኑት ወደ ሌላ ስፈራ ተጓጉዘዋል ብሏል፡፡ በዱለቻ ወረዳ ካሉት 20ሺሕ ተጋላጭ ነዋሪዎችም፣ እስከ አሁን ከ6ሺሕ በላይ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን አክሏል። በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳም ከአምስት ቀበሌዎች 16 ሺሺ 182 ነዋሪዎች ለአደጋው ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቅሷል። እስከ አሁን ድረስ 7 ሺህ 350 ነዋሪዎች ከስፍራው መውጣታቸውን አስታውቋል፡ቀሪዎቹ ነዋሪዎችም በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ከስፍራው እንደሚንቀሳቀሱ የጠቀሰው የኮሚሽኑ መግለጫ፣ በአጠቃላይ ለ70 ሺሕ ነዋሪዎች ድጋፍ እየተደረገ መኾኑን አክሏል። ንዝረቱ የተሰማቸው ነዋሪዎች የአቦምሳ ከተማ ነዋሪ የኾነችው ዙምራ ማሞ፣ አርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢያ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጡን ንዝረት መስማቷን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጻለች። “ልጄ አልተኛ ስላለኝ ይዤው መሬት ላይ ተኝቼ ነበር፣ ከዚያ መሬቱ ተንቀጠቀጠ፣ የቤቴ መስታዎት አኹን ረግፏል” ስትል ገልፃለች። ዙመራ ክስተቱ ለደቂቃ መቆየቱን ገልጻ ከዚህ ቀደም ከተነገረው የጠነከረ እንደነበር ተናግራለች። ሌላው በፈንታሌ ወረዳ ነዋሪ የኾነው አቶ አባይኔ ኡርጎ፣ የተሰማው ንዝረት ከዚኽ ቀደሞቹ ከፍ ያለ እንደነበር ተናግሯል። አቶ አባይነህ የሌሊቱ ንዝረት ለአንድ ደቂቃ ያህል መቆየቱን ገልጸው፣ ኃይሉም ከዚኽ ቀደሞቹ ጠንከር ያለ እንደነበር ጠቁመዋል። ክስተቱ በአፋር ክልልና በፈንታሌ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እንደሚከሰት አቶ አባይነህ ጠቅሰው፣ የአካባቢው ነዋሪዎች በፍራቻ ከቤታቸው እያደሩ እንደኾነም ተናግረዋል።   ሌላው ንዝረቱ የተሰማበት አዲስ አበባ ከተማ ሲኾን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ከዚኽ ቀደሞቹ ኹሉ ጠንከር ያለ ያለና ዘለግ ላለ ሰከንዶች የቆየ መኾኑን ገልጸውልናል። አዲስ አበባ ከተማ ኮተቤ አካባቢ ነዋሪ የኾነው አዲስ ወንድሙ፣ ሕምፃ ላይ አራተኛ ፎቅ እንደሚኖር ገልጾ፣ በሰዓቱ ወንበር ላይ ተቀምጦ የጹሑፍ ሥራ እየሠራ እንደነበር ገልጾልናል። “ድንገት ነው የተከሰተው እንደ መወዝወዝ ነው የምቆጥረው። ለጥቂት ሰከንዶች ሕንፃው ቦታውን የለቀቀ ነገር መሰለኝ። ልክ እንደ ፔንዱለም ዐይነት ነገር ነው የተሰማኝ። ከዚኽ ቀደሞቹ የአኹኑ ትንሽ ጠንከር ያለ ነው። እንቅልፍ ላይ የነበረችው ባለቤቴም በንዝረቱ ነቅታ ወደ እኔ መጣች”  ብሎናል። ኤፍሬም ዋቅጅራ  የተባለ በአዲስ አበባ መካኒሳ አካባቢ ነዋሪ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ ላለፉት አምስት ቀናት በተለያየ ጊዜ ሲሰማው እንደነበር ገልጾ፣ የትላንት ምሽቱ ግን “ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ ከባድ ነበር” ሲል ጠቅሷል። በአፋር ክልል ርዕደ መሬቱ ሲከሰት የመጀመሪያ አይደለም። እስካኹን በነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሚያሳዩ ሪፖርቶች አልወጡም። ኾኖም በአፋር ክልል በዐሥሮች የተቆጠሩ ቤቶች መፍረሳቸው ተዘግቧል። ከዚኹ ጋራ በተያያዘም፣ በኢትዮጵያ አፋር ክልል፣ አዋሽ ፈንታሌ የእሳተ ገሞራ መፈንዳት ምልክቶችን እንዳሳየ የኢትዮጵያ ከርሰ ምድር ጥናት ተቋም ዛሬ ትላንት በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ከአጭር ቪዲዮ ጋራ ባጋራው መረጃ አስታወቀ። ተቋሙ በአዋሽ ፈንታሌ ጭስ ሲወጣ ከሚያሳየው የቪዲዮ ምስል ጋራ ባጋራው መረጃም፣ «ሰሞኑን ሲጠበቅ የነበረው አዋሽ ፈንታሌ በአሁኑ ሰዓት በአፋር ክልል ዱላቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የታመቀ ውሃ እና እንፋሎት ተከሰተ» ብሏል። በዚህም ምክኒያት ባለሥልጣናት ነዋሪዎችን ወደ ጊዜያዊ መጠለያ እንዲያዘዋውሩ ማድረጋቸውን የሀገር ውስጥ ብዙኅን መገናኛ ዘግበዋል። በመንግሥት የሚደገፈው ፋና ብሮድ ካስቲንግ በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ጠቅሶ በአወጣው ዘገባ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ነዋሪዎችን ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ መኾኑን ጠቅሷል። «ፍንዳታ ለመሆኑ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም፣ ባለሥልጣናት ጥንቃቄ ማድረግን መርጠዋል» ሲሉ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማሪያም ማስታወቃቸውን ደግሞ ሮይተርስ ዘግቧል። ከአንዳንድ ሥፍራዎች ሰዎች መውጣት መጀመራቸውንና በትንበያው መሠረት ሰዎችን ሥርዐት ባለው መንገድ እንደሚያስወጡም ኮሚሽነሩ ጨምረው አስታውቀዋል።አካባቢው ከመስከረም ወር ጀምሮ መሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልበት ቆይቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት እስካኹን የመሬት መንቀጥቀጡ በዋና ከተሞች እስካኹን የጎላ ተጽዕኖ እንዳላሰደረ ገልጾ፣በባለሞያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እንዲከታተሉ እና በጥብቅ እንዲተገብሩ አሳስቧል።   በሌላ በኩል በኢትዮጵያ አብዛኞቹ ህንፃዎች ለርእደ መሬት ተጋላጭ መኾናቸውን ባለሞያዎች ገለጸዋል። በኢትዮጵያ ያሉት አብዛኞቹ ህንፃዎች በዲዛይን ወቅት በሚፈጠር ክፍተትና በግንባታ ጥራት ጉድለት የተነሳ ለርዕደ መሬት አደጋ የተጋላጡ እንደሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ህንፃዎች ርዕደ መሬትን እንዲቋቋሙ በሚያስችል መልኩ ዲዛይን እንዲደረጉ አስገዳጅ የህንፃ ኮድ ብታዘጋጅም፣ መስፈርቱን ከመከተል አኳያ ክፍተቶች አሉ ብለዋል፡፡ መንግሥት በበኩሉ፣ “በህንፃዎች ግንባታ ወቅት፣ መስፈርቱ እንዲተገበር ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ነው፣ ህንፃዎቹም የተወሰነ የርዕደ መሬት መጠንን የመቋቋም አቅም አላቸው” ብሏል። 

