Ethiopia



በኒው ዮርክ ከተማ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አድርጎ መዘዋወር ይከልከል የሚለው ጥያቄ ጭቅጭቅ አስነስቷል

በዩናይትድ ስቴትስ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ «የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ) አድርጎ መዘዋወር ይከልከል» በሚል የተነሳው ጥያቄ ጭቅጭቅ አምጥቷ

ስጋት ላይ የወደቀው የእናቶች እና የሴቶች ጤና አገልግሎት አቅርቦት

የዋይት ኃውስ ድረ ገጽ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመላከተው፤ በጎርጎርሳውያኑ 2022 ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ 11.5 ቢሊየን ዶላር ለኤች አይቪ ኤድስ ድጋፍ፤ እን
የአሜሪካ ድምፅ

ስጋት ላይ የወደቀው የእናቶች እና የሴቶች ጤና አገልግሎት አቅርቦት

የዋይት ኃውስ ድረ ገጽ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመላከተው፤ በጎርጎርሳውያኑ 2022 ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ 11.5 ቢሊየን ዶላር ለኤች አይቪ ኤድስ ድጋፍ፤ እንዲሁም ሁለት ቢሊየን ዶላር ደግሞ ለቤተሰብ ምጣኔና፣ ለስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት አቅርቦቶች፣ የእናቶች እና ጨቅላ ህጻናት ጤና ላይ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቋል። ይሁን እንጂ ይህ አቅርቦት የ47ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ሆነው ወደ ሥልጣን በተመለሱት ዶናልድ ትራምፕ በሀገር ውስጥ ሮ እና ዌድ ተብሎ በሚጠራው የጽንስ ማቋረጥን ከሚከለክለው መብት ጋር ተያይዞ ያላቸው አቋም የተነሳ የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት በሚሰጡ አለም አቀፍ አጋሮቻቸውን ለስጋት ዳርጓል። ፕሬዝዳንቱ ወደ ሥልጣን በመጡ ዕለት ሀገራቸው ከአለም የጤና ተቋም ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጣቸው ዩናይትድ ስቴትስ ከስነ ተዋልዶ ጤና ጋር የሚኖራት አቋም እንደሚያጠራጥር ባለሞያው ይገልጻሉ፡፡ https://amharic.voanews.com/a/voa-amharic-global-gag-rule-uncertainty-in-african-reporductive-health-care-/7949538.html በኢትዮጵያ የማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር ዶ/ር አበበ ሽብሩ የስነ ተዋልዶ ጤና ድጋፍ መቋረጥ በጽንስ ማቋረጥ ብቻ ሳይሆን፤ ይህን አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት በሚያደርጓቸው በኤች አይ ቪ ኤድስ መድሃኒት ተደራሽነት ላይ ጭምር ጫና ያሳድራል ይላሉ። በሌላ በኩል ገርማቸር ተቋም ከፍተኛ የስነተዋልዶ ጤና ሳይንስ ተመራማሪ. የሆኑት ኤሊዛቤት ሱሊ በአለም ዙሪያ ያሉ የዩናይትድ ስቴትስን ድጋፍ የሚቀበሉ ሀገራት እና የጤና ሚንስትሮች፤ በትራምፕ አስተዳደር ሊከሰት ለሚችል የስነ ተዋልዶ ጤና ድጋፍ መስተጓጎል እንዲዘጋጁ ይመክራሉ። በተጨማሪም ወሲባዊ እና የስነ ተዋልዶ መብቶችን በመቃወም የሚታወቁት የዩናይትድ ስቴትስ የክርስቲያን መብት ቡድኖች ከጎሮጎሳውያኑ 2019 ጀምሮ በአፍሪካ ያላቸውን ድጋፍ እና እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸውን፤ የጋዜጠኝነት እና ማህበራዊ ለውጥ ኢንስቲትዩት (IJSC) አዲስ የመረጃ ትንተና አመልክቷል። አለም አቀፉ ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎትን እንደማያቋርጥ እና ይህን ተክትሎ ሊቋረጡ ለሚችሉ ድጋፎች እየተዘጋጀ መሆኑን የተቋሙ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶ/ር አበበ ሽብሩ ገልጸዋል።  

ትረምፕ ሩሲያ የዩክሬይኑን ጦርነት እንድታቆም ብርቱ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው

ከጥቂት ቀናት በፊት አስተዳደሩን ተረክበው ሥራቸውን የጀመሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሩሲያ ከዩክሬይን ጋራ የሰላም ንግግር እንድትጀ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ ሩሲያ የዩክሬይኑን ጦርነት እንድታቆም ብርቱ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው

ከጥቂት ቀናት በፊት አስተዳደሩን ተረክበው ሥራቸውን የጀመሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሩሲያ ከዩክሬይን ጋራ የሰላም ንግግር እንድትጀምር ግፊታቸውን በማጠናከር ላይ ናቸው። «የሰላም ንግግር አላደርግም ብትል ዩናይትድ ስቴትስ አዳዲስ ማዕቀቦች እና ታሪፎች ትጥልባታለች» በማለት ትረምፕ ያሰሙትን ዛቻ ሩሲያ አጣጥላዋለች። የአሜሪካ ድምጿ ቬሮኒካ ባልዴራስ ኢግሊሲያስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሁቲ አማጺያን ያገቷቸውን 25 የመርከብ ሠራተኞች ለቀቁ

በየመን የሁቲ አማጺያን በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘር በጀመሩበት ወቅት፣ ባለፈው ኅዳር ያገቷቸውን የአንድ መኪና ጫኝ መርከብ 25 ሠ
የአሜሪካ ድምፅ

የሁቲ አማጺያን ያገቷቸውን 25 የመርከብ ሠራተኞች ለቀቁ

በየመን የሁቲ አማጺያን በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘር በጀመሩበት ወቅት፣ ባለፈው ኅዳር ያገቷቸውን የአንድ መኪና ጫኝ መርከብ 25 ሠራተኞች ለቀዋል። በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የሁቲ አማጺያን በጋዛ ተኩስ አቁም ከተጀመረ ወዲህ ውጥረቱን ለማርገብ ያደረጉት ጥረት አካል እንደሆነ ተነግሯል። ነገር ግን ፕሬዝደንት ትረምፕ፣ በፕሬዝደንት ጆ ባይደን የተሰረዘውን የሽብርተኝነት ፍረጃ መልሶ እንዲፀና በማድረጋቸው አዲስ ውጥረት እንደይከሰት ተሰግቷል። ታጋቾቹን የለቀቁት ኦማን ባደረገችው ሽምግልና ምክንያት መሆኑን የሁቲ አማጺያን አስታውቀዋል። ኦማን ከሁቲዎች ጋራ የሚደረግን ድርድር ስትሸመግል ቆይታለች፡፡ አንድ የኦማን አየር ኃይል አውሮፕላን ታጋቾቹን ከየመን ማውጣቱም ታውቋል። በተጨማሪም 25 የሚሆኑት የመርከቡ ዓባላት እንዲለቀቁ ከሐማስ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦ እንደነበር ሁቲዎቹ አስታውቀዋል። የመርከቡ ዓባላት ከፊሊፒንስ፣ ቡልጋሪያ፣ ሮማኒያ፣ ዩክሬን እና ሜክሲኮ የተውጣጡ መሆናቸውም ተመልክቷል። “እርምጃው የተወሰደው በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ስምምነት ላይ መደረሱን ለመደገፍ ነው”  ሲሉ አማጺያኑ በሚቆጣጠሩት ሳባ የዜና አገልግሎት በኩል ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የፊሊፒንሱ ፕሬዝደንት ፈርዲናንድ ማርቆስ ሁለተኛ፣ 17 የሃገሪቱ ዜጎች መለቀቃቸውን አስታውቀዋል። የቡልጋሪያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርም ሁለት ዜጎቹ እንደተለቀቁ አስታውቋል። በተመድ የየመን ልዩ ልዑክ የሆኑት ሃንስ ግረንድበርግ፣ በዘፈቀደ የታገቱ ሰዎችን ሰቆቃ ያስቆመ ነው ያሉትን እርንምጃ በመልካም ተቀብለዋል።

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ 400 ሺሕ ሰዎች ተፈናቀሉ

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ባለው ሁከት ምክንያት 400ሺሕ ሰዎች ተፈናቅለዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዛሬ ዓርብ አስታውቋል። በሩዋንዳ እንደሚደገ
የአሜሪካ ድምፅ

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ 400 ሺሕ ሰዎች ተፈናቀሉ

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ባለው ሁከት ምክንያት 400ሺሕ ሰዎች ተፈናቅለዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዛሬ ዓርብ አስታውቋል። በሩዋንዳ እንደሚደገፍ የሚነገረውና ኤም 23 የተሰኘው ቡድን ከኮንጎ ሠራዊት ጋራ በመፋለም ላይ ሲሆን፣ የሃገሪቱ የሰሜን ኪቩ ግዛት መዲና በሆነችው ጎማ አካባቢ ያለውን ቁጥጥር በማጥበቅ ላይ መሆኑ ተነግሯል። በምሥራቅ የሃገሪቱ ክፍል የሚገኙ ሲቪሎችና የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሁኔታ እንደሚያሳስበው የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በተጨማሪም ሁሉም ወገኖች ሲቪሎችን ከአደጋ እንዲጠብቁ፣ የተፈናቃይ መጠለያዎችን እንዲያከብሩ እንዲሁም ሲቪሎች በብዛት በተሰባሰቡባቸው አካባቢዎች ከባድ መሣሪያ ከመጠቀም እንዲቆጠቡ አሳስቧል። አዲስ በተያዘው የፈርንጆች ዓመት ብቻ እስከ አሁን 400 የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ይህም ባለፈው ሳምንት ሪፖርት ከተረገው ቁጥር እጥፍ የጨመረ መሆኑን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ማቲው ሳልትማርሽ አስታውቀዋል። ለሃገሪቱ ሕዝብና ለቀጠናው ሲባል የተራዘመው ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝም ጥሪ አስተላልፈዋል። በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ያለው ቀውስ የተረሳ መሆኑንና ለሃገሪቱ ከተጠየቀው የገንዘብ ድጋፍ ውስጥ እስከ አሁን የተገኘው 10 በመቶ ብቻ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።  

ስደተኞችን ለመያዝ በተደረገ ዘመቻ ዜጎችና አንድ የአሜሪካ የቀድሞ ወታደር ተያዙ

በአሜሪካ ኒው ጀርሲ ግዛት፣ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ የስደተኞች እና የጉምሩክ ኅይል (አይስ) ባደረገው አፈሳ የመኖሪያ ፈቃድ ከሌላቸው ግለሰቦች በተጨማሪ አንድ
የአሜሪካ ድምፅ

