ሩቢዮ ቀጣዩ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኾኑ
newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትላንት ሰኞ ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ ቀጣዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኾነው እንዲያገለግሉ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። በዚህምሩቢዮ ቀጣዩ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኾኑ
የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትላንት ሰኞ ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ ቀጣዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኾነው እንዲያገለግሉ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። በዚህም ሩብዮ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመታቸው በምክር ቤቱ የጸደቀላቸው የመጀመሪያው የአዲሱ ካቢኔ አባል ኾነዋል። ከፍሎሪዳ ክፍለ ግዛት የሆኑት የሪፐብሊካን ሴናተር ሩቢዮ ከትራምፕ እጩዎች መካከል እምብዛም ውዝግብ የማይነሳባቸው ሲሆኑ 99 ለዜሮ በሆነ ወሳኝ ድምጽ ነው የተመረጡት። «ማርኮ ሩቢዮ ስለ አሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ጥልቅ ግንዛቤ ያላቸው እጅግ አስተዋይ ሰው ናቸው» ሲሉ በምክር ቤቱ ከፍተኛው የሪፐብሊካን አባል የአይዋው ሴናተር ቸክ ግራስሌ በምክር ቤቱ መክፈቻ ባሰሙት ንግግራቸው አመልክተዋል። ሌላው የትራምፕ እጩ የዩናይትድ ስቴትስን የደኅንነት መሥሪያ ቤት እንዲመሩ የተመረጡት ጆን ራትክሊፍ ሹመታቸው በፍጥነት ይጸድቃል ተብሎ ከሚጠበቁ ዕጩዎች ውስጥ ናቸው። ለመከላከያ ሚንስትርነት የታጩትን የቀድሞውን የፎክስ ኒውስ ቴሌቭዥን ፕሮግራም አቅራቢ ፒት ሄግሰትን ጨምሮ የሌሎች እጩዎች ሹመት የማጽደቅ ሂደት በሳምንቱ መገባደጂያ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። የዩናይትድ ስቴትሱ እንደራሴዎች ምክር ቤት በተለመደ አሠራሩ የፕሬዝዳንታዊው በዓለ ሲመት ሥነ ስርዐት እንደተጠናቀቀ ፈጥኖ የአዲሱን ፕሬዝዳንት ካቢኔ በተለይም የብሔራዊ ደኅንነት ባለሥልጣናት እጩዎች ሥራቸውን እንዲጀምሩ ያደርጋል። Read more