ትረምፕ ቅዳሜ በዋሽንግተን የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ አመሹ
newsare.net
ነገ ሰኞ ሁለተኛው በዓለ ሲመታቸው የሚከናወነው ዶናልድ ትረምፕ በዋዜማው ትላንት ቅዳሜ ምሽት ወደዋሽንግተን መጥተው የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ ተገኝተዋል።ትረምፕ ቅዳሜ በዋሽንግተን የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ አመሹ
ነገ ሰኞ ሁለተኛው በዓለ ሲመታቸው የሚከናወነው ዶናልድ ትረምፕ በዋዜማው ትላንት ቅዳሜ ምሽት ወደዋሽንግተን መጥተው የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ ተገኝተዋል። ከአራት ዓመታት በፊት ደጋፊዎቻቸው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ወርረው ጥቃት ባደረሱበት ሁናቴ ከተማዋን ለቅቀው የሄዱት ሪፐብሊካኑ ትረምፕ አሁን በድል አድራጊነት ተመልሰዋል። ትላንት ማታ ዋሽንግተን አቅራቢያ ስተርሊንግ ቨርጂኒያ በሚገኘው የጎልፍ መጫወቻቸው ትረምፕ ናሽናል ጎልፍ ክለብ በተካሄደው ድግሥ ቤተሰቦቻቸው፥ ደጋፊዎቻቸው እና የፖለቲካ አጋሮቻቸው ታድመዋል። የኦፔራ ስልት ድምጻዊው ክሪስቶፈር ማኪዮ የዘፈነ ሲሆን ርችትም ተተኩሷል። የነገው በዓለ ሲመት እጅግ ኃይለኛ ብርድ ይኖራል መባሉን ተከትሎ በልማዱ ካፒቶል ሕንጻ ደረጃ ላይ የሚከናወነውን ቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት ጨምሮ አብዛኛውን ደጅ የሚካሄድ ዝግጅት ወደሕንጻው ውስጥ ለማዛወር አዘጋጆቹ ጥድፊያ ላይ ናቸው። ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ በአርሊንግተን መካነ መቃብር የአበባ ጉንጉን ማስቀመጥ ሥነ ሥርዓት ላይ ይገኙና በመቀጠል በዋሽንግተን ዲሲ የደጋፊዎቻቸው ስብሰባ ላይ ይገኛሉ። Read more