«ልጄስ» ተከታታይ ድራማ በፓን አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ በሁለት ዘርፎች ተሸለመ
newsare.net
«ልጄስ» ተከታታይ ድራማ፣ በካሜሩን በሚዘጋጀው ፓን አፍሪካን ዶውላ ፊልም ፌስቲቫል ላይ፣ በምርጥ የፊልም መቼት ማስዋብ እና በምርጥ ሲኒማ ዘርፍ አሸናፊ«ልጄስ» ተከታታይ ድራማ በፓን አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ በሁለት ዘርፎች ተሸለመ
«ልጄስ» ተከታታይ ድራማ፣ በካሜሩን በሚዘጋጀው ፓን አፍሪካን ዶውላ ፊልም ፌስቲቫል ላይ፣ በምርጥ የፊልም መቼት ማስዋብ እና በምርጥ ሲኒማ ዘርፍ አሸናፊ ኾኗል። «ልጄስ»- ልጁ ለትምህርት ወደ አንድ አነስተኛ የገጠር ከተማ አምርቶ በዚያው የጠፋበት አርሶ አደር ልጁን በመፈለግ ሒደት ውስጥ የሚያሳልፋቸው ገጠመኞች እና ተግዳሮቶች የተቃኘበት ነው፡፡ የፊልሙ ጸሓፊ እና አዘጋጅ ሰማኝጌታ አይዝሉህም፣ «እኔ መምከር በምችልበት ዕድሜ ላይ ባለመኾኔ፣ ድራማው ከማስተማር ይልቅ ጠያቂ እና ደንበር ተሻጋሪ የኾነ ሐሳብ እንዲኖረው ማድረግ ላይ አተኩሪያለኹ፤» ብሏል፡፡ በ«ጉዞ ፊልሞች» የተዘጋጀው ይኸው ተከታታይ ድራማ፣ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በቃና ቴሌቭዥን በኩል ለእይታ እንደሚበቃ፣ የፊልሙ ዲሬክተር፣ ጸሓፊ እና አዘጋጅ ሰማኝጌታ አይችሉህም ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል። ወጣት የፊልም ባለሞያዎቹን ሰማኝጌታን አይችሉህም እና ሲኒማቶግራፈር ጋድ ክፍሎም ጋራ ቆይታ አድርገናል። ከተያያዘው ፋይል ሙሉውን ይከታተሉ። Read more