የጂሚ ካርተር መንግሥታዊ የአስክሬን ሽኝት ሥነ ሥርዐት ዛሬ ጀመረ

በ100 ዓመታቸው እሑድ ታኅሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር፣ ስድስት ቀናት የሚቆየው የቀብር እና የሽኝ
የአሜሪካ ድምፅ

የጂሚ ካርተር መንግሥታዊ የአስክሬን ሽኝት ሥነ ሥርዐት ዛሬ ጀመረ

በ100 ዓመታቸው እሑድ ታኅሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር፣ ስድስት ቀናት የሚቆየው የቀብር እና የሽኝት ሥነ ሥርዐት ዛሬ ጀመረ። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ጥር 1 ቀን 2017 ዓ/ም እንደሚፈፀም ታውቋል። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለጂሚ ካርተር ብሔራዊ የሐዘን ቀን ባወጁበት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ/ም፣ የቀብራቸውም ሥነ ሥርዓት በዛው ዕለት እንዲፈፀም ፕሮግራም እንዲያዝ አድርገዋል። በተጨማሪም የመንግሥት ሕንፃዎች ሰንደቅ ዓላማቸውን ለ30 ቀናት ዝቅ አድርገው እንዲሰቅሉ መመሪያ አስተላልፈዋል። የጂሚ ካርተር ሕይወት ወደ ኋላ ሲቃኝ ጂሚ ካርተር ፕሬዝደንት ከመሆናቸው በፊት፣ የለውዝ ገበሬ እንዲሁም የጆርጂያ ግዛት አገረ ገዥ ነበሩ። በእ.አ.አ ጥር 20 ቀን 1977 ዓ.ም ቃለ መሃላ በመፈጸም ሥልጣን ሲረክከቡ፣ 39ኛው የአሜሪከ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር “እንደ ሕዝቡ መልካም የኾነ” ያሉትን መንግሥት እንደሚያቋቁሙ ቃል ገብተው ነበር። “በዚህ አዲስ ምዕራፍ በምንከፍትበት ዕለት፣ ፍትህና ሰላም የሰፈነበት ዓለምን ከመቅረጽ የበለጠ የተከበረና ከባድ ተግባር የለም፣” ሲሉ በቃለ መሃላ ሥነ ሥርዐታቸው አከባበር ላይ ተናግረዋል። ይህን ቃላቸውን ከአንድ የሥልጣን ዘመን በኋላም በነበራቸው ሕይወት ቀጥለውት ነበር። የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ከመሆናቸው በተጨማሪ በስማቸው የተሰየመውንና ለትርፍ ያልተቋቋመውን ዓለም አቀፍ ድርጅት፣ የካርተር ማዕከልን መርተዋል። “ሠላምን ማስፈን፣ በሽታን ማጥፋት እና ተስፋን ማለምለም” የማዕከሉ ተልዕኮዎች ናቸው። “የካርተር ማዕከልን ሥራ የምመለከተው ፕሬዝደንት በነበርኩበት ወቅት ለመሥራት የሞከርኩት ተቀጽላ እንደሆነ አድርጌ ነው” ብለዋል ካርተር። ጂሚ ካርተር ፕሌይንስ በተሰነች የጆርጂያ ከተማ በእ.አ.አ 1924 ተወለዱ። ከአሜሪካው የባሕር ኃይል ማሰልጠኛ በ1946 ተመረቁ። የአባታቸውን ሞት ተከትሎ የቤተሰቡን የግብርና ሥራ ለማስተዳደር በ1953 ወደ ትውልድ ከተማቸው ፕሌይንስ እስኪመለሱ ድረስ በባሕር ኃይሉ በሰብመሪን ኦፊሰርነት አገልግለዋል። ካርተር ወደ ፖለቲካው ዓለም የገቡት በ1960ዎቹ የሰብአዊ መብት ንቅናቄዎች በሚካሄዱበት ወቅት ነበር። በጆርጅያ ግዛት ምክር ቤት ለሁለት የሥራ ዘመን አገልግለው ከዛም በ1971 የግዛቲቱ አገረ ገዥ ለመሆን በቅተዋል። በወቅቱ ስለነበረውና በዘር መድልኦ ላይ የሚደረገውን ትግል በተመለከተ ሲናገሩም፣ “በግልጽ የምነግራችሁ ቢኖር የዘር መድልኦ ዘመን አብቅቷል” ብለው ነበር። በ1971 ብዙም ያልታወቁትና በደቡብ የሃገሪቱ ክፍል አገረ ገዥ የነበሩት ካርተር፣ በ1976 ሪፐብሊካኑን ጀራልድ ፎርድ በጠባብ ውጤት በማሸነፍ ፕሬዝደንት ሆኑ። በሶስተኛው ዓመት፣ 1979 “የካምፕ ዴቪድ ስምምነት” ተብሎ የሚጠራውን፣ በግብጽ እና በእስራኤል መካከል የሰላም ስምምነት እንዲፈጸም አስቻሉ። ይህም የፕሬዝደንትነት ዘመናቸው ዋና ስኬት ተደርጎ ይታያል። “ወደ ፕሬዝደንትነት ከመምጣቴ በፊት በአረቦች እና በእስራኤል መካከል በ25 ዓመታት ውስጥ የተደረጉ አራት ጦርነቶች ነበሩ። በሶቪዬት ኅብረት የምትደገፈው ግብጽ በዚህ ውስጥ የመሪነት ሚና ነበራት፡፡ እነዚህ ሃገራት እስራኤልን በወታደራዊ መንገድ ሊገዳደሩ የሚችሉ ብቸኛ ሃገራት ነበሩ” ሲሉ ካርተር ተናግረዋል። ካርተር በተጨማሪም የፓናማ መተላለፊያ በፓናማ ቁጥጥር ሥር እንዲሆን እና ከቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ጋራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲመሠረት አድርገዋል። በ1979 በኢራን የተከሰተው የእስልምና አብዮት ግን የፕሬዝደንታዊ አስተዳደራቸውን አቅጣጫ እንዲቀይር አድርጓል። በሻይት የእስልምና መሪዎች የተመራው ተቃውሞ በአሜሪካ የሚደገፉትን ሻህ ወይም መሪ ከስልጣን ገርስሶ፣ ሻሁም ሃገር ጥለው እንዲወጡ አድርጓል። በ1979 ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ እስላማዊ ነውጠኞቹ ቴህራን ውስጥ የሚገኘውን የአሜሪካን ኤምባሲ ሰብረው በመግባት 66 አሜሪካውያንን አገቱ፡፡ ከአስር ቀናት በኋላ 13 የሚሆኑትን ቢለቁም የተቀሩትን ግን ለ 444 ቀናት አግተው ቆዩ። የቀሩትን ታጋቾች ለማስለቀቅ በሚያዚያ 1980 ካርተር ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ አዘዙ። ሙከራው ሳይሳካ ቀርቶ ስምንት የኤምባሲው ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ። ካርተር በሃገር ውስጥም ፈተና ገጠማቸው። የዋጋ ግሽበትና እየጨመረ የመጣው ሥራ አጥነት ኢኮኖሚውን አንገዳገደው። ይህም በ1980 በተደረገው ምርጫ በሪፕብሊካኑ ሮናልድ ሬገን እንዲረቱ አስተዋጽኦ አድርጓል። ሬገን ቃለ መሃላ በፍጸሙበት ዕለት፣ ኢራን አሜሪካውያን ታጋቾቹን ለቀቀች፡፡ ሽንፈቱ እና ድባቴ የተጫናቸው ካርተር፣ ፕሬዝደንታዊ ቤተ መጽሃፍት ለመገንባት ወደ ትውልድ ከተማቸው አቀኑ። ሐሳባቸው ከቤተ መጻሕፍት ግንባታም አልፎ ወደ ታወቀ ዓለም አቀፍ ትርፋማ ያልሆነ ድርጅትነት ተሸጋገረ። የካርተር ማዕከል ከመቶ በላይ ምርጫዎችን ታዘበ። ከሰሜን ኮሪያ ጋራ ከነበረውን የኑክሌር ፍጥጫ ከመሸምገል፣ በዩጋንዳ እና ሱዳን መካከል የሰላም ስምምነት እንዲፈረም እስከማድረግ ባሉ ተግባራት ሚና ተጫወተ። በጤና መስክ ደግሞ የጊኒ ዎርም በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶ ወደ መጥፋት ደረጃ እንዲደርስ አድርጓል። ካርተር በሰብአዊ መስክ ላደረጉት አስተዋጽኦ በእ.አ.አ 2002 የኖቤል የሰላም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የካርተር ማዕከል በእ.አ.አ 1989 በወቅቱ በኤርትራ የነበሩትን የአማጺያን መሪዎች በኢትዮጵያ ከነበሩት የደርግ መሪዎች ጋራ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ አትላንታ እና ኬንያ እንዲወያዩ አመቻችቷል። ማዕከሉ በኢትዮጵያም ሠላም እና ጤናን ለማስፈን፣ ግጭቶች እንዲቆሙ በማሸማገል፣ ምርጫን በመታዘብና የሰብአዊ መብትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ለረጅም ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል። ጂሚ ካርተር ከአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ሁሉ ረጅም ዕድሜ የኖሩ ናቸው። ከባለቤታቸው ራዝሊን ጋራ የቆዩበት የትዳር ዘመንም እንደ አሜሪካ ፕሬዝደንት እና ቀዳማዊ እመቤት ረጅሙ ነው።

