Ethiopia



አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ኾነው ተሾሙ

ዛሬ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ/ም መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ብርሃኑ አዴሎን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽ

የፈረንሳይ ኃይሎች ከቻድ ሙሉ ለሙሉ ለቀው ወጡ

የፈረንሳይ ኃይሎች ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ቻድ ሙሉ ለሙሉ ለቀው ወጥተው መጨረሳቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድርስ በደስታ ተቀብለውታል። ይህም ፈረንሳ
የአሜሪካ ድምፅ

የፈረንሳይ ኃይሎች ከቻድ ሙሉ ለሙሉ ለቀው ወጡ

የፈረንሳይ ኃይሎች ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ቻድ ሙሉ ለሙሉ ለቀው ወጥተው መጨረሳቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድርስ በደስታ ተቀብለውታል። ይህም ፈረንሳይ ጂሃዲስት ታጣቂዎች በስፋት ከሚንቀሳቀሱበት የአፍሪካ ሳህል ቀጠና የመውጣቷ ሂደት የመጨረሻው ምዕራፍ ነው ተብሏል። ከአንድ ቀን በፊት በዋና ከተማው ን'ጃሚና በዝግ በተካሄደ ወታደራዊ ስነስርዓት ዴቢ ለቻድ ኃይሎች እና ዲፕሎማቶች ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ፈረንሳይ በመካከለኛው አፍሪካውቷ ሀገር የነበራትን የመጨረሻ የጦር ሰፈር አስረክባለች። ቻድም ከቀድሞ ቅኝ ገዢዋ ጋር የነበራትን ወታደራዊ ትብብር ሙሉ ለሙሉ አቋርጣለች። ከዚህ በኃላ የቻድ ባንዲራ ብቻ በሚውለበለብበት የጦር ሰፈር ሆነው ንግግር ያደረጉት ዴቢም፣ ከፈረንሳይ ጋር ያለንን ወታደራዊ ትብብር ብናቋርጥም፣ ግንኙነታችንን ግን እንቀጥላለን ብለዋል። አክለውም ቻድ የበለጠ ጠንካራ እና የተሻለ ጦር እንደምትገነባ እና በመከባበር፣ እንዲሁም ነፃነትን እና በሉዓላዊነትን በአማከለ መልኩ አዳዲስ ትብብሮችን እንደምትፈጥር አመልክተዋል። ቻድ ከቅኝ ግዛት ነፃ መሆኗን ካወጀችበት እ.አ.አ 1960 አንስቶ፣ የፈረንሳይ ወታደሮች እና ተዋጊ አውሮፕላኖች በቻድ ቋሚ መቀመጫ የነበራቸው ሲሆን፣ የቻድን ጦር በመገንባት እንደረዱ ተመልክቷል። በተለይ ፈረንሳይ በማሊ፣ በቡርኪናፋሱ እና ኒጀር የተደረጉትን መፈንቅለ መንግስቶች ተከትሎ ከሀገራቱ እንድትወጣ ስትደረግ፣ በሳህል ቀጠና ውስጥ የነበራት ብቸኛው ትስስር የቻድ ጦር ሰፈር ነበር። 

በዋሽንግተኑ የአውሮፕላን አደጋ ላይ ምርመራ ቀጥሏል

ረቡዕ ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በረራ ላይ እያሉ በመጋጨታቸው ለ67 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑትን ሁለት አውሮፕላኖች ከወደቁበት የፖቶማክ ወንዝ ለ
የአሜሪካ ድምፅ

በዋሽንግተኑ የአውሮፕላን አደጋ ላይ ምርመራ ቀጥሏል

ረቡዕ ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በረራ ላይ እያሉ በመጋጨታቸው ለ67 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑትን ሁለት አውሮፕላኖች ከወደቁበት የፖቶማክ ወንዝ ለማውጣት የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው። ከበርካታ የአሜሪካ ተቋማት የተውጣጡት መርማሪዎች፣ ከሄሊኮፕተር ጋር ተጋጭቶ ወንዙ ውስጥ በገባው የአሜሪካ አየር መንገድ ውስጥ የሚገኘውን እና «ጥቁሩ ሳጥን» በመባል የሚታወቀውን የበረራ መረጃ የሚያስቀምጥ መሳሪያ ማግኘት ችለዋል። ዋናተኞች ወደ ወንዙ ውስጥ ጠልቀው በመግባት ተጨማሪ የአውሮፕራኑን ስብርባሪ አካል ለማግኘት እንደሚሞክሩም የእሳት አደጋ መከላከያ ባለስልጣናት አመልክተዋል። የብሔራዊ ትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ የበረራ መረጃ መመዝገቢያውን ሳጥን እና በአብራሪዎቹ ክፍል ውስጥ የተቀዱ የድምፅ መረጃዎችን ከመረመረ በኃላ፣ አውሮፕላኖቹ በምን ምክንያት እንደተጋጩ ፍንጭ ሊያገኝ እንደሚችል እየተጠበቀ ነው። በአሜሪካ አየር መንገድ ከተሳፈሩት መንገዶችን እና የበረራ ሰራተኞች መካከል በህይወት የተገኘ የሌለ ሲሆን በወታደራዊ ሄሎኮፍተሩ ውስጥ የነበሩት ሦስት ሰዎች በሙሉ ህይወታቸው ማለፉን የፌደራል እና የአካባቢው ባለስልጣናት ሐሙስ እለት አረጋግጠዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለፌደራሉ የበረራ አስተዳደር መስሪያ ቤት ምክትል አስተዳዳሪ መሾምን ያካተተ ሁለት የሥራ ማስፈፀሚያ ትዕዛዞችን ሐሙስ ከሰዓት በኃላ ፈርመዋል። ትዕዛዙን በፈረሙበት ወቅትም፣ ለደረሰው የግጭት አደጋ የብዝሃነት መርሃ ግብሩ ተጠያቂ ነው ሲሉ ያለምንም ማስረጃ ከሰዋል። ትራምፕ በፌደራል መንግስት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የተተገበሩ የብዝሃነት፣ እኩልነት እና አካታችነት ፖሊሲዎችን በመጥቀስ፣ በዲሞክራት ፕሬዝዳንቶች ባራክ ኦባማ እና የጆ ባይደን የተመሩት የቀድሞ አስተዳደሮች የትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን የቅጥር መስፈርት ዝቅ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ይህን ለማወቅ «ምክንያታዊ አስተሳሰባቸውን» መጠቀማቸውን ገልጸዋል። በሄሊኮፕተሩ ላይ የነበሩትን ሦስቱንም ወታደሮች ጨምሮ ቢያንስ 28 አስክሬኖች እስካሁን ከወንዙ ማውጣት ተችሏል።   

ትረምፕ ስደተኞችን ወደ ጓንታናሞ ቤይ እንደሚልኩ አስታወቁ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ኪዩባ በሚገኘው ጓንታናሞ ቤይ እንዲያዙ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ለዚህም አስተዳደራቸው እ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ ስደተኞችን ወደ ጓንታናሞ ቤይ እንደሚልኩ አስታወቁ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ኪዩባ በሚገኘው ጓንታናሞ ቤይ እንዲያዙ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ለዚህም አስተዳደራቸው እስር ቤቱን ዝግጁ እንዲያደርግ የሚያስችል ሰነድ እንደፈረሙም ታውቋል። በኪዩባ የሚገኘው የአሜሪካ እስር ቤት፣ ጓንታናሞ ቤይ፤ ወታደራዊ እስረኞችን፣ የታሊባንና የመስከረም 11 የሽብር ጥቃት ተጠርጣሪዎችን በመያዙ ይታወቃል። የመከላከያ እና የሃገር ውስጥ ደህንነት መሥሪያ ቤቶች እስር ቤቱ 30 ሺሕ ስደተኞችን ለማስተናገድ እንዲችል ዝግጅት እንዲያደርጉም ትረምፕ አዘዋል። አንዳንዶቹ ስደተኞች ከፍተኛ ወንጀል የፈጸሙ በመሆኑና፣ የሃገራቸው መንግሥት አግቶ ያቆያቸዋል የሚል እምነት ስለሌላቸው፣ ወደ ጓንታናሞ እንድሚልኳቸው ትረምፕ አስታውቀዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የዋይት ሃውስ ባለሥልጣን፣ ትረምፕ ጓንታናሞን የተመለከተውን ሰነድ ቀድመው መፈረማቸውን ተናግረዋል። ሰነዱ ከተለመደው ፕሬዝደንታዊ ትዕዛዝ ለየት ያለ እና ‘ፌዴራል ሬጂስተር’ ተብሎ ለሚታወቀውና የመንግስት ሰነዶችን ለሚያትመው መሥሪያ ቤት እንደማይላክም ታውቋል። ለዕቅዱ ማስፈጸሚያ ገንዘብ እንዲመደብ ለማድረግ የአሜሪካ ምክር ቤት ይሁንታ እንደሚያስፈልገውም ታውቋል።

የባሕር ዳር ህፃናት "እናት' የኾነችው አሜሪካዊት

ኢትዮጵያ ውስጥ በወጣላት «ምህረት» የሚለው ስሟ የምታወቀው አሜሪካዊቷ ሜርሲ ኤሪክሰን ኢትዮጵያ ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ኖራለች፣ አማርኛም ትናገራለች።
የአሜሪካ ድምፅ

የባሕር ዳር ህፃናት "እናት' የኾነችው አሜሪካዊት

ኢትዮጵያ ውስጥ በወጣላት «ምህረት» የሚለው ስሟ የምታወቀው አሜሪካዊቷ ሜርሲ ኤሪክሰን ኢትዮጵያ ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ኖራለች፣ አማርኛም ትናገራለች። ምህረት በአማራ ክልል፣ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ለ20 ዓመታት የበጎ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ግሬስ ፋውንዴሽን መስራች ስትኾን፣ ተቋሙ አሳዳጊ አልባ ሆነው ተጥለው የተገኙ ጨቅላ ህፃናትን ሰብስቦ በማሳደግ እና የቀን ሥራ እየሠሩ ኑሯቸውን ለሚገፉ እናቶች ልጆቻቸውን በመያዝ የማቆያ አገልግሎትም ይሰጣል። ከኢትዮጵያዊ የትዳር አጋሯ ጋራ በመኾንም አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችንም ገንብተው ከ800 በላይ ልጆችን በነፃ እያስተማሩ ይገኛሉ። ከሜርሲ ኤሪክሰን ጋራ የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በምስራቅ ኮንጎ በሩዋንዳ የሚደገፉት አማፂያን ወደ ዋናው ከተማው እንደሚገፉ አስታወቁ

