Ethiopia



ቲክ ቶክ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አገልግሎት መስጠት አቆመ

ማኅበራዊ መገናኛው ቲክ ቶክ ከትላንት ቅዳሜ ማታ ጀምሮ በዩናይትድ ስቴትስ አገልግሎት መስጠት አቁሟል። አሜሪካ ውስጥ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ቲክቶክ ከአ

ተኩስ አቁሙ ተግባራዊ ኾነ፣ ሃማስ የመጀመሪያዎቹን ታጋቾች ለቀቀ

በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ውል ዛሬ እሁድ ሥራ ላይ ውሏል። ስምምነቱ ጋዛ ላይ ለዐስራ አምስት ወራት የቀጠለውን ጦርነት ለስድስት
የአሜሪካ ድምፅ

ተኩስ አቁሙ ተግባራዊ ኾነ፣ ሃማስ የመጀመሪያዎቹን ታጋቾች ለቀቀ

በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ውል ዛሬ እሁድ ሥራ ላይ ውሏል። ስምምነቱ ጋዛ ላይ ለዐስራ አምስት ወራት የቀጠለውን ጦርነት ለስድስት ሳምንታት በሚገታው የተኩስ አቁም ውል መሠረት   የሃማስ ታጣቂዎች የያዟቸውን በርካታ ታጋቾች እንዲለቅቁ ይጠይቃል። ዛሬ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ በሰዓታት ውስጥ ሃማስ የመጀመሪያዎቹን ሦስት ወጣት ሴቶች የለቀቀ ሲሆን ቀይ መስቀል በአጀብ ወደ ጋዛ በመግባት የተለቀቁትን ታጋቾች ተረክቧል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሃማስ ዛሬ እሁድ ይለቃል የተባለውን ሦስት ታጋቾች ስም ዝርዝር ሳይሰጠን ስምምነቱ ተግባራዊ አይሆንም በማለታቸው ተግባራዊ የሆነው ከታቀደው ሰዓት በሦስት ሰዓት ገደማ ዘግይቶ ነው። ኔታንያሁ በአገሩ ሰዓት ጠዋት ሁለት ተኩል ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የታቀደው ተኩስ አቁም ሃማስ «እሰጣለሁ» ያለውን የሚለቀቁ ታጋቾች ስም ዝርዝር ሳይሰጥ ተግባራዊ እንዳይሆን ለመከላከያ ኃይሎች ትዕዛዝ ሰጥተዋል ሲል ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አስታውቋል። ይህንኑ ተከትሎ ሃማስ ስም ዝርዝሩን ከሰጠ በኋላ እስራኤል ተኩስ አቁሙ አምስት ሰዓት ተኩል ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቃለች። ሃማስ ስም ዝርዝሩ የዘገየው በቴክኒክ እክል ምክንያት እንደሆነ ጠቅሶ ስምምነቱን እንደማከብር በድጋሚ አረጋግጣለሁ ሲል መግለጫ አውጥቷል። ይህ በዚህ እንዳለ አክራሪ ብሔርተኛው የእስራኤል የብሔራዊ ጸጥታ ሚንስትር ኢታማር ቤን ጋቪር የተኩስ አቁም ውሉን በመቃወም ሥራ መልቀቃቸው ተዘግቧል።

አዲስ አበባ ላይ ዛሬ የተከበረው የጥምቀት በዓል

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ የተ
የአሜሪካ ድምፅ

አዲስ አበባ ላይ ዛሬ የተከበረው የጥምቀት በዓል

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ የተመዘገበው የጥምቀት በዓል ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በድምቀት ተከብሯል። በዓል ከሚከበርባቸው ቀደምት ቦታዎች አንዱ ጃን ሜዳ ሲኾን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተገኙበት፣ የጥምቀት ሥነ-ስርዐቱ ተከናውኗል፡፡ ፓትሪያርኩ በንግግራቸው፣ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል። የእምነቱ ተከታዮች እና ጎብኚዎችም አስተያየት ሰጥተውናል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ትረምፕ ቅዳሜ በዋሽንግተን የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ አመሹ

ነገ ሰኞ ሁለተኛው በዓለ ሲመታቸው የሚከናወነው ዶናልድ ትረምፕ በዋዜማው ትላንት ቅዳሜ ምሽት ወደዋሽንግተን መጥተው የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ  ተገኝተዋል።
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ ቅዳሜ በዋሽንግተን የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ አመሹ

ነገ ሰኞ ሁለተኛው በዓለ ሲመታቸው የሚከናወነው ዶናልድ ትረምፕ በዋዜማው ትላንት ቅዳሜ ምሽት ወደዋሽንግተን መጥተው የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ  ተገኝተዋል። ከአራት ዓመታት በፊት ደጋፊዎቻቸው  የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ወርረው ጥቃት ባደረሱበት ሁናቴ ከተማዋን ለቅቀው የሄዱት ሪፐብሊካኑ ትረምፕ አሁን በድል አድራጊነት ተመልሰዋል።   ትላንት ማታ ዋሽንግተን አቅራቢያ  ስተርሊንግ ቨርጂኒያ በሚገኘው የጎልፍ መጫወቻቸው ትረምፕ ናሽናል ጎልፍ ክለብ በተካሄደው ድግሥ ቤተሰቦቻቸው፥ ደጋፊዎቻቸው እና የፖለቲካ አጋሮቻቸው ታድመዋል።  የኦፔራ ስልት ድምጻዊው ክሪስቶፈር ማኪዮ  የዘፈነ ሲሆን   ርችትም  ተተኩሷል። የነገው በዓለ ሲመት  እጅግ ኃይለኛ ብርድ ይኖራል መባሉን ተከትሎ በልማዱ ካፒቶል ሕንጻ ደረጃ ላይ የሚከናወነውን ቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት ጨምሮ አብዛኛውን ደጅ የሚካሄድ ዝግጅት ወደሕንጻው ውስጥ ለማዛወር አዘጋጆቹ ጥድፊያ ላይ ናቸው።   ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ በአርሊንግተን መካነ መቃብር የአበባ ጉንጉን ማስቀመጥ ሥነ ሥርዓት ላይ ይገኙና በመቀጠል በዋሽንግተን ዲሲ የደጋፊዎቻቸው ስብሰባ ላይ ይገኛሉ።  

በደምበል ሐይቅ ላይ የተከበረው የጥምቀት ከተራ በዓል

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ደምበል ሐይቅ ላይ የጥምቀት ከተራ በዓል በኃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዐቶች ተከብሯል። የገዳማቱ ዕድሜ
የአሜሪካ ድምፅ

በደምበል ሐይቅ ላይ የተከበረው የጥምቀት ከተራ በዓል

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ደምበል ሐይቅ ላይ የጥምቀት ከተራ በዓል በኃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዐቶች ተከብሯል። የገዳማቱ ዕድሜ ጠገብ መኾንና በዓሉ በሐይቁ ላይ መከበሩ የተለየ ውበትና ትርጉም እንደሚሰጠው፣ በደሴቶቹ ላይ የሚገኙት ቤተ ክርስቲያናት ስብከተ ወንጌል ኃላፊ ዲያቆን ዘነበ ዋቆ ተናግረዋል። የባቱ ከተማ ነዋሪው አቶ አለሙ በዳዶም፣ ታቦታቱ በተለይ ውሃው ላይ ሲገናኙ የሚፈጥረዉ ስሜት ልዩ መኾኑን ገልጸዋል። የበዓሉን ድባብ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

በሐይቅና ዳርቻዎቹ ላይ በሐዋሳ ከተማ የተከበረው የጥምቀት ከተራ በዓል  

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነው የጥምቀት ከተራ በዓል በሐዋሳ ከተማ በሐይቅና ዳርቻዎቹ ተከብሯል። ጥምቀት እና ከተራ፣
የአሜሪካ ድምፅ

