ትራምፕ በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና በቻይና ላይ ታሪፍ ጣሉ
newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ቅዳሜ ከካናዳ እና ሜክሲኮ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25 ከመቶ ታሪፍ የጣሉ ሲሆን ከቻይና ወደ ሀገር በሚገቡትራምፕ በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና በቻይና ላይ ታሪፍ ጣሉ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ቅዳሜ ከካናዳ እና ሜክሲኮ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25 ከመቶ ታሪፍ የጣሉ ሲሆን ከቻይና ወደ ሀገር በሚገቡ ምርቶች ላይ ደግሞ ቀድሞ ከነበረው 10 ከመቶ ተጨማሪ ታሪፍ እንደሚጥሉ ዋይት ኃውስ ገልጿል። የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት አርብ ዕለት በሰጡት መግለጫ “ካናዳ እና ሜክሲኮ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የአሜሪካ ዜጎችን እየገደለ ያለውን ፌንተኒል የተሰኘ ሃሺሽ ስርጭት እና የህገወጥ ሰደተኞች ወረራ ፈቅደዋል ” በማለት ተናግረዋል። ሌቪት ከእርምጃዎቹ ውስጥ በልዩነት የሚታይ ነገር ይኖር እንደሆን አላስታወቁም። ይሁን እንጂ ቃል አቀባይዋ “እነዚህ በፕሬዝዳንቱ እንደሚደረጉ የተገቡ እና የተፈጸሙ ቃልኪዳኖች ናቸው« ሲሉ ተናግረዋል። ስለጉዳዪ አርብ ዕለት በጋዜጠኞች የተጠየቁት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ውሳኔውን ለመቀልበስ ሦስቱ ሀገራት ማድረግ የሚችሉት ምንም ነገር እንደሌለ በመግለጽ ታሪፉ »የመደራደሪያ መሳሪያ አይደለም« ብለዋል። ትራምፕ ከትላንት ቅዳሜ አንስቶ የካናዳ ድፍድፍ ዘይት ላይ የአስር ከመቶ ፤ እንዲሁም በሌሎች የካናዳ ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ መጣሉን አስታውቀዋል። ታሪፉ ከፊታችን ማክሰኞ ጥር 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል። በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ ከአውሮፓ ህብረት በሚወጡ ምርቶች ላይ “ፍፁም” ታሪፍ ሊጥሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። በጉዳዩ ላይ ተሰናባቹ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሀገራቸው ምላሽ እንደምትሰጥ ገልጸዋል። »እነዚህን ታሪፎች ለማስቀረት ጠንክረን እየሰራን ነው፣ ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ በጉዳዩ ላይ ጸንታ ወደፊት የምትቀጥል ከሆነ ካናዳ ለጠንካራ እና ፈጣን ምላሽ ዝግጁ ናት" በማለት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃናቸው አማካኝነት አስታውቀዋል። በአንጻሩ ሜክሲኮ በጉዳዩ ላይ ዝምታን የመረጠች ሲሆን፤ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሚኒስቴር፤ ሜክሲኮ እና ዩናይትድ ስቴትስ “አጋሮች እንጂ ተፎካካሪዎች አይደሉም” በማለት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃናቸው ላይ አስፍረዋል። Read more