ምስራቃዊውን የኮንጎ ትልቅ ከተማ የተቆጣጠሩት በሩዋንዳ የሚደገፉ አማፂያን፣ ዋና ከተማውን ኪንሻን እስከሚቆጣጠሩ ድረስ ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ሐሙስ እለ
የአሜሪካ ድምፅ

በምስራቅ ኮንጎ በሩዋንዳ የሚደገፉት አማፂያን ወደ ዋናው ከተማው እንደሚገፉ አስታወቁ

ምስራቃዊውን የኮንጎ ትልቅ ከተማ የተቆጣጠሩት በሩዋንዳ የሚደገፉ አማፂያን፣ ዋና ከተማውን ኪንሻን እስከሚቆጣጠሩ ድረስ ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ሐሙስ እለት አስታውቀዋል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ በበኩላቸው አማፂያኑን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ወታደራዊ ቅስቀሳ እንዲደረግ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ የመከላከያ ሚንስትራቸውም ለውይይት የቀረበውን ጥሪ ውድቅ አድርገዋል። የኮንጎ መከላከያ ሚኒስትር ጋይ ካቦምቦ ሙአዲያምቪታ በቪዲዮ አማካኝነት ባስስተላለፉት መልዕክት፣ ውይይት ለማድረግ የሚደረግ ማንኛውም እቅድ «ወዲያውኑ እንዲከሽፍ ይደረጋል» ብለዋል። የፕሬዝዳንቱ የቅርብ አጋር የሆኑት ሙአዲያምቪታ በዚሁ መልዕክታቸው «እዚሁ ኮንጎ ቆይተን እንዋጋለን። እዚህ በህይወት መኖር ካልቻልን ደግሞ፣ እዚሁ እንሞታለን» ብለዋል። የኤም 23 አማፂያን በበኩላቸው ከመንግስት ጋራ ንግግር ለመጀመር ፈቃደኛ መሆናቸውን የተናገሩ ቢሆንም፣ ዓላማቸው ግን የፖለቲካ ስልጣን ለማግኘት መሆኑን ከቡድኑ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት ኮርኔል ናንጋአ ገልፀዋል። «ወደ ኪንሻሳ ሄደን ስልጣን መረከብ እና አገሪቱን መምራት እንፈልጋለን» ያሉት ናንጋአ፣ 1ሺህ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ዋና ከተማ እንዴት ለመግፋት እንዳሰቡ የገለጹት ነገር የለም። የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፓል ካጋሜ በኮንጎ ጉዳይ ከአንጎላ አቻቸው ጃአዎ ሎሬንኮ ጋራ መነጋገራቸውን አመልክተዋል። ሎሬንኮ ግጭቱ እንዲቆም ለማሸማገል እየሞከሩ ሲሆን፣ ከአንድ ቀን በፊት ከፕሬዝደንት ቲሺሴኬዲ ጋራ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር ሞክረዋል የተባሉ ክስ እንደቀረበባቸው ተገለጸ

ትላንት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ቡድን የተሾሙ ግለሰብ በትግራይ ክልል የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር መሞከራቸ
የአሜሪካ ድምፅ

የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር ሞክረዋል የተባሉ ክስ እንደቀረበባቸው ተገለጸ

ትላንት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ቡድን የተሾሙ ግለሰብ በትግራይ ክልል የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር መሞከራቸውን የጣቢያው ጊዜያዊ ሥራ አስከያጅ ገለጹ። ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰብ ላይም ጣቢያው ክስ መመስረቱን ተናገሩ። ጣቢያውን ሊቆጣጠሩ ነበር በሚል ወቀሳ ከቀረበባቸው ፣ አቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ ምላሽ ለማግኘት በእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ደውለን ስብሰባ ላይ መሆናቸው ስለገለፁን ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም። ጉዳዩ ኣስመልክቶ ከመቐለ ፖሊስ አዘዥ ኮማንደር አንድነት ነገሰ ተጨማሪ ማብራርያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም የመቐለ ከተማ ፖሊስ መምርያ በፌስቡክ ገጹ በአወጣው መረጃ፣ ትላንት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ኤፍኤም 104.4 “የተሾመኩት እኔ ነኝ” በሚል የተነሳ፣ ጊዜያዊ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበርና ፖሊሰ ሁኔታው ለማረጋጋት በቦታው ተገኝቶ እንደነበር አስታውቋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

እስራኤልና ሐማስ የእስረኛ እና ታጋች ልውውጥ አደረጉ

እስራኤል እና ሐማስ ዛሬ ሐሙስ ባደረጉት የእስረኞችና የታጋቾች ልውውጥ፣ ሶስት እስራኤላውያንና አምስት የታይላንድ ዜጎች የሚገኙበት ስምንት ታጋቾች መለቀቃ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤልና ሐማስ የእስረኛ እና ታጋች ልውውጥ አደረጉ

እስራኤል እና ሐማስ ዛሬ ሐሙስ ባደረጉት የእስረኞችና የታጋቾች ልውውጥ፣ ሶስት እስራኤላውያንና አምስት የታይላንድ ዜጎች የሚገኙበት ስምንት ታጋቾች መለቀቃቸውን የእስራኤል ሠራዊት አስታውቋል። በስምምነቱ መሠረት እስራኤል 110 ወታደሮችን ለቃለች፡፡ እስራኤላውያኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ እንዲገናኙ እንደሚደረግና የታይላንድ ዜጎችንም ከመግሥታቸው ጋራ እንደሚያገናኝ ሠራዊቱ ጨምሮ አስታውቋል። በተመሳሳይም 110 ፍልስጤማውያንን እስረኞችን የያዘ አውቶብስ ራማላህ፣ ዌስት ባንክ መድረሱ ታውቋል። በመቶ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞቹን በደስታ ተቀብለዋል። ከተለቀቁት ውስጥ የቀድሞ የፍልስጤማውያን ወታደራዊ ቡድን መሪ ዘካሪያ ዙቤዲ እንደሚገኝበት ታውቋል። ዙቤዲ በእስራኤል ላይ በርካታ ሕይወትን የቀጠፉ ጥቃቶችን በማቀነባበር ይከሰሳል።

ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ የአምስት ዓመት እስር ተፈረደባቸው

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለማዘዋወር በመሞከር
የአሜሪካ ድምፅ

ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ የአምስት ዓመት እስር ተፈረደባቸው

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለማዘዋወር በመሞከር ተጠርጥረው የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ በተመሠረተባቸው እነ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን ላይ ዛሬ ሐሙስ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም የእስር ቅጣት ወስኗል።  ቀሲስ በላይ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር የአምስት ዓመት እስር እና 10 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ማሳለፉን ከቀሲስ በላይ ጠበቆች አንዱ አቶ ዮናታን ዘውዴ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።   ቀሲስ በላይ የእስር ጊዜያቸውን  ከጨረሱ በኋላም ለሁለት ዓመት ከማንኛውም ማኅበራዊ ተሳትፎ እንዲገደቡም ፍርድቤቱ ወስኗል፡፡ ከቀሲስ በላይ ጋራ አንድ ላይ ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት 2ኛና 3ኛ ተከሳሾች ላይ ደግሞ እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት ከሦስት ወር እስራት እና የ3 ሺህ ብር ቅጣት  እንደተላለፈባቸው ጠበቃ ዮናታን ተናግረዋል፡፡ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአድራሻቸው ባለመገኘታቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ክሳቸው መቋረጡ ታውቋል።  በቀሲስ በላይ መዝገብ ስር ከተከሰሱት በሦስቱ ላይ ፍርድቤቱ ባለፈው  ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም “ በከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል”  የጥፋተኝነት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ በቀሲስ በላይ ላይ ፍርድቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው ካስገቡት የቅጣት ማቅለያ መካከል የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውና ህመምተኛ መሆናቸውን ጨምሮ አራት ማቅለያዎችን በመቀበል የወንጀል ደረጃቸው ከነበረበት “ እርከን 25” ወደ እርከን 21 ዝቅ በማድረግ መሆኑን ጠበቃቸው አቶ ዮናታን ተናግረዋል፡፡  ይሁንና በዚህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለጠቅላይ ፍርድቤት ይግባኝ ለመጠየቅ እየተዘጋጁ መሆኑንም ጠበቃቸው ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት ሒሳብ ቁጥር ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር በመሞከር ተጠርጥረው መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡

ኤም 23 ወደ ኪንሻሳ እንደሚገሰግስ አስታወቀ

ትላንት የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ከተማ ጎማን በአብዛኛው የተቆጣጠሩትና በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን፣ ወደ መዲናዋ ኪንሻሳ ግስጋሴያቸ
የአሜሪካ ድምፅ

ኤም 23 ወደ ኪንሻሳ እንደሚገሰግስ አስታወቀ

ትላንት የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ከተማ ጎማን በአብዛኛው የተቆጣጠሩትና በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን፣ ወደ መዲናዋ ኪንሻሳ ግስጋሴያቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። “የነጻነት ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን ነው” ያለው የአማጺያኑ መግለጫ፡፡ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቺሰኬዲ በበኩላቸው ከበድ ያለ ወታደራዊ ምላሽ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። አማጺያኑን የምትደግፈው ሩዋንዳ ፍላጎቷ በእ.አ.አ 1994 በሃገሪቱ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ላይ የተሳተፉ ተዋጊዎችን ለመደምሰስ እንደሆነ ብታስታውቅም፣ በማዕድን ሃብት ከበለጸገችው ኮንጎ ለዓለም የኤሌክትሮኒክስ ምርት ተፈላጊ ከሆነው ማዕድን ለማትረፍ ትሻለች የሚል ነቀፌታ ይቀርብባታል። “የነጻነት ግስጋሴያችንን እስከ ኪንሻሳ ድረስ እንቀጥላለን” ነው ያሉት ኤም 23ትን የሚጨምረው የአማጺያን ቅንጅት መሪ የሆኑት ኮርኔሊ ናጋ። በጎማ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት እንዲመለስ እንደሚያደርጉ የገለጹት የአማጺያኑ መሪ፣ የፀጥታ ጥበቃውም እንደሚደረግ ተናግረዋል። የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቺሰኬዲ ትላንት ለሃገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር፣ አሸባሪ ብለው ለጠሯቸው አማጺያኑ ግስጋሴ “ጠንከር ያለና የተቀናጀ” ያሉት ወታደራዊ ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

