Ethiopia



በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናትን ህይወት የቀየረው የባህርዳሩ ግሬስ ማዕከል

ከ20 አመት በፊት በአማራ ክልል፣ ባህርዳር ከተማ ውስጥ የተመሰረተው ግሬስ ፋውንዴሽን ማዕከል አሳዳጊ አልባ ኾነው ተጥለው የተገኙ ጨቅላ ህፃናትን ሰብስቦ በማሳ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በትግራዩ ውጥረት ዙሪያ የሰጡት አስተያየት 

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል የፖለቲካ ኃይሎች መካከል በቀጠለው የፖለቲካ ልዩነት ዙሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት ሰጡ። በዛ
የአሜሪካ ድምፅ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በትግራዩ ውጥረት ዙሪያ የሰጡት አስተያየት 

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል የፖለቲካ ኃይሎች መካከል በቀጠለው የፖለቲካ ልዩነት ዙሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት ሰጡ። በዛሬው ዕለት በፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ "የትግራይ የፖለቲካ መሪዎች እና ልሂቃን የውስጥ ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ’ ሲሉ ጥሪ ያሰሙት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ፣ ከሌሎች ክልሎች ይሁን ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር የሚነሱ ማናቸውም ልዩነቶች የሃገሪቱ ሕገ መንግሥት በሚያዘው መሠረት ሊፈቱ ይገባል’ ብለዋል። የትግራዩ የፖለቲካ አለመግባባት በቅርቡ አንዳንድ የክልሉ የጦር አዛዦች ድጋፋቸውን ለሕወሐት ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከገለጹ በኋላ ከክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ጋራ የገቡት ብርቱ የፖለቲካ ውዝግብ ተባብሶ መቀጠሉ ተዘግቧል። የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ የክልሉ ምክር ቤት  ከተበተነ ከዓመታት በኋላ በትላንትናው ዕለት አማካሪ ምክር ቤት ተመስርቷል። የአማካሪው ምክር ቤት ፕሬዝዳንቱን ከመሰየም በመለስ የክልል ምክር ቤቱን ሥራ እንደሚሠራ ተገልጿል። እርምጃውን የተቃወሙት የሕወሐት መሪ አማካሪ ጉባኤውን ድርጅታቸውን ለመበተን የታለመ ሲሉ ተከራክረዋል። ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ የትግራይ ሕዝብ “የትላንት ቁስሉ ሳይጠግ፣ አሁንም በፍርሃት እና በተሸበረ ሥሜት እንዳለ ነው” ብለዋል።

የትረምፕ አስተዳደር በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና ላይ ስለሚጣለው ታሪፍ አስፈላጊነት ማስረዳቱን ቀጥሏል

የትረምፕ አስተዳደር በካናዳ፣ ቻይና እና ሜክሲኮ ላይ ለምን ታሪፍ መጣል አስፈላጊ እንደሆነ በሳምቱ መጨረሻም ክርክሩን ማቅረብ ቀጥሎ ነበር። ሶስቱ ሃገራት የ
የአሜሪካ ድምፅ

የትረምፕ አስተዳደር በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና ላይ ስለሚጣለው ታሪፍ አስፈላጊነት ማስረዳቱን ቀጥሏል

የትረምፕ አስተዳደር በካናዳ፣ ቻይና እና ሜክሲኮ ላይ ለምን ታሪፍ መጣል አስፈላጊ እንደሆነ በሳምቱ መጨረሻም ክርክሩን ማቅረብ ቀጥሎ ነበር። ሶስቱ ሃገራት የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀው፣ ነገር ግን ከአሜሪካ ጋር ለመነጋገርና ለመተባበር በራቸው ክፍት እንደሆነ ገልጸዋል። ዛሬ ጠዋት ላይ ደግሞ ዶናልድ ትረምፕ ከካናዳው ጠቅላይ ምኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋራ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል። ዶናልድ ትረምፕ “ትሩዝ ሶሻል” በተወሰኘው ማኅበራዊ መድረክ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ እኩለ ቀን ላይም ከትሩዶ ጋራ ለመነጋገር ቀጠሮ እንደያዙ አስታውቀው፣ አዲስ ታሪፍ በካናዳ ላይ የጣሉት በአሜሪካ የበርካቶችን ሕይወት በመቅጠፍ ላይ የሚገኘውን ፈንትነል የተሰኘው ሱስ አሲያዥ መድሃኒት በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ መግባቱን ለመከላከል ካናዳ ተጨማሪ ጥረት እንድታደርግ ጫና ለመፍጠር መሆኑን አስታውቀዋል። ትረምፕ በተጨማሪም ከሜክሲኮ ፕሬዝደንት ክላውዲያ ሼይንባውም ጋራ ለመነጋገር ዕቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል። ቬሮኒካ ባልዴራስ ኤግሌሲያስ የላከችው ዘገባ ነው።

ትረምፕ አዲስ የቀረጥ ክፍያ የጣሉባቸውን የካናዳን እና የሜክሲኮን መሪዎችን ሊነጋገሩ ነው

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሁለቱ ጎረቤቶቻቸው ካናዳ እና ሜክሲኮ፣ እንዲሁም ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ አዲስ ቀረጥ ከጣሉ እና በምላሹ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ አዲስ የቀረጥ ክፍያ የጣሉባቸውን የካናዳን እና የሜክሲኮን መሪዎችን ሊነጋገሩ ነው

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሁለቱ ጎረቤቶቻቸው ካናዳ እና ሜክሲኮ፣ እንዲሁም ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ አዲስ ቀረጥ ከጣሉ እና በምላሹ ሁለቱ አገሮች በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የአጻፋ ቀረጥ መጣላቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ከመሪዎቹ ጋር ለመነጋገር ማቀዳቸውን አመለከቱ። ትረምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ከካናዳ እና ሜክሲኮ ጋር ተደራድረው ‘ነጻ-የንግግድ ስምምነት’ ተግባራዊ ቢያደርጉም፤ ከነገ ማክሰኞ አንስቶ ተፈጻሚ የሚሆን አዲስ የሃያ አምስት በመቶ ቀረጥ ሲጥሉባቸው፤ በቻይና ላይ ደግሞ ቀደም ሲል ከተደነገገው በተጨማሪ የአሥር በመቶ ቀረጥ ጥለዋል። ትረምፕ ሕገ-ወጥ ፍልሰትን ለማስቆም እና ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለብዙዎች ህልፈት ምክኒያት የሆነው ‘ፌንቲኔል’ የተባለ አደገኛ መድሃኒት ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ለመከላከል በቂ ጥረት አላደረጉም’ ሲሉ ሦስቱን ሃገራት ከሰዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዶናልድ ትረምፕ ትላንት ዕሁድ ማለዳ ላይ ‘ትሩዝ ሶሻል’ በተባለው የራሳቸው የማኅበራዊ ሚዲያ አውታር ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ በቀረጥ ጭማሪዎቹ የተነሳ አሜሪካውያን ሸማቾች ከፍተኛ የገበያ ዋጋ ጭማሪ ሊገጥማቸው እንደሚችል አምነዋል። በሌላ በኩል ለፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ ቀረጥ የሚከፍሉ የአሜሪካ ኩባንያዎች ከሌሎች ሃገራት ለሚያስገቧቸው የተለያዩ ምርቶች እና ሸቀጦች የሚጠየቁትን ተጨማሪ ወጭ ሙሉውን አለያም የሚበዛውን ወደሸማቹ ያሳፋሉ። “በአዲሱ ቀረጥ የተነሳ ጥቂት ቆንጠጥ የሚያደርግ ሕመም ሊኖር ይችላል?” ሲሉ ትረምፕ ራሳቸው ለሰነዘሩት ጥያቄ ሲመልሱ፡ “አዎን! ምናልባት! ሊኖርም ላይኖርም ይችላል! ነገር ግን አሜሪካን ዳግም ታላቅ እናደርጋለን። እናም ቢከፍሉት የማያስከፋ ዋጋ ይሆናል" ብለዋል።

የመንግስታቱ ድርጅት በኮንጎ ጾታዊ ጥቃት እንደጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ ውሏል ሲል አስታወቀ

በምሥራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኤም 23 አማፂያን እና በኮንጎ የታጠቁ ወታደሮች መካከል ውጊያው እየተባባሰ በመጣበት ወቅት፤ ተፋላሚዎቹ ወገኖች አስገድ
የአሜሪካ ድምፅ

የመንግስታቱ ድርጅት በኮንጎ ጾታዊ ጥቃት እንደጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ ውሏል ሲል አስታወቀ

በምሥራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኤም 23 አማፂያን እና በኮንጎ የታጠቁ ወታደሮች መካከል ውጊያው እየተባባሰ በመጣበት ወቅት፤ ተፋላሚዎቹ ወገኖች አስገድዶ መድፈርን እና ጾታዊ ጥቃትን እንደ ጦርነት መሳሪያ ጥቅም ላይ እያዋሉት መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት ሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ፅህፈት ቤት አስጠንቅቋል። የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዋና ሃላፊ ቮልከር ተርክ ቃል አቀባይ የሆኑት ጀርሚ ላውረንስ ሁኔታው “ከግጭት ጋር ተያይዞ ለብዙ አስርት ዓመታት በኮንጎ ታጣቂዎች እየፈጸሙት ያለ ነገር ነው” ብለዋል፡፡ ከፍተኛ ኮሚሽነሩ በተለይም የቅርብ ጊዜው ግጭት “ከግጭት ጋር የተያያዘውን የጾታ ጥቃት የበለጠ ሊያባብሰው ይችላል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። በግጭቱ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት፣ የኤም 23 አማፂያን እና ሩዋንዳ በአካባቢው ላለው ቀውስ እርስ በራሳቸው እየተወነንጃጀሉ ነው።