በሐይቅና ዳርቻዎቹ ላይ በሐዋሳ ከተማ የተከበረው የጥምቀት ከተራ በዓል  

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነው የጥምቀት ከተራ በዓል በሐዋሳ ከተማ በሐይቅና ዳርቻዎቹ ተከብሯል። ጥምቀት እና ከተራ፣ በሐይቅ ዳርቻ በሚገኘው ደብረ ምጥማቅ መድኃኔዓለም ገዳም አንዱ  ሲኾን በከተማው የሚገኙት ዐሥራ አንድ ደብር ታቦታት ሄደው ያደሩት በዚኽ ስፍራ ነው። በተጨማሪም ከሐዋሳ ሐይቅ ማዶ ከሚገኘው ሎቄ ደብረ መድኃኒት መስቀለ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያ ሁለት ታቦታት በ25 ጀልባዎች ታጅበው በሐይቁ ላይ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ተጉዘው አንድ ላይ ያከብራሉ።   ቁጥራቸው የበዛ የእምነቱ ተከታዮች በታደሙበት የቤተ ክርስቲያን ካህናት መዘምራንና የእምነቱ ተከታዮች በሐይቁ ላይ ታቦታቱን በሕብረ ዝማሬ፣ በወረብ፣ በውዳሴ በጸሎት እና በምስጋና አጅበው በደማቅ ሥነ ሥርዐት ወደ መድኃኔዓለም ጥምቀተ ባሕር ገዳም አቅንተዋል።

የጥምቀት ከተራ በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ተከብሯል

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነው የጥምቀት ከተራ በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ተከብሯል። በዩኔስኮ ከተመዘገቡ የኢትዮጵያ መ
የአሜሪካ ድምፅ

የጥምቀት ከተራ በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ተከብሯል

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነው የጥምቀት ከተራ በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ተከብሯል። በዩኔስኮ ከተመዘገቡ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ቅርሶች አንዱ የሆነው የጥምቀት ከተራ በዓል በየዓመቱ በድምቀት የሚከበር በዓል ነው። በርካታ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንዲኹም ጎብኚዎች ታቦታትን ወደ ባህረ-ጥምቀቶች በመንፈሳዊ ክዋኔዎች አጅበው ሸኝተዋል፡

በከባድ ብርድ ምክኒያት የትረምፕ ቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐት በምክር ቤቱ ሕንፃ እንዲከናወን ተወሰነ

የፊታችን ሰኞ በዋሽንግተን እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ ይኖራል በመባሉ ተመራጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ  የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐታቸው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት
የአሜሪካ ድምፅ

በከባድ ብርድ ምክኒያት የትረምፕ ቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐት በምክር ቤቱ ሕንፃ እንዲከናወን ተወሰነ

የፊታችን ሰኞ በዋሽንግተን እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ ይኖራል በመባሉ ተመራጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ  የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐታቸው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ካፒቶል ውስጥ እንዲከናወን ወስነዋል። ሰኞ የምክር ቤቱ አካባቢ የቅዝቃዜ ደረጃ ከዜሮ በታች 11 ዲግሪ ሴልሲየስ እንደሚኾን እና ንፋሱ ብርዱን የበለጠ አስከፊ እንደሚሆን ይጠበቃል። የአየር ሁኔታ ባለሞያዎች እንዳሉት የትረምፕ በዓለ ሲመት የአየር ሁኔታ ቅዝቃዜ በ40 ዓመታት ያልታየ እንደሚሆን ተብየዋል። ትረምፕ በትሩዝ ሶሺያል ማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው በአወጡት ጽሑፍ «የሕዝባችንን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለብኝ። ማንም እንዲጎዳ አልፈልግም» ብለዋል። የበዓለ ሲመት ንግግራቸው የጸሎት ሥነ ሥርዐቱ እና የሚደረጉት ሌሎች ንግግሮች በምክር ቤቱ ግዙፉ ክብ አዳራሽ «ካፒቶል ሮታንዳ» ውስጥ ታላላቅ እንግዶች እና ተሳታፊዎች በተገኙበት እንዲከናወን ማዘዛቸውን ትላንት አስታውቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቻይና ምክትል ፕሬዝደንቷን ሃን ዤንግን በበዓለ ሲመቱ ላይ እንዲገኙ እንደምትልክ ትላንት ዐርብ አስታውቃለች። በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት በዓለ ሲመት ላይ ከፍተኛ የቻይና መሪ ሲገኝ ይኽ የመጀመሪያ ጊዜ እንደሚሆን ተመልክቷል።  

የእስራኤል ካቢኔ የተኩስ አቁም ስምምነቱን አጸደቀ

የእስራኤል ሚኒስትሮች ካቢኔ  በጋዛ ተኩስ እንዲቆም እና ታጋቾቹ እንዲለቀቁ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት አጽድቋል። ስምምነቱን ሀያ አራት ሚንስትሮ
የአሜሪካ ድምፅ

የእስራኤል ካቢኔ የተኩስ አቁም ስምምነቱን አጸደቀ

የእስራኤል ሚኒስትሮች ካቢኔ  በጋዛ ተኩስ እንዲቆም እና ታጋቾቹ እንዲለቀቁ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት አጽድቋል። ስምምነቱን ሀያ አራት ሚንስትሮች ሲደግፉ ስምንት ሚንስትሮች ውድቅ አድርገውታል። ተኩስ አቁሙ ሰኞ ከሚከናወነው  በዩናይትድ ስቴትስ የተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በዓለ ሲመት ዋዜማ  እሑድ ጀምሮ ሥራ ላይ ሊውል ታቅዷል። እስራኤል እና ሀማስ ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የደረሱት በዩናይትድ ስቴትስ በካታር እና በግብጽ ሽምግልና ከአንድ ዓመት በላይ የፈጀ ድርድር ከተካሄደ በኋላ  ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በግንቦት ወር  ያጸደቁትን የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለቱ ወገኖች በዚህ ሳምንት ረቡዕ ፈርመዋል። በማስከተልም የእስራኤል ካቢኔ ይሁንታ ሰጥቶታል። ሰኞ ቃለ መሐላቸውን ፈጽመው አስተዳደሩን የሚረከቡት  ዶናልድ ትረምፕ የስምምነቱን ተግባራዊነት መከታተሉ የእርሳቸው አስተዳደር ኃላፊነት ይሆናል።

በኢትዮጵያ በ25 ዓመት ውስጥ ከ400 በላይ ርዕደ መሬቶች ተከስተዋል  

በኢትዮጵያ ባለፉት 25 ዓመታት ከ400 በላይ ርዕደ መሬቶች መከሰታቸውን ጥናቶች አመለከቱ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለሞያዎች ዛሬ በተዘጋጀ፣ በግንባታ ኮዶች
የአሜሪካ ድምፅ

በኢትዮጵያ በ25 ዓመት ውስጥ ከ400 በላይ ርዕደ መሬቶች ተከስተዋል  

በኢትዮጵያ ባለፉት 25 ዓመታት ከ400 በላይ ርዕደ መሬቶች መከሰታቸውን ጥናቶች አመለከቱ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለሞያዎች ዛሬ በተዘጋጀ፣ በግንባታ ኮዶችና መስፈርቶች ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ ላይ ባቀረቡት ጥናት፣ ስምጥ ሸለቆን መነሻው ያደረገው ርዕደ መሬት ድግግሞሹ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ 2024 ወዲህ ባለው አንድ ዓመት ብቻ እስከ 150 ርዕደ መሬቶች መመዝገባቸውን የተናገሩት ባለሞያዎቹ፣ በተለይም፣ ካለፈው መስከረም ጀምሮ የታየው ርዕደ መሬት በግንባታዎችና መሰረተልማቶች ላይ መጠነኛ ጉዳት ማስከተሉን ጠቅሰዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የዱር እንስሳት መብት ተሟጋቿ ግሬታ ዩሪ

ግሬታ ፍራንቼስካ ዩሪ፣ የጣሊያንና የኢትዮጵያ ትውልድ ያላት የአካባቢ ጥበቃ እና የዱር እንስሳት ጥበቃ መብት ባለሞያ ናት።  ግሬታ በተለይም የዝኆን ጥበቃ ተ
የአሜሪካ ድምፅ

የዱር እንስሳት መብት ተሟጋቿ ግሬታ ዩሪ

ግሬታ ፍራንቼስካ ዩሪ፣ የጣሊያንና የኢትዮጵያ ትውልድ ያላት የአካባቢ ጥበቃ እና የዱር እንስሳት ጥበቃ መብት ባለሞያ ናት።  ግሬታ በተለይም የዝኆን ጥበቃ ተነሣሽነት ሥራዎች ላይ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ 25 የአፍሪካ ሀገራት ተሳታፊ በኾኑበት ተቋም አማካኝነት ብዙ ሥራዎችን ሠርታለች። በአሁን ሰዓት፣ አፍሪካውያን ሴቶች በአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ በሚቀሰቅስ 'ሴቶች ለአካባቢ ጥበቃ' የተባለ ድርጅት መሥራች እና ባልደረባ ናት።  ስለ ሥራዋ እና የዱር እንስሳት ጥበቃ እንቅስቃሴዎቿ በተመለከተ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ያደረገችውን ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በሩዋንዳ የማርበርግ ወረርሽኝ እና የሕክምና ባለሞያዋ ተሞክሮ

