ለጋዛ የእርቅ ስምምነት ማምጣት ይችላል የተባለ የመጨረሻ ረቂቅ ሐሳብ ለሁለቱም ወገኖች ቀረበ
newsare.net
በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም፣ አሸማጋዮች የመጨረሻ ያሉትን የእርቅ ስምምነት ረቂቅ ሐሳብ ለእስራኤል እና ለሐማስ ማቅረባቸውን፣ በድርድሩ ዙሪያ ማብለጋዛ የእርቅ ስምምነት ማምጣት ይችላል የተባለ የመጨረሻ ረቂቅ ሐሳብ ለሁለቱም ወገኖች ቀረበ
በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም፣ አሸማጋዮች የመጨረሻ ያሉትን የእርቅ ስምምነት ረቂቅ ሐሳብ ለእስራኤል እና ለሐማስ ማቅረባቸውን፣ በድርድሩ ዙሪያ ማብራሪያ የቀረበላቸው አንድ ባለሥልጣን አስታወቁ። በድርድሩ ላይ የጆ ባይደን እና የዶናልድ ትራምፕ ልዑካን መገኘታቸውንም አመልክተዋል። ባለሥልጣኑ እንደተናገሩት፣ የተኩስ ማቆምን እና የታጋቾችን መለቀቅ በሚመለከት ኳታር ያቀረበችው ረቂቅ የስምምነት ጹሑፍ ዶሃ ውስጥ በተደረገ ውይይት ላይ ለሁለቱም ወገኖች የቀረበ ሲሆን፣ የእስራኤል 'ሞሳድ' እና 'ሺን ቤት' የተሰኙት የስለላ ተቋማት እንዲሁም የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር በቦታው መገኘታቸውም ተመልክቷል። በመጪው ሳምንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን ሲመለሱ የዩናይትድ ስቴትስ ልዑክ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ስቲቭ ዊትኮፍም ድርድሩ ላይ መገኘታቸውን ባለሥልጣኑ ጨምረው ገልጸዋል። በተጨማሪም፣ የተሰናባቹ ባይደን አስተዳደር ልዑክ ብሬት ማክጉርክ በድርድሩ መሳተፋቸውን አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ምንጭ ለሮይተርስ ተናግረዋል። «ስምምነት ላይ ለመድረስ መጪዎቹ 24 ሰዓታት ወሳኝ ናቸው» ያሉት ባለሥልጣኑ ረቂቁ ዛሬ ሰኞ ባለቀ ሰዓት የተገኘ ውጤት መሆኑን አመልክተዋል። የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችል ድርድር ለማካሄድ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ኳታር እና ግብፅ ከአንድ ዓመት በላይ ሲሠሩ ቢቆዩም እስካሁን ውጤት ማግኘት አልቻሉም። Read more