በኢትዮጵያ በ25 ዓመት ውስጥ ከ400 በላይ ርዕደ መሬቶች ተከስተዋል
newsare.net
በኢትዮጵያ ባለፉት 25 ዓመታት ከ400 በላይ ርዕደ መሬቶች መከሰታቸውን ጥናቶች አመለከቱ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለሞያዎች ዛሬ በተዘጋጀ፣ በግንባታ ኮዶችበኢትዮጵያ በ25 ዓመት ውስጥ ከ400 በላይ ርዕደ መሬቶች ተከስተዋል
በኢትዮጵያ ባለፉት 25 ዓመታት ከ400 በላይ ርዕደ መሬቶች መከሰታቸውን ጥናቶች አመለከቱ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለሞያዎች ዛሬ በተዘጋጀ፣ በግንባታ ኮዶችና መስፈርቶች ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ ላይ ባቀረቡት ጥናት፣ ስምጥ ሸለቆን መነሻው ያደረገው ርዕደ መሬት ድግግሞሹ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ 2024 ወዲህ ባለው አንድ ዓመት ብቻ እስከ 150 ርዕደ መሬቶች መመዝገባቸውን የተናገሩት ባለሞያዎቹ፣ በተለይም፣ ካለፈው መስከረም ጀምሮ የታየው ርዕደ መሬት በግንባታዎችና መሰረተልማቶች ላይ መጠነኛ ጉዳት ማስከተሉን ጠቅሰዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more