ካታር «እስራኤል እና ሃማስ ወደተኩስ አቁም ስምምነት ተቃርበዋል» አለች
newsare.net
ካታር ጋዛ ሰርጥ ላይ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ የተያዘው ድርድር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተናገረች፡፡ ሁለካታር «እስራኤል እና ሃማስ ወደተኩስ አቁም ስምምነት ተቃርበዋል» አለች
ካታር ጋዛ ሰርጥ ላይ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ የተያዘው ድርድር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተናገረች፡፡ ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ ለመድረስ በእጅጉ “የተቃረቡ” መሆኑን ካታር ዛሬ ማክሰኞ አስታውቃለች፡፡ የካታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጅድ አል-አንሷሪ በሳምንታዊ መግለጫቸው ድርድሩ አዎንታዊ እና ውጤታማ መሆኑን ገልፀው ሆኖም «ተስማሙ» ተብሎ ከመታወጁ አስቀድሞ ከመጠን በላይ ከመፈንደቅ መቆጠብ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል። ካታር፣ ግብፅ እና ዩናይትድ ስቴትስ ጦርነቱን ለማስቆም ወራት የፈጀውን ጥረት የመሩ ሲሆን ዛሬ ማክሰኞ በዶሃ የተደረጉ ንግግሮች በስምምነቱ የመጨረሻ ዝርዝሮች ላይ አትኩረዋል። ትላንት ሰኞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስምምነቱ “በመጨረሻ እውን ወደ መሆን ”ተቃርቧል« ብለዋል፡፡ ባይደን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸውን ስኬት ለማጉላት ባደረጉት ንግግር ስምምነቱ “ታጋቾቹን ነፃ ያወጣል፣ ጦርነቱን ያስቆማል፣ ለእስራኤል ደህንነቷን ይሰጣል፣ በዚህ ጦርነት ውስጥ ከባድ መከራ ለደረሰባቸው ፍልስጤማውያን ሰብአዊ ርዳታ እንድንሰጥ ያስችለናል” ብለዋል። የተኩስ አቁሙ መሠረታዊ መለኪያዎች የሂደቱን የተለያዩ ደረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ሃማስ እ.ኤ.አ ጥምቅት 2023 ታጣቂዎቹ በእስራኤል ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ የያዛቸውን ታጋቾች ሲለቅ፣ የእስራኤል ባለስልጣናት ደግሞ የፍልስጤም እስረኞችን ይፈታሉ። የእስራኤል ወታደሮች ደረጃ በደረጃ ከጋዛ ይወጣሉ፣ በግጭቱ የተፈናቀሉ አንዳንድ ፍልስጤማውያንም፣ ለፍልስጤማውያን ሲቪሎች እየጨመረ ከሚመጣው እርዳታ ጋር አብረው እንዲመለሱ ይፈቀድላቸዋል። በዩናይትድ ስቴትስ፣ በግብፅ እና በካታር እየተመራ ለወራት ሲካሄድ የቆየው ድርድር ጦርነቱን ማቆም ባይችልም፣ አሜሪካ የአመራር ለውጥ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ካለችበት ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን ጥረቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ኤም ኤስ ኤን ቢሲ ለተባለው የአሜሪካ ቴሌቪዥን ትላንት ሰኞ በሰጡት ቃል ሁለቱ ወገኖች »ስምምነት ላይ ለመድረስ አሁን ከምንጊዜውም ይበልጥ ተቃርበዋል« ብለው » አሁን ኳሷ ሃማስ ሜዳ ውስጥ ናት" ብለዋል፡፡ የባይደን የብሐራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሰለቫን ትላንት ሰኞ እንደተናገሩት የባይደን አስተዳደር ባለስልጣናት ስለድርድሩ ሂደት በየጊዜው ለተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የመካከለኛ ምሥራቅ አማካሪዎች ገለጻ ሲያደርጉላቸው ቆይተዋል፡፡ የትረምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ በኋለኞቹ የድርድሩ ዙሮች ተሳትፈዋል። Read more