በኢትዮጵያ የኤች.አይ.ቪ ስርጭት ወቅታዊ ኹኔታ
newsare.net
በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭት በአገር አቀፍ ደረጃ እየቀነሰ ቢኾንም፣ በጋምቤላ ክልል እና በከተሞች ውስጥ እየጨመረ እንደሚገኝ፣ የተባበሩት መንግሥታበኢትዮጵያ የኤች.አይ.ቪ ስርጭት ወቅታዊ ኹኔታ
በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭት በአገር አቀፍ ደረጃ እየቀነሰ ቢኾንም፣ በጋምቤላ ክልል እና በከተሞች ውስጥ እየጨመረ እንደሚገኝ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤችአይቪ/ኤድስ ፕሮግራም(ዩኤንኤድስ) አስታውቋል። የተቋሙ ከፍተኛ አማካሪ የኾኑትና ኢትዮጵያን ጨምሮ በአምስት የአፍሪካ ሀገራት እየተሠራበት ባለው የኤች.አይ.ቪ መቆጣጠርያ የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ እና ስትራቴጂ ዝግጅት ላይ እንደተሳተፉ የገለጹልን ዶክተር አምኃ ኀይሌ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የበሽታው ስርጭት መቀነሱን ገልጸዋል፡፡ ይኹንና፣ አሁንም ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ለበሽታው ተጋላጭ የኾኑ ቦታዎች እና የኅብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን አማካሪው ጠቁመዋል፡፡ግጭት እና ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች፣ የበሽታው ተጋላጭነት እየጨመረ እንዳለ የሚያሳዩ መረጃዎች መኖራቸውን፣ ዶክተር አምኃ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቃለ ምልልስ ወቅት ገልጸዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more