በ2017 ዓ.ም. መባቻ ላይ በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ሩዋንዳ፣ በዓይነቱ ለየት ያለና ገዳይ የኾነ በቫይረስ የሚተላለፍ ማርበርግ የተሰኘ ወርርሽኝ መገኘቱን አገሪ
የአሜሪካ ድምፅ

በሩዋንዳ የማርበርግ ወረርሽኝ እና የሕክምና ባለሞያዋ ተሞክሮ

በ2017 ዓ.ም. መባቻ ላይ በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ሩዋንዳ፣ በዓይነቱ ለየት ያለና ገዳይ የኾነ በቫይረስ የሚተላለፍ ማርበርግ የተሰኘ ወርርሽኝ መገኘቱን አገሪቱ ይፋ አደረገች። አገሪቱ በወቅቱ የሕክምና ባለሞያዎችን ጨምሮ በበሽታው የተጠቁ ዜጎቿን ብታጣም፣ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ግን የበሽታውን ስርጭት መቆጣጠር ችላለች።  ኪጋሊ በሚገኘው በሩዋንዳ ዩኒቨርሲቲ የድንገተኛ ሕክምና ሳይንስ ክፍል ባልደረባ እና ኒውዮርክ በሚገኘው ሮናልድ ኦ ፕሬልማን ዩኒቨርሲቲ መምህርት የኾነችው ዶር. ጽዮን ፍሬው፣ በወቅቱ በሕክምና ሒደቱ ላይ ከተሳተፉ ሐኪሞች መካከል አንዷ ነበረች።  ማርበርግ፣ አብረዋት የሠሩ ባልደረቦችዋን ሕይወት መቅጠፉንና በሰዓቱ በሽታው በንክኪ የሚተላለፍ ከመኾኑ የተነሳም ለተወሰኑ ቀናት ከሕፃናት ልጆቿ መነጠል እንደነበረባት አስታውለች።  ከዶር. ጽዮን ጋራ የተደረገውን ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በአማራ ክልል አምስት ወረዳዎች የተከሰተው የምግብ እጥረት ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እያስከተለ ነው

በሰሜን ወሎ ዞን በቡግና ወረዳ እና በዋግምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አራት ወረዳዎች ከፍተኛ የሆነ ምግብና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መከሰቱን ወልድያ ዩኒቨ
የአሜሪካ ድምፅ

በአማራ ክልል አምስት ወረዳዎች የተከሰተው የምግብ እጥረት ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እያስከተለ ነው

በሰሜን ወሎ ዞን በቡግና ወረዳ እና በዋግምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አራት ወረዳዎች ከፍተኛ የሆነ ምግብና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መከሰቱን ወልድያ ዩኒቨርሲቲ አስጠንቶታል የተባለ አንድ የዳሰሳ ጥናት አመለከተ። የአካባቢው ባለሥልጣናት በአካባቢው ያለው የሰብአዊ ድጋፍ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የሚገኘው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በሁለቱ ዞኖች ሰሞኑን አደረኩት ባለው የዳሰሳ ጥናት በአካባቢዎቹ ባጋጠመው የምግብ እጥረት ቀውስ ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። የአሜሪካ ድምፅ የአፍሪካ ቀንድ የአማርኛው አገልግሎት ከታኅሳስ 12 እስከ ታኅሳስ 13 ድረስ በቡግና ወረዳ አራት ቀጠናዎች የተደረገውን የዳሰሳ ጥናት ግልባጭ አግኝቷል። የዳሰሳ ጥናቱን ለማድረግ በወልደያ ዩንቨርስቲ ከተመረጡት አምስት አባላት መካከል አንዱ እንደኾኑና የጥናቱ ቡድን መሪ መኾናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት አቶ ጌታነው ሰውነት ከተመረጡ የከአካባቢው ነዋሪ ጋራ ባደረጉት ውይይት የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን እንደሰሙ ገልጸዋል። ስለ ዳሰሳ ጥናቱ የተጠየቁት የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽነር አቶ ተስፋው ባታብል ፣ «በቡግና ወረዳ የተመጣጠነ የምግብ ችግር መኖሩ የታወቀ ነው። ይህንን መሰረት በማድረግ የሰብአዊ ድጋፍ ወደ ስፍራው እየላክን ነው።» ብለዋል። እየተደረገ ባለው ድጋፍም ህፃናቱ በማገገም ላይ መኾናቸውን ገልጸው፣ «በወልደያ ዩንቨርስቲ የተደረገው ጥናት የጋራ እውቅና የለውም። የጋራ መገምገሚያ ነጥብ ተይዞ የታየ አይደለም። ወደ ፊት የሚታይ ይሆናል። አሁን ግን በመንግሥት በኩል ዕውቅና የለውም። እንደዚኽ ዐይነት ችግር ሲገጥም ሰው ሊሞት ይችላል ይህ ደግሞ በጥናት መረጋገጥ አለበት። ስለዚህ ዩንቨርስቲው ያጠናው ጥናት የጋራ ያልኾነና ከመንግሥት እውቅና ውጭ ነው» ብለዋል።

አደራዳሪዎች በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ “ቴክኒካዊ” ውይይት በማደረግ ላይ ናቸው

ከግብፅ፣ ቃጣር፣ አሜሪካ እና እስራኤል የተውጣጡ አደራዳሪዎች በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ “ቴክኒካዊ” ያሉትን መላ ለመሻት ካይሮ ላይ ዛሬ ተገናኝተዋል
የአሜሪካ ድምፅ

አደራዳሪዎች በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ “ቴክኒካዊ” ውይይት በማደረግ ላይ ናቸው

ከግብፅ፣ ቃጣር፣ አሜሪካ እና እስራኤል የተውጣጡ አደራዳሪዎች በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ “ቴክኒካዊ” ያሉትን መላ ለመሻት ካይሮ ላይ ዛሬ ተገናኝተዋል። ስምምነቱ ከዕሁድ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን እንደሚጠበቅ መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በዛሬው ስብሰባ ላይ ወደ ጋዛ በቀን 600 ዕርዳታ የጫኑ መኪኖች እንዲገቡ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ዕርዳታ የጫኑ ከባድ መኪናዎች በግብጽ ድንበር በኩል በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል። የእስራኤል የፀጥታ ካቢኔም ስምምነቱን ለማጽደቅ ዛሬ እንደሚሰበሰብ ይጠበቃል። ካቢኔው የሚያጸድቀው ከሆነም በጋዛ ድብደባውና ጦርነቱ ቆሞ፣ ታጋቾች የሚለቀቁበት ሁኔታ ይመቻቻል ተብሏል። ለረዥም ጊዜ ይጠበቅ የነበረው የእስራኤል እና የሐማስ የተኩስ ማቆም ስምምነት ጦርነቱን የሚያቆመው ከሆነ፣ በጋዛ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ወደ መኖሪያቸው ለመመልስ እንደጓጉ ተመልክቷል። ፍልስጤማውያኑ ወደ መኖሪያቸው የሚመለሱ ቢሆን እንኳ፣ አብዛኞቹ ምንም የቀረ ንብረት እንደማይኖራቸው፣ መልሶ ግንባታ ቢያስቡም የማይቻል እንደሆነ ተነግሯል። የእስራኤል ድብደባ በርካታ መንደሮችን ወደ አመድነት ቀይሯል።

የንግድ ቤታቸው ከካሊፎርኒያው ሰደድ እሳት የተረፈላቸው ኢትዮጵያዊት ኀዘንና ተስፋ

በካሊፎርኒያ ግዛት የተስፋፋው ሰደድ እሳት፣ 82 በመቶ የነዋሪዎችን ንብረት ባወደመባት ፓሊሴድስ ውስጥ የሚገኝ «ፓሊሴድስ ዋይን ኤንድ ስፕሪት» የተባለ የ
የአሜሪካ ድምፅ

