ጣሊያን 49 ፍልሰተኞችን ወደአልቤኒያ ላከች
newsare.net
ጣሊያን ባህር ላይ ያገኘቻቸውን 49 ፍልሰተኞች በባሕር ኃይል መርከብ አሳፍራ ወደአልቤኒያ ልካለች። ጣሊያን ስደተኞችን በሦስተኛ ሀገር ለማስፈር ያላት ዕቅድጣሊያን 49 ፍልሰተኞችን ወደአልቤኒያ ላከች
ጣሊያን ባህር ላይ ያገኘቻቸውን 49 ፍልሰተኞች በባሕር ኃይል መርከብ አሳፍራ ወደአልቤኒያ ልካለች። ጣሊያን ስደተኞችን በሦስተኛ ሀገር ለማስፈር ያላት ዕቅድ በፍርድ ቤት ክስ ቢከፈትበትም በዕቅዷ ለመግፋት ባደረገችው ሙከራ የላከቻቸው ስደተኞች ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ አልቤኒያ ወደብ መድረሳቸውን ሮይተርስ እማኞቹን ጠቅሶ ዘግቧል። ፍልሰተኞቹ ተመዝግበው ከወደቡ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኝ ማቆያ ካምፕ እንደሚላኩ ታውቋል። የጣሊያኑ የጆርጂያ መሎኒ መንግሥት አልቤኒያ ውስጥ ሁለት ፍልሰተኛ መቀበያ ማዕከሎችን አቋቁሟል። የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር በባህር ወደግዛቱ የሚፈልሱ ስደተኞችን ቁጥር ለመገደብ በሚል የህብረቱ አባል ካልሆነ ሀገር ጋር እንዲህ ያለ ስምምነት በማድረግ የመጀመሪያ መሆኑ ተመልክቷል። ባለፈው ሕዳር በዕቅዱ ሕጋዊነት ዙሪያ ጥያቄ ያነሱ የሮም ፍርድ ቤት ዳኞች ወደአልቤኒያ የተላኩት ስደተኞች ትዕዛዝ መስጠታቸውን ተከትሎ በሁለቱም የማቆያ ካምፖቹ እስካሁን ስደተኞች እለመኖራቸውን ዘገባው ጨምሮ አውስቷል። Read more