ዶናልድ ትራምፕ ለአፍ ማስያዣ በሰጡት ገንዘብ ጉዳይ ተበየነባቸው፤ መቀጮ ግን አልተጣለባቸውም
newsare.net
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለአፍ ማስያዣ ከሰጡት ገንዘብ ጉዳይ ጋራ በተያያዘ ጥፋተኛ ሆነው በተገኙበት እና ብይን ቢሰጣቸውም፤ ለወንጀሉ መቀጫ ግን ዳዶናልድ ትራምፕ ለአፍ ማስያዣ በሰጡት ገንዘብ ጉዳይ ተበየነባቸው፤ መቀጮ ግን አልተጣለባቸውም
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለአፍ ማስያዣ ከሰጡት ገንዘብ ጉዳይ ጋራ በተያያዘ ጥፋተኛ ሆነው በተገኙበት እና ብይን ቢሰጣቸውም፤ ለወንጀሉ መቀጫ ግን ዳኛው ምንም ዐይነት ቅጣት አልጣሉባቸውም። ዛሬ አርብ በኒው ዮርክ ማንሃተን የሚገኘው ችሎት ዳኛ ሁዋን ኤም መርቻን በትራምፕ ላይ የሰጡት ይህ ብይን፣ እስር ወይም የገንዘብ ቅጣት የማይጨምር በመሆኑ ወደ ዋይት ሀውስ ከመመለስ የማያግዳቸው ቢሆንም፤ ጥፋተኛ የተባሉበትን ወንጀል ግን የሚያጸና ነው። ትራምፕ በበኩላቸው ‘የፈጸምኩት ወንጀል የለም’ ሲሉ ይግባኝ እንደሚሉ ተናግረዋል። ከ2016ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጋራ የተያያዘ መረጃ ለመሸፋፈን በተፈጸመው እና ‘የተለምዶ አሠራሮችን የናደ ነው’ የተባለው የወንጀል ጉዳይ በ34 ክሶች ጥፋተኛ ኾነው ቢገኙም፤ ፍርዱ በምርጫ ውጤት ላይ ያስከተለው አሉታዊ ተጽዕኖ የለም። Read more