ተቃውሞ በበረታባት ሞዛምቢክ ዐዲሱ ፓርላማ ሥራ ጀምሯል
newsare.net
በሞዛምቢክ አከራካሪ የነበረውን ምርጫ ውጤት ተቃውመው፣ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሥራ ማቆም አድማ መጥራታቸውን ተከትሎ ዋና ከተማው ጭር ባለበት ዕለት አዲተቃውሞ በበረታባት ሞዛምቢክ ዐዲሱ ፓርላማ ሥራ ጀምሯል
በሞዛምቢክ አከራካሪ የነበረውን ምርጫ ውጤት ተቃውመው፣ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሥራ ማቆም አድማ መጥራታቸውን ተከትሎ ዋና ከተማው ጭር ባለበት ዕለት አዲሱ ፓርላማ ሥራ ጀምሯል። ሁለት አነስተኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ ውጤቱን አንቀበልም በማለት ተቃውሟቸውን ለመግለፅ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ያልተገኙ ሲሆን፣ ለወራት የተካሄደው እና የሰው ህይወት የጠፋበትን አለመረጋጋት ተከትሎ በተከፈተው ፓርላማ፣ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ቻፖ መረጋጋት እና አንድነት እንዲሰፍን ጠይቀዋል። በሞዛምቢክ ተሰሚነት አጥተናል በሚሉ ወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት ቬናንሲዮ ሞንድላኔ፣ የምርጫው ውጤት መጭበርበሩን እና ከ50 ዓመት በላይ በሥልጣን ላይ የቆየው የቻፖ ፓርቲ እንዲያሸንፍ መደረጉን ተናግረዋል። ቻፖ ቃለ መሃላ ፈፅመው ሥልጣን እንዲረከቡ በሚጠበቅባቸው ከሰኞ እስከ ረቡዕ ባሉት ቀናትም፣ ደጋፊዎቻቸው ተቃውሟቸውን ለመግለፅ የሥራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ፓርላማው ዛሬ የመክፈቻ ሥነ-ስርዐቱን ሲያካሂድ፣ በተለምዶ ከፍተኛ ግርግር ይታይበት በነበረው የዋና ከተማው ማዕከል፣ አብዛኞቹ ሱቆች መዘጋታቸውን እና መንገዶችም ጭር ማለታቸውን በቦታው ተገኝቶ ሁኔታውን የተመለከተው የአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘጋቢ አመልክቷል። Read more