ትራምፕ እና ኔታኒያሁ በጋዛ፣ በኢራን እና በአረብ ሀገራት ጉዳዮች ላይ ሊወያዩ ነው

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የፊታችን ማክሰኞ ከዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር፤ በዋይት ሀውስ ሲገናኙ፤ የኢራን ጥቃት
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ እና ኔታኒያሁ በጋዛ፣ በኢራን እና በአረብ ሀገራት ጉዳዮች ላይ ሊወያዩ ነው

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የፊታችን ማክሰኞ ከዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር፤ በዋይት ሀውስ ሲገናኙ፤ የኢራን ጥቃትን በመቃወም፣ ከአረብ ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በማስፋፋት እንዲሁም ሀገራቸው «በሀማስ ላይ ድል» ስለማድረጓ እንደሚወያዩ በዛሬው ዕለት ተናግረዋል ። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሁለት ሳምንት በፊት ለሁለተኛ ጊዜ ለቀጣዩ አራት ዓመታት ሀገሪቱን ለመምራት ሥልጣን ከተረከቡ በኋላ የሚያገኟቸው የመጀመሪያው የውጭ ሀገር መሪ ቀዳሚው ኔታንያሁ ሊሆኑ ነው። ትራምፕ እና ኔታንያሁ የረዥም ጊዜ አጋሮች ሲሆኑ፤ ፕሬዝዳንቱ  የመካከለኛው ምሥራቅ መልዕክተኛውን ስቲቭ ዊትኮፍን ልከው እስራኤል ከሃማስ ጋር በከፈተችው ጦርነት እና በእስረኞች መካከል ያለውን ልውውጥ፤ የስድስት ሳምንት የተኩስ አቁም በማድረግ እንዲያደራድሩም በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ምንም እንኳን የሃማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ተይዘው የነበሩትን በመቶዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም እስረኞች ለውጥ 18 ታጋቾችን ነጻ ቢለቁም፣ ሁለተኛው የእርቁ ሂደት ከፍተኛ ተግዳሮት ገጥሞታል። እስራኤል ይህ እንዲሆን አልፈቅድም ብላ ብትናገርም፤  የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተደረገበት ከባለፈው ወር አንስቶ በዩናይትድ ስቴትስ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የሃማስ ቡድን ሙሉ ለሙሉ በድጋሚ ጋዛን በቁጥጥሩ ስር ማድረጉን አረጋጧል። ይህን ተከትሎ፤ ጦርነቱ ሙሉ ለሙሉ ሳይቆም እና የእስራኤል ጦር በሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ካለው ጠባብ የጋዛ ሰርጥ ክፍል በሙሉ ለቆ ሳይወጣ በሁለተኛው የእርቅ ሂደት ነፃ ሊወጡ የታቀዱ ተጨማሪ ታጋቾችን እንደማይለቅ ሃማስ አስታውቋል። የመጀመሪያው የእርቅ ሂደት የፊታችን መጋቢት መጀመሪያ ላይ ካበቃ በኋላ ጦርነቱን እንዲቀጥሉ ኔታንያሁ ከቀኝ ቀኝ ዘመም አጋሮቻቸው ጫናው አይሎባቸዋል። ይሁን እንጂ በጉዳዩ ላይ ትራምፕ ያላቸው አቋም እስካሁን ግልፅ አይደለም። ምንም እንኳን ትራምፕ የእስራኤል ጠንካራ ደጋፊ ቢሆኑም፤  በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉትን ጦርነቶች ለማስቆም እና የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማደራደር ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ የአይ ኤስ አሸባሪ ቡድን ጠንካራ ይዞታ ላይ ጥቃት ፈጸመች

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር አውሮፕላኖች በሶማሊያ የሚገኘውን እስላማዊ መንግሥት በመባል የሚታወቀው የአሸባሪ ቡድን ጋር ተያያዥ ያላቸውን ሽብርተኛ ቡድኖች ይ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ የአይ ኤስ አሸባሪ ቡድን ጠንካራ ይዞታ ላይ ጥቃት ፈጸመች

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር አውሮፕላኖች በሶማሊያ የሚገኘውን እስላማዊ መንግሥት በመባል የሚታወቀው የአሸባሪ ቡድን ጋር ተያያዥ ያላቸውን ሽብርተኛ ቡድኖች ይገኙበታል የተባለውን ተራራማ ምሽግ ላይ ፤ ጥቃት መፈጸማቸውን የሶማሊያ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች አስታውቀዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት በማኅበራዊ ድረ-ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ጥቃቱ “ከፍተኛ የአይኤስ ጥቃት እና እቅድ አውጪ እንዲሁም አይ ኤስ የመለመላቸው እና የሚመራቸው አሸባሪዎች” ያነጣጠረ ዒላማ ነው ሲሉ ገልጸዋል። «ዩናይትድ ስቴትስን እና አጋሮቻችን የሚያስፈራሩትን እነዚህ አሸባሪዎች  በዋሻ ውስጥ ተደብቀው አግኝተናቸዋል» ብለዋል ትራምፕ። አያይዘውም ጥቃቱ ሲቪሎችን ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ አሸባሪዎቹ ይኖሩባቸው የነበሩትን ዋሻዎች  ሙሉ በሙሉ በማውደም ገድለዋል” ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግ ሴዝ  በሰጡት የተናጥል መግለጫ ፤ ጥቃቱ በሶማሊያ ጎሊስ ተራሮች አካባቢ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን «ጥቃቱ አይኤስ በአሜሪካ ዜጎች እና  አጋሮቻችን እንዲሁም ንፁሀን ዜጎችን የሚያሰጉ የሽብር ጥቃቶችን የማሴር እና የማካሄድ አቅሙን አሳንሷል» ብለዋል። ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ጥቃቱ የተፈፀመው ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ጋር በመተባበር ነው ቢሉም ትራምፕም ሆነ ሄግ ሴዝ የአይኤስ እቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ዝርዝር አልሰጡም። የፑንትላንድ ጄኔራል አዳን አብዲ ሃሺ  የአየር ጥቃቱ፤ የጎሊስ ተራሮች አካል በሆነው ካል ሚስካድ በተባለው አካባቢ፤  የእስላማዊ መንግስት ታጣቂዎች ላይ በሚገኙባቸው በትንሹ አስር የሚሆኑ ስፍራዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል። በፑንትላንድ ባሪ ግዛት ቃንዳላ በተሰኘች ትንሽ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ በደህንነት ስጋት ምክንያት ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪዎች፤  ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት፤  ከሩቅ የሚነሳ የጭስ እና የእሳት ነበልባል ማየታቸውን እና በትንሹ ሰባት የሚሆኑ ግዙፍ ፍንዳታዎች መስማታቸውን ተናግረዋል። የሶማሊያ ከፊል ራስ ገዝ ግዛት የሆነችው ፑንትላንድ ባለሥልጣናት በማህበራዊ መገናኛቸው፤ ተልዕኮው የተሳካ መሆኑን በመግለጽ  ለዩናይትስ ስቴትስ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።  

ትራምፕ በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና በቻይና ላይ ታሪፍ ጣሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ቅዳሜ ከካናዳ እና ሜክሲኮ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25 ከመቶ ታሪፍ  የጣሉ ሲሆን ከቻይና ወደ ሀገር በሚገቡ
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና በቻይና ላይ ታሪፍ ጣሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ቅዳሜ ከካናዳ እና ሜክሲኮ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25 ከመቶ ታሪፍ  የጣሉ ሲሆን ከቻይና ወደ ሀገር በሚገቡ ምርቶች ላይ ደግሞ ቀድሞ ከነበረው 10 ከመቶ ተጨማሪ ታሪፍ እንደሚጥሉ  ዋይት ኃውስ ገልጿል። የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት አርብ ዕለት በሰጡት መግለጫ “ካናዳ እና ሜክሲኮ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የአሜሪካ ዜጎችን እየገደለ ያለውን ፌንተኒል የተሰኘ ሃሺሽ ስርጭት እና የህገወጥ ሰደተኞች ወረራ ፈቅደዋል ” በማለት ተናግረዋል። ሌቪት ከእርምጃዎቹ ውስጥ በልዩነት የሚታይ ነገር ይኖር እንደሆን አላስታወቁም። ይሁን እንጂ ቃል አቀባይዋ “እነዚህ በፕሬዝዳንቱ እንደሚደረጉ የተገቡ እና የተፈጸሙ ቃልኪዳኖች  ናቸው« ሲሉ ተናግረዋል። ስለጉዳዪ አርብ ዕለት በጋዜጠኞች የተጠየቁት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ውሳኔውን ለመቀልበስ ሦስቱ ሀገራት ማድረግ የሚችሉት ምንም ነገር እንደሌለ በመግለጽ ታሪፉ »የመደራደሪያ መሳሪያ አይደለም« ብለዋል። ትራምፕ ከትላንት ቅዳሜ አንስቶ የካናዳ ድፍድፍ ዘይት ላይ የአስር ከመቶ ፤ እንዲሁም በሌሎች የካናዳ ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ መጣሉን አስታውቀዋል። ታሪፉ ከፊታችን ማክሰኞ ጥር 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል። በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ ከአውሮፓ ህብረት በሚወጡ ምርቶች ላይ “ፍፁም” ታሪፍ ሊጥሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። በጉዳዩ ላይ ተሰናባቹ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሀገራቸው ምላሽ እንደምትሰጥ ገልጸዋል። »እነዚህን ታሪፎች ለማስቀረት  ጠንክረን እየሰራን ነው፣ ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ በጉዳዩ ላይ ጸንታ ወደፊት የምትቀጥል ከሆነ ካናዳ ለጠንካራ እና ፈጣን ምላሽ ዝግጁ ናት" በማለት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃናቸው አማካኝነት አስታውቀዋል። በአንጻሩ ሜክሲኮ በጉዳዩ ላይ ዝምታን የመረጠች ሲሆን፤ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሚኒስቴር፤ ሜክሲኮ እና ዩናይትድ ስቴትስ “አጋሮች እንጂ ተፎካካሪዎች አይደሉም” በማለት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃናቸው ላይ አስፍረዋል።