ከሄሊኮፕተር ጋራ የተጋጨው የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጓዦች በሙሉ አይተርፉም ተባለ

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ 60 መንገደኞችን የያዘ አንድ አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ረቡዕ ምሽት ተጋጭተው ፖቶማክ ወንዝ ውስ
የአሜሪካ ድምፅ

ከሄሊኮፕተር ጋራ የተጋጨው የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጓዦች በሙሉ አይተርፉም ተባለ

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ 60 መንገደኞችን የያዘ አንድ አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ረቡዕ ምሽት ተጋጭተው ፖቶማክ ወንዝ ውስጥ ተከስክሰዋል።  የአደጋ ሠራተኞች እስከ አሁን 28 አስከሬኖች ከወንዙ ማውጣቸውንም ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል። በአውሮፕላን ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች በሙሉ ሕይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉም ባለሥልጣናት ዛሬ ማለዳ አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት ሰዎችን በሕይወት ከማግኘት ወደ አስከሬን ፍለጋ ሥራ መሠማራታቸውን የዋሽንግተን ዲሲ የእሳት አደጋ መከላከያ ሃላፊ ጃን ዳናሊ አስታውቀዋል። “የሚተርፍ ሰው ይኖራል ብለን አናምንም” ብለዋል ኃላፊው። ስድሳ መንገደኞችን እና አራት ሠራተኞችን ይዞ ከካንሳስ የተነሳው የአሜሪካን አየር መንገድ አውሮፕላን በዋሽንግተን ሬገን አየር ማረፊያ ለማረፍ በመዘጋጀት ላይ ሳለ ነበር ሦስት ወታደሮችን ከያዘውና በሥልጠና ላይ ከነበረው ‘ብላክ ሆክ’ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ጋራ የተጋጨው። ከአደጋው የተረፉ እንዳሉ ለማግኘት ሦስት መቶ የሚሆኑ የአደጋ ሠራተኞችና ባሕር ሰርጓጆች ቀዝቃዛውን የፖቶማክ ወንዝ ውሃ ምሽቱን ሁሉ ሲያስሡ ቢያድሩም በሕይወት ያገኙት ሰው እንደሌለ ታውቋል። የአሜሪካ ብዙኅን መገናኛ በርካታ አስከሬኖች ከወንዙ ውስጥ መውጣታቸውን በመዘገብ ላይ ናቸው። ከተሳፋሪዎች ውስጥ የአሜሪካ ‘ፊገር ስኬቲንግ’ ወይም የበረዶ ላይ ትርዒት ስፖርት ቡድን ዓባላትና ቤተሰቦቻቸው እንደሚገኙበት የስፖርት ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከእነዚህም ውስጥ ሁለቱ አሠልጣኞች ሩሲያዊ የቀድሞ የበረዶ ላይ ትርዒት የኦሎምፒክ አሸናፊዎች መሆናቸውን ክሬምሊን አረጋግጧል።

አንድ የመንገደኞች አውሮፕላንና ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ዋሽንግተን ዲሲ አየር ማረፊያ አቅራቢያ ተጋጩ

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄኪኮፕተር ረቡዕ ምሽት ተጋጭተው ፖቶማክ ወንዝ ውስጥ ተከስ
የአሜሪካ ድምፅ

አንድ የመንገደኞች አውሮፕላንና ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ዋሽንግተን ዲሲ አየር ማረፊያ አቅራቢያ ተጋጩ

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄኪኮፕተር ረቡዕ ምሽት ተጋጭተው ፖቶማክ ወንዝ ውስጥ ተከስክሰዋል። በአሜሪካ አየር መንገድ የሚተዳደረው አውሮፕላን 60 መንገደኞችን እንደያዘ ሲታወቅ ሄሊኮፕተሩ ደግሞ ሶስት ሰዎችን ይዞ ነበር ተብሏል። የአደጋ ሠራተኞች ይህ ዜና በሚታተምበት ሰዓት ርብርብ ላይ ሲሆኑ፡ ሕይወታቸውን ያጡ በርካታ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ሪፖርቶች አመልክተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት እንዲቀር ትረምፕ ግፊት እያደረጉ ነው

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ “በመወለድ የሚገኝ ዜግነት” በመባል የሚታወቀው የዜግነት መብት’ እንዲቀር ወይም እንዲቋረጥ የሚያደርግ ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ (ትዕ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት እንዲቀር ትረምፕ ግፊት እያደረጉ ነው

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ “በመወለድ የሚገኝ ዜግነት” በመባል የሚታወቀው የዜግነት መብት’ እንዲቀር ወይም እንዲቋረጥ የሚያደርግ ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ (ትዕዛዝ) ፈርመዋል፡፡ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1868 የጸደቀው 14ኛው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ አንድ ሰው የወላጆቹ የዜግነት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ውስጥ እስከተወለደ ድረስ የዜግነት መብቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን የሲቪል መብቶች ዋና አካል ተደርጎ ይታያል፡፡ የፕሬዝደንት ትረምፕ ትዕዛዝ ታዲያ በአስፈጻሚው አካል ሥልጣን እና በሕገ መንግሥት ማሻሻያው ዙሪያ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ ክርክሮች ቀስቅሷል። የአሜሪካ ድምጿ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዘጋቢ አሊን ባሮስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የትረምፕ አስተዳደር ሥራቸውን ለሚለቁ የመንግሥት ሠራተኞች ጉርሻ እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲሱ የዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር፣ ፍላጎት ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች በመጪው መስከረም መጨረሻ ሥራቸውን በፈቃዳቸው የሚለቁ ከሆነ የስምንት ወር ደመወዝ
የአሜሪካ ድምፅ

የትረምፕ አስተዳደር ሥራቸውን ለሚለቁ የመንግሥት ሠራተኞች ጉርሻ እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲሱ የዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር፣ ፍላጎት ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች በመጪው መስከረም መጨረሻ ሥራቸውን በፈቃዳቸው የሚለቁ ከሆነ የስምንት ወር ደመወዝ ጉርሻ እንደሚሰጥ ትላንት ለመንግሥት ሠራተኞች በላከው ኢሜይል አስታውቋል። ፕሮግራሙ የዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችንና ሠራተኞችን ለመቀነስ የያዘው ዕቅድ አካል መሆኑ ተመልክቷል። ሠራተኞች ፍላጎታቸውን እስከ መጪው ሐሙስ ማለትም እአአ የካቲት 6 ቀን ድረስ ማሳወቅ እንዳለባቸው ተመልክቷል። ይህን የሚያደርጉ ሠራተኞች፣ የመንግሥት ሠራተኞች ሙሉ ለሙሉ ከቢሮ እንዲሠሩ የሚያዘው ደንብ ላይመለከታቸው እንደሚችልም ታውቋል። በስደተኞችና በብሔራዊ ፀጥታ ጉዳይ ላይ የሚሠሩ እንዲሁም የፖስታ ቤት ሠራተኞች ፕሮግራሙ እንደማይመለከታቸውም ተመልክቷል። የመንግሥት ሠራተኞችን የሚወክሉ የሠራተኛ ማኅበራት የአስተዳደሩን ሐሳብ ተቃውመዋል። ሠራተኞች እንዳይስማሙም መክረዋል። “የፌዴራል ሠራተኞች ታማኝ፣ አስተማማኝና በየቀኑ ለመሻሻል የሚጥሩ መሆን አለባቸው” ብሏል ከአስተዳደሩ የተላከው መልዕክት፡፡ የቪኦኤ ሠራተኞችን ጭምር የሚወክለው የአሜሪካ መንግሥት ሠራተኞች ፌዴሬሽን ኃላፊ ኤቨረት ኬሊ፣ «ሠራተኞች አዲሱ ፕሮግራም በፈቃደኝነት የሚያደርጉት ጉዳይ አድርገው እንዳያዩት» አሳስበዋል። አክለውም ፣"የአስተዳደሩ ተግባር የሚያሳየው በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ጤናማ ያልሆነ አካባቢን መፍጠርና ሠራተኞች መቆየት ቢሹ እንኳ ሥራቸውን መቀጠል እንዳይችሉ ለማድረግ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ የመጀመሪያው በመርከብ የተጫነ ዕርዳታ ወደ ጋዛ ተላከ

ያዝ ለቀቅ የሚያደርገው የጋዛ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተባለ ርዳታ የያዘ የቱርክ መርከብ ግብጽ ወደብ መድረሱን አንድ የቱርክ ባ
የአሜሪካ ድምፅ

ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ የመጀመሪያው በመርከብ የተጫነ ዕርዳታ ወደ ጋዛ ተላከ

ያዝ ለቀቅ የሚያደርገው የጋዛ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተባለ ርዳታ የያዘ የቱርክ መርከብ ግብጽ ወደብ መድረሱን አንድ የቱርክ ባለሥልጣን እና የግብጽ ምንጮች አስታውቀዋል። መርከቡ ብርድ ልብስ፣ ድንኳን፣ ተንቀሳቃሽ መጸዳጃና ጄኔሬተሮች ጨምሮ 871 ቶን የሰብአዊ ርዳታ እንደያዘም ተነግሯል። “የጋዛ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ቁስል ለማዳንና ጊዜያዊ የመጠለያ ፍላጎታቸውንም ለማሟላት ተዘጋጅተናል” ሲሉ የቱርኩ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ምኒስትር አሊ የርሊካያ በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ አስታውቀዋል። ከግብጽ የቀይ ጨረቃ ማኅበር የተዋቀረ ቡድን ከቱርክ የተላከውን ዕርዳታ ተረክቦ ወደ ጋዛ ሠርጥ ለማድረስ በዝግጅት ላይ መሆኑን ከጋዛ ሠርጥ 50 ኪሎ ሜትር ላይ በሚርቀው ወደብ የሚገኙ ምንጭ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል። የተኩስ ማቆም ስምምነቱን ተከትሎ በመቶ የሚቆጠሩና ርዳታ የጫኑ ከባድ መኪናዎች ጋዛ ሲገቡ የተወሰነ ርዳታ ደግሞ በአየር ተጓጉዟል።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ መወያየቱን አስታወቀ

