በከባድ ብርድ ምክኒያት የትረምፕ ቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐት በምክር ቤቱ ሕንፃ እንዲከናወን ተወሰነ
newsare.net
የፊታችን ሰኞ በዋሽንግተን እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ ይኖራል በመባሉ ተመራጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐታቸው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤትበከባድ ብርድ ምክኒያት የትረምፕ ቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐት በምክር ቤቱ ሕንፃ እንዲከናወን ተወሰነ
የፊታችን ሰኞ በዋሽንግተን እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ ይኖራል በመባሉ ተመራጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐታቸው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ካፒቶል ውስጥ እንዲከናወን ወስነዋል። ሰኞ የምክር ቤቱ አካባቢ የቅዝቃዜ ደረጃ ከዜሮ በታች 11 ዲግሪ ሴልሲየስ እንደሚኾን እና ንፋሱ ብርዱን የበለጠ አስከፊ እንደሚሆን ይጠበቃል። የአየር ሁኔታ ባለሞያዎች እንዳሉት የትረምፕ በዓለ ሲመት የአየር ሁኔታ ቅዝቃዜ በ40 ዓመታት ያልታየ እንደሚሆን ተብየዋል። ትረምፕ በትሩዝ ሶሺያል ማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው በአወጡት ጽሑፍ «የሕዝባችንን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለብኝ። ማንም እንዲጎዳ አልፈልግም» ብለዋል። የበዓለ ሲመት ንግግራቸው የጸሎት ሥነ ሥርዐቱ እና የሚደረጉት ሌሎች ንግግሮች በምክር ቤቱ ግዙፉ ክብ አዳራሽ «ካፒቶል ሮታንዳ» ውስጥ ታላላቅ እንግዶች እና ተሳታፊዎች በተገኙበት እንዲከናወን ማዘዛቸውን ትላንት አስታውቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቻይና ምክትል ፕሬዝደንቷን ሃን ዤንግን በበዓለ ሲመቱ ላይ እንዲገኙ እንደምትልክ ትላንት ዐርብ አስታውቃለች። በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት በዓለ ሲመት ላይ ከፍተኛ የቻይና መሪ ሲገኝ ይኽ የመጀመሪያ ጊዜ እንደሚሆን ተመልክቷል። Read more