አንድ የሕክምና ማጓጓዣ አውሮፕላን ፊላደልፊያ ውስጥ ተከሰከሰ

አንድ ሕጻንና እናቱን እንዲሁም ሌሎች አራት ተሳፋሪዎችኝ የያዘ የሕክምና አውሮፕላን ፊላደልፊያ ውስጥ መኖሪያ ቤቶች ላይ ተከስክሷል። አውሮፕላኑ ሕክምናው
የአሜሪካ ድምፅ

አንድ የሕክምና ማጓጓዣ አውሮፕላን ፊላደልፊያ ውስጥ ተከሰከሰ

አንድ ሕጻንና እናቱን እንዲሁም ሌሎች አራት ተሳፋሪዎችኝ የያዘ የሕክምና አውሮፕላን ፊላደልፊያ ውስጥ መኖሪያ ቤቶች ላይ ተከስክሷል። አውሮፕላኑ ሕክምናውን ያጠናቀቀ ሕጻንና ሌሎቹን የሕክምና ተጓጓዦች ይዞ ሰሜን ምሥራቅ ፊላደልፊያ ከሚገኝ አየር ማረፊያ በተነሳ በግማሽ ደቂቃ ውስጥ ነበር የተከሰከሰው። አውሮፕላኑ የወደቀው መኖሪያ ቤቶች አካባቢ እንደሆነም ዘገባዎች አመልክተዋል። ተሳፋሪዎቹ በሙሉ ከሜክሲኮ የመጡ እንደሆኑም ታውቋል። አደጋው የደረሰው ዋሽንግተን ዲስ አየር ማረፊያ 60 መንገዶኞችን ይዞ ሊያርፍ የተቃረበ አውሮፕላን ከአንድ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ጋራ ተጋጭቶ በተከሰከሰና ሁሉም ተሳፋሪዎች ሕይወታቸውን ባጡ በሁለተኛው ቀን ነው።

ፑንትላንድ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያንን ያዘች

በሶማሊያ የፑንትላንድ ባለሥልጣናት በቦሳሶ ከተማ የሚገኙና የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ሰነድ የሌላቸውን በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲያዙ አድርገዋል። ወ
የአሜሪካ ድምፅ

ፑንትላንድ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያንን ያዘች

በሶማሊያ የፑንትላንድ ባለሥልጣናት በቦሳሶ ከተማ የሚገኙና የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ሰነድ የሌላቸውን በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲያዙ አድርገዋል። ወደ ሀገራቸው እንደሚመልሱም አስታውቀዋል። እርምጃው ሰነድ አልባ የውጪ ዜጎችን ከሀገሪቱ የማስወጣት ዘመቻ አካል እንደሆነም ተመልክቷል። የተያዙት ስደተኞች በመኪና ተጭነው ከከማዋ ውጪ ተወስደዋል። ይህም ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በማሰብ ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል። እርምጃው የተወሰደው ፑንትላንድ በአይሲስ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ባልችበት ወቅት ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት አንድ በአይሲስ አባልነት የተጠረጠረን ግለሰብ የፀጥታ ኅይሎች ተኩሰው መግደላቸውን ተከትሎ ነው። የተያዙት ስደተኞች ከሽብር እንቅስቃሴ ጋራ ግንኙነት ይኖራቸው ባለሥልጣናት ማስረጃ አላቀረቡም። ዩሱፍ ሞሐመድ ዩሱፍ ያጠናቀረውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።

አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

አምባሳድር ብናልፍ አንዱአለም በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን የሀገር ውስጥ ብዙኅን መገናኛ
የአሜሪካ ድምፅ

አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

አምባሳድር ብናልፍ አንዱአለም በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን የሀገር ውስጥ ብዙኅን መገናኛ ዘግበዋል። ዛሬ ከኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የሹመት ደብዳቤ እና የሥራ መመሪያ የተቀበሉት አምባሳደር ብናልፍ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ቴዎድሮስ ምሕረት አማካኝነት ቃለ መሐላ መፈፀማቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አመልክቷል። አምባሳደር ብናልፍ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስቴር ሆነው ያገለገሉ ሲኾን ከብሔራዊ ደኅንነት እና ሰላም ግንባታ ጋራ በተያያዙ የመንግስት እንቅስቃሴዎች ውስጥም ተሳትፈዋል። ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲን በአምባሳደርነት ሲያገለግሎ የቆዩት አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከለቀቁ በኋላ ኢምባሲው በጉዳይ ፈጻሚነ ሲመራ ቆይቷል።  አምባሳደር ብናልፍ ሥራቸውን በይፋ ከመጀመራቸው በፊት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያን በመወከል ከዩናትይድ ስቴትስ ጋራ በሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶች ውስጥ እንዲሳተፉና፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዕለት ተዕለት ሥራም እንዲመሩ ኃላፊነት እንደተሰጣቸው ፕሬዝዳንቱን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።  ፕሬዝዳንት ታዬ ሹመቱን በሰጡበት ወቅት፣ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ዘመን ግንኙነት የሚመጥን ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ያመለከተው የዜና ተቋሙ አምባሳደር ብናልፍ ይህን ታሳቢ ያደረገ አመራር እንዲሰጡ ማሳሰባቸውን አመልክቷል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና አስተዳደራዊ ዘርፎች በርካታ የአመራር ቦታዎች ላይ ያገለገሉት አምባሳደር ብናልፍ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን በሚኒስትርነት ማዕረግ ያገለገልሉ ሲሆን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሥር የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሆነውም ሠርተዋል። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዲግ) ወደ ብልፅግና ፓርቲ ከመቀየሩ በፊትም፣ በአማራ ክልል መንግሥት ውስጥ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በመኾን እና የክልሉን ትምህርት ቢሮ በመምራት አገልግለዋል።   

ከዋሽንግተኑ የአውሮፕላኖች ግጭት በህይወት የተረፈ ሰው እንደሌለ ተረጋገጠ

60 መንገደኞችን እና አራት የበረራ ሠራተኞችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ የአሜሪካ አየር መንገድ  አውሮፕላን፤ ሦስት ወታደሮችን ከጫነ  የአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር ጋራ
የአሜሪካ ድምፅ

ከዋሽንግተኑ የአውሮፕላኖች ግጭት በህይወት የተረፈ ሰው እንደሌለ ተረጋገጠ

60 መንገደኞችን እና አራት የበረራ ሠራተኞችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ የአሜሪካ አየር መንገድ  አውሮፕላን፤ ሦስት ወታደሮችን ከጫነ  የአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር ጋራ አየር ላይ  በመጋጨቱ ሁሉም ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ማለፉ በትላንትናው ዕለት ተረጋግጧል። ባለሥልጣናቱ ትክክለኛው የአደጋው ምክንያት ምን እንደሆነ እየመረመሩ ቢሆንም፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሬገን ዋሽንግተን ብሔራዊ አየር ማረፊያ አካባቢ ለተከሰተው አደጋ ምክንያቱ «የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ብዛሃነትን መሠረት ያደረገ የሠራተኛ ቅጥር ፖሊሲ ሊሆን ይችላል» ሲሉ ተናግረዋል። የዋይት ኃውስ ዋና ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ያጠናቀረችው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የቆዳን ቀለም ለማፍካት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቅባቶች እና አደጋቸው

በአለም ዙሪያቆዳቸው ፈካ ብሎእንዲታይ ለማድረግ የሚጥሩሰዎች ቁጥር ከፍተኛነው። ባለሞያዎች ቆዳንለማቅላት ወይም ለማፍካትጥቅም ላይ የሚውሉቅባቶች 
የአሜሪካ ድምፅ

የቆዳን ቀለም ለማፍካት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቅባቶች እና አደጋቸው

በአለም ዙሪያቆዳቸው ፈካ ብሎእንዲታይ ለማድረግ የሚጥሩሰዎች ቁጥር ከፍተኛነው። ባለሞያዎች ቆዳንለማቅላት ወይም ለማፍካትጥቅም ላይ የሚውሉቅባቶች እና መድሃኒቶችእንደሜርኩሪ ያሉ ሰዎችላይ ጉዳት የሚያደርሱየኬሚካል ንጥረነገሮችን በመያዛቸው ከጥቅማቸውጉዳታቸው እንደሚያመዝን ይናገራሉ።  የአለም የጤና ድርጅት ለረዥምጊዜ ሜሪኩሪ ንጥረነገር ያለው መድሃኒትእና ቅባት መጠቀም በኩላሊት እና በነርቭ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ አስታውቋል። 