የሚያንማር ወታደራዊ መንግስት 6ሺሕ እስረኞችን በምህረት ፈታ 

ሚያንማር ከብሪታንያ ነጻ የወጣችበትን 77ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የሀገሪቱ ወታደራዊ መንግሥት ከ6 ሺሕ በላይ እስረኞች በምህረት ለቀቀ። የሌሎች እስረኞች ቅ
የአሜሪካ ድምፅ

የሚያንማር ወታደራዊ መንግስት 6ሺሕ እስረኞችን በምህረት ፈታ 

ሚያንማር ከብሪታንያ ነጻ የወጣችበትን 77ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የሀገሪቱ ወታደራዊ መንግሥት ከ6 ሺሕ በላይ እስረኞች በምህረት ለቀቀ። የሌሎች እስረኞች ቅጣት መጠንም ቀንሷል። ወታደራዊው መንግሥት በሕዝብ ከተመረጠው የኦንግ ሳን ሱ ቺን አስተዳደር ሥልጣን ከነጠቀበት የአውሮፓዊያኑ የካቲት 2021 ዓ.ም ጀምሮ በወታደራዊ አገዛዝ ከታሰሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች መካከል በአኹኑ ምህረት የተካተቱት ጥቂቶቹ ናቸው። ወታደራዊው አገዛዝ ሥልጣን ላይ የወጣበት ሂደት በወቅቱ ከፍተኛ ሰላማዊ ተቃውሞ የገጠመው ሲኾን ፣ አሁን ላይ ግን ወደተንሰራፋ የትጥቅ ትግል ተቀይሯል። በመንግሥት የሚተዳደረው ኤምአርቲቪ ቴሌቪዥን የወታደራዊው መንግሥት መሪ ከፍተኛ ጄኔራል ሚን አንግ ህላይንግ፣ለ5 ሺሕ የሀገሪቱ ዜጋ እስረኞች እንዲሁም 180 የውጭ ዜጎች ምህረት እንዳደረጉ ዘግቧል። በሚያንማር በበዓላት እና በጉልህ ሁነቶች ወቅት እስረኞችን በብዛት መልቀቅ የተለመደ ነው። ከእስር የተፈቱት እስረኞች እንደገና ሕጉን ከጣሱ፣ ከአዲስ ቅጣት በተጨማሪ ቀሪውን የቅጣት ፍርዳቸውን እንዲጨርሱ እንደሚደረግ በምህረት የተለቀቁበት ቅደመ ሁኔታ ያስጠነቅቃል። በሌላ ዘገባ ሚን አውንግ ህላይንግ የ144 እስረኞችን የዕድሜ ልክ እስራት ወደ 15 ዓመት እስራት ዝቅ እንዲል መወሰናቸው ተሰምቷል። ዘገባው በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም። በጸረ - ፈንጂ፣ በሕገ-ወጥ ማኅበራት፣ በጦር መሳሪያ እና በፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ ከተከሰሱት በስተቀር ሁሉም እስረኞች ቅጣታቸው በአንድ ስድስተኛ እንደሚቀነስላቸው ዘገባው አክሏል። የወታደራዊ መንግሥት ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ዛው ሚን ቱን ፣ለጋዜጠኞች በተውት የድምጽ ማስታወሻ፣ ከእስር ከተፈቱት መካከል ወደ 600 የሚጠጉ እስረኞች በሚያንማር የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 505(A) የተከሰሱ መሆናቸውን ተናግረዋል ። አንቀጹ ሕዝባዊ ብጥብጥ ወይም ስጋት መፍጠር፣ ሐሰተኛ ዜና እና አስተያየቶች ማሰራጨትን በወንጀልነት ይደነግጋል።

ሩሲያ 8 ሚሳኤሎችን መምታቷን እና ተጨማሪ የዩክሬን መንደር መቆጣጠሯን አስታወቀች

የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር የሀገሪቱ ጦር በዩክሬን ምሥራቃዊ ሉሃንስክ ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ናዲያ የተባለችውን መንደር መቆጣጠሩን እና በዩናይትድ ስቴት
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ 8 ሚሳኤሎችን መምታቷን እና ተጨማሪ የዩክሬን መንደር መቆጣጠሯን አስታወቀች

የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር የሀገሪቱ ጦር በዩክሬን ምሥራቃዊ ሉሃንስክ ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ናዲያ የተባለችውን መንደር መቆጣጠሩን እና በዩናይትድ ስቴትስ የተሠሩ ስምንት የአርሚ ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም (ATACMS) ሚሳኤሎችን መምታቱን ሮይተርስ ዘገበ።  የጦር ሜዳውን ውሎ መረጃዎች ግን ማረጋገጥ እንዳልቻለ በዘገባው ጠቅሷል።  ሚኒስቴሩ ፣ የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ስርዓት ቅዳሜ ማለዳ በሰሜናዊ ሌኒንግራድ አካባቢ የተመቱትን ሦስቱን ጨምሮ ፣ በሩሲያ አየር ክልል ውስጥ የገቡ ዐሥር የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አክሏል። በሴንት ፒተርስበርግ የሚገኘው ፑልኮቮ አየር ማረፊያ ቅዳሜ ማለዳ ላይ ማናቸውም በረራዎችን ለጊዜው አቁሟል።