(ዝርዝሩን ከላይ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ) ከፋኖ ታጣቂ ቡድኖች ውስጥ የአንዱ መሪ የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ በእርሳቸው የሚመራው ቡድን ባለፈው ሳም
የአሜሪካ ድምፅ

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ መወያየቱን አስታወቀ

(ዝርዝሩን ከላይ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ) ከፋኖ ታጣቂ ቡድኖች ውስጥ የአንዱ መሪ የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ በእርሳቸው የሚመራው ቡድን ባለፈው ሳምንት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ በአማራ ክልል ተገናኝቶ መነጋገሩን ለአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል አስታውቀዋል። የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የተሰኘውና በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂ የፋኖ ቡድኖች አንዱ መሪ እንደሆኑ የሚገልጹት አቶ እስክንድር ነጋ፣ ከእርሳቸው ቡድን ወገን እና ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች የተውጣጡ የቴክኒካል ቡድኖች ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በስም ባልተጠቀሰ ሥፍራ ውይይት ማድረጋቸውን ከአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል። ከዓለም አቀፍ ቡድኑ ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት፣ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)፣ የአውሮፓ ኅብረት እንዲሁም በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ተወካዮች እንደሚገኙበት አቶ እስክንድር አስታውቀዋል። ስብሰባው የተካሂደው ከእነዚሁ ዓለም አቀፍ ተወካዮች ጋራ ከአንድ ወር በፊት የተደረገን የስልክ ውይይት ተከትሎ እንደሆነ አቶ እስክንድር ጠቁመዋል። “ይህ በቴክኒካል ቡድኖች መካከል የተካሄደ ስብሰባ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ስብሰባ ነው ያደረግነው።  የተወያየነውም በሃገሪቱ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መገናኘትና መነጋገር በምንችልበት ላይ ነው።” የውይይቱ ርዕሶች ምን እንደነበሩ የተጠየቁት አቶ እስክንድር፣ ከዓለም አቀፍ ቡድኑ ጋራ ለመተዋወቅ የተደረገና ቡድናቸው በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን አቋም ለመግልጽ የተፈጠረ ዕድል እንደነበር ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህምድ ባለፈው ወር ሲናገሩ፣ አማጺ ቡድኖች ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጡ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል። “ለአንድ ሺሕ ዓመት ብትዋጉንም፣ አታሸንፉንም፣ ስለዚህ ወደ ሰላም ኑ” ሲሉ ጠቅላይ ምኒስትሩ መናገራቸውም ይታወሳል። ከፌዴራል መንግሥት ጋራ መደራደር የሚለው ጉዳይ በውይይቱ ወቅት እንዳልተነሳም አቶ እስክንድር ገልጸዋል።  “ይህ ጉዳይ አልተነሳም” ያሉት አቶ እስክንድር “እናም ጉዳዩ ሳይነሳ መልስ መስጠት አልችልም። ይህ እኔ የምወስነው ጉዳይ አይደለም። ይህ በሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ የሚወሰን ነው። ጥያቄው ሲመጣ፣ ወደ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እወስደዋለሁ። እናም ሥራ አስፈጻሚው ምን እንደሚል እናያለን።” ብለዋል። መንግሥት በሃገሪቱ የሚገኙ ታጣቂዎችን በትኖ በፌዴራል መንግሥቱ ኅይል ሥር ለማካተትና ወደ ማኅበረሰቡ መልሰው እንዲቀላቀሉ ለማድረግ መወሰኑን ተከትሎ፣ በፋኖ ታጣቂዎችና በፌዴራል መንግሥት ኅይሎች መካከል በሚያዚያ 2015 ግጭት ተቀስቅሷል። በዛው ዓመት ነሐሴ ላይ መንግሥት 23 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በሚኖርበት በአማራ ክልል አስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል።  የአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ኅብረት፣ ኢጋድ፣ የአውሮፓ ኅብረት እንዲሁም ኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቋል። አስተያየታቸው እንደደረሰን እናቀርባለን።

ቴምብር አሰባሳቢው ህንዳዊ ዲፕሎማት 

የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቴምብሮች አሰባስቦ የያዘው ህንዳዊ ዲፕሎማት፣ ቴምብር አገልግሎት ላይ መዋል ከጀመረበት ጀምሮ የተለያዩ ሀገራት ቴምብሮችን ሰብስቧል።
የአሜሪካ ድምፅ

ቴምብር አሰባሳቢው ህንዳዊ ዲፕሎማት 

የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቴምብሮች አሰባስቦ የያዘው ህንዳዊ ዲፕሎማት፣ ቴምብር አገልግሎት ላይ መዋል ከጀመረበት ጀምሮ የተለያዩ ሀገራት ቴምብሮችን ሰብስቧል። ከ13 ዓመቱ ጀምሮ መሰብሰብ የጀመረው በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ ሠራተኛ ሃች ቬንካታቻላም ከ50 በላይ ሀገራትን ቆየት ያሉ ቴምብሮች አሰባስቦ ይዟል።   ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዩናይትድ ስቴትስ ኤም 23 ቡድን በምሥራቅ ኮንጎ ያደረሰውን ጥቃት አወገዘች

በሩዋንዳ የሚታገዘው ኤም 23 የተባለው ታጣቂ ቡድን ቁልፍ የሆነችውን የምሥራቅ ኮንጎ ዋና ከተማ ተቆጣጥሬአለሁ ማለቱን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ድርጊቱን አውግ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ ኤም 23 ቡድን በምሥራቅ ኮንጎ ያደረሰውን ጥቃት አወገዘች

በሩዋንዳ የሚታገዘው ኤም 23 የተባለው ታጣቂ ቡድን ቁልፍ የሆነችውን የምሥራቅ ኮንጎ ዋና ከተማ ተቆጣጥሬአለሁ ማለቱን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ድርጊቱን አውግዛለች። በተያያዘ ዜና የኬኒያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ  ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፌሊክስ ቲሺኬሴዲ እና ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ቀውሱን በሚመለከት  ነገ ረቡዕ ለመወያየት ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል።  የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር  እንዳስታወቀው  ትላንት ሰኞ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ቲሺሴኬዲን  በስልክ  ያነጋገሯቸው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ « በሩዋንዳ የሚታገዘው ኤም 23 ጎማ ላይ ያደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል። ዩናይትድ ስቴትስ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክን ሉዓላዊነት እንደምታከብር አረጋግጠውላቸዋል» ብሏል። ግጭቱ ወታደራዊ መፍትሄ የማይገኝለት እንደሆነ የጠቆሙት የኬኒያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ፕሬዝደንት ሺሴኬዲ እና ፕሬዝደንት ካጋሜ  ነገ ረቡዕ  ለመወያየት እንደተስማሙ አመልክተዋል። ይህ በዚህ እንዳለ ታጣቂው ቡድን ጎማን እንደያዘ ከተናገረም በኋላ ከተማዋ ውስጥ በቡድኑ እና በኮንጎ ኃይሎች መካከል ውጊያው እንደቀጠለ መሆኑን ኮንጎ የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለሥልጣን ትላንት ሰኞ ተናግረዋል። ኮንጎ ተቀማጩ የመንግሥታቱ ድርጅት አስተባባሪ ብሩኖ ለማርኪስ ከኪንሳሻ በሰጡት ቃል ውጊያው ጎማ ውስጥ በሁሉም አቅጣጫ መስፋፋቱን ጠቁመው ሁኔታው እጅግ አደገኛ እንደሆነ ገልጸዋል። የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት፥ የድርጅቱ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ እና ሌሎችም የድርጅቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ታጣቂው ቡድን በአስቸኳይ ውጊያ እንዲያቆም እና ከያዛቸው ግዛቶች እንዲወጣ ጠይቀዋል። የሩዋንዳ ኃይሎችም እንዲወጡ የጠየቁት ባለሥልጣናቱ ሁለቱ ወገኖች የአንጎላ  ፕሬዝደንት ዡዋው ሎሬንሶ ወደሚመሩት የሽምግልና ሂደት እንዲመለሱ አሳስበዋል።

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ለዳርፉር ወንጀል ተፈላጊዎች ማዘዣ እንደሚያወጣ አስታወቀ

በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ክፍለ ግዛት ሲቪሎች ላይ ግፍ በመፈጸም የተወነጀሉ ሰዎች እንዲያዙ የእሥር ማዘዣ ለማውጣት እየተዘጋጁ መሆኑን የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍ
የአሜሪካ ድምፅ

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ለዳርፉር ወንጀል ተፈላጊዎች ማዘዣ እንደሚያወጣ አስታወቀ

በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ክፍለ ግዛት ሲቪሎች ላይ ግፍ በመፈጸም የተወነጀሉ ሰዎች እንዲያዙ የእሥር ማዘዣ ለማውጣት እየተዘጋጁ መሆኑን የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ አስታወቁ። ላለፉት 19 ወራት ከሱዳን መንግሥት ኃይሎች ጋር እየተዋጉ ያሉት ታጣቂ ኃይሎች የጎሣ ማጽዳት አድራጎት በመፈጸም ተወንጅለዋል። የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ ካሪም ኻን ትላንት ለመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ትላንት ሰኞ በሰጡት ማብራሪያ ዳርፉር ውስጥ እነዚህ ወንጀሎች  «በየቀኑ አሁን በዚህ ሰዓትም ጭምር እየተፈጸሙ ነው» ብለዋል። ታጣቂዎቹ ድርጊቱን በጦር መሣሪያነት እየተጠቀመበት ነው ያሉት አቃቤ ህጉ ቢሮአቸው ከዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው የምስክሮች ቃል እና ሌሎችም መረጃዎች አሰባስቦ ጥልቅ የሆነ ግምገማ አካሂዶ መሆኑን ለምክር ቤቱ ገልጸዋል። የባይደን አስተዳደር ከመሰናበቱ ጥቂት ቀደም ብሎ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ቡድን እና ተባባሪዎቹ በሀገሪቱ እየተካሂደ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸሙ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን እንዳስታወቀ ይታወሳል።

ከሦስት መቶ ሺህ በላይ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮች ወደጋዛ ከተማ መመለሳቸው ተገለጸ