የፈረንሳይ ኃይሎች ከቻድ ሙሉ ለሙሉ ለቀው ወጡ

የፈረንሳይ ኃይሎች ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ቻድ ሙሉ ለሙሉ ለቀው ወጥተው መጨረሳቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድርስ በደስታ ተቀብለውታል። ይህም ፈረንሳ
የአሜሪካ ድምፅ

የፈረንሳይ ኃይሎች ከቻድ ሙሉ ለሙሉ ለቀው ወጡ

የፈረንሳይ ኃይሎች ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ቻድ ሙሉ ለሙሉ ለቀው ወጥተው መጨረሳቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድርስ በደስታ ተቀብለውታል። ይህም ፈረንሳይ ጂሃዲስት ታጣቂዎች በስፋት ከሚንቀሳቀሱበት የአፍሪካ ሳህል ቀጠና የመውጣቷ ሂደት የመጨረሻው ምዕራፍ ነው ተብሏል። ከአንድ ቀን በፊት በዋና ከተማው ን'ጃሚና በዝግ በተካሄደ ወታደራዊ ስነስርዓት ዴቢ ለቻድ ኃይሎች እና ዲፕሎማቶች ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ፈረንሳይ በመካከለኛው አፍሪካውቷ ሀገር የነበራትን የመጨረሻ የጦር ሰፈር አስረክባለች። ቻድም ከቀድሞ ቅኝ ገዢዋ ጋር የነበራትን ወታደራዊ ትብብር ሙሉ ለሙሉ አቋርጣለች። ከዚህ በኃላ የቻድ ባንዲራ ብቻ በሚውለበለብበት የጦር ሰፈር ሆነው ንግግር ያደረጉት ዴቢም፣ ከፈረንሳይ ጋር ያለንን ወታደራዊ ትብብር ብናቋርጥም፣ ግንኙነታችንን ግን እንቀጥላለን ብለዋል። አክለውም ቻድ የበለጠ ጠንካራ እና የተሻለ ጦር እንደምትገነባ እና በመከባበር፣ እንዲሁም ነፃነትን እና በሉዓላዊነትን በአማከለ መልኩ አዳዲስ ትብብሮችን እንደምትፈጥር አመልክተዋል። ቻድ ከቅኝ ግዛት ነፃ መሆኗን ካወጀችበት እ.አ.አ 1960 አንስቶ፣ የፈረንሳይ ወታደሮች እና ተዋጊ አውሮፕላኖች በቻድ ቋሚ መቀመጫ የነበራቸው ሲሆን፣ የቻድን ጦር በመገንባት እንደረዱ ተመልክቷል። በተለይ ፈረንሳይ በማሊ፣ በቡርኪናፋሱ እና ኒጀር የተደረጉትን መፈንቅለ መንግስቶች ተከትሎ ከሀገራቱ እንድትወጣ ስትደረግ፣ በሳህል ቀጠና ውስጥ የነበራት ብቸኛው ትስስር የቻድ ጦር ሰፈር ነበር። 

በዋሽንግተኑ የአውሮፕላን አደጋ ላይ ምርመራ ቀጥሏል

ረቡዕ ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በረራ ላይ እያሉ በመጋጨታቸው ለ67 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑትን ሁለት አውሮፕላኖች ከወደቁበት የፖቶማክ ወንዝ ለ
የአሜሪካ ድምፅ

በዋሽንግተኑ የአውሮፕላን አደጋ ላይ ምርመራ ቀጥሏል

ረቡዕ ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በረራ ላይ እያሉ በመጋጨታቸው ለ67 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑትን ሁለት አውሮፕላኖች ከወደቁበት የፖቶማክ ወንዝ ለማውጣት የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው። ከበርካታ የአሜሪካ ተቋማት የተውጣጡት መርማሪዎች፣ ከሄሊኮፕተር ጋር ተጋጭቶ ወንዙ ውስጥ በገባው የአሜሪካ አየር መንገድ ውስጥ የሚገኘውን እና «ጥቁሩ ሳጥን» በመባል የሚታወቀውን የበረራ መረጃ የሚያስቀምጥ መሳሪያ ማግኘት ችለዋል። ዋናተኞች ወደ ወንዙ ውስጥ ጠልቀው በመግባት ተጨማሪ የአውሮፕራኑን ስብርባሪ አካል ለማግኘት እንደሚሞክሩም የእሳት አደጋ መከላከያ ባለስልጣናት አመልክተዋል። የብሔራዊ ትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ የበረራ መረጃ መመዝገቢያውን ሳጥን እና በአብራሪዎቹ ክፍል ውስጥ የተቀዱ የድምፅ መረጃዎችን ከመረመረ በኃላ፣ አውሮፕላኖቹ በምን ምክንያት እንደተጋጩ ፍንጭ ሊያገኝ እንደሚችል እየተጠበቀ ነው። በአሜሪካ አየር መንገድ ከተሳፈሩት መንገዶችን እና የበረራ ሰራተኞች መካከል በህይወት የተገኘ የሌለ ሲሆን በወታደራዊ ሄሎኮፍተሩ ውስጥ የነበሩት ሦስት ሰዎች በሙሉ ህይወታቸው ማለፉን የፌደራል እና የአካባቢው ባለስልጣናት ሐሙስ እለት አረጋግጠዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለፌደራሉ የበረራ አስተዳደር መስሪያ ቤት ምክትል አስተዳዳሪ መሾምን ያካተተ ሁለት የሥራ ማስፈፀሚያ ትዕዛዞችን ሐሙስ ከሰዓት በኃላ ፈርመዋል። ትዕዛዙን በፈረሙበት ወቅትም፣ ለደረሰው የግጭት አደጋ የብዝሃነት መርሃ ግብሩ ተጠያቂ ነው ሲሉ ያለምንም ማስረጃ ከሰዋል። ትራምፕ በፌደራል መንግስት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የተተገበሩ የብዝሃነት፣ እኩልነት እና አካታችነት ፖሊሲዎችን በመጥቀስ፣ በዲሞክራት ፕሬዝዳንቶች ባራክ ኦባማ እና የጆ ባይደን የተመሩት የቀድሞ አስተዳደሮች የትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን የቅጥር መስፈርት ዝቅ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ይህን ለማወቅ «ምክንያታዊ አስተሳሰባቸውን» መጠቀማቸውን ገልጸዋል። በሄሊኮፕተሩ ላይ የነበሩትን ሦስቱንም ወታደሮች ጨምሮ ቢያንስ 28 አስክሬኖች እስካሁን ከወንዙ ማውጣት ተችሏል።   

ትረምፕ ስደተኞችን ወደ ጓንታናሞ ቤይ እንደሚልኩ አስታወቁ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ኪዩባ በሚገኘው ጓንታናሞ ቤይ እንዲያዙ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ለዚህም አስተዳደራቸው እ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ ስደተኞችን ወደ ጓንታናሞ ቤይ እንደሚልኩ አስታወቁ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ኪዩባ በሚገኘው ጓንታናሞ ቤይ እንዲያዙ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ለዚህም አስተዳደራቸው እስር ቤቱን ዝግጁ እንዲያደርግ የሚያስችል ሰነድ እንደፈረሙም ታውቋል። በኪዩባ የሚገኘው የአሜሪካ እስር ቤት፣ ጓንታናሞ ቤይ፤ ወታደራዊ እስረኞችን፣ የታሊባንና የመስከረም 11 የሽብር ጥቃት ተጠርጣሪዎችን በመያዙ ይታወቃል። የመከላከያ እና የሃገር ውስጥ ደህንነት መሥሪያ ቤቶች እስር ቤቱ 30 ሺሕ ስደተኞችን ለማስተናገድ እንዲችል ዝግጅት እንዲያደርጉም ትረምፕ አዘዋል። አንዳንዶቹ ስደተኞች ከፍተኛ ወንጀል የፈጸሙ በመሆኑና፣ የሃገራቸው መንግሥት አግቶ ያቆያቸዋል የሚል እምነት ስለሌላቸው፣ ወደ ጓንታናሞ እንድሚልኳቸው ትረምፕ አስታውቀዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የዋይት ሃውስ ባለሥልጣን፣ ትረምፕ ጓንታናሞን የተመለከተውን ሰነድ ቀድመው መፈረማቸውን ተናግረዋል። ሰነዱ ከተለመደው ፕሬዝደንታዊ ትዕዛዝ ለየት ያለ እና ‘ፌዴራል ሬጂስተር’ ተብሎ ለሚታወቀውና የመንግስት ሰነዶችን ለሚያትመው መሥሪያ ቤት እንደማይላክም ታውቋል። ለዕቅዱ ማስፈጸሚያ ገንዘብ እንዲመደብ ለማድረግ የአሜሪካ ምክር ቤት ይሁንታ እንደሚያስፈልገውም ታውቋል።

የባሕር ዳር ህፃናት "እናት' የኾነችው አሜሪካዊት

ኢትዮጵያ ውስጥ በወጣላት «ምህረት» የሚለው ስሟ የምታወቀው አሜሪካዊቷ ሜርሲ ኤሪክሰን ኢትዮጵያ ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ኖራለች፣ አማርኛም ትናገራለች።
የአሜሪካ ድምፅ