ዳኛው በትራምፕ ጉዳይ ላይ ጥር 10 ውሳኔ ያስተላልፋሉ 

  ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጥፋተኛ በተባሉበት «አፍ ማስያዣ»  ገንዘብ መክፈል ክስ ውሳኔ ለማስተላለፍ ጉዳዩን የያዙት ዳኛ በትናንትናው ዕለ
የአሜሪካ ድምፅ

ዳኛው በትራምፕ ጉዳይ ላይ ጥር 10 ውሳኔ ያስተላልፋሉ 

  ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጥፋተኛ በተባሉበት «አፍ ማስያዣ»  ገንዘብ መክፈል ክስ ውሳኔ ለማስተላለፍ ጉዳዩን የያዙት ዳኛ በትናንትናው ዕለት  ቀጠሮ ሰጥተዋል። ያልተጠበቀ እንደሆነ በተነገረለት የዳኛው እርምጃ መሰረት ፣ ትራምፕ ወደ ዋይት ሀውስ ከሚመለሱበት  ቀን 10 ቀናት አስቀድሞ -በአውሮፓዊያኑ ጥር 10 ቀን  ውሳኔው ይፋ ይደረጋል። የቅጣት ውሳኔው  ግን እስርን እንደማይጨምር ተመላክቷል ።  የዳኛው ውሳኔ  ትራምፕ በወንጀሎች የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸው ስልጣን የተረከቡ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ያደርጋቸዋል። የትራምፕን ችሎት የመሩት ዳኛ ሁዋን ኤም ሜርካን  በፅሁፍ ባሰፈሩት ሀተታ፣ የቀድሞውን እና የወደፊቱን ፕሬዝደንት ሁኔታዎችን ያገናዘበ ውሳኔ እንደሚተላለፍባቸው አመላክተዋል ። በዚህም መሰረት ጉዳዩ ያለ  እስራት፣ የገንዘብ ቅጣት ወይም አመክሮ ጊዜ ይዘጋል። ሜርካን ፣ ፕሬዚደንታዊ ያለመከሰስ መብትን እንዲሁም ወደ ዋይት ሀውስ የመመለሻቸው ጊዜ መቃረቡን በመጥቀስ ውሳኔው ውድቅ እንዲደረግ ትራምፕ ያደረጉትን ግፊት አልተቀበሉም። ዳኛው በትራምፕ ላይ ውሳኔ ከማስተላለፍ  የሚከለክላቸው የህግ አግባብ እንደሌለ ገልጸው  ጥር 20 ቀን ቃለ መሃላ ከመፈጸሙ  በፊት ትራምፕ ላይ ውሳኔውን  ማስተላለፍ «ግዴታ ነው» ብለዋል ። የፍትህ መሻቶች የሚፈጸሙት «ይህ ጉዳእ  የመጨረሻው እልባት ሲያገኝ ብቻ ነው» ሲሉ ሜርካን ጽፈዋል። ትራምፕ በአውሮፓዊያኑ ግንቦት ወር 34 የንግድ መዝገቦችን በማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል።በአውሮፓዊያኑ 2016 የትራምፕ የመጀመሪያ የምረጡኝ ዘመቻ የመጨረሻ ሳምንታት ውስጥ ለወሲብ ፊልም ተዋናይቷ ስቶርሚ ዳኒልስ የተከፈለውን ገንዘብ ለመደበቅ ያለሙት ጥረቶችም በእነዚህ ጥፋቶች  ውስጥ ተካተዋል። ለስቶርሚ ዳኔልስ ክፍያዎቹ የተፈጸሙት ከባለትዳሩ ትራምፕ ጋር ከዓመታት በፊት ስጋዊ ግንኙነት እንደነበራቸው ለሕዝብ እንዳያሳውቁ ለማድረግ ነው።ትራምፕ ታሪኩ ሀሰተኛ እና ምንም ዓይነት ጥፋት እንዳልፈጸሙ ተናግረዋል።  የመከላከያ ጠበቆች እና ዐቃቤ ህግ ጉዳዩን ዕጣ ፋንታ በተመለከተ አቋማቸውን ይፋ እስኪያደርጉ ድረስ፣ከህዳር  5 ምርጫ በኋላ፣ ሜርካን ሂደቱን አቁመው የቅጣት ውሳኔውን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝመውት ነበረ።  የትራምፕ ጠበቆች መርካን መዝገቡን እንዲዘጉት ጠይቀዋል። ይህ ካልሆነ ጉዳዩ በተመራጩ ፕሬዝደንት ሀገሪቱን የመምራት አቅም ላይ ኢ-ህገመንግስታዊ «ሁከት» እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ዐቃቤነ ህጎች በበኩላቸው  ተመራጩ ፕሬዝዳንት ሊስተናገዱበት የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን ተቀብለው ፣  የጥፋተኝነት ውሳኔው ግን እንዳይለወጥ ተከራክረዋል። ትራምፕ የስልጣን ዘመናቸው እስኪያበቃ ድረስ  ጉዳዩ በይደር እንዲቆይ  ወይም እስር የማይኖረው ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ማረጋገጫ መስጠትን ጨምሮ  የተለያዩ አማራጮች ተጠቁመዋል።