የንግድ ቤታቸው ከካሊፎርኒያው ሰደድ እሳት የተረፈላቸው ኢትዮጵያዊት ኀዘንና ተስፋ

በካሊፎርኒያ ግዛት የተስፋፋው ሰደድ እሳት፣ 82 በመቶ የነዋሪዎችን ንብረት ባወደመባት ፓሊሴድስ ውስጥ የሚገኝ «ፓሊሴድስ ዋይን ኤንድ ስፕሪት» የተባለ የዋይን እና ለምግብነት የሚውሉ ቀለል ነገሮች መሸጫ ባለቤቷ ወይዘሮ ተዋበች ፈረደ፣ በአካባቢው ብቸኛ ኢትዮጵያዊት የንግድ ቤት ባለቤት መኾናቸውን ነግረውናል። ወሮ. ተዋበች፣ አሁን ወደ ስፍራው ተመልሰው ገብተው ለማየት ባይችሉም፣ በአካባቢው በሰደድ እሳቱ ከመቃጠል ተርፏል ከተባለው 18 በመቶ ንብረት ውስጥ የእርሳቸው ንግድ ቤት አንዱ ሊኾን እንደሚችል ተነግሮኛል፤ ይላሉ። ከሰደድ እሳቱ ነበልባል አምልጠው መውጣታቸውን ቢገልጹም፣ «ለስምንት ዓመት የሠራኹበትና እንደ ቤተሰብ የማያቸው ደንበኞቼ እና ጎረቤቶቼ ንብረት በመውደሙ ግን በቃላት ልገልጸው የማልችለው እጅግ ከባድ ኀዘን ተሰምቶኛል፤» ብለውናል። በሌላ በኩል እሳቱ በተነሳበት ወቅት በሥራ ላይ የነበሩትና የአስቸኳይ ጊዜ አደጋ ማስጠንቀቂያውን ሰምተው በፍጥነት የደረሱላቸው ባለቤታቸው አቶ ዮሴፍ መቅድም “እዛው እሳቱ ውስጥ ነበርን። የእሳቱ ሙቀት እየተሰማን ነው የወጣነው” ብለውናል። ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሰላም ማስከበር በሚኖራት ሚና ላይ ስምምነት መደረሱን ገለጸች

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ለሶማሊያ ሰላም መረጋገጥ በሚኖረው ሚና ላይ፣ በሁለቱ ሀገራት መንግሥታት መካከል ስምምነት መደረሱን ኢትዮጵያ ገለጸች።
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሰላም ማስከበር በሚኖራት ሚና ላይ ስምምነት መደረሱን ገለጸች

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ለሶማሊያ ሰላም መረጋገጥ በሚኖረው ሚና ላይ፣ በሁለቱ ሀገራት መንግሥታት መካከል ስምምነት መደረሱን ኢትዮጵያ ገለጸች። የሁለቱ አገራት መሪዎች፣ በሰላም ማስከበሩ ሒደት ኢትዮጵያ በሚኖራት ሚና ላይ እንዲሁም አምባሳደሮችን ዳግም ከመሾም ጀምሮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአክሱም ፍርድ ቤት የሒጃብ ክልከላ ውሳኔን በጊዜያዊነት አገደ

የአክሱም ትምህርት ቤቶች በሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ ያሳለፉትን የሒጃብ ክልከላ፣ የከተማዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጊዜያዊነት እንዲታገድ ወስኗል። በተመሳሳይ
የአሜሪካ ድምፅ

የአክሱም ፍርድ ቤት የሒጃብ ክልከላ ውሳኔን በጊዜያዊነት አገደ

የአክሱም ትምህርት ቤቶች በሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ ያሳለፉትን የሒጃብ ክልከላ፣ የከተማዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጊዜያዊነት እንዲታገድ ወስኗል። በተመሳሳይ፣ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ በ159 የከተማዋ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ ትምህርት ቤቶች የጣሉትን ክልከላ እንዲነሣ መወሰኑን አስታውቋል።

ብሪታኒያ እና ዩክሬን «ለመቶ  ዓመት የሚዘልቅ አጋርነት» ስምምነት

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር የሀገራቸውን እና የዩክሬንን ግንኙነት የሚያጠናክር የ«100 ዓመት ስምምነት» ለመፈራረም ዛሬ ሀሙስ ኪቭ ገብተዋ
የአሜሪካ ድምፅ

ብሪታኒያ እና ዩክሬን «ለመቶ  ዓመት የሚዘልቅ አጋርነት» ስምምነት

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር የሀገራቸውን እና የዩክሬንን ግንኙነት የሚያጠናክር የ«100 ዓመት ስምምነት» ለመፈራረም ዛሬ ሀሙስ ኪቭ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደኪቭ የተጓዙት ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ ዋይት ሀውስ ከመመለሳቸው በፊት የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት እና የጦር ሜዳ ውጥረቶች እያየሉ በመጡበት በዚህ ወቅት ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ወቅት በኪቭ ከፍተኛ ፍንዳታ እና የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደወል ሲጮኽ ተሰምቷል፡፡ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ውስጥ ስልጣን የያዙት ስታርመር ወደዩክሬን ሲጓዙ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ሲሆን የተጓዙትም የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ትረምፕ በሚቀጥለው ሳምንት አስተዳደራቸውን ከመጀመራቸው በፊት ከዩክሬን አእጋሮች ጋራ በተከታታይ እየተነጋገሩ ባሉበት በዚህ ወቅት መሆኑ ነው፡፡   ስምምነቱ የመከላከያ፣ የጦር ሜዳ ቴክኖሎጂ እና ወደ ውጭ በሚላከው እህል ክትትል ላይ ያተኩራል። ስታርመር ለዩክሬን መልሶ ማቋቋሚያ የ40 ሚሊዮን ፓውንድ ርዳታ ይፋ አድርገዋል። ብሪታኒያ እኤአ ከ 2022 ጀምሮ ለዩክሬን የ12.8 ቢሊዮን ፓውንድ ርዳታ ሰጥታለች። ዘገባው የኤኤፍፒ ነው፡፡

የትራምፕ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምን ሊመስል ይችላል?

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ከቀናት በኋላ ቃለ መሐላ ፈጽመው ሥራቸውን በይፋ ይጀምራሉ። ቀዳሚ ትኩረት እንደሚሰጡት በተጠቀሰው
የአሜሪካ ድምፅ

የትራምፕ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምን ሊመስል ይችላል?

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ከቀናት በኋላ ቃለ መሐላ ፈጽመው ሥራቸውን በይፋ ይጀምራሉ። ቀዳሚ ትኩረት እንደሚሰጡት በተጠቀሰው የኢኮኖሚው ዘርፍ፣ የታክስ ቅነሳን ጨምሮ የኩባንያዎችን ምርታማነት የሚያሳድጉ ማሻሽያዎችን ያደርጋሉ፤ ተብሎ እንደሚጠበቅ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ጠቁመዋል። እንደ መጀመሪያው ፕሬዝዳንታዊ የሥልጣን ዘመናቸው፣ የግብር ጭማሬን በተመለከተ፣ ከሀገራት ጋራ ውዝግብ ውስጥ የሚገቡ ከኾነ የኑሮ ውድነትን ሊያባብስ ይችላል፤ ሲሉ ስጋታቸውን ገልጰዋል። ከአፍሪካ ጋራ በሚደረጉ የንግድ ትብብሮች፣ ከአህጉራዊ ግንኙነት ይልቅ ከሀገራት ጋራ የሁለትዮሽ ግኑኙነቶች ላይ ሊያተኩሩ እንደሚችሉም ባለሞያዎቹ አክለዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የዶናልድ ትረምፕ ዕጩ የመከላከያ ሚንስትር በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ብርቱ ጥያቄ ገጠማቸው

ትላንት ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፊት የቀረቡት የተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ዕጩ የመከላከያ ሚንስትር ፒት ሄግሴት የሴኔቱ
የአሜሪካ ድምፅ

የዶናልድ ትረምፕ ዕጩ የመከላከያ ሚንስትር በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ብርቱ ጥያቄ ገጠማቸው

ትላንት ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፊት የቀረቡት የተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ዕጩ የመከላከያ ሚንስትር ፒት ሄግሴት የሴኔቱ ወታደራዊ አገልግሎት ኮሚቴ አባላት ከሆኑ ዲሞክራት አባላት የበረታ ሙግት ገጥሟቸዋል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ የመከላከያ ሚንስቴር ዘጋቢ ካርላ ባብ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች፡፡ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡

«በሱስ የተጠቁ ሰዎች ፈጽመው መዳን ይችላሉ» ዶክተር መስከረም አበበ

ሥር በሰደደ የአደንዛዥ ዕፅ ሱስ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ሳይቀሩ፣ «ለመዳን ከቆረጡና ተገቢውን ርዳታ ካገኙ ከችግሩ መውጣት ይችላሉ፤» ያሉን፣ በቅዱስ ጳውሎስ
የአሜሪካ ድምፅ

«በሱስ የተጠቁ ሰዎች ፈጽመው መዳን ይችላሉ» ዶክተር መስከረም አበበ

ሥር በሰደደ የአደንዛዥ ዕፅ ሱስ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ሳይቀሩ፣ «ለመዳን ከቆረጡና ተገቢውን ርዳታ ካገኙ ከችግሩ መውጣት ይችላሉ፤» ያሉን፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሜዲካል ኮሌጅ ሥር በሚገኘው የሱስ ማገገሚያ ማዕከል የሥነ አእምሮ ጤና ባለሞያ እና በሆስፒታሉ የአእምሮ ሕክምናና ትምህርት ክፍል ሓላፊ ዶክተር መስከረም አበበ የምሽቱ እንግዳችን ናቸው። ሱስ እና ሱሰኛነት ምን እንደኾነ በማስረዳት የሰጡንን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

«እጅግ ከፍተኛ» የሰውነት ክብደትን ለማከም የዋሉት ዐዲሶቹ መድኃኒቶች የሚሹት ጥንቃቄ

እንደ ብርቱ የጤና ችግር የሚታየው «እጅግ ከፍተኛ» የሰውነት ክብደት፣ ሊያስከትላቸው የሚችላቸው ልዩ ልዩ የጤና ጠንቆች እንዳሉ ይታመናል። በሕክምና
የአሜሪካ ድምፅ

«እጅግ ከፍተኛ» የሰውነት ክብደትን ለማከም የዋሉት ዐዲሶቹ መድኃኒቶች የሚሹት ጥንቃቄ

እንደ ብርቱ የጤና ችግር የሚታየው «እጅግ ከፍተኛ» የሰውነት ክብደት፣ ሊያስከትላቸው የሚችላቸው ልዩ ልዩ የጤና ጠንቆች እንዳሉ ይታመናል። በሕክምናው ዓለም የእንግሊዘኛው አጠራር ‘ኦቤሲቲ’ በመባል የሚታወቀውን ይህን ‘እጅግ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት’ በማከሙ ረገድ፣ «ከአሁን ቀደም ያልታየ» የተባለን ውጤት ያሳዩትና ከፍተኛ ትኩረት የሳቡት እነኚኽ መድኃኒቶች፥ “የጥቅማቸውን ያህል በሐኪም የቅርብ ክትትል እና በጥንቃቄ መወሰድ ያለባቸው ናቸው” - እንደ ባለሞያዎች ማብራሪያ። የምሽቱ «ሐኪምዎን ይጠይቁ» ዝግጅት፣ ይኸው የጤና ችግር በሕክምና የሚረዳባቸውን መድኃኒቶች ምንነት፣ ፋይዳ እና ፈተናዎች የሚፈትሽ የባለሞያ ትንታኔን ይዟል። ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን የውስጥ ደዌ እና የኢንዶክሪኖሎጂ ልዩ ሕክምና ባለሞያው ዶክተር አቤል ተካ ናቸው።

‘ዩናይትድ ስቴትስ በውጭ ፖሊሲዋ የተነሳ ይበልጥ ጠንካራ ነች’ - ባይደን

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከስልጣን ጊዜያቸው ማብቂያ አንድ ሳምንት አስቀድሞ ትላንት ሰኞ ባሰሙት ንግግር የተመሩበትን የውጭ ፖሊሲ መርህ ዘርዝረዋል። አገሪቱ
የአሜሪካ ድምፅ

‘ዩናይትድ ስቴትስ በውጭ ፖሊሲዋ የተነሳ ይበልጥ ጠንካራ ነች’ - ባይደን

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከስልጣን ጊዜያቸው ማብቂያ አንድ ሳምንት አስቀድሞ ትላንት ሰኞ ባሰሙት ንግግር የተመሩበትን የውጭ ፖሊሲ መርህ ዘርዝረዋል። አገሪቱን ወደ ፍጹም አዲስ ወደ ሆነ አቅጣጫ እንደሚመሩ በመግለጽ የዛቱት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመንግስቱን ሥልጣን ሊረከቡ የቀናት እድሜ ብቻ በቀረበት ሰዓት ባይደን ባሰሙት በዚህ ንግግራቸው፤ ዩናይትድ ስቴትስ ለምን በያዘችው መንገድ መቀጠል እንዳለባት መከራከሪያ አቅርበዋል። የአሜሪካ ድምጿ ዘጋቢ አኒታ ፓውል ከኋይት ሃውስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር አሉላ ከበደ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።

የትረምፕ የሀገር ውስጥና የውጪ ፖሊሲዎች ምን ይመስላሉ?

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ በምርጫ ዘመቻዎቻቸው ወቅት በእርሳቸው የአስተዳደር ዘመን ሊፈጽሙ ያሰቧቸውን በርካታ የሀገር ውስጥም ኾነ የውጪ ፖሊሲ ጉ
የአሜሪካ ድምፅ

የትረምፕ የሀገር ውስጥና የውጪ ፖሊሲዎች ምን ይመስላሉ?

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ በምርጫ ዘመቻዎቻቸው ወቅት በእርሳቸው የአስተዳደር ዘመን ሊፈጽሙ ያሰቧቸውን በርካታ የሀገር ውስጥም ኾነ የውጪ ፖሊሲ ጉዳዮችን በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ሲያተዋውቁ እንደነበር ይታወሳል። ሊፈጽሙ ያቀዷቸው በርካታ የፖሊሲ ለውጦች በአጭርና ረጅም ጊዜ በአሜሪካ የውስጥ ጉዳይ እና በዓለም አቀፍ ግንኙነት ላይ ትልቅ አንድምታ እንደሚኖረው ተንታኞች ይገልጻሉ። የፖሊሲ ለውጦቹን የሚደግፉ አሜሪካውያን እንዳሉ ሁሉ፣ የሚቃወሙትም በርካቶች ናቸው። የትረምፕ የሃገር ውስጥና የውጪ ፖሊሲ ለውጦችን የሚዳስሰውን ቀጣዩን ጥንቅር ያዘጋጀው እንግዱ ወልዴ ነው።

ቻይና አሜሪካ የሰው ሰራሽ ልህቀትን አስመልክታ ያወጣችን ህግ እንደምቃወም አስታወቀች

ቻይና የዩናይትድ ስቴትስ ወደ ውጭ የሚላከውን የሰው ሰራሽ ልህቀት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) በሚመለከት ያወጣቻቸውን አዳዲስ የቁጥጥር እርምጃዎች “በጽኑ እን
የአሜሪካ ድምፅ