የባሕር ዳር ህፃናት "እናት' የኾነችው አሜሪካዊት

ኢትዮጵያ ውስጥ በወጣላት «ምህረት» የሚለው ስሟ የምታወቀው አሜሪካዊቷ ሜርሲ ኤሪክሰን ኢትዮጵያ ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ኖራለች፣ አማርኛም ትናገራለች። ምህረት በአማራ ክልል፣ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ለ20 ዓመታት የበጎ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ግሬስ ፋውንዴሽን መስራች ስትኾን፣ ተቋሙ አሳዳጊ አልባ ሆነው ተጥለው የተገኙ ጨቅላ ህፃናትን ሰብስቦ በማሳደግ እና የቀን ሥራ እየሠሩ ኑሯቸውን ለሚገፉ እናቶች ልጆቻቸውን በመያዝ የማቆያ አገልግሎትም ይሰጣል። ከኢትዮጵያዊ የትዳር አጋሯ ጋራ በመኾንም አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችንም ገንብተው ከ800 በላይ ልጆችን በነፃ እያስተማሩ ይገኛሉ። ከሜርሲ ኤሪክሰን ጋራ የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በምስራቅ ኮንጎ በሩዋንዳ የሚደገፉት አማፂያን ወደ ዋናው ከተማው እንደሚገፉ አስታወቁ

ምስራቃዊውን የኮንጎ ትልቅ ከተማ የተቆጣጠሩት በሩዋንዳ የሚደገፉ አማፂያን፣ ዋና ከተማውን ኪንሻን እስከሚቆጣጠሩ ድረስ ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ሐሙስ እለ
የአሜሪካ ድምፅ

በምስራቅ ኮንጎ በሩዋንዳ የሚደገፉት አማፂያን ወደ ዋናው ከተማው እንደሚገፉ አስታወቁ

ምስራቃዊውን የኮንጎ ትልቅ ከተማ የተቆጣጠሩት በሩዋንዳ የሚደገፉ አማፂያን፣ ዋና ከተማውን ኪንሻን እስከሚቆጣጠሩ ድረስ ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ሐሙስ እለት አስታውቀዋል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ በበኩላቸው አማፂያኑን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ወታደራዊ ቅስቀሳ እንዲደረግ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ የመከላከያ ሚንስትራቸውም ለውይይት የቀረበውን ጥሪ ውድቅ አድርገዋል። የኮንጎ መከላከያ ሚኒስትር ጋይ ካቦምቦ ሙአዲያምቪታ በቪዲዮ አማካኝነት ባስስተላለፉት መልዕክት፣ ውይይት ለማድረግ የሚደረግ ማንኛውም እቅድ «ወዲያውኑ እንዲከሽፍ ይደረጋል» ብለዋል። የፕሬዝዳንቱ የቅርብ አጋር የሆኑት ሙአዲያምቪታ በዚሁ መልዕክታቸው «እዚሁ ኮንጎ ቆይተን እንዋጋለን። እዚህ በህይወት መኖር ካልቻልን ደግሞ፣ እዚሁ እንሞታለን» ብለዋል። የኤም 23 አማፂያን በበኩላቸው ከመንግስት ጋራ ንግግር ለመጀመር ፈቃደኛ መሆናቸውን የተናገሩ ቢሆንም፣ ዓላማቸው ግን የፖለቲካ ስልጣን ለማግኘት መሆኑን ከቡድኑ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት ኮርኔል ናንጋአ ገልፀዋል። «ወደ ኪንሻሳ ሄደን ስልጣን መረከብ እና አገሪቱን መምራት እንፈልጋለን» ያሉት ናንጋአ፣ 1ሺህ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ዋና ከተማ እንዴት ለመግፋት እንዳሰቡ የገለጹት ነገር የለም። የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፓል ካጋሜ በኮንጎ ጉዳይ ከአንጎላ አቻቸው ጃአዎ ሎሬንኮ ጋራ መነጋገራቸውን አመልክተዋል። ሎሬንኮ ግጭቱ እንዲቆም ለማሸማገል እየሞከሩ ሲሆን፣ ከአንድ ቀን በፊት ከፕሬዝደንት ቲሺሴኬዲ ጋራ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር ሞክረዋል የተባሉ ክስ እንደቀረበባቸው ተገለጸ

ትላንት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ቡድን የተሾሙ ግለሰብ በትግራይ ክልል የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር መሞከራቸ
የአሜሪካ ድምፅ

የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር ሞክረዋል የተባሉ ክስ እንደቀረበባቸው ተገለጸ

ትላንት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ቡድን የተሾሙ ግለሰብ በትግራይ ክልል የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር መሞከራቸውን የጣቢያው ጊዜያዊ ሥራ አስከያጅ ገለጹ። ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰብ ላይም ጣቢያው ክስ መመስረቱን ተናገሩ። ጣቢያውን ሊቆጣጠሩ ነበር በሚል ወቀሳ ከቀረበባቸው ፣ አቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ ምላሽ ለማግኘት በእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ደውለን ስብሰባ ላይ መሆናቸው ስለገለፁን ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም። ጉዳዩ ኣስመልክቶ ከመቐለ ፖሊስ አዘዥ ኮማንደር አንድነት ነገሰ ተጨማሪ ማብራርያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም የመቐለ ከተማ ፖሊስ መምርያ በፌስቡክ ገጹ በአወጣው መረጃ፣ ትላንት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ኤፍኤም 104.4 “የተሾመኩት እኔ ነኝ” በሚል የተነሳ፣ ጊዜያዊ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበርና ፖሊሰ ሁኔታው ለማረጋጋት በቦታው ተገኝቶ እንደነበር አስታውቋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

እስራኤልና ሐማስ የእስረኛ እና ታጋች ልውውጥ አደረጉ

እስራኤል እና ሐማስ ዛሬ ሐሙስ ባደረጉት የእስረኞችና የታጋቾች ልውውጥ፣ ሶስት እስራኤላውያንና አምስት የታይላንድ ዜጎች የሚገኙበት ስምንት ታጋቾች መለቀቃ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤልና ሐማስ የእስረኛ እና ታጋች ልውውጥ አደረጉ

እስራኤል እና ሐማስ ዛሬ ሐሙስ ባደረጉት የእስረኞችና የታጋቾች ልውውጥ፣ ሶስት እስራኤላውያንና አምስት የታይላንድ ዜጎች የሚገኙበት ስምንት ታጋቾች መለቀቃቸውን የእስራኤል ሠራዊት አስታውቋል። በስምምነቱ መሠረት እስራኤል 110 ወታደሮችን ለቃለች፡፡ እስራኤላውያኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ እንዲገናኙ እንደሚደረግና የታይላንድ ዜጎችንም ከመግሥታቸው ጋራ እንደሚያገናኝ ሠራዊቱ ጨምሮ አስታውቋል። በተመሳሳይም 110 ፍልስጤማውያንን እስረኞችን የያዘ አውቶብስ ራማላህ፣ ዌስት ባንክ መድረሱ ታውቋል። በመቶ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞቹን በደስታ ተቀብለዋል። ከተለቀቁት ውስጥ የቀድሞ የፍልስጤማውያን ወታደራዊ ቡድን መሪ ዘካሪያ ዙቤዲ እንደሚገኝበት ታውቋል። ዙቤዲ በእስራኤል ላይ በርካታ ሕይወትን የቀጠፉ ጥቃቶችን በማቀነባበር ይከሰሳል።

ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ የአምስት ዓመት እስር ተፈረደባቸው

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለማዘዋወር በመሞከር
የአሜሪካ ድምፅ

ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ የአምስት ዓመት እስር ተፈረደባቸው

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለማዘዋወር በመሞከር ተጠርጥረው የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ በተመሠረተባቸው እነ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን ላይ ዛሬ ሐሙስ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም የእስር ቅጣት ወስኗል።  ቀሲስ በላይ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር የአምስት ዓመት እስር እና 10 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ማሳለፉን ከቀሲስ በላይ ጠበቆች አንዱ አቶ ዮናታን ዘውዴ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።   ቀሲስ በላይ የእስር ጊዜያቸውን  ከጨረሱ በኋላም ለሁለት ዓመት ከማንኛውም ማኅበራዊ ተሳትፎ እንዲገደቡም ፍርድቤቱ ወስኗል፡፡ ከቀሲስ በላይ ጋራ አንድ ላይ ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት 2ኛና 3ኛ ተከሳሾች ላይ ደግሞ እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት ከሦስት ወር እስራት እና የ3 ሺህ ብር ቅጣት  እንደተላለፈባቸው ጠበቃ ዮናታን ተናግረዋል፡፡ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአድራሻቸው ባለመገኘታቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ክሳቸው መቋረጡ ታውቋል።  በቀሲስ በላይ መዝገብ ስር ከተከሰሱት በሦስቱ ላይ ፍርድቤቱ ባለፈው  ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም “ በከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል”  የጥፋተኝነት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ በቀሲስ በላይ ላይ ፍርድቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው ካስገቡት የቅጣት ማቅለያ መካከል የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውና ህመምተኛ መሆናቸውን ጨምሮ አራት ማቅለያዎችን በመቀበል የወንጀል ደረጃቸው ከነበረበት “ እርከን 25” ወደ እርከን 21 ዝቅ በማድረግ መሆኑን ጠበቃቸው አቶ ዮናታን ተናግረዋል፡፡  ይሁንና በዚህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለጠቅላይ ፍርድቤት ይግባኝ ለመጠየቅ እየተዘጋጁ መሆኑንም ጠበቃቸው ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት ሒሳብ ቁጥር ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር በመሞከር ተጠርጥረው መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡

ኤም 23 ወደ ኪንሻሳ እንደሚገሰግስ አስታወቀ

ትላንት የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ከተማ ጎማን በአብዛኛው የተቆጣጠሩትና በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን፣ ወደ መዲናዋ ኪንሻሳ ግስጋሴያቸ
የአሜሪካ ድምፅ