የሉሲ ቅሪተ አካል የሰውን ልጅ ለመረዳት ያላትን አስተዋጽኦ ተመራማሪዎች አደነቁ

ሉሲ ወይም ድንቅነሽ ተብላ የተሰየመችው ቅሪተ አካል በአፋር ክልል ከተገኘች ዘንድሮ ኅዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም 50 ዓመቷን ደፍናለች፡፡ ቅሪተ አካሏን ካገኙት ዶናልድ
የአሜሪካ ድምፅ

የሉሲ ቅሪተ አካል የሰውን ልጅ ለመረዳት ያላትን አስተዋጽኦ ተመራማሪዎች አደነቁ

ሉሲ ወይም ድንቅነሽ ተብላ የተሰየመችው ቅሪተ አካል በአፋር ክልል ከተገኘች ዘንድሮ ኅዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም 50 ዓመቷን ደፍናለች፡፡ ቅሪተ አካሏን ካገኙት ዶናልድ ጆንሰን እንዲሁም፣ ከሉሲም በዕድሜ ቀደም ያለችውን ሌላ ቅሪተ አካል ያገኙትን ዶ/ር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ አነጋግረናል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

ኢትዮጵያ በሶማሊያ ከሚሰማራው አዲስ ተልዕኮ ጋራ እንደምትተባበር አስታወቀች

በሶማሊያ አዲሱ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ተልዕኮ ከአል ሻባብ ጋራ ለሚያደርገው ፍልሚያ እንደምትተባበር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡ በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረ
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ በሶማሊያ ከሚሰማራው አዲስ ተልዕኮ ጋራ እንደምትተባበር አስታወቀች

በሶማሊያ አዲሱ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ተልዕኮ ከአል ሻባብ ጋራ ለሚያደርገው ፍልሚያ እንደምትተባበር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡ በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ተልዕኮ በቅርቡ ወደ ሶማሊያ እንደሚሰማራ በመጠበቅ ላይ ነው። ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋራ የፈጸመቸው የባሕር በር አቅርቦትን የተመለከተ የመግባቢያ ስምምነት በፈጠረው ውጥረት ምክንያት፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ተሳተፎ እንደማይኖራቸው ሶማሊያ ስታስታውቅ ብትሰነብትም፣ቱርክ ላይ በተፈጸመው የሰላም ስምምነት ውጥረቱ ሊረግብ ችሏል። የኢትዮጵያው መከላከያ ሚኒስትር አይሻ ሞሃመድ ትላንት ሐሙስ በሶማሊያ ጉብኝት በማድረግ ከሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼኽ ሞሃሙድ ጋራ ተወያይተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ መልዕክት ማድረሳቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአወጣው መግለጫ አስታውቋል። “ውይይቱ በሶማሊያ እና በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ደግመው ያረጋገጡበት ነው” ሲል የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በአወጣው መግለጫ አስታውቋል። “ሁለቱ ሀገራት የኅብረቱን ተልዕኮ በተመለከተ ትብብር ለማድረግና የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል” ሲል  የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስፍሯል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው፣ ዛሬ አርብ ታኅሣሥ 25 ቀን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣  “በአንካራው ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ግንኙነት እንዲታደስ እየሠራን እንገኛለን” ብለዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጉብኝቶችም የዚሁ አካል እንደኾኑ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ የተመራ ልዑክ፣ ትላንት በሞቃዲሾ ከሶማሊያ ባለሥልጣናት ጋራ መወያየቱንም የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ ውይይቱ “ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የኤዩሶምን ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ በትብብር ለመሥራት የተስማሙበት ነው” ብለዋል፡፡ “ኢትዮጵያ በኤዩሶም ትሳተፋለች ወይስ አትሳተፍም ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “አሁን ባለንበት ደረጃ ውይይቶች እየተካሔዱ ነው” ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ እና በሞቃዲሾ ሰሞኑን ከተደረጉት ውይይቶች በተጨማሪ “በቅርቡም በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ አዲስ አበባ ላይ ተመሳሳይ ውይይት ለማድረግ እና በጉዳዩ ዙሪያ ለመነጋገር ቀጠሮ ተይዟል” ብለዋል፡፡ በሰሞናዊው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ባለሥልጣናት ውይይት ላይ አልሻባብን ለመዋጋት የሚደረጉ ጥረቶችን ለማጠናከር መግባባት መኖሩን ጠቅሰው፣ “ከድህረ-አትሚስ በኋላ የሚኖረው የኃይል ስምሪት፣ ኢትዮጵያ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲሆን ትፈልጋለች” ብለዋል፡፡ የሶማሊያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ በዐዲሱ ተልዕኮ ለመሳተፍ “የኢትዮጵያን ጥያቄ ለመመልከት ፍላጎት አለው” ቢልም፣ ተጨማሪ ዝርዝር አልሰጠም። በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረገው ውይይት አስፈላጊ መሆኑን ያመለከተው የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ “ለሶማሊያ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ክብር መኖሩን በድጋሚ ለማረጋገጥ” ቁልፍ እርምጃ ነው ብሏል። ኢትዮጵያ ከተገንጣይዋ የሶማሊያ ራስ ገዝ አስተዳደር ሶማሊላንድ ጋራ የተፈራረመችውን የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት አምርራ የተቃወመችው ሶማሊያ፣ የመግባቢያ ስምምነቱን እስካልሰረዘች ድረስ ኢትዮጵያ በኤዩሶም ተልዕኮ እንደማትሳተፍ አቋም ይዛ ቆይታለች፡፡ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መሪዎች፣ በአገሮቻቸው መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ በቅርቡ በአንካራ ከተስማሙ በኋላም ቢኾን፣ በሶማሊያ ሰላም የማስከበር ተልዕኮ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛውን ሚና ስትጫወት የቆየችው ኢትዮጵያ በዚህ ተሳትፎዋ የመቀጠሏ ጉዳይ እልባት አላገኘም፡፡ የሶማሊያ ባለሥልጣናት በኤዩሶም ስር የሚሰለፉ አስፈላጊ 11 ሺሕ ወታደሮችን ከዩጋንዳ፣ ጅቡቲ እና ኬንያ ማግኘታቸውን የገለፁ ሲኾን፣ ከዓባይ ውሃ አጠቃቀም ጋር በተገናኘ ከኢትዮጵያ ጋራ አለመግባባት ውስጥ የምትገኘው ግብፅም፣ በሶማሊያው የአፍሪካ ሕብረት ተልዕኮ ስር ወታደሮቿን እንደምታሳትፍ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ገልጻለች፡፡ አዲሱ የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ - ኤዩሶም ከአውሮፓውያኑ ጥር 1 ቀን 2025 ዓ.ም ጀምሮ በሶማሊያ ኃላፊነቱን መረከቡ፣ በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ ኃላፊ ሞሀመድ ኤል አሚኒ ሱፍ በእለቱ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።  