ስደተኞችን ለመያዝ በተደረገ ዘመቻ ዜጎችና አንድ የአሜሪካ የቀድሞ ወታደር ተያዙ

በአሜሪካ ኒው ጀርሲ ግዛት፣ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ የስደተኞች እና የጉምሩክ ኅይል (አይስ) ባደረገው አፈሳ የመኖሪያ ፈቃድ ከሌላቸው ግለሰቦች በተጨማሪ አንድ የቀድሞ ወታደርን ጨምሮ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ነዋሪዎች መያዙን የከተማዋ ከንቲባ አስታውቀዋል። ከኒው ዮርክ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ኑወርክ ከተማ ስደተኞችን የሚቀበል ፖሊሲ ስታራምድ የቆይች ሲሆን፣ ባለፈው ሰኞ ወደ ሥልጣን ተመልሰው የመጡት ዶናልድ ትረምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞች ተይዘው ከሃገሪቱ እንዲወጡ በሰጡት ትዕዛዝ መሠረት የፊዴራል ኅይሎች በከተማዋ በሚገኙ የሥራና የንግድ ሥፍራዎች አሰሳ አካሂደዋል። ትረምፕ በሰጡት ፕሬዝደንታዊ ትዕዛዝ፣ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ለመያዝ የሚደረገውን ጥረት ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ባለሥልጣናትን እንደሚቀጡ አስታውቀዋል። በኑወርክ በተካሄደው አፈሳ የፌዴራል ኅይሎች የመያዢያ ትዕዛዝ እንዳሊያዙ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል። በዘመቻው የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ብቻ ሳይሆን፣ ዜጎችንም መያዛቸው ታውቋል። “ከተያዙት አንዱ የአሜሪካ የቀድሞ ወታደር ሲሆን፣ ያቀረበውን ወታደራዊ ሰነዶች የፌዴራል ኅይሎች በጥርጣሬ በማየታቸው ክብሩ ተነክቷል” ሲሉ የከተማዋ ከንቲባ የሆኑት ራስ ባራካ ተናግረዋል። የአይስ ቃል አቀባይ በአወጣው መግለጫ፣ ኅይሎቹ አሰሳ በሚያደርጉበት ወቅት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ሊያጋጥሟቸው እንደሚችል አመልክቶ፣ ያላቸውን ሰንድ እንዲያቀርቡ ሊጠይቁ እንደሚችሉ፣ በኑወርክ ያጋጠመውም ይህ ሊሆን እንደሚችል አመልክቷል። አይስ ሁኔታውን እየመረመረ እንደሆነም የቃል አቀባዩ መግለጫ ጨምሮ አመልክቷል። “አፈሳው የአሜሪካ ሕገ መንግሥትን የሚጥስ ነው” ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል። “ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ሽብር ሲፈፀምባቸው ኑወርክ ዝም ብላ አትመለከትም” ሲሉም አክለዋል። የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ካሮላይን ለቪት በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ እንዳስታወቁት፣ የትረምፕ አስተዳደር ትላንት ሐሙስ 538 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማድረጉንና “ሁሉም ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችና ወንጀለኞች ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል። ስደተኞች አሜሪካ ከተወለዱት ዜጎች በላይ ወንጀል እንደማያፈጽሙ በርካታ የምሁራን እና ሌሎች የምርምር ተቋማት ጥናቶች እንደሚያመለክቱ የሮይተርስ ዘገባ ጠቁሟል።

ትረምፕ በሰደድ እሳት እና በአውሎ ነፋስ የተጠቁ ግዛቶችን ሊጎበኙ ነው

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በአሜሪካ በሰደድ እሳትና አደገኛ አውሎ ነፋስ የተጠቁ አካባቢዎችን ነገ ዓርብ እንደሚጎበኙ ታውቋል። ፕሬዝደንቱ በአውሎ ነፋስ ኼሊ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ በሰደድ እሳት እና በአውሎ ነፋስ የተጠቁ ግዛቶችን ሊጎበኙ ነው

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በአሜሪካ በሰደድ እሳትና አደገኛ አውሎ ነፋስ የተጠቁ አካባቢዎችን ነገ ዓርብ እንደሚጎበኙ ታውቋል። ፕሬዝደንቱ በአውሎ ነፋስ ኼሊን የተጠቃችውን የሰሜን ካሮላይና እንዲሁም የሰደድ እሳት በቀጠለባት ካልፎርኒያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ታውቋል። አንድ መቶ ሺሕ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ በተላለፈባት ካልፎርኒያ አዲስ እሳት መቀስቀሱም ታውቋል። ጄንያ ዱሉ ከሎስ ኤንጀለስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ትረምፕ የፓናማ ቦይን ለመቆጣጠር ግፊት እያደረጉ ባሉበት ሩቢዮ ወደ መካከለኛው አሜሪካ ሊያቀኑ ነው

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የፓናማ ቦይን ለመቆጣጠር ግፊት እያደረጉ ባሉበት እና ዋሽንግተን ሕገ-ወጥ ስደትን ለመግታት ጥረት በያዘችበት በአሁኑ ወቅት አዲሱ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ የፓናማ ቦይን ለመቆጣጠር ግፊት እያደረጉ ባሉበት ሩቢዮ ወደ መካከለኛው አሜሪካ ሊያቀኑ ነው

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የፓናማ ቦይን ለመቆጣጠር ግፊት እያደረጉ ባሉበት እና ዋሽንግተን ሕገ-ወጥ ስደትን ለመግታት ጥረት በያዘችበት በአሁኑ ወቅት አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ፓናማን እና በመካከለኛው አሜሪካ የሚገኙ ሌሎች ሃገራትን ሊጎበኙ ነው። ጉዞው የሩቢዮ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ከሆኑ በኋላ የመጀመሪያው የውጭ አገር ጉብኝታቸው ነው። ‘ፖለቲኮ’ የተባለው የዩናይትድ ስቴትስ የዜና ወኪል እንደዘገበው የሩቢዮ ጉዞ ፓናማን፣ ጓቲማላን፣ ኤልሳልቫዶርን፣ ኮስታሪካን እና ዶሚኒካን ሪፑብሊክን ያካትታል። በአንጻሩ ጉዳዩን አስመልክቶ የተጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት “በአሁኑ ወቅት ይፋ የምናደርገው ጉዞ የለም” ሲሉ መልሰዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዝዳንት ትረምፕ የፓናማ ቦይን በዩናይትድ ስቴትስ ቁጥጥር ስር ለማድረግ የያዙትን አላማ ለማሳካት የወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች አማራጭነት ውድቅ አለማድረጋቸውን ተናግረዋል። ሩቢዮ ወደ አሜሪካ የሚገቡት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች ማስቆምን ጨምሮ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን የውጭ ፖሊሲ ዕቅዶች በሳምንት መጀመሪያ ላይ ይፋ አድርገው ነበር።

የአርበኞች መካነ መቃብር እንዲሆን የታጸነው ጥንታዊው ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል

የአርበኞች መካነ መቃብር እንዲኾን የታጸነው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እድሳት ማክሰኞ ጥር 6 ቀን 2017 ተጠናቆ ሕንጻው ተመርቋል። ከ1924 ዓ.ም ጀምሮ ግንባታው መጀመ
የአሜሪካ ድምፅ

የአርበኞች መካነ መቃብር እንዲሆን የታጸነው ጥንታዊው ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል

የአርበኞች መካነ መቃብር እንዲኾን የታጸነው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እድሳት ማክሰኞ ጥር 6 ቀን 2017 ተጠናቆ ሕንጻው ተመርቋል። ከ1924 ዓ.ም ጀምሮ ግንባታው መጀመሩን በካቴድራሉ ድረ ገጽ ላይ የሰፈረው ጹሑፍ ያስረዳል።  “አስደናቂ የኪነ - ሕንጻ ንድፍ” እንዳለው የሚነገረው ሕንጻ የመጀመሪያው መሰረተ ድንጋይ የተጣለውም በቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉሠ ቀዳማዊ ዐጼ ኃይለ ሥላሴ የንግስና ዘመን  ነው። ግንባታው ሳይጠናቀቅ ኢትዮጵያ በጣሊያን በመወረሯ፣ ከ1928 ዓ.ም እስከ 1933 ዓ.ም. ድረስ ለአምስት ዓመታት ግንባታው ተቋርጦ መቆየቱን ጹሑፍ ያስረዳል፡፡ ጣሊያን በጦርነቱ ተሸንፎ ከኢትዮጵያ ከወጣ እና ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ከሁለት ዓመት በኋላ ግንባታው ተጠናቆ ከ81 ዓመት በፊት ጥር 7 ቀን 1936 ዓ.ም መመረቁን ለታሪክ በተቀመጠው ሰነድ ላይ ሰፍሯል። ካቴድራሉ ከተመረቀ ከ81 ዓመታት በኋላ ከሁለት ዓመት በላይ የፈጀ ዕድሳት ተደርጎለታል። አብዛኛው የእድሳቱ ሥራም ተጠናቆ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና በብፁአን አባቶች ተመርቆ ታቦተ ሕጉ ወደ መቅደሱ ተመልሶ ገብቷል። እድሳቱ 200 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ገዘብ ቫርኔሮ ኮንስትራክሽን በተባለ ተቋራጭ መከናወኑን የካቴድራሉ ዋና ጸሐፊ ላዕከ-ሰላም ሽታው ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡ የካቴድራሉ ዋና ጸሐፊ፣ ላዕከ-ሰላም ሽታው ብርሃኑ፣ በወቅቱ በነበሩት የኢትዮጵያ መሪ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በወቅቱ በአስተላለፉት ውሳኔ፣ ለሀገራቸው ነጻነት ሲታገሉ ሕይወታቸውን ያጡ አርበኞች አርበኞች መካነ ዕረፍታቸው በዚሁ ካቴድራል እንዲኾን መደረጉ ተናግረዋል። በተጨማሪም፣ ኢትዮጵያን እስከ ሀገር መሪነት ያገለገሉትን ጨምሮ በተለያዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶች ላይ የነበሩ ፣ቤተ ክህነትንም በከፍተኛ ኃላፊነት የመሩ የሃይማኖት አባቶች መካነ መቃብራቸው የሚገኘው በካቴድራሉ ውስጥ መኾኑን አክለው ገልጸዋል። ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን እና ባለቤታቸውን እንዲሁም የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ በተለያየ ኃላፊነት ያገለገሉ መሪዎች እና የነጻነት ታጋዮች፣ የተለያዩ የቤተክርስቲያኗ ፓትሪያርኮች መካነ ዕረፍታቸው በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መሆኑን የካቴድራሉ ኃላፊዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል። ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር ጉልህ ታሪካዊ ትርጉም ያለው እና ከኪነ-ሕንጻው ጀምሮ በውስጡ በርካታ ቅርሶችን የያዘው ካቴድራሉ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው መኾኑንም አስረድተዋል፡፡ ቤተ ክርስትያኗ የራሷን ፓትርያርክ መሾም ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ የቅዱሳን ፓትርያርኮችና የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሹመት እና በዓለ ሲመት የሚፈጸመው በካቴድራሉ ነው፡፡ በዚህ ካቴድራል ውስጥ በተለያዩ ክፍሎች የተሳሉት ብሥዕሎች፣ ስለነፃነት የተደረጉ ታሪካዊ ሂደቶችን በማመላከት የታሪክ አሻራነታቸውን ለትውልድ በማስተላለፍ ላይ አንደሚገኙም ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል፡፡

ትራምፕ የየመኑን ሁቲዎችን በውጭ አሸባሪ ድርጅትነት ፈረጁ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ረቡዕ በወሰዱት ርምጃ፣ በመደበኛ ሥያሜያቸው ‘አንሳር አላህ’ በሚል መጠሪያ የሚታወቁትን የየመኑን ሁ
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ የየመኑን ሁቲዎችን በውጭ አሸባሪ ድርጅትነት ፈረጁ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ረቡዕ በወሰዱት ርምጃ፣ በመደበኛ ሥያሜያቸው ‘አንሳር አላህ’ በሚል መጠሪያ የሚታወቁትን የየመኑን ሁቲዎች በውጭ አሸባሪ ድርጅትነት እንዲፈረጁ ማዘዛቸውን ዋይት ሀውስ አስታወቀ። ርምጃው በኢራን የሚደገፈው ቡድን በቀይ ባህር በሚተላለፉ የንግድ መርከቦች እና ወሳኝ ለሆኑት የባህር ኬላዎች ከለላ እና ጥበቃ በሚያደርጉ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር መርከቦች ላይ ለሚያደርሷቸው ተደጋጋሚ ጥቃቶች የባይደን አስተዳደር ወስዶት ከነበረው ምላሽ የበረቱ የኢኮኖሚ ገደቦችን የሚጥል መሆኑ ተመልክቷል። ዋይት ሀውስ በመግለጫው አክሎም "የሁቲዎች እንቅስቃሴ በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ በአሜሪካውያን ሲቪሎች እና ሠራተኞች ደኅንነት፣ በክልሉ የሚገኙ የቅርብ አጋሮቻችን እና ብሎም ዓለም አቀፍ የባህር ንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ አደጋ የደቀነ ነው” ብሏል። ‘ርምጃውን የሚደግፉ ወገኖች እስካሁንም መደረግ የነበረበት ነው’ ሲሉ፤ የጉዳዩ አዋቂዎች በበኩላቸው የርዳታ ድርጅቶችን ጨምሮ ሁቲዎችን ከመደገፍ የሚቆጠር ሥራ የሠራ ማንኛውንም ወገን ለቅጣት ሊዳርግ የሚችል ነው ይላሉ። አብዛኛውን የመን ግዛቶች የሚቆጣጠሩት ሁቲዎች እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከኅዳር 2023 ዓ.ም አንስቶ እስራኤል ጋዛ ውስጥ ከሃማስ ጋራ እያደረገች በነበረው ጦርነት ከፍልስጤማውያን ጋራ በማበር ቀይ ባህር ላይ በሚጓጓዙ መርከቦች ላይ ከ100 በላይ ጥቃቶች አድርሰዋል። በጥቃቶቹም ሁለት መርከቦችን ሲያሰጥሙ፣ አንዲት መርከብ በመያዝ፤ አራት መርከበኞችን ገድለዋል። በተጨማሪም በጥቃቱ ዓለም አቀፍ የመርከብ ጉዞዎችን በማስተጓጎል የንግድ ድርጅቶች ለአንድ ዓመት ያህል ጥቃቶቹን ለመሸሽ በደቡባዊ አፍሪካ ዞረው ረዥም እና ከፍ ያለ ዋጋ የሚያስከፍሉ ጉዞዎችን እንዲያደርጉ አስገድደው እንደ ነበር ይታወቃል።

ትራምፕ ስርዐተ-ፆታን አስመልክቶ የፈረሙት ፕሬዝዳንታዊ ትእዛዝ አፍሪካ ውስጥ የተለያየ ምላሾች እየቀረቡበት ነው

በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ያሉ ጠበቅ ያለ ወግ የሚያራምዱ ወገኖች የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሥርዓተ ፆታን እና ብዝሃነትን አስመልክቶ የፈ
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ ስርዐተ-ፆታን አስመልክቶ የፈረሙት ፕሬዝዳንታዊ ትእዛዝ አፍሪካ ውስጥ የተለያየ ምላሾች እየቀረቡበት ነው

በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ያሉ ጠበቅ ያለ ወግ የሚያራምዱ ወገኖች የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሥርዓተ ፆታን እና ብዝሃነትን አስመልክቶ የፈረሙትን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ሲያደንቁ፤ በአህጉሪቱ ውስጥ ያሉ የተመሳሳይ ጾታ መብት ተሟጋቾች እና የማህበረሰብ አባላት በበኩላቸው ከፍተኛ ስጋት እንዳሳደረባቸው እየገለጹ ነው። ቲሞቲ ኦቢዙ ከናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃ ያደረሰንን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

አፍሪካውያን ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያስተላለፉት መልዕክት

ኬንያ፣ ሲማሊያ እና ናይጄሪያ ጎዳናዎች ላይ ያገኘናቸው ነዋሪዎች፣ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መልዕክት አስተላልፈዋል። አስተያየታቸው
የአሜሪካ ድምፅ

አፍሪካውያን ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያስተላለፉት መልዕክት

ኬንያ፣ ሲማሊያ እና ናይጄሪያ ጎዳናዎች ላይ ያገኘናቸው ነዋሪዎች፣ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መልዕክት አስተላልፈዋል። አስተያየታቸውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የላቀ ውጤት ያስመዘገቡት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች

የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርትን አጠናቆ ከፍተኛ የኮሌጅ መግቢያ ነጥብ ማግኘት ለብዙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በከፍተኛ ስኬት የሚታይ ነው። በዘንድሮው ዓመት ከሁሉ
የአሜሪካ ድምፅ

የላቀ ውጤት ያስመዘገቡት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች

የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርትን አጠናቆ ከፍተኛ የኮሌጅ መግቢያ ነጥብ ማግኘት ለብዙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በከፍተኛ ስኬት የሚታይ ነው። በዘንድሮው ዓመት ከሁሉም ክልል የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በአንድ ላይ በተሸለሙበትና አዲስ አበባ ላይ በተሰናዳ ሥነ ሥርዐት ላይ ሽልማት የተበረከተላቸው ተማሪዎች አስተያየታቸውን አካፍለውናል። ከተቋቋመ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረው  የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት ድርጅት የተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም፣ ባለፈው ዕረቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ጊቢ በአዘጋጀውና የመጀመሪያ ነው በተባለው በዚኽ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ውጤታ ያስመዘገቡ 16 ተማሪዎች ተሸላሚ ኾነዋል።

በአስመራ ከተማ በጥምቀተ ባሕር የተከበረው ጥምቀት

በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በአደባባይ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የእየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል እሑድ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ.
የአሜሪካ ድምፅ

በአስመራ ከተማ በጥምቀተ ባሕር የተከበረው ጥምቀት

በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በአደባባይ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የእየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል እሑድ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ.ም. በመላው ኤርትራ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች በአስመራ ከተማ ጥምቀተ ባህር ላይ ተከብሯል። የአከባበር ሥነ ሥርዐቱ ምን ይመስል እንደነበር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የቲክቶክ የአሜሪካ ህልውና በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ ተንጠልጥሏል

በሚሊየን የሚቆጠሩ የዩናይትድ ስቴትስ ቲክቶክ ተጠቃሚዎች፣ ቃለ መሐላ ፈፅመው ሥልጣን የተረከቡትን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ እየተጠባበቁ ነው። ፕ
የአሜሪካ ድምፅ

የቲክቶክ የአሜሪካ ህልውና በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ ተንጠልጥሏል

በሚሊየን የሚቆጠሩ የዩናይትድ ስቴትስ ቲክቶክ ተጠቃሚዎች፣ ቃለ መሐላ ፈፅመው ሥልጣን የተረከቡትን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ እየተጠባበቁ ነው። ፕሬዝዳንቱ ቲክቶክን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው የቻይናው ባይት ዳንስ፣ መተግበሪያውን ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ የ75 ቀናት የጊዜ ገደብ ሰጥተዋል። ማት ዴቢ በዚህ ዙሪያ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የትራምፕ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕጩ አምባሳደር የማሻሻያ ለውጥ ጥሪ

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር እንዲሆኑ ያጯቸው ኤሊስ ስቴፋኒክ ትላንት ማክሰኞ በእንደራሴዎች ምክር ቤት
የአሜሪካ ድምፅ

የትራምፕ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕጩ አምባሳደር የማሻሻያ ለውጥ ጥሪ

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር እንዲሆኑ ያጯቸው ኤሊስ ስቴፋኒክ ትላንት ማክሰኞ በእንደራሴዎች ምክር ቤት በተካሄደው ሥነ ስርዐት ወቅት በርካታ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል። በምክር ቤቱ ከፍተኛው የሪፐብሊካን መሪ በዓለም አቀፉ ድርጅት “ቅድሚያ ለአሜሪካ” የሚለውን የትራምፕ አጀንዳ ያራምዳሉ ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን ያደረሰችንን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉል

በኬንያ የትዳር አጋሩን የተቆራረጠ አስከሬን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ግለሰብ ተያዘ

የትዳር አጋሩን የተቆራረጠ አስከሬን በጀርባ በሚንጠለጠል ሻንጣ ውስጥ ይዞ ሲጓዝ የነበረን ግለሰብ መያዙን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል። የፖሊስ ዓባላት ግለሰ
የአሜሪካ ድምፅ

በኬንያ የትዳር አጋሩን የተቆራረጠ አስከሬን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ግለሰብ ተያዘ

የትዳር አጋሩን የተቆራረጠ አስከሬን በጀርባ በሚንጠለጠል ሻንጣ ውስጥ ይዞ ሲጓዝ የነበረን ግለሰብ መያዙን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል። የፖሊስ ዓባላት ግለሰቡን የኮንትሮባንድ ሸቀጥ ይዟል በሚል ጥርጣሬ ሲፈትሹ የተቆራረጠ አስከሬን ማግኘታቸው ታውቋል። በምርመራ ወቅትም አስከሬኑ የ19 ዓመት ዕድሜ ያላት ባለቤቱ እንደኾነ የ 29 ዓመቱ ተጠርጣሪ ጃን ኪያማ ዋምቡዋ ለፖሊስ አስታውቋል። አሳዛኙ ሁኔታ የተሰማው በሴቶች ላይ የሚፈፀመውን ግድያ በመቃወምና ባለሥልጣናት ርምጃ እንዲወስዱ በመጠየቅ በመቶ የሚቆጠሩ ሴቶች በመዲናዋ ናይሮቢ ሰልፍ ባደረጉ በሳምንታት ውስጥ ነው። ፖሊስ ሰልፈኞቹን በአስለቃሽ ጋዝ በትኖ ነበር። ጃን ዋምቡዋ በተያዘበት ወቅት መረበሽ እንዳልታየበት  ፖሊስ ጨምሮ አስታውቋል። ፖሊስ የዋምቡዋን ቤት የፈተሸ ሲሆን፣ ወለሉ እና ልብሶች በደም መለወሳቸውን አስተውሏል። ለግድያው የተጠቀመበት ሳይሆን አይቀርም የተባለ ስለታማ ቢላም ተገኝቷል። ተጨማሪ የአስከሬን አካላት ከአልጋ ሥር ማግኘቱንም ፖሊስ አስታውቋል ባለፈው ዓመት ዩጋንዳዊቷ ኦሊምፒክ ሯጭ ረቤካ ቼፕቴጂን ፍቅረኛዋ ነዳጅ አርከፍክፎ ማቃጠሉ ይታወሳል። አግነስ ቲሮፕ እና ዳማሪስ ሙትዋ የተባሉ ሴት አትሌቶችም በፍቅር አጋሮቻቸው መገደላቸው ይታወሳል።

የትረምፕ በዓለ ሲመት ንግግር ሲዳሰስ

በየአራት ዓመቱ እንደሚደረገው ሁሉ፣ በ2024ቱ ምርጫ አሸናፊ የሆኑት ዶናልድ ትረምፕ በትላንትናው ዕለት በዓለ ሲመታቸው ተከናውኗል። ትረምፕ በበዓለ ሲመታቸው
የአሜሪካ ድምፅ