ኤም 23 ወደ ኪንሻሳ እንደሚገሰግስ አስታወቀ

ትላንት የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ከተማ ጎማን በአብዛኛው የተቆጣጠሩትና በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን፣ ወደ መዲናዋ ኪንሻሳ ግስጋሴያቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። “የነጻነት ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን ነው” ያለው የአማጺያኑ መግለጫ፡፡ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቺሰኬዲ በበኩላቸው ከበድ ያለ ወታደራዊ ምላሽ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። አማጺያኑን የምትደግፈው ሩዋንዳ ፍላጎቷ በእ.አ.አ 1994 በሃገሪቱ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ላይ የተሳተፉ ተዋጊዎችን ለመደምሰስ እንደሆነ ብታስታውቅም፣ በማዕድን ሃብት ከበለጸገችው ኮንጎ ለዓለም የኤሌክትሮኒክስ ምርት ተፈላጊ ከሆነው ማዕድን ለማትረፍ ትሻለች የሚል ነቀፌታ ይቀርብባታል። “የነጻነት ግስጋሴያችንን እስከ ኪንሻሳ ድረስ እንቀጥላለን” ነው ያሉት ኤም 23ትን የሚጨምረው የአማጺያን ቅንጅት መሪ የሆኑት ኮርኔሊ ናጋ። በጎማ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት እንዲመለስ እንደሚያደርጉ የገለጹት የአማጺያኑ መሪ፣ የፀጥታ ጥበቃውም እንደሚደረግ ተናግረዋል። የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቺሰኬዲ ትላንት ለሃገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር፣ አሸባሪ ብለው ለጠሯቸው አማጺያኑ ግስጋሴ “ጠንከር ያለና የተቀናጀ” ያሉት ወታደራዊ ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ኾነው ተሾሙ

ዛሬ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ/ም መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ብርሃኑ አዴሎን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽ
የአሜሪካ ድምፅ

አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ኾነው ተሾሙ

ዛሬ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ/ም መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ብርሃኑ አዴሎን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አድርጐ ሾሟል። ለምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ የሰጡት አፈጉባኤ ታገሰ ጫ፣ አቶ ብርሃኑ በርካታ ዕጬዎች የተፎካከሩበትን ሂደት አልፈው ያሸነፉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በምክር ቤቱ የተቃዋሚ ተመራጭ አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በበኩላቸው፣ አቶ ብርሃኑ በኢሕአዴግ የሥልጣን ዘመን በከፍተኛ ኃላፊነት ያገለገሉ መሆናቸው የገለልተኝነት ጥያቄ እንዳያስነሳና በሚመሩት ተቋም ገጽታ ላይም አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳያሳድር ስጋታቸውን ገልጸዋል ። «በግልጽ የሚታይ የፖለቲካ ገለልተኝነት ያላቸው ሰዎች የሉም ወይ?» በማለትም ጠይቀዋል። አፈ ጉባኤ ታገሰ በሰጡት ምላሽ፣ ተሿሚው ባለፉት ዐሥራ  አምስት ዓመታት በግል የሕግ ማማከር ሥራ ላይ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል። አቶ ብርሃኑን በቅርበት እንደሚያውቁ የገለጹ ሌሎች የፓርላማ አባላት በበኩላቸው፣ ለተሾሙበት ኃላፊነት የሚመጥን ስብዕና፣የትምህርት ዝግጅት፣የሥራ ልምድና ገለልተኝነት ያላቸው ናቸው ሲሉ ድጋፋቸውን ገልጸዋል ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፣«የዋና ኮሚሽነር ሹመት በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ 210/1992 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) አንቀጽ 10፣ 11 እና 12 በተደነገገው መሠረት የተካሄደ ነው» ብሏል። አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ያገለገሉ መሆናቸውን የጠቀሰው የኮሚሽኑ መግለጫ፣ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር፣ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንደነበሩ አስታውሷል። ሹመቱን በማስመልከት መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፣ወቅታዊው የሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጠንካራ አመራር እና ውጤታማ የሰብአዊ መብቶች ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል ። የኢሰመኮን ኮሚሽነሮች እና ባልደረባዎች በመወከልም ለዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ መልካም የሥራ ዘመን ተመኝተዋል ።

ከሄሊኮፕተር ጋራ የተጋጨው የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጓዦች በሙሉ አይተርፉም ተባለ

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ 60 መንገደኞችን የያዘ አንድ አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ረቡዕ ምሽት ተጋጭተው ፖቶማክ ወንዝ ውስ
የአሜሪካ ድምፅ

ከሄሊኮፕተር ጋራ የተጋጨው የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጓዦች በሙሉ አይተርፉም ተባለ

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ 60 መንገደኞችን የያዘ አንድ አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ረቡዕ ምሽት ተጋጭተው ፖቶማክ ወንዝ ውስጥ ተከስክሰዋል።  የአደጋ ሠራተኞች እስከ አሁን 28 አስከሬኖች ከወንዙ ማውጣቸውንም ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል። በአውሮፕላን ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች በሙሉ ሕይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉም ባለሥልጣናት ዛሬ ማለዳ አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት ሰዎችን በሕይወት ከማግኘት ወደ አስከሬን ፍለጋ ሥራ መሠማራታቸውን የዋሽንግተን ዲሲ የእሳት አደጋ መከላከያ ሃላፊ ጃን ዳናሊ አስታውቀዋል። “የሚተርፍ ሰው ይኖራል ብለን አናምንም” ብለዋል ኃላፊው። ስድሳ መንገደኞችን እና አራት ሠራተኞችን ይዞ ከካንሳስ የተነሳው የአሜሪካን አየር መንገድ አውሮፕላን በዋሽንግተን ሬገን አየር ማረፊያ ለማረፍ በመዘጋጀት ላይ ሳለ ነበር ሦስት ወታደሮችን ከያዘውና በሥልጠና ላይ ከነበረው ‘ብላክ ሆክ’ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ጋራ የተጋጨው። ከአደጋው የተረፉ እንዳሉ ለማግኘት ሦስት መቶ የሚሆኑ የአደጋ ሠራተኞችና ባሕር ሰርጓጆች ቀዝቃዛውን የፖቶማክ ወንዝ ውሃ ምሽቱን ሁሉ ሲያስሡ ቢያድሩም በሕይወት ያገኙት ሰው እንደሌለ ታውቋል። የአሜሪካ ብዙኅን መገናኛ በርካታ አስከሬኖች ከወንዙ ውስጥ መውጣታቸውን በመዘገብ ላይ ናቸው። ከተሳፋሪዎች ውስጥ የአሜሪካ ‘ፊገር ስኬቲንግ’ ወይም የበረዶ ላይ ትርዒት ስፖርት ቡድን ዓባላትና ቤተሰቦቻቸው እንደሚገኙበት የስፖርት ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከእነዚህም ውስጥ ሁለቱ አሠልጣኞች ሩሲያዊ የቀድሞ የበረዶ ላይ ትርዒት የኦሎምፒክ አሸናፊዎች መሆናቸውን ክሬምሊን አረጋግጧል።

አንድ የመንገደኞች አውሮፕላንና ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ዋሽንግተን ዲሲ አየር ማረፊያ አቅራቢያ ተጋጩ

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄኪኮፕተር ረቡዕ ምሽት ተጋጭተው ፖቶማክ ወንዝ ውስጥ ተከስ
የአሜሪካ ድምፅ

አንድ የመንገደኞች አውሮፕላንና ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ዋሽንግተን ዲሲ አየር ማረፊያ አቅራቢያ ተጋጩ

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄኪኮፕተር ረቡዕ ምሽት ተጋጭተው ፖቶማክ ወንዝ ውስጥ ተከስክሰዋል። በአሜሪካ አየር መንገድ የሚተዳደረው አውሮፕላን 60 መንገደኞችን እንደያዘ ሲታወቅ ሄሊኮፕተሩ ደግሞ ሶስት ሰዎችን ይዞ ነበር ተብሏል። የአደጋ ሠራተኞች ይህ ዜና በሚታተምበት ሰዓት ርብርብ ላይ ሲሆኑ፡ ሕይወታቸውን ያጡ በርካታ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ሪፖርቶች አመልክተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት እንዲቀር ትረምፕ ግፊት እያደረጉ ነው

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ “በመወለድ የሚገኝ ዜግነት” በመባል የሚታወቀው የዜግነት መብት’ እንዲቀር ወይም እንዲቋረጥ የሚያደርግ ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ (ትዕ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት እንዲቀር ትረምፕ ግፊት እያደረጉ ነው

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ “በመወለድ የሚገኝ ዜግነት” በመባል የሚታወቀው የዜግነት መብት’ እንዲቀር ወይም እንዲቋረጥ የሚያደርግ ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ (ትዕዛዝ) ፈርመዋል፡፡ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1868 የጸደቀው 14ኛው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ አንድ ሰው የወላጆቹ የዜግነት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ውስጥ እስከተወለደ ድረስ የዜግነት መብቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን የሲቪል መብቶች ዋና አካል ተደርጎ ይታያል፡፡ የፕሬዝደንት ትረምፕ ትዕዛዝ ታዲያ በአስፈጻሚው አካል ሥልጣን እና በሕገ መንግሥት ማሻሻያው ዙሪያ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ ክርክሮች ቀስቅሷል። የአሜሪካ ድምጿ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዘጋቢ አሊን ባሮስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የትረምፕ አስተዳደር ሥራቸውን ለሚለቁ የመንግሥት ሠራተኞች ጉርሻ እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲሱ የዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር፣ ፍላጎት ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች በመጪው መስከረም መጨረሻ ሥራቸውን በፈቃዳቸው የሚለቁ ከሆነ የስምንት ወር ደመወዝ
የአሜሪካ ድምፅ