ጥቁር አሜሪካውያን የጋና ዜግነት እያገኙ ነው

ጋና በመላው ዓለም የሚገኙ ጥቁሮችን ወደ ሀገሯ እንዲመጡ በመጋበዝ ላይ ስትኾን፣ በቅርቡም 524 ለሚሆኑና በአብዛኛው ጥቁር አሜሪካውያን ለኾኑ ሰዎች ዜግነት ሰጥ
የአሜሪካ ድምፅ

ጥቁር አሜሪካውያን የጋና ዜግነት እያገኙ ነው

ጋና በመላው ዓለም የሚገኙ ጥቁሮችን ወደ ሀገሯ እንዲመጡ በመጋበዝ ላይ ስትኾን፣ በቅርቡም 524 ለሚሆኑና በአብዛኛው ጥቁር አሜሪካውያን ለኾኑ ሰዎች ዜግነት ሰጥታለች። ጋና ከአምስት ዓመታት በፊት “የመመለስ ዓመት” የሚል ተነሳሽነት ከጀመረች ወዲህ የተሰጠ ከፍተኛው የዜግነት ቁጥር መሆኑም ታውቋል። ተነሳሽነቱ የመጀመሪያዎቹ አፍሪካውያን በበባሪያ ፍንገላ በ1619 ዓ.ም ወደ አሜሪካ የመጡበትን አራት መቶኛ ዓመት ለማሰብ ያለመ ነው። ከረጅም ጊዜ በፊት የተሰበረው ቁርኝት መልሶ በመጠገኑ ሰዎች እጅግ ሲደሰቱ መስተዋሉን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። በዜግነት አሰጣጥ ሥነ ሥርዐት ላይ አንዳንዶች የጋናን ባንዲራ በማውለብለብ በደስታ ሲያለቅሱም ተሰተውሏል። ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ ሳሉ ያልተሰማቸው ደስታና የማንነት ስሜት እንደተሰማቸውም አንዳንዶች ተናግረዋል።

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንትን ለመያዝ የተደረገው ሙከራ ከሸፈ

የደቡብ ኮሪያ መርማሪዎች ተከሳሹን የአገሪቱ ፕሬዝደንት ዩን ሶክ ዮል በቁጥጥር ሥር ለማድረግ የነበራቸውን ሙከራ አቁመዋል። መርማሪዎቹ ሙከራውን የተውት ፕሬ
የአሜሪካ ድምፅ

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንትን ለመያዝ የተደረገው ሙከራ ከሸፈ

የደቡብ ኮሪያ መርማሪዎች ተከሳሹን የአገሪቱ ፕሬዝደንት ዩን ሶክ ዮል በቁጥጥር ሥር ለማድረግ የነበራቸውን ሙከራ አቁመዋል። መርማሪዎቹ ሙከራውን የተውት ፕሬዝደንቱን ከመኖሪያ ቤታቸው ለመያዝ ያደርጉት ሙከራ በጠባቂዎቻቸው በመገታቱ ነው። የሀገሪቱ ሕግ አውጪ ምክር ቤት ፕሬዝደንቱን ከሥራቸው ያገደ ሲሆን፣ የመያዣ ትዕዛዙ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ ዩን ሶክ ዮል በደቡብ ኮሪያ ታሪክ የተያዙ የመጀመሪያ ፕሬዝደንት ይሆናሉ። ባለፈው ወረ የማርሻል ሕግ አውጀው ሀገሪቱን ወደ ወታደራዊ አስተዳደር ለመቀየር የሞከሩት ፕሬዝደንቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቻው ሐሳባቸውን ወዲያው እንዲተው ተገደዋል። በዚህም እሥራት፣ ከከፋ ደግሞ የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ሃያ የሚሆኑ መርማሪዎችና 80 የሚሆኑ ፖሊሶች መኖሪያ ግቢያቸው ገብተው ፕሬዝደንቱን ለመያዝ ሲሞክሩ፣ 200 የሚሆኑ ወታደሮችና ጠባቂዎቻቸው ገተዋቸዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ድርድር ተሞክሮ ሳይሳከ በመቅረቱ መርማሪዎችና ፖሊሶች ወደ መጡበት ተመልሰዋል። የመያዣ ትዕዛዙ የቀን ገደብ ሰኞ የሚያበቃ ሲሆን፣ ፕሬዝደንቱ ራሳቸውን ለመከላከል “እንደሚፋለሙ” ዝተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመያዣ ትዕዛዙ የቀን ገደብ በሚያከትምበት ሰኞ ዕለት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከሰሜን ኮሪያው አቻቸው ጋራ ለመነጋገር ሶል እንደሚገቡ ታውቋል። በደቡብ ኮሪያ የፖለቲካ ጉዳይ ላይ አስተያየት ሰጥታ የማታውቀው ሰንሜን ኮሪያ፣ ዮንን ለመያዝ በሚደረግ ጥረት ምክንያት፣ ሶል የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብታለች ሲሉ የሃገሪቱ የመንግሥት ብዙኅን መገናኛ አስታውቀዋል።