በእስራኤል እና በሐማስ ጦርነት የተፈናቀሉ ከሦስት መቶ ሺህ የሚበልጡ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮች ትላንት ሰኞ ወደ ሰሜናዊ ጋዛ  መመለሳቸውን በሐማስ የሚመራ
የአሜሪካ ድምፅ

ከሦስት መቶ ሺህ በላይ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮች ወደጋዛ ከተማ መመለሳቸው ተገለጸ

በእስራኤል እና በሐማስ ጦርነት የተፈናቀሉ ከሦስት መቶ ሺህ የሚበልጡ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮች ትላንት ሰኞ ወደ ሰሜናዊ ጋዛ  መመለሳቸውን በሐማስ የሚመራው የጋዛ ሰርጥ መንግሥት ባለስልጣናት ተናገሩ። ተፈናቃዮቹ የተመለሱት እስራኤል የፍተሻ ኬላዎቹን ከፍታ እንዲመለሱ መፍቀዷን ተከትሎ ነው። ፍልስጥኤማዊያኑ አብዛኞቹ በእግራቸው  የቻሉትን ያህል ዕቃ ተሸክመው  ጦርነቱ እንደተጀመረ ጥለውት ወደሸሹት እና ይኑር ይፍረስ ወደማያውቁት የቀድሞ መኖሪያቸው ተጉዘዋል።  እስራኤል የሐማስ ታጣቂዎችን እና ፈንጂ ያጠመዱባቸውን ህንጻዎች ዒላማ አድርጋ ባደረሰችው የቦምብ ድብደባ አብዛኛው አካባቢ ወድሟል። እስራኤል እ አ አ በ2023 ጥቅምት ውስጥ ጥቃቱን እንደጀመረች  ወደአንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ነዋሪዎች ከሰሜናዊ ጋዛ እንዲወጡ ማዘዟ ሲታወስ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ለመጀመሪያ ጊዜ መፈቀዱ ነው። ፍልስጥኤማዊያኑ ወደጋዛ ከተማ የተመለሱት በእስራኤል እና በሐማስ የተደረሰው የስድስት ሳምንታት የተኩስ አቁም የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት መሆኑ ነው። የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተከትሎ  እስካሁን  ሰባት ታጋቾች ከጋዛ ሲለቀቁ  እስራኤል  ሦስት መቶ የሚሆኑ ፍልስጥኤማዊያን እሥረኞች ለቅቃለች። ሰብዓዊ ረድዔትም በብዛት ወደጋዛ መግባት ጀምሯል። ትላንት እስራኤል እንዳለችው ሐማስ በመጀመሪያው የተኩሥ አቁም ውሉ ምዕራፍ ስለሚለቀቁት ታጋቾች እና ከቀሩት ታጋቾቹ መካከል ስምንቱ በሕይወት እንደሌሉ አሳውቋታል።  ሐማስ ተጨማሪ ታጋቾችን በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ እንደሚለቅቅ ተመልክቷል። ይህ በዚህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ « ጋዛን ለማጽዳት የሚደረገው » ሲሉ በገለጹት ጥረት ዮርዳኖስ እና ግብጽ ተጨማሪ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮችን እንዲቀበሉ የሚፈልጉ መሆኑን ተናግረዋል። ሆኖም ሁለቱ ሀገሮች ብቸኛው የመፍትሄ  እርምጃ ከእስራኤል ጎን ለጎን የፍልስጤም መንግሥት መመሥረት ብቻ መሆኑን በማመልከት ሃሳቡን ውድቅ አድርገውታል። ዩናይትድ ስቴትስ የፍልስጤም አገረ መንግሥት መቋቋምን ሃሳብ ለረጅም ጊዜ ስትደግፍ ቆይታለች። የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ግን ይቃወማሉ።

ሲ ዲ ሲ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያካሂዳቸውን ሥራዎች በአስቸኳይ እንዲያቆም ታዘዘ

የዩናይትድ ስቴትስ የጤና ባለሥልጣናት ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር የሚሠሯቸውን ሥራዎች በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል። ድንገተኛው ትዕዛዝ ያተ
የአሜሪካ ድምፅ

ሲ ዲ ሲ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያካሂዳቸውን ሥራዎች በአስቸኳይ እንዲያቆም ታዘዘ

የዩናይትድ ስቴትስ የጤና ባለሥልጣናት ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር የሚሠሯቸውን ሥራዎች በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል። ድንገተኛው ትዕዛዝ ያተኮረው በዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ተቋም ላይ ሲሆን የተቋሙ ባለሥልጣን የሆኑት ጆን ኒኬንጋሶንግ  ለከፍተኛ አመራሮች ዕሁድ ማታ በላኩት ማሳሰቢያ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር የሚሠሩ የተቋሙ ሠራተኞች በአስቸኳይ አቁመው ቀጣይ መመሪያ እስከሚሰጥ እንዲጠብቁ ማዘዛቸውን መመሪያውን የተመለከተው አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል። የጤና ጥበቃ አዋቂ ባለሞያዎች ድንገተኛው ትዕዛዝ አፍሪካ ውስጥ ማርበርግ ቫይረስ እና ኤምፖክስ የመሳሰሉ ወረርሽኞችን እና ሌሎችንም ዓለም አቀፍ የጤና ስጋቶችለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶች እና ምርምሮችን ያስተጓጉላል የሚል ስጋት እንዳላቸው አመልክተዋል። ትዕዛዙ የተሰጠው በዓለም ዙሪያ ያሉ የጤና ባለሥልጣናት በአሜሪካ እንስሳት ላይ የተቀሰቀሰውን የአእዋፍ ወረርሽኝ ለመከታተል ጥረት እያደረጉ ባለበት በዚህ ወቅት መሆኑ ተጠቁሟል። የተላለፈው መመሪያ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር  በትብብር የሚሠሩ ሥራዎች በሙሉ እንዲቋረጡ የሚያዝ ሲሆን የድርጅቱ መሥሪያ ቤቶች በአካል መጎብኘትም ይሁን በኢንተርኔት አማካይነት መገናኘት ይከለክላል። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስን ከዓለም የጤና ድርጅት አባልነት የማስወጣት ሂደት እንዲጀመር ባለፈው ሳምንት አስፈጻሚ ትዕዛዝ የፈረሙ ቢሆንም  ሂደቱ ወዲያውኑ አልተጀመረም። ከዓለሙ የጤና ድርጅት እንድትወጣ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት መፍቀድ አለበት። እስከዛ አሜሪካ የዓመቱን ክፍያዋን መፈጸም ያለባት ሲሆን ከድርጅቱ ለመውጣት የአንድ ዓመት ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መስጠት ይኖርባታል።

ጣሊያን 49 ፍልሰተኞችን ወደአልቤኒያ ላከች

ጣሊያን ባህር ላይ ያገኘቻቸውን 49 ፍልሰተኞች በባሕር ኃይል መርከብ አሳፍራ ወደአልቤኒያ ልካለች። ጣሊያን  ስደተኞችን በሦስተኛ ሀገር ለማስፈር ያላት ዕቅድ
የአሜሪካ ድምፅ

ጣሊያን 49 ፍልሰተኞችን ወደአልቤኒያ ላከች

ጣሊያን ባህር ላይ ያገኘቻቸውን 49 ፍልሰተኞች በባሕር ኃይል መርከብ አሳፍራ ወደአልቤኒያ ልካለች። ጣሊያን  ስደተኞችን በሦስተኛ ሀገር ለማስፈር ያላት ዕቅድ በፍርድ ቤት ክስ ቢከፈትበትም በዕቅዷ ለመግፋት  ባደረገችው ሙከራ የላከቻቸው ስደተኞች ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ አልቤኒያ  ወደብ መድረሳቸውን ሮይተርስ እማኞቹን ጠቅሶ ዘግቧል። ፍልሰተኞቹ ተመዝግበው ከወደቡ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ  ወደሚገኝ ማቆያ ካምፕ እንደሚላኩ ታውቋል። የጣሊያኑ የጆርጂያ መሎኒ መንግሥት አልቤኒያ ውስጥ ሁለት ፍልሰተኛ መቀበያ ማዕከሎችን አቋቁሟል። የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር በባህር ወደግዛቱ የሚፈልሱ ስደተኞችን ቁጥር ለመገደብ  በሚል የህብረቱ አባል ካልሆነ ሀገር ጋር እንዲህ ያለ ስምምነት በማድረግ የመጀመሪያ መሆኑ ተመልክቷል። ባለፈው ሕዳር በዕቅዱ ሕጋዊነት ዙሪያ ጥያቄ ያነሱ የሮም ፍርድ ቤት ዳኞች ወደአልቤኒያ የተላኩት ስደተኞች ትዕዛዝ መስጠታቸውን ተከትሎ በሁለቱም  የማቆያ ካምፖቹ እስካሁን ስደተኞች እለመኖራቸውን ዘገባው  ጨምሮ አውስቷል።  

በማርኮ ሩቢዮ  የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት  የአሜሪካ የአፍሪካ ፖሊሲ ምን ይመስል ይኾን? 

ማርኮ ሮቢዮ አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኾነዋል፡፡ ሩቢዮ ቻይናን በሚመለከት ጠንካራ አቋም ያላቸው ናቸው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአሜሪካ
የአሜሪካ ድምፅ

በማርኮ ሩቢዮ  የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት  የአሜሪካ የአፍሪካ ፖሊሲ ምን ይመስል ይኾን? 