የትረምፕ በዓለ ሲመት ንግግር ሲዳሰስ

በየአራት ዓመቱ እንደሚደረገው ሁሉ፣ በ2024ቱ ምርጫ አሸናፊ የሆኑት ዶናልድ ትረምፕ በትላንትናው ዕለት በዓለ ሲመታቸው ተከናውኗል። ትረምፕ በበዓለ ሲመታቸው ላይም ሆነ ከዛ በኋላ በነበሩት ፕሮግራሞች ላይ ንግግር አድርገዋል። በበዓለ ሲመታቸው ሥነ ስርዐት ላይ ባደረጉት ንግግር በርካታ የሃገር ውስጥ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ ጉዳዮችን አንስተዋል። አሜሪካ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ ስለሚኖራት ሚና፣ እንዲሁም አንዳንድ አወዛጋቢ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው የሚታመኑ ጉዳዮችን አንስተዋል። ትረምፕ ንግግራቸውን የጀመሩት “የአሜሪካ ወርቃማ ጊዜ ዛሬ ይጀምራል” ብለው ነበር። ደኅንነቷን፣ ሉአዓላዊነቷኣ እና ፍትህን እንድሚያስክብሩ ደጋግመው አውስተዋል። ኩሩ፣ የበለጸገና ነጻ ሃገር እንገነባለን ያሉት ትረምፕ፣ ከእርሳቸው በፊት የነበረው አስተዳደር የሃገሪቱን ደኅንነት እና ድንበር አልጠበቀም ሲሉ ነቅፈዋል። ሕገ ወጥ ወይም ሰነድ አልባ ስደተኞችን በተመለከተም በበዓለ ሲመታቸው ላይ አንስተዋል። ድንበሩን በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ እንደሚያሰጠብቁ ለዚህም የአሜሪካንን መከላከያ ኅይል እንደሚጠቀሙ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን ከሃገር እንደሚያስወጡ ተናግረዋል። ይህን ለማስፈጸምም በዚሁ በበዓለ ሲመታቸው ቀን የሥራ አስፈጻሚ ወይም ፕሬዝደንታዊ ትዕዛዝ ፈርመዋል። ሃገሪቱ ገጥሟታል ያሉትን ፈተናዎች ሁሉ እንደሚያሰወግዱ ቃል የገቡት ትረምፕ፣ ሃገራዊ አንድነትን ለማምጣት እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል። ትረምፕ በትላንትናው ዕለት ባደረጉት ንግግር በተወሰኑት ጉዳዮች ላይ የባለሞያ አስተያየት ጠይቀናል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሩቢዮ ቀጣዩ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኾኑ

የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትላንት ሰኞ ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ ቀጣዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኾነው እንዲያገለግሉ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። በዚህም
የአሜሪካ ድምፅ

ሩቢዮ ቀጣዩ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኾኑ

የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትላንት ሰኞ ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ ቀጣዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኾነው እንዲያገለግሉ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። በዚህም ሩብዮ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ  ሲመታቸው በምክር ቤቱ የጸደቀላቸው የመጀመሪያው የአዲሱ ካቢኔ አባል ኾነዋል። ከፍሎሪዳ ክፍለ ግዛት የሆኑት የሪፐብሊካን ሴናተር ሩቢዮ ከትራምፕ እጩዎች መካከል እምብዛም ውዝግብ የማይነሳባቸው ሲሆኑ 99 ለዜሮ በሆነ ወሳኝ ድምጽ ነው የተመረጡት። «ማርኮ ሩቢዮ ስለ አሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ጥልቅ ግንዛቤ ያላቸው እጅግ አስተዋይ ሰው ናቸው» ሲሉ በምክር ቤቱ ከፍተኛው የሪፐብሊካን አባል የአይዋው ሴናተር ቸክ ግራስሌ በምክር ቤቱ መክፈቻ ባሰሙት ንግግራቸው አመልክተዋል። ሌላው የትራምፕ እጩ የዩናይትድ ስቴትስን የደኅንነት መሥሪያ ቤት እንዲመሩ የተመረጡት ጆን ራትክሊፍ ሹመታቸው በፍጥነት ይጸድቃል ተብሎ ከሚጠበቁ ዕጩዎች ውስጥ ናቸው። ለመከላከያ ሚንስትርነት የታጩትን የቀድሞውን የፎክስ ኒውስ ቴሌቭዥን ፕሮግራም አቅራቢ ፒት ሄግሰትን ጨምሮ የሌሎች እጩዎች ሹመት የማጽደቅ ሂደት በሳምንቱ መገባደጂያ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። የዩናይትድ ስቴትሱ እንደራሴዎች ምክር ቤት በተለመደ አሠራሩ የፕሬዝዳንታዊው በዓለ ሲመት ሥነ ስርዐት እንደተጠናቀቀ ፈጥኖ የአዲሱን ፕሬዝዳንት ካቢኔ በተለይም የብሔራዊ ደኅንነት ባለሥልጣናት እጩዎች ሥራቸውን እንዲጀምሩ ያደርጋል።

'ከትግሉ አንርቅም' ከ50 ዓመታት በኋላ ዋሽንግተንን የለቀቁት ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ባይደን

ከ50 ዓመታት አገልግሎት በኋላ የፖለቲካ ሥልጣናቸውን ያገባደዱት ጆ ባይደን ዋይት ሃውስን ተሰናብተው ፊታቸውን ወደ ግል ህይወታቸው ለማዞር ከቤተሰባቸው ጋራ ወ
የአሜሪካ ድምፅ

'ከትግሉ አንርቅም' ከ50 ዓመታት በኋላ ዋሽንግተንን የለቀቁት ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ባይደን

ከ50 ዓመታት አገልግሎት በኋላ የፖለቲካ ሥልጣናቸውን ያገባደዱት ጆ ባይደን ዋይት ሃውስን ተሰናብተው ፊታቸውን ወደ ግል ህይወታቸው ለማዞር ከቤተሰባቸው ጋራ ወደ ካሊፎርኒያ ቢያቀኑም "የያዝነውን ትግል ግን ቸል ብለን አንተውም” ብለዋል። ባይደንን የተኩት አዲሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከእርሳቸው በፊት የነበሩት ዲሞክራቱ ፕሬዝዳንት ባይደን ያደረጉትን “ሙሉ በሙሉ እና ጨርሶ ለመቀልበስ” ቃል የገቡበትን የመክፈቻ ንግግራቸውን ከተከታሉ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ተናግረዋል። ባይደን ከአራት ዓመታት በፊት ሥልጣን ላስለቀቋቸው ሰው የአክብሮት አስተያየት ሰንዝረዋል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2020 በተካሄደው ምርጫ መሸነፋቸውን ያላመኑት ትራምፕ በአንጻሩ በ2021 የባይደን በዓለ ሲመት በተካሄደበት ወቅት በወጉ መሠረት ለባይደን ተመሳሳይ መልካም አስተያየት ለመስጠት እና አክብሮት ለማሳየት ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ይታወሳል።

ትረምፕ በአፍጋኒስታን የሚገኝ የአሜሪካ ጦር መሣሪያዎች እንዲመለሱ ጠየቁ

ወደፊት ለአፍጋኒስተን የሚሠጥ የገንዘብ ድጋፍ፣ በሥልጣን ላይ የሚገኙት የታሊባን መሪዎች በሃገሪቱ የሚገኙትን የአሜሪካ ጦር መሣሪያዎች በመመለሳቸው ላይ እ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ በአፍጋኒስታን የሚገኝ የአሜሪካ ጦር መሣሪያዎች እንዲመለሱ ጠየቁ

ወደፊት ለአፍጋኒስተን የሚሠጥ የገንዘብ ድጋፍ፣ በሥልጣን ላይ የሚገኙት የታሊባን መሪዎች በሃገሪቱ የሚገኙትን የአሜሪካ ጦር መሣሪያዎች በመመለሳቸው ላይ እንደሚወሰን ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ አስታውቀዋል። ትረምፕ ይህን ያስታወቁት ከትላንት በስቲያ ለደጋፊዎቻቸው በተዘጋጀ ሥነ ሥርዐት ላይ በአደረጉት ንግግር ነው። የባይደን አስተዳደር በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላርና የጦር መሣሪያዎችን ጠላት ብለው ለጠሩት ወገን ሰጥቷል ያሉት ትረምፕ፣ የታሊባን መሪዎች የአሜሪካን የጦር መሣሪያዎችን የማይመልሱ ከኾነ የገንዘብ ርዳታ እንደማይደረግ አስታውቀዋል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 2021 አሜሪካ በጥድፊያ ከአሜሪካ ስትወጣ 7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የጦር መሣሪያ ጥላ እንደወጣች የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። ትረምፕ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ብለው የጠቀሱት ገንዘብ ለተመድ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች የሚሰጥ መኾኑን ሪፖርቶች አመልክተዋል። ለዚህም አሜሪካ ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር ገደማ እንዳዋጣች ጠቁመዋል።

ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝደንትነት ሥልጣናቸውን ተረከቡ

ዛሬ ሰኞ በድጋሚ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትነትን የተረከቡት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትረምፕ «ምክንያት ላይ የተመሠረተ የአስተሳሰብ አብዮት» ጥሪ በማቅ
የአሜሪካ ድምፅ

ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝደንትነት ሥልጣናቸውን ተረከቡ

ዛሬ ሰኞ በድጋሚ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትነትን የተረከቡት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትረምፕ «ምክንያት ላይ የተመሠረተ የአስተሳሰብ አብዮት» ጥሪ በማቅረብ፣ በሚፈልጉት መንገድ የአሜሪካን የፖለቲካ ምሕዳር ለመለወጥ በርካታ አስፈፃሚ ትዕዛዞችን መፈረም እንደሚጀምሩ ተናግረዋል፡፡ ትረምፕ ቃለ መሐላቸውን በምክር ቤቱ ህንፃ ውስጥ በፈጸሙበት ወቅት በአሰሙት ንግግራቸው “የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን” መጀመሩን እና ለፈጣን የፖሊሲ ለውጦች የአስፈፃሚ ትእዛዝ መሰጠቱን”ተናግረዋል። ትረምፕ ዋሽንግተን ውስጥ እጅግ ቀዝቃዛ በኾነው ቀን፣ የጀመሩት ከባለቤታቸው ሜላኒያ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋራ ሲኾን ስነ ስርዐቱን የጀመሩት በወጉ መሰረት ለአዲስ ፕሬዝዳንቶች በሚደረገው ከዋይት ሐውስ ፊት ለፊት ካለው የመናፈሻ ስፍራአቅራቢያ በሚገኘው በቅዱስ ዮሀንስ ኤጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን በተደረገው ጸሎት ነው፡፡ ትራምፕ ከተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ከቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን ጋራ ከበዓለ ሲመቱ አስቀድሞ በኋይት ሃውስ ለሻይ ሥነ ሥርዐት ተገናኝተው ነበር፡፡ 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶናልድ ትረምፕ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ካፒቶል ውስጥ ነው ወደ 600 ሰዎች በተገኙበት ሥነ ሥርዐት፣ ለሁለተኛ ጊዜ 47ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት በመኾን ቃለ ቃለ መሐማ ፈጽመዋል። “እኔ ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በሚያዘው መሰረት፣ ሕግ መንግሥቱን ለማስጠበቅ፣ ለመመከት እና ለመከላከል አቅሜ በፈቀደው ሁሉ ኃላፊነቴን በታማኝነት ለመወጣት ቃል እገባለሁ። ለዚህም ፈጣሪ ይርዳኝ!” ብለዋል። በ1890ዎቹ ከግሮቨር ክሊቭላንድ በኋላ ፕሬዝዳንት ተከታታይ ባልኾኑ የሥልጣን ዘመናት በማገልገል ትረምፕ ሁለተኛው ይሆናሉ፡፡ በ78 ዓመታቸው ፕሬዝዳንት በመሆን ትረምፕ በዕድሜ ትልቁ ሲሆኑ፣ ባይደን ከአራት ዓመት በፊት ቃለ መሐላ ሲፈጽሙ ከሳቸው በአምስት ወር ያንሱ ነበር፡፡ የ40 ዓመቱ ቫንስ፣ 50ኛው ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን በታሪክ ሦስተኛው በእድሜ ትንሹ ያደርጋቸዋል ፡፡ ትረምፕ ባለፈው ዓመት ለወሲብ ፊልም ተዋናይ ስቶርሚ ዳንኤልን የተከፈለውን የ130 ሺሕ ዶላር የአፍ ማስያዣ ገንዘብ ለመደበቅ የቢዝነስ ሰነድ አጭበርብረዋል በሚል ተከሰዋል፡፡ በዚሁ ክስ በ34 የወንጀል ክሶች ጥፋተኛ ተብለው ተፈረደባቸዋል፥፥ በኋላ ምንም ዳኛው ቅጣት ውሳኔ እንደማይሰጡ ቢያስታውቁም፣ በወንጀል ክስ በጥፋተኝነት የተፈረደባቸው የመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ይሆናሉ። ሪፐብሊካኑ ትረምፕ ባይደን እንደ አውሮፓያን አቆጣጠር በ2020 ያሸነፉበትን የምርጫ ውጤት በሕገ ወጥ መንገድ ለመቀልበስ ሞክረዋል የሚለው ክስ ተቋርጧል፡፡ ክሱ የተቋረጠው ትረምፕ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ተቀናቃኛቸውን ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስን በምርጫ አሸንፈው በመመረጣቸው ሥልጣን ላይ ያሉ ፕሬዚዳንቶች አይከሰሱም በሚለው በፍትህ ሚኒስቴር ፖሊሲ ምክንያት ነው። ፕሬዝደንታዊ በዓለ ሲመቱ ወደ 250 ዓመት የሚጠጋው የአሜሪካ ዲሞክራሲ መለያ የሆነው በየአራት ዓመታት የሚመጣው ሰላማዊ የፕሬዚዳንት ስልጣን ሽግግር ሲሆን፣ ለወትሮው የሚከናወነው250 ሺሕ ሰዎችን ወይም ከዚያ በላይ በሚይዘው በተንጣለለው ናሽናል ሞል መስክ ትይዩ በሚገኘው የምክር ቤቱ ህንፃ ደጃፍ ላይ ነው፡፡ በቃለ መሐላው ስነ ሥርዐት ዋዜማ እሁድ ሌሊቱን ወደ ዋሽንግተን የነፈሰው ቀዝቃዛ አየር፣ እጅግ ከባድ ብርድ ማስከተሉ በፈጠረው ስጋት የተነሳ ሥነ ሥርዐቱ ምክር ቤት ህንጻ «ካፒቶል ሮተንዳ» አዳራሽ እንዲከናወን ተውስኗል፥ ስነ ስርዐቱ በትረምፕ ትዕዛዝ ወደ ምክር ቤቱ ህንጻ ውስጥ እንዲዛወር በመደረጉ፣ በአካል ተገኝተው የሚመለከቱት ወደ 600 የሚጠጉ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ካፒቶል 2 ሺሕ የሚደርሱ የትረምፕ ደጋፊዎች እ.ኤ.አ. በ2021ዓ.ም የምክር ቤቱን ህንፃ በመውረር በባይደን የተሸነፉበትን የምርጫ ውጤት እንዳያጸድቅ ለማድረግ የሞከሩበት ስፍራ ነው፡፡ በአርባ ሰባተኛው ፕሬዚደንት የቃለ መሐላ ሥነ ስርዐት ላይ የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ፣የሜታው ማርክ ዘከርበርግ እና የቴስላ እና የቀድሞው ትዊተር የአሁኑ ኤክስ ባለቤት ኢላን መስክን ጨምሮ በርካታ አሜሪካዊያን ባለብዙ ቢሊዮን ዶላር ባለ ሀብቶች ላይ ተገኝተዋል። የቲክቶክ የሥራ አስፈጻሚ ሹ ዚ ቼውም እንዲሁ ተገኝተዋል። የቻይና ምክትል ፕሬዝደንት ሃን ዤንግ የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ መሎኒ እና የአርጀንቲናው ፕሬዝደንት ሃቪየር ሚሌ እና የኤኳዶሩ ዳኒየል ኖቦዋ ከተጋበዙት የውጭ መሪዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ዶናልድ ትረምፕ ከአራት ዓመታት በፊት ባሸነፏቸው በጆ ባይደን በዓለ ሲመት ላይ ሳይገኙ ከመቅረታቸውም ሌላ እስከዛሬ በዚያ ምርጫ በተፈጸመ በድምጽ መጭበርበር በድጋሚ እንዳልመረጥ ተደርጌአለሁ የሚለውን የሐሰት ውንጀላቸውን ገፍተውበታል። በዛሬው የእርሳቸው በዓለ ሲመት ላይ ግን የቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንቶች ቢል ክሊንተን፣ ጆርጅ ደብሊው ቡሽ እና ባራክ ኦባማ ተገኝተዋል።

ፕሬዝደንት ትረምፕ ወደ ሥልጣን ተመልሰው የመጡበት መንገድ ወደ ኋላ ሲቃኝ

በ2024ቱ ምርጫ ዶናልድ ትረምፕ ሕዝባዊውንም ኾነ ኢሌክቶራል ካሌጅ ተብለው የሚጠሩትን የአስመራጮች ድምፅ አሸንፈው ዛሬ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ትረምፕን ለድል ያ
የአሜሪካ ድምፅ

ፕሬዝደንት ትረምፕ ወደ ሥልጣን ተመልሰው የመጡበት መንገድ ወደ ኋላ ሲቃኝ

በ2024ቱ ምርጫ ዶናልድ ትረምፕ ሕዝባዊውንም ኾነ ኢሌክቶራል ካሌጅ ተብለው የሚጠሩትን የአስመራጮች ድምፅ አሸንፈው ዛሬ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ትረምፕን ለድል ያበቋቸው በርካታ ጉዳዮችና ሁኔታዎች እንዳሉ የፖለቲካ ተንታኞችም ሆነ የትረምፕ ደጋፊዎቻቸው ያስረዳሉሉ። ትረምፕ ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ በ34 ወንጀሎች ጥፋተኝዐ ቢባሉም ለድል በቅተዋል። አሜሪካውያን በኢኮኖሚውም ሆነ በሌሎች ሁኔታዎች የገጠማቸውን ችግር እንድሚረዱ እና ችግሩንም ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸው የድምጽ ሰጪዎችና ደጋፊዎቻቸው ጆሮ መድረሱ፣ “አሜሪካ ትቅደም” የሚለውና ጠንከር ያለ ነው የተባለው መልዕክታቸው፣ ቁልፍ የሆኑ ድምጽ ሰጪዎችን ኢላማ አድርገው መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸው፣ ኢኮኖሚው በፈጠረው ሁኔታ ኑሮ የከበዳቸውን ድምጽ ሰጪዎችን ኢላማ ማድረጋቸውም ተጠቃሽ ነው። ትረምፕ ለድል የበቁበት መንገድ ምን ይመስላል? በምንስ ይግለጻል? ለድል የበቁባቻው ሌሎች ምክንያቶችስ ምንድን ናቸው ስንል በቴክሳስ ካሊንስ ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑትን ፕሮፌሰር ሞሃመድ ጣሂሮን ጋብዘናል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

“ከዚህ በፊት ባልታየ መንገድ” ወደ ሥልጣን የተመለሱት ዶናልድ ትረምፕ

ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ቃለ መሐላ ፈጽመው 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ኾነዋል። ወደሥልጣን የተመለሱበት ሁኔታ ታሪካዊ በሚል በመገለጽ ላይ ነው። ትረምፕ፣ ክፍፍሉ
የአሜሪካ ድምፅ

“ከዚህ በፊት ባልታየ መንገድ” ወደ ሥልጣን የተመለሱት ዶናልድ ትረምፕ

ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ቃለ መሐላ ፈጽመው 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ኾነዋል። ወደሥልጣን የተመለሱበት ሁኔታ ታሪካዊ በሚል በመገለጽ ላይ ነው። ትረምፕ፣ ክፍፍሉ እየጨመረ ባለበት አገር ውስጥ፣ የሪፐብሊካን ፓርቲውን ቅርጽ ለመቀየር የፈጀባቸው ከዘጠኝ ዓመት ያህል ብቻ ነው። ትረምፕ ወደ ፖለቲካ ሥልጣን የተመለሱበትን ሂደት የቪኦኤዋ ቲና ትሪን ተመልክታዋለች፡፡ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የ60ኛው ፕሬዝዳንታዊ በዓለ ሲመት ጥብቅ ጥበቃ እና በመጨረሻው ሰዓት የተደረጉት ለውጦች አንድምታ

በከፍተኛ ጥበቃ ታጅቦ የሚካሄደው የተመራጩ ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት ልዩ ትኩረት ከሚሰጣቸው እና ረዥም ዕድሜ ከዘለቁ መንግስታዊ ክንዋኔዎች አንዱ ሲሆን፤ ቁጥ
የአሜሪካ ድምፅ

የ60ኛው ፕሬዝዳንታዊ በዓለ ሲመት ጥብቅ ጥበቃ እና በመጨረሻው ሰዓት የተደረጉት ለውጦች አንድምታ

በከፍተኛ ጥበቃ ታጅቦ የሚካሄደው የተመራጩ ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት ልዩ ትኩረት ከሚሰጣቸው እና ረዥም ዕድሜ ከዘለቁ መንግስታዊ ክንዋኔዎች አንዱ ሲሆን፤ ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ይታደምበታል። ቃለ መሃላ ፈጽመው አርባ ሰባተኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት የሚሆኑት ትራምፕ፤ ሥነ ስር አቱ የሚካሄድባት የዛሬዋ ዕለት ከመድረሷ ሶስት ቀናት አስቀድመው ያደረጉት ለውጥ፣ በአንጻሩ አጠቃላዩን በሥነ ስርአቱ ዙሪያ የሚካሄደውን የጥበቃ ሥራ በእጅጉ ለውጦታል። አሉላ ከበደ የጥበቃውን ይዘት እና የተደረጉትን ለውጦች አስመልክቶ ያጠናቀረውን ዘገባ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።

ዶናልድ ትረምፕ የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ዳግም እየተረከቡ ነው

ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ሰኞ ዋሽንግተን ውስጥ በሚካሄድ በዓለ ሲመት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትነት ሥልጣናቸው ይመለሳሉ፡፡ ይህ እ.ኤ.አ. ከ1890ዎቹ ወዲህ ተከ
የአሜሪካ ድምፅ