ትረምፕ ለትምሕርት ሚንስትርነት ያጯቸው የቀድሞዋ የነጻ ትግል ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ

እንደ ብዙዎቹ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካቢኔ እጩዎች ሁሉ፣ የትምህርት ሚኒስትር እጩዋ ሊንዳ ሜክሜሃን በትረምፕ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ ዋና ደጋፊ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ ለትምሕርት ሚንስትርነት ያጯቸው የቀድሞዋ የነጻ ትግል ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ

እንደ ብዙዎቹ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካቢኔ እጩዎች ሁሉ፣ የትምህርት ሚኒስትር እጩዋ ሊንዳ ሜክሜሃን በትረምፕ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ ዋና ደጋፊ እና መዋጮ ለጋሽ ነበሩ። በአብዛኛው የሠሩትም የዓለም የነጻ ትግል መዝናኛ የተባለውን ዘርፈ ብዙ ድርጅት በመምራት ነበር፡፡ ምንም እንኳን ብዙ ተንታኞች እና መምሕራን በትምሕርት ላይ ያላቸው ልምድ ውስን ነው ቢሉም፣ በእርሳቸው አመራር ትልቅ የአቅጣጫ ለውጥ እንደሚኖር ይጠበቃል። የቪኦኤዋ ሎረል ቦውማን ያደረሰችንን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።    

በላስ ቬጋሱ የቴስላ ተሽከርካሪ ፍንዳታ የሞተው የአሜሪካ ወታደር ነበር ተባለ

ዩናይትድ ስቴትስ ላስ ቬጋስ ከተማ በተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሆቴል ደጃፍ በቴስላ ሳይበር ትራክ መኪና ፍንዳታ የሞተው ግለሰብ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት
የአሜሪካ ድምፅ

በላስ ቬጋሱ የቴስላ ተሽከርካሪ ፍንዳታ የሞተው የአሜሪካ ወታደር ነበር ተባለ

ዩናይትድ ስቴትስ ላስ ቬጋስ ከተማ በተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሆቴል ደጃፍ በቴስላ ሳይበር ትራክ መኪና ፍንዳታ የሞተው ግለሰብ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት አባል ነው ብለው ባለሥልጣናት እንደሚያምኑ ተነገረ። ይህን የተናገሩት አሶሼትድ ፕሬስ ትላንት ሐሙስ ያነጋገራቸው ሦስት የአሜሪካ ባለሥልጣናት ናቸው፡፡ ባለሥልጣናቱ ምርመራ ላይ ባለ ጉዳይ ለመናገር ሥልጣን ስላልነበራቸው ስማቸው አልተገለጸም፡፡ ሁለት የሕግ አስከባሪ ባለሥልጣናት ተሽከርካሪዋ ውስጥ የነበረው ማቲው ሊቭልስበርገር የተባለ ሰው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ሊቭልስበርገር ሰሜን ካሮላይና ውስጥ ቀድሞ ፎርት ብራግ በተባለው የጦር ሠራዊቱ የልዩ ኃይሎች መምሪያ የሚገኝበት ግዙፍ የጦር ሠፈር ያገለግል እንደነበር ሦስቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡ የላስ ቬጋሱ የመኪና ፍንዳታ የተከሰተው የ42 ዓመቱ ሻምሱድ-ዲን ባህር ጃባር በአውሮፓውያኑ የዘመን መለወጫ ቀን በኒው ኦርሊየንስ 15 ሰዎችን የገደለበትን አደጋ ባደረሰበት ዕለት ነው፡፡ አደጋው የተከሰተው ኒው ኦርሊየንስ ውስጥ ፍሬንች ኳርተር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ ጃባር በፖሊስ ከመገደሉ በፊት ዐዲሱን ዓመት ለማክበር ተሰባስበው በነበሩ ሰዎች ላይ መኪናውን በፍጥነት በመንዳት ቢያንስ 15 ሰዎችን ገድሏል፡፡ ድርጊቱ በሽብር አድራጎትነት ተይዞ በመመርመር ላይ ሲሆን ፖሊስ አጥቂው ጥቃቱን የፈጸመው ብቻውን አይደለም ተብሎ እንደሚያምን ቢገልጽም የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ዛሬ ሐሙስ ለጋዜጠኞ በሰጠው መግለጫ «ግለሰቡ ጥቃቱን የፈጸመው ብቻውን ነው» ብሏል፡፡ “ጥቃቱን የፈጸመው በእስላማዊ መንግሥት ሽብርተኞች ተገፋፍቶ ነው” ሲልም አክሏል፡፡ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት አባል የሆነው ጃባርም በፎርት ብራግ የጦር ሠፈር ያገለገለ ቢሆንም አንድ ላይ አለመስራታቸውን አንደኛው ባለሥልጣን ተናግረዋል፡፡

Get more results via ClueGoal