ቻይና አሜሪካ የሰው ሰራሽ ልህቀትን አስመልክታ ያወጣችን ህግ እንደምቃወም አስታወቀች

ቻይና የዩናይትድ ስቴትስ ወደ ውጭ የሚላከውን የሰው ሰራሽ ልህቀት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) በሚመለከት ያወጣቻቸውን አዳዲስ የቁጥጥር እርምጃዎች “በጽኑ እንደምትቃወም” ገልጻ የኩባንያዎቿን ጥቅም ለመጠበቅ “ቆራጥ እርምጃዎችን” እንደምትወስድ አስታውቃለች። የባይደን አስተዳደር ትላንት ሰኞ የሰው ሰራሽ ልህቀትን ለማዳበር የሚያገለግሉ ቺፕስ የተባሉትን ልዩ የዘመናዊ ኮምፒውተር ክፍሎችን ወደ ውጭ መላክን አስመልክቶ አዲስ የቁጥጥር ማዕቀፍ አቅርቧል። ርምጃው ከአምራቾች እና ከሌሎች ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ጋር ተያይዘው በቴክኖሎጂው ላይ የሚከሰቱ የብሔራዊ የደህንነት ስጋቶችን ሚዛን ለመጠበቅ የሚደረግ ሙከራ መሆኑም በአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ ተጠቅሷል፡፡ አዲሱ ደንብ አብዛኛው ትኩረቱ ቻይና ላይ ቢሆንም ሜክሲኮ፣ ፖርቱጋል፣ እስራኤል እና ስዊዘርላንድ ለሰው ሠራሽ ልህቀት መረጃ ማዕከላት እና ምርቶች የሚያስፈልጉ ቺፖች ተደራሽነት ገደብ ከሚገጥማቸው ሀገራት መካከል ሊሆኑ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉኦ ጂያኩን አሜሪካ ቻይናን በ“እኩይ ዓላማ” ትከተላታለች ሲሉ ከሰዋታል፡፡ ቃል አቀባዩ አያይዘው “የዓለም አቀፉን የኢንዱስትሪ እና የአቅርቦት ሰንሰለቶች መረጋጋት የሚያናጋ፣ የሁለቱን ሀገራት ጥቅም እና የሁሉም አገሮች የንግድ ዘርፎች የሚጎዳ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ውሳኔው የተደረገው ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሥራ ከመጀመራቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ መሆኑ ነው፡፡ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቫን “በጭራሽ በፓርቲ ወገንተኝነት የሚታይ ጉዳይ መሆን የለበትም” ብለው ያለውን አካሄድ መከተል ወይም መተው የትረምፕ ፋንታ እንደሚሆን ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እገዳ የተደነቀነበት ቲክ ቶክ፣ ብዙዎቹ ተጠቃሚዎች፣ ሲያሆምሹ ወደተባለው ወደ ሌላኛው የቻይና መተግበሪያ እየፈለሱ መሆኑን ተመልክቷል፡፡ መተግበሪያው በቅርቡ አሜሪካ ውስጥ የአፕል ስልክ ተጠቃሚዎች ወደ ስልኮቻቸው ከጫኑት መተግበሪያ ትልቁ መሆኑን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ሲያምሹ ቀጣዩ የአሜሪካ ኢላማ ሊሆን ይችል እንደሆነ የተጠየቁት ቃል አቀባዩ “መላ ምት አዘል ለሆኑ ጥያቄዎች” ብለው በመደቧቸው ውስጥ የሚካተት በመሆኑ ምላሽ እንደማይሰጡበት በመግለጽ አልፈውታል፡፡

ኢትዮጵያ ከአሜሪካው «አጎዋ» እና ከቻይናው ነጻ ታሪፍ ተጠቃሚ ናት?

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው በተለይም የቡና ምርት ትልቋ ተቀባይ ሀገር የኾነችው አሜሪካ፣ የቀረጥ ነጻ ዕድል(አጎዋ) ተጠቃሚነትን ስትከለክል፤ የኢትዮጵያ
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ ከአሜሪካው «አጎዋ» እና ከቻይናው ነጻ ታሪፍ ተጠቃሚ ናት?

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው በተለይም የቡና ምርት ትልቋ ተቀባይ ሀገር የኾነችው አሜሪካ፣ የቀረጥ ነጻ ዕድል(አጎዋ) ተጠቃሚነትን ስትከለክል፤ የኢትዮጵያ የውጪ ምርቶች አነስተኛ ተቀባይ የኾነችው ቻይና፣ የቀረጥ ወይም የዜሮ ታሪፍ ተጠቃሚነትን ፈቅዳለች፡፡ በዚኽ ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ተጠቃሚ ነው? በዚኽ ጉዳይ ላይ፣ የአሜሪካ ድምፅ በውጭ ንግድ ላይ የተሰማሩትን የኢትዮጵያ ጥራጥሬ እና ቅባት እህል ላኪዎች ማኅበር የቦርድ ሊቀ መንበር አቶ ኤዳኦ አብዲንና ከዊሊያም ፓተርሰን ኒውጀርሲ ዩኒቨርስቲ መምህር እና “China in Ethiopia: The Long-Term Perspective” የሚል መጽሐፍ እ.አ.አ በ2020 ያሳተሙት ፕሮፌሰር አሮን ተስፋዬን አነጋግሯል፡፡ ፕሮፌሰር አሮን፣ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ በምትልካቸው ምርቶች ላይ ተጨማሪ ዕሴቶችን በማከል የተጠናቀቁ ምርቶችን ካላቀረበች፣ «ለየትኛውም ሀገር ብትልክ አትራፊ አትኾንም፤» ይላሉ፡፡ በዚኽ የሚስማሙት አቶ ኤዳኦም፣ ብዙ ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅ ይመክራሉ፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በዳርፉር «የዘር ማጥፋት እየተፈጸመ ነው» ማለቷን የመብት ተሟጋቾች «ድል» ሲሉ ገለጹ

ዩናይትድ ስቴትስ፣ በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኀይሎች እና ተባባሪዎቹ ሚሊሽያዎች «የዘር ማጥፋት እየፈጸሙ ነው፤» ስትል ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ  አስታውቃለ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ በዳርፉር «የዘር ማጥፋት እየተፈጸመ ነው» ማለቷን የመብት ተሟጋቾች «ድል» ሲሉ ገለጹ

ዩናይትድ ስቴትስ፣ በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኀይሎች እና ተባባሪዎቹ ሚሊሽያዎች «የዘር ማጥፋት እየፈጸሙ ነው፤» ስትል ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ  አስታውቃለች፡፡ ሄነሪ ዊልኪንስ ባስተላለፈው ዘገባ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ይፋ ያደረገችውን ብይን በተመለከተ፣ ተንታኞች እና የመብት ተሟጋቾች የሰጡትን አስተያየት በማካተት ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

ካታር «እስራኤል እና ሃማስ ወደተኩስ አቁም ስምምነት  ተቃርበዋል» አለች

ካታር ጋዛ ሰርጥ ላይ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ የተያዘው ድርድር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተናገረች፡፡ ሁለ
የአሜሪካ ድምፅ

ካታር «እስራኤል እና ሃማስ ወደተኩስ አቁም ስምምነት  ተቃርበዋል» አለች

ካታር ጋዛ ሰርጥ ላይ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ የተያዘው ድርድር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተናገረች፡፡ ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ ለመድረስ በእጅጉ “የተቃረቡ” መሆኑን ካታር ዛሬ ማክሰኞ አስታውቃለች፡፡ የካታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጅድ አል-አንሷሪ በሳምንታዊ መግለጫቸው ድርድሩ አዎንታዊ እና ውጤታማ መሆኑን ገልፀው ሆኖም «ተስማሙ» ተብሎ ከመታወጁ አስቀድሞ ከመጠን በላይ ከመፈንደቅ መቆጠብ እንደሚገባ  አስጠንቅቀዋል። ካታር፣ ግብፅ እና ዩናይትድ ስቴትስ ጦርነቱን ለማስቆም ወራት የፈጀውን ጥረት የመሩ ሲሆን ዛሬ ማክሰኞ በዶሃ የተደረጉ ንግግሮች በስምምነቱ የመጨረሻ ዝርዝሮች ላይ አትኩረዋል። ትላንት ሰኞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን  ስምምነቱ “በመጨረሻ እውን ወደ መሆን ”ተቃርቧል« ብለዋል፡፡ ባይደን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸውን ስኬት ለማጉላት ባደረጉት ንግግር ስምምነቱ “ታጋቾቹን ነፃ ያወጣል፣ ጦርነቱን ያስቆማል፣ ለእስራኤል ደህንነቷን ይሰጣል፣ በዚህ ጦርነት ውስጥ ከባድ መከራ ለደረሰባቸው ፍልስጤማውያን ሰብአዊ ርዳታ እንድንሰጥ ያስችለናል” ብለዋል።  የተኩስ አቁሙ መሠረታዊ መለኪያዎች የሂደቱን የተለያዩ ደረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ሃማስ እ.ኤ.አ ጥምቅት 2023 ታጣቂዎቹ በእስራኤል ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ የያዛቸውን ታጋቾች ሲለቅ፣ የእስራኤል ባለስልጣናት ደግሞ የፍልስጤም እስረኞችን ይፈታሉ። የእስራኤል ወታደሮች ደረጃ በደረጃ ከጋዛ ይወጣሉ፣ በግጭቱ የተፈናቀሉ አንዳንድ ፍልስጤማውያንም፣ ለፍልስጤማውያን ሲቪሎች እየጨመረ ከሚመጣው እርዳታ ጋር አብረው እንዲመለሱ ይፈቀድላቸዋል። በዩናይትድ ስቴትስ፣ በግብፅ እና በካታር እየተመራ ለወራት ሲካሄድ የቆየው ድርድር ጦርነቱን ማቆም ባይችልም፣ አሜሪካ የአመራር ለውጥ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ካለችበት ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን ጥረቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን  ኤም ኤስ ኤን ቢሲ ለተባለው የአሜሪካ ቴሌቪዥን ትላንት ሰኞ በሰጡት ቃል ሁለቱ ወገኖች »ስምምነት ላይ ለመድረስ አሁን ከምንጊዜውም ይበልጥ ተቃርበዋል« ብለው  » አሁን ኳሷ ሃማስ ሜዳ ውስጥ ናት" ብለዋል፡፡ የባይደን የብሐራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሰለቫን ትላንት ሰኞ እንደተናገሩት የባይደን አስተዳደር ባለስልጣናት ስለድርድሩ ሂደት በየጊዜው ለተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የመካከለኛ ምሥራቅ አማካሪዎች ገለጻ ሲያደርጉላቸው ቆይተዋል፡፡   የትረምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ በኋለኞቹ የድርድሩ ዙሮች  ተሳትፈዋል።

በደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ 8 የማዕድን ቆፋሪዎች አስክሬን ተገኘ

በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ማውጫ የነፍስ አድን ሠራተኞ ዛሬ ማክሰኞ 8 ተጨማሪ አስክሬኖችን ከጉድጓዱ አውጥተዋል፡፡መውጣት ያልቻሉ ከ400 የሚበልጡ ቆፋሪዎች አሁን
የአሜሪካ ድምፅ

በደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ 8 የማዕድን ቆፋሪዎች አስክሬን ተገኘ

በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ማውጫ የነፍስ አድን ሠራተኞ ዛሬ ማክሰኞ 8 ተጨማሪ አስክሬኖችን ከጉድጓዱ አውጥተዋል፡፡መውጣት ያልቻሉ ከ400 የሚበልጡ ቆፋሪዎች አሁንም ጉድጓዱ ውስጥ እንዳሉ ተነግሯል፡፡ የሞቱት ማዕድን ቆፋሪዎች   ቁጥር 100 መድረሱም ተመልክቷል፡፡ በጎ ፈቃደኛ የነፍስ አድን ሠራተኞች በጉድጓዱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁኔታ እየተከታተሉ ሲሆን ፖሊስ ህገ ወጥ የማዕድን ሠራተኞች ናቸው ያላቸውን ጉድጓዱ ውስጥ ያሉትን ቆፋሪዎች የግዳቸውን ሲወጡ ለማሰር የርዳታ አቅርቦት እንዳይገባላቸው መከልከሉን አስታውቋል፡፡ የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ሞት ለማስቀረት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ለማዕድን ቆፋሪዎቹ የምግብ፣ የውሃ እና የህክምና እርዳታ ያለማቋረጥ እንዲደርስ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። አንድ የሲቪክ ድርጅት ተወካይ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ስለ ሁኔታው ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የድርጅታቸውን በጎ ፈቃደኞች ወደ ማዕድን ማውጫው ልከዋል። የነፍስ አድን ሥራው የቀጠለው ባለፈው ሳምንት፣ «ስቃዩን አልቻልነውም እንደ ዝንብ እየሞትን ነው» በማለት የማዕድን ቆፋሪዎቹ ብጣቂ ወረቀቶች ላይ በጻፏቸው ደብዳቤዎች መማጸናቸውን ተከትሎ ነው።

በሱስ የተጠቁ ወጣቶችን ለማዳን ተጠቃሽ ሚና ያላቸው ማገገሚያ ተቋማት

በኢትዮጵያ በሱስ እና ተያያዥ ችግሮች የሚጠቁ ወጣቶች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ቢኾንም፣ ከሱስ ለማገገም የሚረዱ ተቋማት ግን በስፋት አለመኖራቸውን ባለሞያዎች ይገ
የአሜሪካ ድምፅ

በሱስ የተጠቁ ወጣቶችን ለማዳን ተጠቃሽ ሚና ያላቸው ማገገሚያ ተቋማት

በኢትዮጵያ በሱስ እና ተያያዥ ችግሮች የሚጠቁ ወጣቶች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ቢኾንም፣ ከሱስ ለማገገም የሚረዱ ተቋማት ግን በስፋት አለመኖራቸውን ባለሞያዎች ይገልጻሉ።  ይኹን እንጂ፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሜዲካል ኮሌጅ ሥር የሚገኘው የሱስ ማገገሚያ ማዕከል፣ ለበርካታ ወጣቶች ድጋፍ በማድረግ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ እየረዳ ይገኛል። በተቋሙ ውስጥ ከነበረበት ሱስ ለማገገም መቻሉን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገረ አንድ ወጣትም፣ ለሌሎች ወጣቶች ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።  ወጣቶችን እና የሥነ ልቦና ባለሞያ አነጋግረናል ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

ከታሪክ ማኅደር ፦  በኢትዮጵያ የዛሬ 40 ዓመት ከ400 የሚበልጡ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው አሰቃቂ  የባቡር አደጋ

ከድሬዳዋ  ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ ወደ አዋሽ ከተማ ሲቃረብ  ሐዲዱን ስቶ በመገልበጥ ቁጥሩ ከ418 የሚበልጥ ሕይወት የጠፋበት የባቡር አደጋ የደረሰው 
የአሜሪካ ድምፅ

ከታሪክ ማኅደር ፦  በኢትዮጵያ የዛሬ 40 ዓመት ከ400 የሚበልጡ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው አሰቃቂ  የባቡር አደጋ

ከድሬዳዋ  ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ ወደ አዋሽ ከተማ ሲቃረብ  ሐዲዱን ስቶ በመገልበጥ ቁጥሩ ከ418 የሚበልጥ ሕይወት የጠፋበት የባቡር አደጋ የደረሰው  ከአርባ ዓመታት በፊት በ1977 ዓ.ም. በዛሬው ዕለት ነበር፡፡ የፈረንሳይ እና ኢትዮጵያ የባቡር መስመር ኩባኒያን ጠቅሶ  አሶሲየትድ ፕሬስ በዕለቱ ያስነበበው ዘገባ እንዳተተው በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ 559 ሰዎች ቆስለዋል፡፡ 1 ሺሕ የሚኾኑ መንገደኞችን  በሰባት ፉርጎዎች አሳፍሮ  ይጓዝ የነበረው ባቡር  አዋሽ  ድልድይ ላይ  በፍጥነት እየበረረ ደርሶ ተጠምዝዞ ለማለፍ ሲል ሐዲዱን ስቶ ሸለቆው ውስጥ በመገልበጡ መኾኑን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ የባቡር ኩባኒያውን እና የርዳታ  ባለሥልጣናትን ጠቅሶ አሶሲየትድ ፕሬስ በዕለቱ የወጣው ዘገባ ያትታል፡፡ በወቅቱ የደረሰው አደጋም ፣ ለረሀብ ተጎጂዎች የሚውል አቅርቦት ማጓጓዝ ላይም ከባድ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል አንድ  የኢትዮጵያ መንግሥት መናገራቸውን ዘገባው አያያዞ ጠቅሷል፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን  በአጠቃላይ በአፍሪካ አህጉርም ኾነ በዓለም ላይ  ከደረሱ እጅግ ከባድ እና ዘግናኝ የባቡር አደጋዎች መካከል አንዱ የኾነው ይህ አደጋ  በታሪክ  « የአዋሹ የባቡር  አደጋ» እየተባለ ይታወሳል፡፡

ከ450 በላይ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለጸ

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሱሉላ ፊንጫ ወረዳ በሚገኘው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ፣ ከ450 በላይ ቋሚ እና የኮንትራት ቅጥር ሠራተኞች መታሰራቸውን፣ ቤተሰቦቻቸው እና የፋ
የአሜሪካ ድምፅ

ከ450 በላይ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለጸ

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሱሉላ ፊንጫ ወረዳ በሚገኘው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ፣ ከ450 በላይ ቋሚ እና የኮንትራት ቅጥር ሠራተኞች መታሰራቸውን፣ ቤተሰቦቻቸው እና የፋብሪካው ሠራተኞች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። የሱሉላ ፊንጫ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ፋንታሁን ታዬ፣ ሠራተኞቹ የታሰሩት «በፋብሪካው ይዞታ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የግብርና ሥራ ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው ነው፤» ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ፣ ከፊንጫ ስኳር ፋብሪካ አስተዳደር እና ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።    

የካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት ከቁጥጥር ውጪ ኾኖ ሊባባስ ይችላል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ትንበያዎች አስጠነቀቁ

በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ግዛት ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰው ያለውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ባሉበት ወቅት፣ እንደአዲ
የአሜሪካ ድምፅ

የካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት ከቁጥጥር ውጪ ኾኖ ሊባባስ ይችላል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ትንበያዎች አስጠነቀቁ

በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ግዛት ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰው ያለውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ባሉበት ወቅት፣ እንደአዲስ ሊባባስ ይችላል ተብሎ የተሰጋው ጠንካራ ንፋስ እሳቱን ሊያባብሰው እና ከቁጥጥር ውጪ ሊያደርገው ይችላል ሲሉ የትንበያ ባለሞያዎች አስጠንቅቀዋል። የአሜሪካ ብሔራዊ የአየር ትንበያ አገልግሎት በአወጣው ማስጠንቀቂያ፣ ነገ ማክሰኞ ሊጨምር ይችላል ተብሎ የተሰጋው ጠንካራ ንፋስ በሰዓት ከ80 እስከ 110 ኪሎሜትር ሊጓዝ ይችላል ብሏል። ከስምንት ወራት በላይ በቂ ዝናብ ሳይገኝ በቆየው አካባቢ የሚገኘው ደረቅ የአየር ሁኔታ እና ጠንካራ ንፋስ፣ ሰደድ እሳቱ እንዲባባስ ምክንያት ኾኗል። ለአንድ ሳምንት በዘለቀው እሳት እስካሁን የ24 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲኾን፣ በቢሊየኖች የሚቆጠር ንብረትም አውድሟል። ከሟቾቹ መካከል ስምንቱ በፓሲፊክ ፓሊሳዴስ አካባቢ በተዛመተው እሳት የሞቱ መሆናቸውን ባለስልጣናት ያስታወቁ ሲሆን ከ12 ሺህ በላይ ቤቶች እና ህንፃዎች ወድመዋል። እስከ ትላንት እሁድ ምሽት ድረስ 100 ሺህ ሰዎች ከአካባቢያቸው ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ሲሆን፣ አዲስ ንፋስ ሊነሳ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መውጣቱን ተከትሎ ነዋሪዎቹ ወደ መኖሪያቸው መመለስ እንደማችሉ ተመልክቷል። እሳቱ እየተስፋፋ መሄድ መቀጠሉን ተከትሎም፣ የአካባቢው ባለስልጣናት፣ ሕዝብ በብዛት የሚኖርባቸውን አካባቢዎች እና እንደ ፖውል ጌቲ ሙዚየም እና ታዋቂ ከሆኑ የአሜሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ የሆነው የካሊፎርኒያ ዩንቨርስቲን የመሳሰሉ፣ የከተማዋን ቁልፍ ምልክቶች ሊያወድም ይችላል የሚል ስጋታቸውን እየገለፁ ነው። እስካሁን በተደረጉ ቅድመ ጥናቶች መሠረት፣ እሳቱ በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት እና የኢኮኖሚ ኪሳራ ከ130 እስከ 150 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። የካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪ ጋቪን ኒውሶም ከኤን ቢ ሲ የቴሌቭዥን ጣቢያ ጋራ ባደረጉት ቃለምልልስ እሳቱ እንዴት ሊነሳ እንደቻለ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቀዋል።   

ለጋዛ የእርቅ ስምምነት ማምጣት ይችላል የተባለ የመጨረሻ ረቂቅ ሐሳብ ለሁለቱም ወገኖች ቀረበ

በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም፣ አሸማጋዮች የመጨረሻ ያሉትን የእርቅ ስምምነት ረቂቅ ሐሳብ ለእስራኤል እና ለሐማስ ማቅረባቸውን፣ በድርድሩ ዙሪያ ማብ
የአሜሪካ ድምፅ

ለጋዛ የእርቅ ስምምነት ማምጣት ይችላል የተባለ የመጨረሻ ረቂቅ ሐሳብ ለሁለቱም ወገኖች ቀረበ

በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም፣ አሸማጋዮች የመጨረሻ ያሉትን የእርቅ ስምምነት ረቂቅ ሐሳብ ለእስራኤል እና ለሐማስ ማቅረባቸውን፣ በድርድሩ ዙሪያ ማብራሪያ የቀረበላቸው አንድ ባለሥልጣን አስታወቁ። በድርድሩ ላይ የጆ ባይደን እና የዶናልድ ትራምፕ ልዑካን መገኘታቸውንም አመልክተዋል። ባለሥልጣኑ እንደተናገሩት፣ የተኩስ ማቆምን እና የታጋቾችን መለቀቅ በሚመለከት ኳታር ያቀረበችው ረቂቅ የስምምነት ጹሑፍ ዶሃ ውስጥ በተደረገ ውይይት ላይ ለሁለቱም ወገኖች የቀረበ ሲሆን፣ የእስራኤል 'ሞሳድ' እና 'ሺን ቤት' የተሰኙት የስለላ ተቋማት እንዲሁም የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር በቦታው መገኘታቸውም ተመልክቷል። በመጪው ሳምንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን ሲመለሱ የዩናይትድ ስቴትስ ልዑክ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ስቲቭ ዊትኮፍም ድርድሩ ላይ መገኘታቸውን ባለሥልጣኑ ጨምረው ገልጸዋል። በተጨማሪም፣ የተሰናባቹ ባይደን አስተዳደር ልዑክ ብሬት ማክጉርክ በድርድሩ መሳተፋቸውን አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ምንጭ ለሮይተርስ ተናግረዋል። «ስምምነት ላይ ለመድረስ መጪዎቹ 24 ሰዓታት ወሳኝ ናቸው» ያሉት ባለሥልጣኑ ረቂቁ ዛሬ ሰኞ ባለቀ ሰዓት የተገኘ ውጤት መሆኑን አመልክተዋል። የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችል ድርድር ለማካሄድ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ኳታር እና ግብፅ ከአንድ ዓመት በላይ ሲሠሩ ቢቆዩም እስካሁን ውጤት ማግኘት አልቻሉም። 

በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ እስላማዊ ታጣቂዎች ቢያንስ 40 ገበሬዎችን መግደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ

በሰሜናዊ ምስራቅ ናይጄሪያ፣ ቦርኖ ግዛት ውስጥ እስላማዊ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት፣ ቢያንስ 40 ገበሬዎች መግደላቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ዛሬ ሰኞ አስታ
የአሜሪካ ድምፅ

በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ እስላማዊ ታጣቂዎች ቢያንስ 40 ገበሬዎችን መግደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ

በሰሜናዊ ምስራቅ ናይጄሪያ፣ ቦርኖ ግዛት ውስጥ እስላማዊ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት፣ ቢያንስ 40 ገበሬዎች መግደላቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ዛሬ ሰኞ አስታወቁ። ጥቃቱ የተፈፀመው እሑድ ዕለት ሲሆን፣ ለጥቃቱ የቦኮ ሃራም ቡድን እና ከቡድኑ ተገንጥሎ የወጣ እና በቦርኖ ግዛት የሚንቀሳቀስ ለእስላማዊ መንግሥት ታማኝ መኾኑ የተገለፀ ቡድን ተጠያቂ መደረጋቸውን የቦርኖ ግዛት አስተዳዳሪ የሆኑት ባባጋና ኡማርራ ዙሉም ተናግረዋል። አስተዳዳሪው አክለው፣ ሲቪሎች «ደኅንነታቸው የተጠበቁ ዞኖች» ተብለው ከጠቀሷቸው እና የጦር አባላት ከፅንፈኞች እና ከተቀበሩ ፈንጂዎች እንዳፀዷቸው ከገልጿቸው አካባቢዎች እንዳያልፉ አስጠንቅቀዋል። አክለውም ታጣቂዎቹ ያደረሱት ጥቃት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቀዋል። በናይጄሪያ የተመሰረተው ቦኮ ሃራም፣ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ምዕራባዊ የትምህርት አሰጣጥን ለመዋጋት እና አክራሪ እስላማዊ ሕግን ለመጫን የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ ቆይቷል። አፍሪካ ከታጣቂዎች ጋራ ካደረገቻቸው ትግሎች ረጅሙን ጊዜ መፍጀቱ የተገለጸው ግጭትም፣ ከናይጄሪያ አልፎ በስተሰሜን የሚገኙ የጎረቤት ሀገራትም ተስፋፍቷል። ታጣቂዎቹ እስካሁን ባደረሷቸው ጥቃቶች ቢያንስ 35 ሺሕ ንፁሃን ዜጎች የተገደሉ ሲኾን፣ በሰሜን ምስራቃዊ የናይጄሪያ አካባቢ የሚኖሩ ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል።    

Get more results via ClueGoal