ዶናልድ ትረምፕ የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ዳግም እየተረከቡ ነው

ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ሰኞ ዋሽንግተን ውስጥ በሚካሄድ በዓለ ሲመት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትነት ሥልጣናቸው ይመለሳሉ፡፡ ይህ እ.ኤ.አ. ከ1890ዎቹ ወዲህ ተከታታይ ባልሆነ የስልጣን ዘመን ያገለገሉ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ያደርጋቸዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን፣ የ78 ዓመቱ ትረምፕ ለአዲሱ የአራት ዓመት የስልጣን ዘመን በዋይት ሀውስ ቃለ መሃላ ሲፈፅሙ ፣ የ82 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደግሞ ከአንድ የስልጣን ዘመን በኋላ የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ ሲለቁ፣ በቴሌቭዥን ይከታተላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የበዓለ ሲመቱ በተፈጠረው ቅዝቃዜ ምክንያት ከታቀደው አነስ ባሉ ታዳሚዎች ይካሄዳል፡፡ እንደወትሮው በመስክ ላይ በሚደረገው ዝግጅት ለመገኘት ትኬት የነበራቸው 250,000 ሰዎች ሲሆኑ፣ ከውጭ ወደ ምክር ቤቱ ህንጻ ውስጥ በተዛወረው በዓለ ሲመት በአካል የሚታደሙ ወደ 600 የሚጠጉ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ የፔንሰልቬንያ ጎዳናን ይዞ ከምክር ቤቱ እስከ ዋይት ሐውስ ድረስ ይደረግ የነበረው ባህላዊ የመክፈቻ ሰልፍ በአየር ሁኔታ ለውጥ ምክንያት ተሰርዟል፡፡ ዛሬ ባንዶች ፣ የሰልፈኞች ቡድን ፣ የወታደራዊ እና የመሳሰሉ ትርኢቶችን የሚያሳዩ ሰልፈኞች 20,000 መቀመጫዎች ባሉት (Capital One Arena በተባለው) ሁለገብ የቤት ውስጥ አዳራሽ ትረምፕ፣ ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ እና በአዲሱ አስተዳደር በተካቱት ሌሎች ባለስልጣናት ፊት ያልፋሉ ። ዛሬ ሰኞ ምሽት ላይ ትላልቅ ግብዣዎች ይካሄዳሉ፡፡ ትረምፕ ትላንት እሁድ አመሻሹ ላይ በዋሽንግተን ውስጥ ለደጋፊዎቻቸው እንደተናገሩት “ሀገራችን የገጠማትን እያንዳንዱን ችግር ሁሉ ለማስተካከል በታሪካዊ ፍጥነት እና ጥንካሬ” እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል። «ነገ እኩለ ቀን ላይ አሜሪካ የወደቀበችበት የአራት ረጅም ዓመታት መጋረጃ ይዘጋና አዲስ የአሜሪካ ጥንካሬ እና የብልጽግና ቀን እንጀምራለን» ሲሉም አክለዋል ትረምፕ በትላንቱ ንግግራቸው። ወደ ቢሮ እንደተመለሱ የሚሻሩትን የባይደን አስተዳደር ፖሊሲዎችን ጨምሮ ብዙ የስራ አስፈፃሚ ትዕዛዞችን ለመፈረም ቃል ገብተዋል። በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ከገቡት ቃል መካከል ጎልቶ የታየው በሀገሪቱ በህገ ወጥ መንገድ የሚገኙ ዜጎችን በብዛት ማባረር ነበር። ትረምፕ ካናዳ፣ ቻይና እና ሜክሲኮን ጨምሮ ቁልፍ በሆኑ የንግድ አጋሮች ላይ ወዲያውኑ ጠበቁ ያለ ታሪፎችን ለመጣል ቃል ገብተዋል። መጪው ፕሬዚደንት እ.ኤ.አ ጥር 6፣ 2021 እኤአ በ2020 ምርጫ ባይደን ማሸነፋቸውን ምክር ቤቱ እንዳያረጋግጥ ለማገድ የምክር ቤቱን ህንፃ ከወረሩት 1,500 ደጋፊዎቻቸው መካከል፣ ለብዙዎቹ ይቅርታ ለማድረግ ማቀዳቸውንም ተናግረዋል፡፡ ትረምፕ ያለ አግባብ ክስ ቀርቦባቸዋል ያሏቸውን በቁጥጥር ስር የዋሉትን እና የተፈረደባቸውን «አርበኞች» እና «ታጋቾች» ብለዋቸዋል፡፡ ሪፐብሊካኑ ትረምፕ ባይደን እ.ኤ.አ. ያገኙትን የ2020 ምርጫ ውጤት በህገ ወጥ መንገድ ለመቀልበስ ሞክረዋል የሚለው ክስ ተቋርጧል፡፡ ክሱ የተቋረጠው ትረምፕ የዲሞክራቲክ ተቀናቃኛቸውን ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስን በ2024 ምርጫ በማሸነፋቸው ሥልጣን ላይ ያሉ ፕሬዚዳንቶች አይከሰሱም በሚለው በፍትህ ሚኒስቴር ፖሊሲ ምክንያት ነው። ትረምፕ ባለፈው ዓመት ለወሲብ ፊልም ተዋናይ ስቶርሚ ዳንኤልን የተከፈለውን የ130,000 ዶላር የአፍ ማስያዣ ገንዘብ ለመደበቅ የቢዝነስ ሰነድ አጭበርብረዋል በሚል ተከሰዋል፡፡ በዚሁ ክስ በ34 የወንጀል ክሶች ጥፋተኛ ተብለው ከተፈረደባቸው በኋላ ምንም እንኳ ዳኛው እንደማይቀጧቸው ቢያሳውቁም ፣ በወንጀል የተፈረደባቸው የመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ይሆናሉ። ትረምፕ ስልጣን ከመረከባቸው በፊት ለወራት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለማስቆም ቃል ገብተዋል፡፡ ከቅርብ ቀናት ወዲህ ግን ረዳቶቻቸው በአስተዳደሩ የመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት በሚያዝያ ወር መጨረሻ ላይ ጦርነቱ ለማስቆም ከሰላም ስምምነት ለመድረስ መሞከር ነው ብለዋል ። ምንም እንኳን እ.ኤ.አ. በ 2023 የአሜሪካ የኃይል አቅርቦት ምርት ከተመዘገበው መጠን በላይ ቢሆንም ትረምፕ አሜሪካ ውስጥ ተጨማሪ የነዳጅ ቁፋሮ እንዲደረግ ይፈልጋሉ ። በውልደት ከነበራቸው ጾታ የተለየ የጾታ ማንነት የወሰዱ ሰዎችን የሚመለከቱ ሁለት ጉዳዮችም የትረምፕን ትኩረት ስበዋል። ትረምፕ በውልደት የነበራቸውን ጾታቸውን ከወንድ ወደ ሴት የቀየሩ ሴቶችን እንደ ወንድ ደጋግመው በመጥቀስ ጾታቸውን የቀየሩት በሴቶች ስፖርት ውድድር ውስጥ መሳተፍ እንደማይችሉ እንደሚያረጋግጡ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል፡፡ ትረምፕ በአንድ የምርጫ ቅሰቀሳ መድረካቸው “ (ሥልጣን ከያዝኩበት) ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ወንዶች መቶ በመቶ በሴቶች ስፖርቶች እንዳይሳተፉ አደርጋለሁ” ብለዋል ። በተጨማሪም በውልደት ከነበራቸው ጾታ የተለየ የጾታ ማንነት ለወሰዱ ሰዎች የሚደረግ የጤና እንክብካቤን ብዙ ጊዜ ተቃውመዋል፡፡ «ሥልጣን በያዝኩበት የመጀመሪያው ቀን 'በውልደት ከነበራቸው ጾታ የተለየ የጾታ ማንነት ለወሰዱ ሰዎች የሚደረግ የተባለውን የጆ ባይደንን የጤና እንክብካቤን' መጥፎ ፖሊሲ እሽራለሁ።» ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች በዓለ ሲመት ታሪክ

በአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ በዓለ ሲመት ትልቅ ቀን ነው፡፡ የራሱ የኾነ ወግ እና ሥርዐትም አሉት። አንዳንዶቹ ከመጀመሪያው ፕሬዝደንት በዓለ ሲመት ጀምሮ የነበሩ የ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች በዓለ ሲመት ታሪክ

በአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ በዓለ ሲመት ትልቅ ቀን ነው፡፡ የራሱ የኾነ ወግ እና ሥርዐትም አሉት። አንዳንዶቹ ከመጀመሪያው ፕሬዝደንት በዓለ ሲመት ጀምሮ የነበሩ የክፍለ ዘመናት ዕድሜ የጠገቡ ወጎች አና ባሕሎች ናቸው፡፡ ታዲያ ሁሉም ፕሬዚደንታዊ በዓላተ ሲመት በሚፈለገው ሥርዓት አና ወግ በታቀደው መሠረት ተከናውነዋል ማለት አይደለም፡፡ እሱም ነው አንዳንዶቹን ከሌሎቹ ይበልጥ አይረሴ የሚያደርጋቸው፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1789 ዓ.ም የተከናወነው የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ጆርጅ ዋሽንግተን በዓለ ሲመት   የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ጆርጅ ዋሽንግተን ቃለ መሐላቸውን የፈጸሙት ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ ነበር፡፡ በወቅቱ ኒውዮርክ የአገሪቱ ጊዜያዊ መዲና ስለነበረች ነው፡፡ አሜሪካዊያን ከዚያ በፊት ፕሬዝዳንት ኖሯቸው ስለማያውቅ የምክር ቤት አባላቱ ሥነ ሥርዐቱ እንዴት ቢከናወን ይሻላል በሚል መክረው እስኪወስኑ ጆርጅ ዋሽንግተን አንድ ሳምንት መጠበቅ ነበረባቸው፡፡ ከዚያ በኋላ እ አ አ ሚያዚያ 30 ቀን ላይ ፕሬzደንቱ እና ምክትላቸው እንዲሁም የምክር ቤቱ አባላት የHግ መወሰኛው ምክር ቤት ውስጥ ከተሰባሰቡ በኋላ በረንዳው ላይ ወጥተው ደጅ ለሚጠባበቀው ታዳሚ እጃቸውን በማውለብለብ ሰላምታ ሰጡ፡፡ በመቀጠል ቃለ መሐላውን የሚያስፈጽሟቸው ዳኛ «በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንትነት የተጣለብዎትን ኅላፊነት በታማኝነት ይወጣሉ? ብለው ጠየቋቸው፡፡ ጆርጅ ዋሽንግተን በአዎንታ ቃለ መሐላቸውን ሰጡ፡፡ ይህ ቃለ መሐላ እንዳለ በአሜሪካ ሕገ መንግሥት ውስጥ የተቀመጠ ነው፡፡ ዳኛው ጆርጅ ዋሽንግተን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ምለው ቃል እንዲገቡ ለማድረግ ነበር ያቀዱት፡፡ ነገር ግን የሚከናወንበት ሰዓት ሲቃረብ ዳኛው መጽሐፍ ቅዱስ እንዳላመጡ ባወቁ ጊዜ በጥድፊያ ሰው ተልኮ ከሌላ ቦታ መጽሐፍ ቅዱስ በውሰት መጥቶ ጆርጅ ዋሽንግተን ቃለ መሐላቸው ፈጸሙ፡፡ ዋሽንግተን ቃለ መሐላቸውን ከፈጸሙ በኋላ ያዘጋጁትን ንግግር በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት ፊት አነበቡ፡፡ ዊሊያም ማክሌይ የተባሉ ሴኔተር በግል ማስታወሻቸው ላይ ዋሽንግተን ንግግራቸውን ሲያነቡ ተጨናንቀው እጃቸው ይንቀጠቀጥ እንደነበር ማንበብ አስቸግሯቸው እንደነበረም ጽፈዋል፡፡ አዲሱ ፕሬዚደንት ዋሽንግተን ግር ቢላቸውም ሥነ ሥርዓቱ እጥር ጥፍጥ ያለ እንደነበር አክለዋል፡፡ ቶማስ ጀፈርሰን በ1801 ዓ.ም   እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1801 ዓ.ም የሦስተኛው ፕሬዝደንት የቶማስ ጄፈርሰን በዓለ ሲመት ደግሞ ከጆርጅ ዋሽንግተን በዓለ ሲመት ይበልጥ ቀለል ብሎ የተከናወነ ነበር፡፡ ቶማስ ጄፈርሰን ወደ በዓለ ሲመቱ ሥነ ሥርዐታቸው የሄዱት ከሳቸው በፊት እንደነበሩት ሁለቱ ቀደምቶቻቸው በሠረገላ ሳይሆን በእግራቸው ተጉዘው ነው፡፡ የአሜሪካ ምክር ቤት ካፒቶል ሲደርሱ ብዙ ሕዝብ ሲጠብቃቸው ነበር፡፡ ንግግራቸውንም አዘጋጅተው ነበር፡፡ ነገር ግን ድምጻቸው በጣም ድክም ያለ ስለነበረ ንግግራቸውን ሊሰማ የቻለው በጣም ጥቂት ሰው እንደነበር ታሪክ መዝግቦታል፡፡ ቢሆንም ዛሬ ያ የቶማስ ጄፈርሰን የበዓለ ሲመት ንግግር በአሜሪካዊያን ዘንድ በሚገባ ይታወቃል፡፡ በምርጫ ዘመቻው ወቅት በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የነበረውን አስቀያሚ ጭቅጭቅ ለማርገብ ያደረጉት ንግግር አድናቆት አትርፏል፡፡ ሆኖም የምርጫው ዘመቻው ጭቅጭቅ የተወው አስከፊ ገጽታ ቀጠለ እና ከጄፈርሰን ጋራ የተፎካከሩት ከሳቸው በፊት የነበሩት ፕሬዚደንት ጆን አዳምስ በጄፈርሰን በዓለ ሲመት ላይ ሳይገኙ ቀሩ፡፡ በዓለ ሲመቱ ነገ ሊሆን በዋዜማው ምሽቱ ላይ ጓዛቸውን ጠቅልለው ከዋይት ሐውስ ወጡ እና ወደቦስተን ተመለሱ፡፡ ዊሊያም ሄንሪ ሃሪሰን በ1841 ዓ.ም   እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1841 የዘጠነኛው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሄንሪ ሃሪሰን የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዓት ታሪክ ሳይወሳ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች በዓለ ሲመት ታሪክ ተወሳ ለማለት አይቻልም፡፡ ሲመረጡ የ68 ዓመት ሰው የነበሩት ዊሊያም ሃሪሰን በዘመኑ ከነበሩት ፕሬዝደንቶች ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ነበሩ፡፡ ታዲያ እንደሚባለው በፕሬዝደንትነት ለማገልገል ጠንካራ መሆናቸውን በጣም ረጅም ንግግር በማድረግ ለማሳየት አስበው ነው ይባላል ኃይለኛ ቅዝቃዜ በነበረበት የበዓለ ሲመታቸው ዕለት ጭንቅላታቸውን በብርድ ቆብ ሳይሸፍኑ ካፖርትም ሳይደርቡ ቆመው ረጅሙን ንግግራቸውን አደረጉ፡፡ ያ በሆነ በወሩ አዲሱ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሃሪሰን ታምመው ሞቱ፡፡ ሥልጣን ላይ ሆነው ሕይወታቸው ያለፈ የመጀመሪያ ፕሬዝደንት ናቸው፡፡ ሐኪማቸው ፕሬዝደንቱን ለሕልፈት የዳረጋቸው የሳምባ ምች ወይም ኒውሞኒያ ነው ብለዋል፡፡፡በተለምዶ ግን ብዙዎች ረጅሙ ንግግራቸው የገደላቸው ፕሬዚደንት ይሏቸዋል፡፡ የሐሪሰን አሟሟት እ አ አ በ2014 ምርምር ተደርጎበት ነበር፡፡ ተመራማሪዎቹ ጄን ሜክሂዩ እና ፊሊፕ ሜክውላክ ሃሪሰን የሞቱት በሳምባ ሕመም ሳይሆን በሌላ ምክንያት ነው ይላሉ፡፡ እነሱ እንደሚሉት ሃሪሰን የታመሙት ከበዓለ ሲመታቸው በኋላ ወዲያውኑ ሳይሆን ቆይተው ከሦስት ሳምንታት በኋላ ነው፡፡ የነበራቸውም የሕመም ስሜት ድካም እና ጭንቀት እንጂ ሳምባቸው ላይ እንዳልነበረ ይናገራሉ፡፡ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት ከሆነ በጊዜው ዋሽንግተን ዲሲ ጥሩ የፍሳሽ ማስወገጃ አገልግሎት ስላልነበራት የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ከኋይት ሐውስ በቅርብ ርቀት ሜዳ ላይ ይፈስ ስለነበረ ምናልባት በባክቴሪያ የተበከለ ውሃ ጠጥተው ሳይታመሙ አልቀሩም ሲሉ ተመራማሪዎቹ ድምዳሜአቸውን ኒው ዮርክ ታይምስ ላይ አስነብበዋል፡፡ የ30ኛው ፕሬዚደንት ካልቭን ኩሊጅ በ1923 ዓ.ም   ስለ ፕሬዝደንቶች በዓለ ሲመት ሲወሳ ታዲያ የሁሉም የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐት አይረሴ ነው ማለት አይደለም፡፡ የ30ኛው ፕሬዚደንት ካልቭን ኩሊጅ በዓለ ሲመት ቀዝቀዝ ባለ ድባብ ከተከናወኑት ውስጥ የሚጠቀስ ነው፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኩሊጅ እ አ አ በ1923 ነሃሴ ወር ውስጥ ብዙም የሥራ ኃላፊነት ስላልነበረባቸው ቨርሞንት ወደሚኖሩት ቤተሰቦቻቸው ቤት ለዕረፍት ሄደው ነበር፡፡ አንድ ቀን ሌሊት በተኙበት አባታቸው ይቀሰቅሷቸው እና ቴሌግራም እንደተላከላቸው ይነግሯቸዋል፡፡ ፕሬዚደንቱ ዋረን ሀርዲንግ አርፈዋል የሚል መርዶ የያዘ ቴሌግራም ነበር፡፡ በዚያ ኩሊጅ ፕሬዝደንት ሆኑ፡፡ ኩሊጅ በግል ማስታወሻቸው ላይ ይህንን ባውቅኩ ጊዜ መጀመሪያ ተነስቼ ቆምኩ እና ጸለይኩ፡፡ ከዚያም ከሕገ መንግሥቱ ውስጥ የፕሬዝደንት ቃለ መሐላው ያለበትን አውጥቼ ለአባቴ ያዘው ብዬ ሰጠሁት፡፡ ከዚያም ተመልሼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ብለው እንደጻፉ ተመልክቷል፡፡ ሊንደን ጆንሰን 1963 ዓ.ም   ቀደም ሲል ከተነገረው በተጻራሪ ድንገተኛ ሐዘን የተመላበትን ሊንደን ጆንሰን 36ኛው ፕሬዚደንት ሆነው ቃለ መሓላ የፈጸሙበትን ቀን አይረሴ ነው፡፡ ጆንሰን ቃለ መሃላ የፈጸሙት ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በሰው እጅ በጥይት ከተገደሉ ከአንድ ሰዓት ተኩል በኃላ ነበር፡፡ ጆንሰን በፕሬዝደንታዊው አውሮፕላን ኤር ፎርስ ዋን ውስጥ ቀኝ አጃቸውን ከፍ አድርገው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ የተነሳው ፎቶግራፍ ታሪኩን ይናገራል፡፡ በስተቀኛቸው ባለቤታቸው በስተግራቸው የሟቹ ፕሬዚደንት ባለቤት ጃኪ ኬኔዲ አጅበዋቸው ይታያሉ፡፡ ሊንደን ጆንሰንን ቃለ መሐላውን ያስፈጸሟቸው ሴት ዳኛ ሲሆኑ እስካሁን በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ፕሬዝደንትን ቃለ መሐላ ያስፈጸሙ ብቸኛዋ ሴት ዳኛ ናቸው፡፡ በፎቶው ላይ ሚስስ ኬኔዲ በባለቤታቸው በሰው እጅ መገደል የነበሩበት ድንጋጤ እና ሐዘን ፊታቸው ላይ ይነበባል፡፡ ጆንሰን ቃለ መሐላ ላይ ሲፈጽሙ ጎናቸው የቆሙትም ባለቤታቸው በጥይት በተገደሉበት ጊዜ ለብሰውት የነበረውን ያንኑ ልብስ እንደለበሱ ነበር፡፡ ምስሉ ፕሬዝደንቱ በሰው እጅ ለተገደሉበት የአሜሪካ ሕዝብ ተተኪ ፕሬዝደንት መሰየሙን በስተቀር ባልተጠበቀ ምስቅልቅል ሁኔታ ውስጥም ቢሆን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሥራ እንደሚቀጥል እምነት እንዲያድርበት ያደረገም ነበር፡፡ ታዲያ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሥራ ሁልጊዜ ያለ እንከን ይከናወናል ማለት አይደለም፡፡ በታቀደላቸው ስርዐት መሠረት ያልተከናወኑ ብዙ በዓለ ሲመቶች አሉ፡፡ በሥነ ሥርዓት ያልተከናወኑ በዓለ ሲመቶች የወፍ ምስል ወደ ጥንት ወደ እ አ እ 1829 ዓም መለስ ብለን የአንድሩው ጃክሰንን በዓለ ታሪክን ብንቃኝ ቃለ መሓላቸውን ከፈጸሙ በኋላ በኋይት በነበረው ድግሥ ላይ የታደሙ ደጋፊዎቻቸው እጃቸውን እየጨበጡ ደስታቸውን ለመግለጽ ጓጉተው ሲረባረቡ አዲሱን ፕሬዝደንት ከግድግዳ ጋር አጣብቀው ሊደፈጥጧቸው ምንም አልቀራቸውም ነበር፡፡ ፕሬዝደንቱ በመስኮት ወጥተው እንዳመለጡ ታሪክ ይናገራል፡፡ በ1865 ደግሞ የፕሬዝደንት አብራሃም ሊንከን ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡት አንድሩ ጆንሰን በቃለ መሐላ ሥነ ስርዐታቸው ላይ በስካር መንፈስ ንግግር ማድረጋቸው ተመዝግቧል፡፡ አሟቸው ስለነበረ ለህመም ማስታገሻ እንዲሆናቸው የወሰዱት ዊስኪ ነው ያሰከራቸው የሚል ምክንያት እንደተሰጠላቸው ተጽፏል፡፡ በ1873 ዩሊሰስ ኤስ ግራንት በበዓለ ሲመታቸው ድግስ ላይ »በድግሱ ቦታ ሰማያዊ ወፎች ቢበሩልኝ እንዴት ደስ ባለኝ ብለው ነበር" እና ሐሳባቸው ይሙላ ተብሎ ወፎች ለትዕይንት እንዲበሩ ተደረገ፡፡ ክፋቱ ብርዱ ነበር እና ወፎቹን ክንፋቸውን እያደረቀ እንዳረገፋቸው ይነገራል፡፡ የወፍ ነገር ከተነሳ እ አ አ በ1973ም ሪቻርድ ኒክሰን ርግቦች የበዓለ ሲመታቸው የሰልፍ ትዕይንት በሚያልፍበት መንገድ እንዳይገኙ ለማባረር ኬሚካል አስረጭተው ነበር እና የበዐሉ ታዳሚዎች የዋሽንግተኑ ፔንሲልቬኒያ አቨኑ ጎዳና ላይ መደዳውን ኬሚካሉ የገደላቸውን ርግቦች ሬሳ እንዳይረግጡ እየዘለሉ ያልፉ እንደነበር በፕሬዝደንታዊ በዓለ ሲመት ታሪክ ተመዝግቧል፡፡  

የጥምቀት በዓል አከባበር - በዋሽንግተን ዲሲ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አምስት አብያተ ክርስቲያናት የጥምቀት በዓልን ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አዘጋጅነ
የአሜሪካ ድምፅ

የጥምቀት በዓል አከባበር - በዋሽንግተን ዲሲ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አምስት አብያተ ክርስቲያናት የጥምቀት በዓልን ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት በጋራ አክብረዋል፡፡ የአከባበር ሥነ ሥርዐቱ ምን ይመስል እንደነበር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ

የትራምፕ ሁለተኛ የሥልጣን ዘመን ለአፍሪካ ምን ሊመስል ይችላል?