ማርኮ ሮቢዮ አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኾነዋል፡፡ ሩቢዮ ቻይናን በሚመለከት ጠንካራ አቋም ያላቸው ናቸው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአሜሪካን ጥቅም በማራመድ እንደሚሠሩም ቃል ገብተዋል፡፡ ይሁን እንጂ አፍሪካን በሚመለከት የሚከተሉት ፖሊሲ እንደምን ያለ እንደሚሆን በዝርዝር አላሳወቁም፡፡ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት በበኩላቸው ሀገራቸው በአዲሱ የትረምፕ አስተዳደር ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ በሚኖራት ግንኙነት እንደሚተማመኑ ተናግረዋል፡፡ ኬት ባርትሌት ከጆሐንስበርግ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የተማሪዎች ፍላጎት አለማሳየት የምልክት ቋንቋ ሥልጠናን ስጋት ላይ ጥሏል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው የምልክት ቋንቋ ትምህርት፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተማሪዎችን እያገኘ ስላልሆነ፣ በስልጠናው ላይ እንቅፋት መፍጠሩን ዩኒቨ
የአሜሪካ ድምፅ

የተማሪዎች ፍላጎት አለማሳየት የምልክት ቋንቋ ሥልጠናን ስጋት ላይ ጥሏል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው የምልክት ቋንቋ ትምህርት፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተማሪዎችን እያገኘ ስላልሆነ፣ በስልጠናው ላይ እንቅፋት መፍጠሩን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ባለሞያዎች በበኩላቸው፣ «ችግሩ በምልክት ቋንቋ ዕድገት ላይ ችግር ይፈጥራል፣ መስማት የተሳናቸው ዜጎች አገልግሎት እንዳያገኙም ያደርጋል» ብለዋል፡፡ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ መስማት የተሳናቸው ዜጎች በአገልግሎት ተቋማት የተለያዩ ችግሮች እንደሚገጥሟቸው ገልፆ፣ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ስልት እየተዘጋጀ መኾኑን አመልክቷል፡፡

አሜሪካ እና ኮሎምቢያ ስደተኞችን የማስወጣት ስምምነት ላይ ደረሱ

ዩናይትድ ስቴትስ የኮሎምቢያ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በምታካሂዳቸው በረራዎች ዙሪያ ሁለቱ ሀገራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ፣ አሜሪካ ኮ
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካ እና ኮሎምቢያ ስደተኞችን የማስወጣት ስምምነት ላይ ደረሱ

ዩናይትድ ስቴትስ የኮሎምቢያ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በምታካሂዳቸው በረራዎች ዙሪያ ሁለቱ ሀገራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ፣ አሜሪካ ኮሎምቢያ ላይ ልትጥል የነበረውን የአጸፋ ርምጃዎች ማንሳቷን ዋይት ሃውስ አስታውቋል። ዋይት ሃውስ ጉዳዩን አስመልክቶ በአወጣው መግለጫ፣ ኮሎምቢያ ስደተኞቿን ያለምንም ክልከላ እንደምትቀበል፣ ይህም በአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች እንዲመለሱ ማድረግን እንደሚጨምር ሁለቱ ሀገራት መስማማታቸውን አስታውቋል። የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ ቀደም ብለው ሁለት የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሀገራቸው ላይ እንዳያልፉ ከልክለው የነበረ ሲሆን፣ ስደተኞችን የሚቀበሉት አሜሪካ በክብር እና በሲቪል አውሮፕላን አሳፍራ ስትልካቸው ብቻ ነው ብለው ነበር። ይህን ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኮሎምቢያ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ እንደሚጥሉ እና በአንድ ሳምንት ውስጥ ውሳኔያቸውን ካልቀየሩ ወደ 50 ከመቶ እንደሚያድግ አስታውቀው ነበር። ቦጎታ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲም የቪዛ አገልግሎቱን እንዲያቋርጥ አድርገዋል። ኮሎምቢያ አዲሱን ስምምነት ካላከበረች አዳዲስ ቀረጦች እና ማዕቀቦች እንደሚጣልባትም የዋይት ኃውስ መግለጫ ጨምሮ አመልክቷል። ስደተኞችን ያሳፈረው የመጀመሪያው አውሮፕላን ኮሎምቢያ እስከሚያርፍ ድረስም፣ በቀደመው ክልከላ ምክንያት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኮሎምቢያ ባለስልጣናት ላይ የጣለው የቪዛ ማዕቀብ እና በጉምሩክ ፍተሻዎች ላይ የሚደረገው የተጠናቀረ ፍተሻ ባለበት እንደሚቆይ ዋይት ኃውስ አመልክቷል። ኮሎምቢያ በበኩሏ ሕዝቦቿን መብታቸው እና ሰብዓውነታቸው በተጠበቀ መልኩ እንደምትቀበል አስታውቃለች። 

ቻይና የበሽታ ስጋት ካለባቸው ሀገራት የእንስሳት ምርቶች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች

ቻይና በእንስሳት በሽታ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ከአፍሪካ፣ ከእስያ እና ከአውሮፓ ወደ ሀገሯ ይገባ የነበረውን የበግ፣ የፍየል እና የዶሮ ስጋ ምርት አገደች።
የአሜሪካ ድምፅ

ቻይና የበሽታ ስጋት ካለባቸው ሀገራት የእንስሳት ምርቶች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች

ቻይና በእንስሳት በሽታ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ከአፍሪካ፣ ከእስያ እና ከአውሮፓ ወደ ሀገሯ ይገባ የነበረውን የበግ፣ የፍየል እና የዶሮ ስጋ ምርት አገደች። ቻይን በማንኛውም ዐይነት የስጋ ምርት ላይ እገዳውን የጣለችው፣ የዓለም ጤና ድርጅት በተለያዩ ሀገራት የበሽታ ወረርሽኝ መከሰቱን የሚገልጽ መረጃ ይፋ ከአደረገ በኋላ መሆኑን፣ የቻይና ጉምሩክ መሥሪያቤት እ.አ.አ ጥር 21 ያወጣችው ተከታታይ ማስታወቂያ አመልክቷል። እገዳው የዓለማችን ትልቅ የስጋ አቅራቢ የሆኑትን እንደጋና፣ ሶማሊያ፣ ካታር፣ ኮንጎ፣ ታንዛኒያ፣ ግብፅ፣ ቡልጋሪያ፣ ምስራቅ ቲሞር እና ኤርትራን እንደሚያጠቃልል ተገልጿል። በተጨማሪም የበግ ስጋ፣ የፍየል ስጋ እና ሌሎች ተያያዥ ምርቶችን ከፓኪስታን፣ ፍልስጤም፣ አፍጋኒስታን፣ ኔፓል እና ባንግላዲሽ ማስገባት ማቆሟንም ቻይና አስትውቃለች። 

ኤሎን መስክ የሚደግፈውን የጀርመን ጽንፈኛ ፓርቲን በመቃወም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰልፍ ወጡ

አሜሪካዊው የቴክኖሎጂ ቱጃር ኤሎን መስክ ኦልተርኔቲቭ ፎር ጀርመኒ (ኤ.ኤፍ.ዲ) ወይም በግርድፉ አማራጭ ለጀርመን የተሰኘውን ጸረ-ስደተኛ ፓርቲ፤ በድጋሚ መደገፉ
የአሜሪካ ድምፅ

ኤሎን መስክ የሚደግፈውን የጀርመን ጽንፈኛ ፓርቲን በመቃወም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰልፍ ወጡ

አሜሪካዊው የቴክኖሎጂ ቱጃር ኤሎን መስክ ኦልተርኔቲቭ ፎር ጀርመኒ (ኤ.ኤፍ.ዲ) ወይም በግርድፉ አማራጭ ለጀርመን የተሰኘውን ጸረ-ስደተኛ ፓርቲ፤ በድጋሚ መደገፉን ተከትሎ፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጀርመናውያን ትላንት ቅዳሜ የተቃውሞ ሰልፍ ወጥተዋል። በጀርመን በሚቀጥለው ወር የሕግ አውጪዎች ምርጫ ይካሄዳል። መስክ፣ በምሥራቅ ጀርመን ሃሌ ከተማ በሺዎች ለሚቆጠሩ የኤ.ኤፍ.ዲ ደጋፊዎች በቪዲዮ ባደርገው ንግግሩ፤ ፓርቲያቸው “ለወደፊቷ ጀርመን ሰናይ ተስፋ” ነው ሲል ተናግሯል። ኤሎን መስክ የቪዲዮ ንግግሩን ሲያደርግ የፓርቲው አጋር መሪ አሊስ ቫይደል ፈገግ እያሉ ሲመለከቱ  የታዩ ሲሆን፤ የሰልፉ ተሳታፊ የነበሩት የኤ.ኤፍ.ዲ ፓርቲዎች ደጋፊዎች ድጋፋቸውን በጩኸት አሳይተዋል።   ይህ በእንዲህ እንዳለ  በበርሊን እና በኮሎኝ ከ35 እስከ 40 ሺህ የሚደርሱ ሰልፈኞች እንደሚሆኑ ፖሊስ የገመታቸው ቁጥራቸው እጅግ የበዛ ተቃዋሚዎች ትዕይንተ ሰልፍ አድርገዋል። በበርሊን ለተቃውሞ የወጡት ሰልፈኞች “ለዴሞክራሲ የበራ የብርሃን ባህር” ሲሉ የሞባይል የስልኮቻቸውን መብራቶች በማብራት በጀርመን ታሪካዊ ስፍራ በሆነው ብራንደር በርግ ግንብ ጋር “መከላከል” የሚል ጽሁፍ ይዘው ወጥተዋል። ኤ.ኤፍ.ዲ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ለብዙ አስርት ዓመታት ነውር ሆኖ የዘለቀውን ቀኝ ዘመም ፓርቲ ድጋፍ  ማሳያት በተለየ መልኩ፤ በዚህ ዓመት 20 ከመቶ የሚሆን የህዝብ ድጋፍ በመያዝ ከመጭው ምርጫ በፊት ሪከርድ ሰብሯል። በተመሳሳይ የኤሎን መስክ የቅርብ አጋር የሆኑት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ  ለኤ.ኤፍ.ዲድ ፓርቲ ደጋፊዎች ምርጫው አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው “እንደሚመስለኝ ምርጫው የአውሮፓን አጠቃላይ ዕድል፣ ምናልባትም የአለምን እጣ ፈንታ ይወስናል” ብለዋል። መስክ በብሪታኒያ የሚገኙትን ጨምሮ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የአውሮፓ ፖለቲከኞችን በማህበራዊ መድረኩ ኤክስ በመጠቀም አስተያየት በመስጠት ሲያጨናንቅ ተስተውሏል። ኤ.ኤፍ.ዲ ፓርቲ ልክ እንደ ትራምፕ ሁሉ የስደተኞች ፍልሰት የሚቃወም፣ የአየር ንብረት ለውጥ የለም የሚል፣ የጾታ ፖለቲካን የሚቃወም፣ መደበኛ መገናኛ ብዙሃን የሀሳብ ነጻነትን የሚጥሱ ናቸው በማለት የሚኮንን ፓርቲ ነው።

ዴሞክራቲክ ኮንጎ አማጺያኑ እያየሉ ባሉበት ሰዓት ከሩዋንዳ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣለች

በሩዋንዳ በሚደገፉት አማፂያን እና በዴሞክራቲክ ኮንጎ መንግስት ኃይሎች መካከል፤  ቁልፍ በሆነችው ጎማ ከተማ ምሥራቃዊ ክፍል ጦርነት የተቀሰቀሰ ሲሆን፣ በት
የአሜሪካ ድምፅ

ዴሞክራቲክ ኮንጎ አማጺያኑ እያየሉ ባሉበት ሰዓት ከሩዋንዳ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣለች

በሩዋንዳ በሚደገፉት አማፂያን እና በዴሞክራቲክ ኮንጎ መንግስት ኃይሎች መካከል፤  ቁልፍ በሆነችው ጎማ ከተማ ምሥራቃዊ ክፍል ጦርነት የተቀሰቀሰ ሲሆን፣ በትንሹ 13 የሰላም አስከባሪ ሃይሎች እና የውጭ ሃገር ወታደሮች ህይወታቸው ሲያልፍ፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ተፈናቅለዋል። ዴሞክራቲክ ሪፐሊክ ኮንጎም  ከሩዋንዳ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች። የኤም 23 አማፂ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ  ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መኖሪያ እና የሰብዓዊና የጸጥታ ማዕከል ወደ ሆነችው ወደ ጎማ ግዛት በመገስገስ ብዙ ስፍራዎችን ተቆጣጥሯል። ኮንጎ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለሞያዎች፤ ሩዋንዳ  ከአስር ዓመት በፊት ከኮንጎ ጦር ሰራዊት  ተገንጥለው በወጡ ቱትሲዎች የሚመራውን ኤም23ን ትደግፋለች ሲሉ ወቅሰዋል። ይህም በዋናነት በማዕድን በበለፀገው ክልል ውስጥ ከሚንቀሳቀሱት በመቶዎች የሚቆጠሩ የታጠቁ ቡድኖች መካከል አንዱ ሲሆን፤ ሁኔታው ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ግጭት በመፍጠር ከዓለም ትልቁ ሰብዓዊ ቀውስን አስከትሏል። የዴሞክራቲክ ኮንጐ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትላንት ቅዳሜ ማምሻውን  ሀገራቸው ከሩዋንዳ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧን በመግለጽ በሩዋንዳ የሚገኙ ሁሉም የኮንጎ ዲፕሎማቲክ ሰራተኞች ከሀገሪቱ “በአፋጣኝ” እንዲወጡ መወሰኑን ተናግረዋል። ሩዋንዳ በጉዳዩ ላይ ወዲያውኑ አስተያየት አልሰጠችም።

ትራምፕ የፌደራል መንግስት ከካሊፎርኒያ ጎን እንደሚቆም አረጋገጡ 

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት አረብ በሰደድ እሳት የተጎዳችውን ካሊፎርኒያን በጎበኙበት ወቅት የፌደራል መንግስት ሙሉ በሙሉ ከካሊፎ
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ የፌደራል መንግስት ከካሊፎርኒያ ጎን እንደሚቆም አረጋገጡ 

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት አረብ በሰደድ እሳት የተጎዳችውን ካሊፎርኒያን በጎበኙበት ወቅት የፌደራል መንግስት ሙሉ በሙሉ ከካሊፎርኒያ ጎን ይቆማል ብለዋል፡፡ እንደአስፈላጊነቱም ተመልሰው ለመጎብኘት ቃል ገብተዋል፡፡  ትራምፕ በሎስ አንጀለስ ፓስፊክ ፓሊሳዴስ ሰፈር ውስጥ በሚገኝ የእሳት አደጋ ጣቢያ ለተሰበሰቡ የአካባቢው መሪዎች  “ እኔና ቀዳማዊት እመቤት በካሊፎርኒያ የተገኘነው ለካሊፎርኒያ ሰዎች ያለንን ፍቅር ለመግለጽ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።  ሰፈሩ በቅርብ ጊዜ በተከሰቱት የእሳት ቃጠሎዎች ክፉኛ ከተጠቁት አንዱ ሲሆን ተከታታይ ቤቶችም ወደ አመድነት ተቀይረዋል፡፡  በሎስ አንጀለስ አካባቢ ያሉ የእሳት አደጋ ተከላካዮች በከፍተኛ ንፋስ እና ደረቅ ሁኔታዎች ውስጥ በርካታ የእሳት ቃጠሎዎችን መጋፈጣቸውን እንደቀጠሉ ነው፡፡  ፕሬዘዳንት ትራምፕ በጉብኝታቸው አስቀድመው በአካባቢው በእግር ጉዞ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በሄሊኮፕተርም በአካባቢው ያለውን የማገገም ጥረቶችን ተመልክተዋል ።  ትራምፕ ካሊፎርኒያን ከመጎበኘታቸው በፊት በሃሪኬን ሄለን የተጎዳችውን ሰሜን ካሮላይና ጎብኝተዋል ፣እዚያም ለወራት የፈጀውን የማገገሚያ ጥረቶች ዙርያ ገለፃ ተደረጎላቸዋል።   

ሄግሴት በጠባብ የድምጽ ብልጫ የመከላከያ ሚንስትርነታቸው ጸደቀ 

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክርቤት በዶናልድ ትራምፕ የመከላከያ ሚንስትር ተደርገው የተመረጡትን ፒት ሄግሴትን ሹመት ትላንት አርብ ምሽት 51 በ50 በሆነ
የአሜሪካ ድምፅ

ሄግሴት በጠባብ የድምጽ ብልጫ የመከላከያ ሚንስትርነታቸው ጸደቀ 

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክርቤት በዶናልድ ትራምፕ የመከላከያ ሚንስትር ተደርገው የተመረጡትን ፒት ሄግሴትን ሹመት ትላንት አርብ ምሽት 51 በ50 በሆነ ድምጽ አጽድቆላቸዋል፡፡  አንድ መቶ አባላት ያሉት ምክርቤቱ ድምጻቸውን እኩል በእኩል ሃምሳ ሃምሳ ድጋፍና ተቃውሞ የሰጡ ሲሆን የመለያ የሆነውን አንድ ድምጽ የሰጡት ምክትል ፕሬዘዳንቱ ጀ ዲ ቫንስ ናቸው፡፡   ይህም በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ የህግ መወሰኛው ምክርቤት መሪ የሆኑት የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዘዳንት የመለያ ድምጽ ሰጥተው ሹመቱ መቋጫ እንዲያገኝ ሲያደርጉ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡  ድምጽ መስጠቱ የተካሄደው  በዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ከፍተኛ የሲቪል ስልጣን በሆነው የሀገሪቱን የጦር ሃይሎች በማስተዳደር ረገድ የሄግሴት ብቃትን አስመልክቶ የህግ መወሰኛ ምክርቤቱ  ለቀናቶች ክርክር ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ነው።  ሄግሴት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በነበራቸው የምክር ቤቱ የሹመት ማረጋገጫ ማብራርያ ላይ በሀገሪቱ ወታደራዊ ሃይል ዘንድ ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍኑ ተናግረዋል፡፡  የፎክስ ኒውስ የውይይት አቅራቢ የነበሩት ሄግሴት  «ጾታዊ ጥቃት ፈጽመዋል እንዲሁም ካለመጠን ይጠጣሉ» በሚል ይወነጀላሉ፡፡  ሄግሴት ሹመታቸው የጸደቀላቸው የሃገሪቱ መከላከያ ሚንስቴር በዓለም ዙሪያ ከሶስት ሚሊየን በላይ አባላት ያሉትና በየ አመቱ 857 ቢሊየን ዶላር በጀት የሚመደብለት ተቋም ነው፡፡   

በሱዳን ዳርፉን ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሰላሳ ሰዎች ተገደሉ 

በሱዳን ዳርፉር ግዛት ኤል ፋሸር ውስጥ ስራ ላይ ከሚገኙት ጥቂት ሆስፒታሎች በአንዱ በሰው አልባ አውሮፕላን በደረሰ ጥቃት 30 ሰዎች መሞታቸውን እና በርካቶች መቁ
የአሜሪካ ድምፅ

በሱዳን ዳርፉን ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሰላሳ ሰዎች ተገደሉ 

በሱዳን ዳርፉር ግዛት ኤል ፋሸር ውስጥ ስራ ላይ ከሚገኙት ጥቂት ሆስፒታሎች በአንዱ በሰው አልባ አውሮፕላን በደረሰ ጥቃት 30 ሰዎች መሞታቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን የህክምና ምንጮች ዛሬ አስታውቀዋል፡፡ አርብ ማምሻውን በሳውዲ ሆስፒታል ላይ በደረሰው በበዚህ የቦምብ ጥቃት የድንገተኛ አደጋ ህክምና የሚሰጥበት የሆስፒታሉ ህንጻን «ለውድመት ዳርጓል» ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የመረጃው ምንጭ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ ከሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የትኛው ጥቃቱን እንዳደረሰ እስካሁን አልታወቀም። ከእአአ ሚያዝያ 2023 ጀምሮ ሰፊውን የዳርፉርን ግዛት ከያዘው የፈጥኖ ደራሹ ሃይል ጋር የሱዳን ጦር ሲዋጋ ቆይቷል፡፡ እንደ የሕክምና የመረጃ ምንጭ ከሆነ፣ ይኸው ሕንፃ “ከጥቂት ሳምንታት በፊት” በፈጥኖ ደራሽ ሰው አልባ አውሮፕላን ተመትቶ ነበር። በኤል-ፋሸር የጤና ተቋማት ላይ ጥቃቶች መበራከታቸው ሲገለጽ ፣የህክምና በጎ አድራጎት ድርጅት የሆነው ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን የሳዑዲ ሆስፒታል “አሁን የቀረ የቀዶ ህክምና የሚሰጥበት ብቸኛው የህዝብ ሆስፒታል ነው” ሲል በዚህ ወር አስታውቋል፡፡ በመላ አገሪቱ እስከ 80 በመቶ የሚደርሱ የጤና አጠባበቅ ተቋማት ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆኑ መደረጋቸውን ይፋዊ አኃዛዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጦርነቱ እስካሁን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን ሱዳናውያንን ለሞት ሲዳርግ፣ ከ12 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን ደግሞ አፈናቅሏል፡፡