የትረምፕ አስተዳደር ሥራቸውን ለሚለቁ የመንግሥት ሠራተኞች ጉርሻ እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲሱ የዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር፣ ፍላጎት ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች በመጪው መስከረም መጨረሻ ሥራቸውን በፈቃዳቸው የሚለቁ ከሆነ የስምንት ወር ደመወዝ ጉርሻ እንደሚሰጥ ትላንት ለመንግሥት ሠራተኞች በላከው ኢሜይል አስታውቋል። ፕሮግራሙ የዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችንና ሠራተኞችን ለመቀነስ የያዘው ዕቅድ አካል መሆኑ ተመልክቷል። ሠራተኞች ፍላጎታቸውን እስከ መጪው ሐሙስ ማለትም እአአ የካቲት 6 ቀን ድረስ ማሳወቅ እንዳለባቸው ተመልክቷል። ይህን የሚያደርጉ ሠራተኞች፣ የመንግሥት ሠራተኞች ሙሉ ለሙሉ ከቢሮ እንዲሠሩ የሚያዘው ደንብ ላይመለከታቸው እንደሚችልም ታውቋል። በስደተኞችና በብሔራዊ ፀጥታ ጉዳይ ላይ የሚሠሩ እንዲሁም የፖስታ ቤት ሠራተኞች ፕሮግራሙ እንደማይመለከታቸውም ተመልክቷል። የመንግሥት ሠራተኞችን የሚወክሉ የሠራተኛ ማኅበራት የአስተዳደሩን ሐሳብ ተቃውመዋል። ሠራተኞች እንዳይስማሙም መክረዋል። “የፌዴራል ሠራተኞች ታማኝ፣ አስተማማኝና በየቀኑ ለመሻሻል የሚጥሩ መሆን አለባቸው” ብሏል ከአስተዳደሩ የተላከው መልዕክት፡፡ የቪኦኤ ሠራተኞችን ጭምር የሚወክለው የአሜሪካ መንግሥት ሠራተኞች ፌዴሬሽን ኃላፊ ኤቨረት ኬሊ፣ «ሠራተኞች አዲሱ ፕሮግራም በፈቃደኝነት የሚያደርጉት ጉዳይ አድርገው እንዳያዩት» አሳስበዋል። አክለውም ፣"የአስተዳደሩ ተግባር የሚያሳየው በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ጤናማ ያልሆነ አካባቢን መፍጠርና ሠራተኞች መቆየት ቢሹ እንኳ ሥራቸውን መቀጠል እንዳይችሉ ለማድረግ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ የመጀመሪያው በመርከብ የተጫነ ዕርዳታ ወደ ጋዛ ተላከ

ያዝ ለቀቅ የሚያደርገው የጋዛ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተባለ ርዳታ የያዘ የቱርክ መርከብ ግብጽ ወደብ መድረሱን አንድ የቱርክ ባ
የአሜሪካ ድምፅ

ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ የመጀመሪያው በመርከብ የተጫነ ዕርዳታ ወደ ጋዛ ተላከ

ያዝ ለቀቅ የሚያደርገው የጋዛ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተባለ ርዳታ የያዘ የቱርክ መርከብ ግብጽ ወደብ መድረሱን አንድ የቱርክ ባለሥልጣን እና የግብጽ ምንጮች አስታውቀዋል። መርከቡ ብርድ ልብስ፣ ድንኳን፣ ተንቀሳቃሽ መጸዳጃና ጄኔሬተሮች ጨምሮ 871 ቶን የሰብአዊ ርዳታ እንደያዘም ተነግሯል። “የጋዛ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ቁስል ለማዳንና ጊዜያዊ የመጠለያ ፍላጎታቸውንም ለማሟላት ተዘጋጅተናል” ሲሉ የቱርኩ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ምኒስትር አሊ የርሊካያ በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ አስታውቀዋል። ከግብጽ የቀይ ጨረቃ ማኅበር የተዋቀረ ቡድን ከቱርክ የተላከውን ዕርዳታ ተረክቦ ወደ ጋዛ ሠርጥ ለማድረስ በዝግጅት ላይ መሆኑን ከጋዛ ሠርጥ 50 ኪሎ ሜትር ላይ በሚርቀው ወደብ የሚገኙ ምንጭ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል። የተኩስ ማቆም ስምምነቱን ተከትሎ በመቶ የሚቆጠሩና ርዳታ የጫኑ ከባድ መኪናዎች ጋዛ ሲገቡ የተወሰነ ርዳታ ደግሞ በአየር ተጓጉዟል።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ መወያየቱን አስታወቀ

(ዝርዝሩን ከላይ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ) ከፋኖ ታጣቂ ቡድኖች ውስጥ የአንዱ መሪ የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ በእርሳቸው የሚመራው ቡድን ባለፈው ሳም
የአሜሪካ ድምፅ

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ መወያየቱን አስታወቀ

(ዝርዝሩን ከላይ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ) ከፋኖ ታጣቂ ቡድኖች ውስጥ የአንዱ መሪ የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ በእርሳቸው የሚመራው ቡድን ባለፈው ሳምንት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ በአማራ ክልል ተገናኝቶ መነጋገሩን ለአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል አስታውቀዋል። የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የተሰኘውና በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂ የፋኖ ቡድኖች አንዱ መሪ እንደሆኑ የሚገልጹት አቶ እስክንድር ነጋ፣ ከእርሳቸው ቡድን ወገን እና ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች የተውጣጡ የቴክኒካል ቡድኖች ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በስም ባልተጠቀሰ ሥፍራ ውይይት ማድረጋቸውን ከአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል። ከዓለም አቀፍ ቡድኑ ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት፣ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)፣ የአውሮፓ ኅብረት እንዲሁም በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ተወካዮች እንደሚገኙበት አቶ እስክንድር አስታውቀዋል። ስብሰባው የተካሂደው ከእነዚሁ ዓለም አቀፍ ተወካዮች ጋራ ከአንድ ወር በፊት የተደረገን የስልክ ውይይት ተከትሎ እንደሆነ አቶ እስክንድር ጠቁመዋል። “ይህ በቴክኒካል ቡድኖች መካከል የተካሄደ ስብሰባ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ስብሰባ ነው ያደረግነው።  የተወያየነውም በሃገሪቱ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መገናኘትና መነጋገር በምንችልበት ላይ ነው።” የውይይቱ ርዕሶች ምን እንደነበሩ የተጠየቁት አቶ እስክንድር፣ ከዓለም አቀፍ ቡድኑ ጋራ ለመተዋወቅ የተደረገና ቡድናቸው በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን አቋም ለመግልጽ የተፈጠረ ዕድል እንደነበር ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህምድ ባለፈው ወር ሲናገሩ፣ አማጺ ቡድኖች ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጡ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል። “ለአንድ ሺሕ ዓመት ብትዋጉንም፣ አታሸንፉንም፣ ስለዚህ ወደ ሰላም ኑ” ሲሉ ጠቅላይ ምኒስትሩ መናገራቸውም ይታወሳል። ከፌዴራል መንግሥት ጋራ መደራደር የሚለው ጉዳይ በውይይቱ ወቅት እንዳልተነሳም አቶ እስክንድር ገልጸዋል።  “ይህ ጉዳይ አልተነሳም” ያሉት አቶ እስክንድር “እናም ጉዳዩ ሳይነሳ መልስ መስጠት አልችልም። ይህ እኔ የምወስነው ጉዳይ አይደለም። ይህ በሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ የሚወሰን ነው። ጥያቄው ሲመጣ፣ ወደ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እወስደዋለሁ። እናም ሥራ አስፈጻሚው ምን እንደሚል እናያለን።” ብለዋል። መንግሥት በሃገሪቱ የሚገኙ ታጣቂዎችን በትኖ በፌዴራል መንግሥቱ ኅይል ሥር ለማካተትና ወደ ማኅበረሰቡ መልሰው እንዲቀላቀሉ ለማድረግ መወሰኑን ተከትሎ፣ በፋኖ ታጣቂዎችና በፌዴራል መንግሥት ኅይሎች መካከል በሚያዚያ 2015 ግጭት ተቀስቅሷል። በዛው ዓመት ነሐሴ ላይ መንግሥት 23 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በሚኖርበት በአማራ ክልል አስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል።  የአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ኅብረት፣ ኢጋድ፣ የአውሮፓ ኅብረት እንዲሁም ኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቋል። አስተያየታቸው እንደደረሰን እናቀርባለን።

ቴምብር አሰባሳቢው ህንዳዊ ዲፕሎማት 

የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቴምብሮች አሰባስቦ የያዘው ህንዳዊ ዲፕሎማት፣ ቴምብር አገልግሎት ላይ መዋል ከጀመረበት ጀምሮ የተለያዩ ሀገራት ቴምብሮችን ሰብስቧል።
የአሜሪካ ድምፅ