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሥልጣን እየተመለሱ ባሉበት ወቅት ከአፍሪካ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት በተለይ ከፀጥታ እና ደህንነት ትብብር አንፃ
የአሜሪካ ድምፅ

የትራምፕ ሁለተኛ የሥልጣን ዘመን ለአፍሪካ ምን ሊመስል ይችላል?

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሥልጣን እየተመለሱ ባሉበት ወቅት ከአፍሪካ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት በተለይ ከፀጥታ እና ደህንነት ትብብር አንፃር ምን ሊመስል ይችላል የሚለው ጥያቄ ጎልቶ ይነሳል። አፍሪካ ለአሜሪካ ቀዳሚ የፖለቲካ፣ የደህንነት እና የስትራቴጂ አቅጣጫ አለመሆኗን የሚገልጹት የአፍሪካ ጉዳይ ተንታኞች፣ ትራምፕ በአፍሪካ ላይ ያላቸው ትኩረት እንደ ሩሲያ እና ቻይና ያሉ ሀያል ሀገራትን በመገዳደር ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል።

ተኩስ አቁሙ ተግባራዊ ኾነ፣ ሃማስ የመጀመሪያዎቹን ታጋቾች ለቀቀ

በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ውል ዛሬ እሁድ ሥራ ላይ ውሏል። ስምምነቱ ጋዛ ላይ ለዐስራ አምስት ወራት የቀጠለውን ጦርነት ለስድስት
የአሜሪካ ድምፅ

ተኩስ አቁሙ ተግባራዊ ኾነ፣ ሃማስ የመጀመሪያዎቹን ታጋቾች ለቀቀ

በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ውል ዛሬ እሁድ ሥራ ላይ ውሏል። ስምምነቱ ጋዛ ላይ ለዐስራ አምስት ወራት የቀጠለውን ጦርነት ለስድስት ሳምንታት በሚገታው የተኩስ አቁም ውል መሠረት   የሃማስ ታጣቂዎች የያዟቸውን በርካታ ታጋቾች እንዲለቅቁ ይጠይቃል። ዛሬ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ በሰዓታት ውስጥ ሃማስ የመጀመሪያዎቹን ሦስት ወጣት ሴቶች የለቀቀ ሲሆን ቀይ መስቀል በአጀብ ወደ ጋዛ በመግባት የተለቀቁትን ታጋቾች ተረክቧል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሃማስ ዛሬ እሁድ ይለቃል የተባለውን ሦስት ታጋቾች ስም ዝርዝር ሳይሰጠን ስምምነቱ ተግባራዊ አይሆንም በማለታቸው ተግባራዊ የሆነው ከታቀደው ሰዓት በሦስት ሰዓት ገደማ ዘግይቶ ነው። ኔታንያሁ በአገሩ ሰዓት ጠዋት ሁለት ተኩል ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የታቀደው ተኩስ አቁም ሃማስ «እሰጣለሁ» ያለውን የሚለቀቁ ታጋቾች ስም ዝርዝር ሳይሰጥ ተግባራዊ እንዳይሆን ለመከላከያ ኃይሎች ትዕዛዝ ሰጥተዋል ሲል ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አስታውቋል። ይህንኑ ተከትሎ ሃማስ ስም ዝርዝሩን ከሰጠ በኋላ እስራኤል ተኩስ አቁሙ አምስት ሰዓት ተኩል ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቃለች። ሃማስ ስም ዝርዝሩ የዘገየው በቴክኒክ እክል ምክንያት እንደሆነ ጠቅሶ ስምምነቱን እንደማከብር በድጋሚ አረጋግጣለሁ ሲል መግለጫ አውጥቷል። ይህ በዚህ እንዳለ አክራሪ ብሔርተኛው የእስራኤል የብሔራዊ ጸጥታ ሚንስትር ኢታማር ቤን ጋቪር የተኩስ አቁም ውሉን በመቃወም ሥራ መልቀቃቸው ተዘግቧል።

አዲስ አበባ ላይ ዛሬ የተከበረው የጥምቀት በዓል

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ የተ
የአሜሪካ ድምፅ

አዲስ አበባ ላይ ዛሬ የተከበረው የጥምቀት በዓል

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ የተመዘገበው የጥምቀት በዓል ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በድምቀት ተከብሯል። በዓል ከሚከበርባቸው ቀደምት ቦታዎች አንዱ ጃን ሜዳ ሲኾን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተገኙበት፣ የጥምቀት ሥነ-ስርዐቱ ተከናውኗል፡፡ ፓትሪያርኩ በንግግራቸው፣ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል። የእምነቱ ተከታዮች እና ጎብኚዎችም አስተያየት ሰጥተውናል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ቲክ ቶክ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አገልግሎት መስጠት አቆመ

ማኅበራዊ መገናኛው ቲክ ቶክ ከትላንት ቅዳሜ ማታ ጀምሮ በዩናይትድ ስቴትስ አገልግሎት መስጠት አቁሟል። አሜሪካ ውስጥ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ቲክቶክ ከአ
የአሜሪካ ድምፅ

ቲክ ቶክ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አገልግሎት መስጠት አቆመ

ማኅበራዊ መገናኛው ቲክ ቶክ ከትላንት ቅዳሜ ማታ ጀምሮ በዩናይትድ ስቴትስ አገልግሎት መስጠት አቁሟል። አሜሪካ ውስጥ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ቲክቶክ ከአፕል እና ጉግል መተግበሪያዎች  የተነሳው አገልግሎቱ እንዲቆም የወጣው ሕግ በዕቅዱ መሠረት ዛሬ ዕሁድ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ነው። ትላንት ቀደም ብሎ ተመራጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ነገ አስተዳደራቸውን ሲጀምሩ እገዳው ተግባራዊ እንዳይሆን ለቲክቶክ የሦስት ወር ጊዜ  ሳልሰጥ አልቀርም ያሉ ሲሆን ቲክ ቶክ ለደምበኞቹ በወጣው ማሳሰቢያ ላይ ጠቅሶታል። የቻይና ባይትዳንስ ኩባኒያ ንብረት የሆነው ቲክቶክ አሜሪካ ውስጥ ላሉት ተጠቃሚዎቹ ወደመተግበሪያው ለመግባት ሲሞክሩ  አገልግሎቱ መቋረጡን ያስታወቀው ትላንት ማታ ለአምስት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ላይ ነው።

ትረምፕ ቅዳሜ በዋሽንግተን የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ አመሹ

ነገ ሰኞ ሁለተኛው በዓለ ሲመታቸው የሚከናወነው ዶናልድ ትረምፕ በዋዜማው ትላንት ቅዳሜ ምሽት ወደዋሽንግተን መጥተው የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ  ተገኝተዋል።
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ ቅዳሜ በዋሽንግተን የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ አመሹ

ነገ ሰኞ ሁለተኛው በዓለ ሲመታቸው የሚከናወነው ዶናልድ ትረምፕ በዋዜማው ትላንት ቅዳሜ ምሽት ወደዋሽንግተን መጥተው የደስታ መግለጫ ድግሥ ላይ  ተገኝተዋል። ከአራት ዓመታት በፊት ደጋፊዎቻቸው  የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ወርረው ጥቃት ባደረሱበት ሁናቴ ከተማዋን ለቅቀው የሄዱት ሪፐብሊካኑ ትረምፕ አሁን በድል አድራጊነት ተመልሰዋል።   ትላንት ማታ ዋሽንግተን አቅራቢያ  ስተርሊንግ ቨርጂኒያ በሚገኘው የጎልፍ መጫወቻቸው ትረምፕ ናሽናል ጎልፍ ክለብ በተካሄደው ድግሥ ቤተሰቦቻቸው፥ ደጋፊዎቻቸው እና የፖለቲካ አጋሮቻቸው ታድመዋል።  የኦፔራ ስልት ድምጻዊው ክሪስቶፈር ማኪዮ  የዘፈነ ሲሆን   ርችትም  ተተኩሷል። የነገው በዓለ ሲመት  እጅግ ኃይለኛ ብርድ ይኖራል መባሉን ተከትሎ በልማዱ ካፒቶል ሕንጻ ደረጃ ላይ የሚከናወነውን ቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት ጨምሮ አብዛኛውን ደጅ የሚካሄድ ዝግጅት ወደሕንጻው ውስጥ ለማዛወር አዘጋጆቹ ጥድፊያ ላይ ናቸው።   ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ በአርሊንግተን መካነ መቃብር የአበባ ጉንጉን ማስቀመጥ ሥነ ሥርዓት ላይ ይገኙና በመቀጠል በዋሽንግተን ዲሲ የደጋፊዎቻቸው ስብሰባ ላይ ይገኛሉ።  

በደምበል ሐይቅ ላይ የተከበረው የጥምቀት ከተራ በዓል

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ደምበል ሐይቅ ላይ የጥምቀት ከተራ በዓል በኃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዐቶች ተከብሯል። የገዳማቱ ዕድሜ
የአሜሪካ ድምፅ

በደምበል ሐይቅ ላይ የተከበረው የጥምቀት ከተራ በዓል

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ደምበል ሐይቅ ላይ የጥምቀት ከተራ በዓል በኃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዐቶች ተከብሯል። የገዳማቱ ዕድሜ ጠገብ መኾንና በዓሉ በሐይቁ ላይ መከበሩ የተለየ ውበትና ትርጉም እንደሚሰጠው፣ በደሴቶቹ ላይ የሚገኙት ቤተ ክርስቲያናት ስብከተ ወንጌል ኃላፊ ዲያቆን ዘነበ ዋቆ ተናግረዋል። የባቱ ከተማ ነዋሪው አቶ አለሙ በዳዶም፣ ታቦታቱ በተለይ ውሃው ላይ ሲገናኙ የሚፈጥረዉ ስሜት ልዩ መኾኑን ገልጸዋል። የበዓሉን ድባብ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

Get more results via ClueGoal