ሀማስ ተጨማሪ አራት እስራኤላውያን ታጋቾችን ዛሬ ለቀቀ 

ሃማስ በጋዛ በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት በሁለተኛው ዙር ልውውጥ የፍልስጤም እስረኞችን ለማስለቀቅ አራት ሴት ታጋች እስራኤላውያንን ለቀቀ፡፡ 
የአሜሪካ ድምፅ

ሀማስ ተጨማሪ አራት እስራኤላውያን ታጋቾችን ዛሬ ለቀቀ 

ሃማስ በጋዛ በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት በሁለተኛው ዙር ልውውጥ የፍልስጤም እስረኞችን ለማስለቀቅ አራት ሴት ታጋች እስራኤላውያንን ለቀቀ፡፡   በእስራኤል የተያዙ 200 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለማስለቀቅ በጋዛ ከተማ ታግተው የነበሩትን አራት እስራኤላውያን ሴቶችን ለቀይ መስቀል ዛሬ አስረክቧል፡፡   አራቱ ሴቶች ካሪና አሪዬቭ፣ ዳንኤላ ጊልቦአ፣ ናአማ ሌቪ እና ሊሪ አልባግ መሆናቸውን ሃማስ ትላንት አርብ አስታውቆ ነበር፡፡ አራቱም ሴቶች የእስራኤል ወታደሮች ሲሆኑ ሀማስ ጥቃቱን በከፈተበት በደቡባዊ እስራኤል ከሚገኘው ናሃል ኦዝ ጣቢያ እአ አ በጥቅምት 7 2023 የተጠለፉ ናቸው።  አራቱ የእስራኤል ወታደሮች ከፍልስጤም አደባባይ መድረክ ላይ ሆነው በፈገግታ ታጅበው ህዝቡን እጃቸውን በማውለብለብ ሰላምታ ሲሰጡም ታይተዋል፡፡ የእስራኤል የእስር ቤት አገልግሎት 200 ፍልስጤማውያንን ለመልቀቅ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ ከሚለቀቁት መካከልም በእስራኤል ላይ ሃማስ ባደርሰው ጥቃት  ተከሰው የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው 120 ሰዎች ይገኙበታል።  የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመርያ ቀን በሆነው ጥር 11 2017 ዓ.ም ፣ ሃማስ 90 የፍልስጤም እስረኞች ልውውጥ ሶስት እስራኤላዊ ታጋች ሴቶችን መልቀቁ ይታወሳል፡፡  በእስራኤልና ሃማስ መካከል ስምምነት እንዲደረስ ግብጽ፣ ኳታርና ዩናይትድ ስቴት የማሸማገል ሚናን ተወጥተዋል፡፡ 

ስጋት ላይ የወደቀው የእናቶች እና የሴቶች ጤና አገልግሎት አቅርቦት

የዋይት ኃውስ ድረ ገጽ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመላከተው፤ በጎርጎርሳውያኑ 2022 ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ 11.5 ቢሊየን ዶላር ለኤች አይቪ ኤድስ ድጋፍ፤ እን
የአሜሪካ ድምፅ

ስጋት ላይ የወደቀው የእናቶች እና የሴቶች ጤና አገልግሎት አቅርቦት

የዋይት ኃውስ ድረ ገጽ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመላከተው፤ በጎርጎርሳውያኑ 2022 ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ 11.5 ቢሊየን ዶላር ለኤች አይቪ ኤድስ ድጋፍ፤ እንዲሁም ሁለት ቢሊየን ዶላር ደግሞ ለቤተሰብ ምጣኔና፣ ለስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት አቅርቦቶች፣ የእናቶች እና ጨቅላ ህጻናት ጤና ላይ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቋል። ይሁን እንጂ ይህ አቅርቦት የ47ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ሆነው ወደ ሥልጣን በተመለሱት ዶናልድ ትራምፕ በሀገር ውስጥ ሮ እና ዌድ ተብሎ በሚጠራው የጽንስ ማቋረጥን ከሚከለክለው መብት ጋር ተያይዞ ያላቸው አቋም የተነሳ የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት በሚሰጡ አለም አቀፍ አጋሮቻቸውን ለስጋት ዳርጓል። ፕሬዝዳንቱ ወደ ሥልጣን በመጡ ዕለት ሀገራቸው ከአለም የጤና ተቋም ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጣቸው ዩናይትድ ስቴትስ ከስነ ተዋልዶ ጤና ጋር የሚኖራት አቋም እንደሚያጠራጥር ባለሞያው ይገልጻሉ፡፡ https://amharic.voanews.com/a/voa-amharic-global-gag-rule-uncertainty-in-african-reporductive-health-care-/7949538.html በኢትዮጵያ የማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር ዶ/ር አበበ ሽብሩ የስነ ተዋልዶ ጤና ድጋፍ መቋረጥ በጽንስ ማቋረጥ ብቻ ሳይሆን፤ ይህን አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት በሚያደርጓቸው በኤች አይ ቪ ኤድስ መድሃኒት ተደራሽነት ላይ ጭምር ጫና ያሳድራል ይላሉ። በሌላ በኩል ገርማቸር ተቋም ከፍተኛ የስነተዋልዶ ጤና ሳይንስ ተመራማሪ. የሆኑት ኤሊዛቤት ሱሊ በአለም ዙሪያ ያሉ የዩናይትድ ስቴትስን ድጋፍ የሚቀበሉ ሀገራት እና የጤና ሚንስትሮች፤ በትራምፕ አስተዳደር ሊከሰት ለሚችል የስነ ተዋልዶ ጤና ድጋፍ መስተጓጎል እንዲዘጋጁ ይመክራሉ። በተጨማሪም ወሲባዊ እና የስነ ተዋልዶ መብቶችን በመቃወም የሚታወቁት የዩናይትድ ስቴትስ የክርስቲያን መብት ቡድኖች ከጎሮጎሳውያኑ 2019 ጀምሮ በአፍሪካ ያላቸውን ድጋፍ እና እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸውን፤ የጋዜጠኝነት እና ማህበራዊ ለውጥ ኢንስቲትዩት (IJSC) አዲስ የመረጃ ትንተና አመልክቷል። አለም አቀፉ ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎትን እንደማያቋርጥ እና ይህን ተክትሎ ሊቋረጡ ለሚችሉ ድጋፎች እየተዘጋጀ መሆኑን የተቋሙ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶ/ር አበበ ሽብሩ ገልጸዋል።  

ትረምፕ ሩሲያ የዩክሬይኑን ጦርነት እንድታቆም ብርቱ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው

ከጥቂት ቀናት በፊት አስተዳደሩን ተረክበው ሥራቸውን የጀመሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሩሲያ ከዩክሬይን ጋራ የሰላም ንግግር እንድትጀ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ ሩሲያ የዩክሬይኑን ጦርነት እንድታቆም ብርቱ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው

ከጥቂት ቀናት በፊት አስተዳደሩን ተረክበው ሥራቸውን የጀመሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሩሲያ ከዩክሬይን ጋራ የሰላም ንግግር እንድትጀምር ግፊታቸውን በማጠናከር ላይ ናቸው። «የሰላም ንግግር አላደርግም ብትል ዩናይትድ ስቴትስ አዳዲስ ማዕቀቦች እና ታሪፎች ትጥልባታለች» በማለት ትረምፕ ያሰሙትን ዛቻ ሩሲያ አጣጥላዋለች። የአሜሪካ ድምጿ ቬሮኒካ ባልዴራስ ኢግሊሲያስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሁቲ አማጺያን ያገቷቸውን 25 የመርከብ ሠራተኞች ለቀቁ

በየመን የሁቲ አማጺያን በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘር በጀመሩበት ወቅት፣ ባለፈው ኅዳር ያገቷቸውን የአንድ መኪና ጫኝ መርከብ 25 ሠ
የአሜሪካ ድምፅ

የሁቲ አማጺያን ያገቷቸውን 25 የመርከብ ሠራተኞች ለቀቁ

በየመን የሁቲ አማጺያን በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘር በጀመሩበት ወቅት፣ ባለፈው ኅዳር ያገቷቸውን የአንድ መኪና ጫኝ መርከብ 25 ሠራተኞች ለቀዋል። በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የሁቲ አማጺያን በጋዛ ተኩስ አቁም ከተጀመረ ወዲህ ውጥረቱን ለማርገብ ያደረጉት ጥረት አካል እንደሆነ ተነግሯል። ነገር ግን ፕሬዝደንት ትረምፕ፣ በፕሬዝደንት ጆ ባይደን የተሰረዘውን የሽብርተኝነት ፍረጃ መልሶ እንዲፀና በማድረጋቸው አዲስ ውጥረት እንደይከሰት ተሰግቷል። ታጋቾቹን የለቀቁት ኦማን ባደረገችው ሽምግልና ምክንያት መሆኑን የሁቲ አማጺያን አስታውቀዋል። ኦማን ከሁቲዎች ጋራ የሚደረግን ድርድር ስትሸመግል ቆይታለች፡፡ አንድ የኦማን አየር ኃይል አውሮፕላን ታጋቾቹን ከየመን ማውጣቱም ታውቋል። በተጨማሪም 25 የሚሆኑት የመርከቡ ዓባላት እንዲለቀቁ ከሐማስ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦ እንደነበር ሁቲዎቹ አስታውቀዋል። የመርከቡ ዓባላት ከፊሊፒንስ፣ ቡልጋሪያ፣ ሮማኒያ፣ ዩክሬን እና ሜክሲኮ የተውጣጡ መሆናቸውም ተመልክቷል። “እርምጃው የተወሰደው በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ስምምነት ላይ መደረሱን ለመደገፍ ነው”  ሲሉ አማጺያኑ በሚቆጣጠሩት ሳባ የዜና አገልግሎት በኩል ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የፊሊፒንሱ ፕሬዝደንት ፈርዲናንድ ማርቆስ ሁለተኛ፣ 17 የሃገሪቱ ዜጎች መለቀቃቸውን አስታውቀዋል። የቡልጋሪያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርም ሁለት ዜጎቹ እንደተለቀቁ አስታውቋል። በተመድ የየመን ልዩ ልዑክ የሆኑት ሃንስ ግረንድበርግ፣ በዘፈቀደ የታገቱ ሰዎችን ሰቆቃ ያስቆመ ነው ያሉትን እርንምጃ በመልካም ተቀብለዋል።

Get more results via ClueGoal