ቴምብር አሰባሳቢው ህንዳዊ ዲፕሎማት 

የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቴምብሮች አሰባስቦ የያዘው ህንዳዊ ዲፕሎማት፣ ቴምብር አገልግሎት ላይ መዋል ከጀመረበት ጀምሮ የተለያዩ ሀገራት ቴምብሮችን ሰብስቧል። ከ13 ዓመቱ ጀምሮ መሰብሰብ የጀመረው በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ ሠራተኛ ሃች ቬንካታቻላም ከ50 በላይ ሀገራትን ቆየት ያሉ ቴምብሮች አሰባስቦ ይዟል።   ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዩናይትድ ስቴትስ ኤም 23 ቡድን በምሥራቅ ኮንጎ ያደረሰውን ጥቃት አወገዘች

በሩዋንዳ የሚታገዘው ኤም 23 የተባለው ታጣቂ ቡድን ቁልፍ የሆነችውን የምሥራቅ ኮንጎ ዋና ከተማ ተቆጣጥሬአለሁ ማለቱን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ድርጊቱን አውግ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ ኤም 23 ቡድን በምሥራቅ ኮንጎ ያደረሰውን ጥቃት አወገዘች

በሩዋንዳ የሚታገዘው ኤም 23 የተባለው ታጣቂ ቡድን ቁልፍ የሆነችውን የምሥራቅ ኮንጎ ዋና ከተማ ተቆጣጥሬአለሁ ማለቱን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ድርጊቱን አውግዛለች። በተያያዘ ዜና የኬኒያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ  ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፌሊክስ ቲሺኬሴዲ እና ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ቀውሱን በሚመለከት  ነገ ረቡዕ ለመወያየት ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል።  የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር  እንዳስታወቀው  ትላንት ሰኞ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ቲሺሴኬዲን  በስልክ  ያነጋገሯቸው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ « በሩዋንዳ የሚታገዘው ኤም 23 ጎማ ላይ ያደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል። ዩናይትድ ስቴትስ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክን ሉዓላዊነት እንደምታከብር አረጋግጠውላቸዋል» ብሏል። ግጭቱ ወታደራዊ መፍትሄ የማይገኝለት እንደሆነ የጠቆሙት የኬኒያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ፕሬዝደንት ሺሴኬዲ እና ፕሬዝደንት ካጋሜ  ነገ ረቡዕ  ለመወያየት እንደተስማሙ አመልክተዋል። ይህ በዚህ እንዳለ ታጣቂው ቡድን ጎማን እንደያዘ ከተናገረም በኋላ ከተማዋ ውስጥ በቡድኑ እና በኮንጎ ኃይሎች መካከል ውጊያው እንደቀጠለ መሆኑን ኮንጎ የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለሥልጣን ትላንት ሰኞ ተናግረዋል። ኮንጎ ተቀማጩ የመንግሥታቱ ድርጅት አስተባባሪ ብሩኖ ለማርኪስ ከኪንሳሻ በሰጡት ቃል ውጊያው ጎማ ውስጥ በሁሉም አቅጣጫ መስፋፋቱን ጠቁመው ሁኔታው እጅግ አደገኛ እንደሆነ ገልጸዋል። የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት፥ የድርጅቱ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ እና ሌሎችም የድርጅቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ታጣቂው ቡድን በአስቸኳይ ውጊያ እንዲያቆም እና ከያዛቸው ግዛቶች እንዲወጣ ጠይቀዋል። የሩዋንዳ ኃይሎችም እንዲወጡ የጠየቁት ባለሥልጣናቱ ሁለቱ ወገኖች የአንጎላ  ፕሬዝደንት ዡዋው ሎሬንሶ ወደሚመሩት የሽምግልና ሂደት እንዲመለሱ አሳስበዋል።

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ለዳርፉር ወንጀል ተፈላጊዎች ማዘዣ እንደሚያወጣ አስታወቀ

በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ክፍለ ግዛት ሲቪሎች ላይ ግፍ በመፈጸም የተወነጀሉ ሰዎች እንዲያዙ የእሥር ማዘዣ ለማውጣት እየተዘጋጁ መሆኑን የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍ
የአሜሪካ ድምፅ

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ለዳርፉር ወንጀል ተፈላጊዎች ማዘዣ እንደሚያወጣ አስታወቀ

በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ክፍለ ግዛት ሲቪሎች ላይ ግፍ በመፈጸም የተወነጀሉ ሰዎች እንዲያዙ የእሥር ማዘዣ ለማውጣት እየተዘጋጁ መሆኑን የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ አስታወቁ። ላለፉት 19 ወራት ከሱዳን መንግሥት ኃይሎች ጋር እየተዋጉ ያሉት ታጣቂ ኃይሎች የጎሣ ማጽዳት አድራጎት በመፈጸም ተወንጅለዋል። የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ ካሪም ኻን ትላንት ለመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ትላንት ሰኞ በሰጡት ማብራሪያ ዳርፉር ውስጥ እነዚህ ወንጀሎች  «በየቀኑ አሁን በዚህ ሰዓትም ጭምር እየተፈጸሙ ነው» ብለዋል። ታጣቂዎቹ ድርጊቱን በጦር መሣሪያነት እየተጠቀመበት ነው ያሉት አቃቤ ህጉ ቢሮአቸው ከዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው የምስክሮች ቃል እና ሌሎችም መረጃዎች አሰባስቦ ጥልቅ የሆነ ግምገማ አካሂዶ መሆኑን ለምክር ቤቱ ገልጸዋል። የባይደን አስተዳደር ከመሰናበቱ ጥቂት ቀደም ብሎ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ቡድን እና ተባባሪዎቹ በሀገሪቱ እየተካሂደ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸሙ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን እንዳስታወቀ ይታወሳል።

ከሦስት መቶ ሺህ በላይ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮች ወደጋዛ ከተማ መመለሳቸው ተገለጸ

በእስራኤል እና በሐማስ ጦርነት የተፈናቀሉ ከሦስት መቶ ሺህ የሚበልጡ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮች ትላንት ሰኞ ወደ ሰሜናዊ ጋዛ  መመለሳቸውን በሐማስ የሚመራ
የአሜሪካ ድምፅ

ከሦስት መቶ ሺህ በላይ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮች ወደጋዛ ከተማ መመለሳቸው ተገለጸ

በእስራኤል እና በሐማስ ጦርነት የተፈናቀሉ ከሦስት መቶ ሺህ የሚበልጡ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮች ትላንት ሰኞ ወደ ሰሜናዊ ጋዛ  መመለሳቸውን በሐማስ የሚመራው የጋዛ ሰርጥ መንግሥት ባለስልጣናት ተናገሩ። ተፈናቃዮቹ የተመለሱት እስራኤል የፍተሻ ኬላዎቹን ከፍታ እንዲመለሱ መፍቀዷን ተከትሎ ነው። ፍልስጥኤማዊያኑ አብዛኞቹ በእግራቸው  የቻሉትን ያህል ዕቃ ተሸክመው  ጦርነቱ እንደተጀመረ ጥለውት ወደሸሹት እና ይኑር ይፍረስ ወደማያውቁት የቀድሞ መኖሪያቸው ተጉዘዋል።  እስራኤል የሐማስ ታጣቂዎችን እና ፈንጂ ያጠመዱባቸውን ህንጻዎች ዒላማ አድርጋ ባደረሰችው የቦምብ ድብደባ አብዛኛው አካባቢ ወድሟል። እስራኤል እ አ አ በ2023 ጥቅምት ውስጥ ጥቃቱን እንደጀመረች  ወደአንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ነዋሪዎች ከሰሜናዊ ጋዛ እንዲወጡ ማዘዟ ሲታወስ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ለመጀመሪያ ጊዜ መፈቀዱ ነው። ፍልስጥኤማዊያኑ ወደጋዛ ከተማ የተመለሱት በእስራኤል እና በሐማስ የተደረሰው የስድስት ሳምንታት የተኩስ አቁም የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት መሆኑ ነው። የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተከትሎ  እስካሁን  ሰባት ታጋቾች ከጋዛ ሲለቀቁ  እስራኤል  ሦስት መቶ የሚሆኑ ፍልስጥኤማዊያን እሥረኞች ለቅቃለች። ሰብዓዊ ረድዔትም በብዛት ወደጋዛ መግባት ጀምሯል። ትላንት እስራኤል እንዳለችው ሐማስ በመጀመሪያው የተኩሥ አቁም ውሉ ምዕራፍ ስለሚለቀቁት ታጋቾች እና ከቀሩት ታጋቾቹ መካከል ስምንቱ በሕይወት እንደሌሉ አሳውቋታል።  ሐማስ ተጨማሪ ታጋቾችን በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ እንደሚለቅቅ ተመልክቷል። ይህ በዚህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ « ጋዛን ለማጽዳት የሚደረገው » ሲሉ በገለጹት ጥረት ዮርዳኖስ እና ግብጽ ተጨማሪ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮችን እንዲቀበሉ የሚፈልጉ መሆኑን ተናግረዋል። ሆኖም ሁለቱ ሀገሮች ብቸኛው የመፍትሄ  እርምጃ ከእስራኤል ጎን ለጎን የፍልስጤም መንግሥት መመሥረት ብቻ መሆኑን በማመልከት ሃሳቡን ውድቅ አድርገውታል። ዩናይትድ ስቴትስ የፍልስጤም አገረ መንግሥት መቋቋምን ሃሳብ ለረጅም ጊዜ ስትደግፍ ቆይታለች። የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ግን ይቃወማሉ።

ሲ ዲ ሲ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያካሂዳቸውን ሥራዎች በአስቸኳይ እንዲያቆም ታዘዘ

የዩናይትድ ስቴትስ የጤና ባለሥልጣናት ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር የሚሠሯቸውን ሥራዎች በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል። ድንገተኛው ትዕዛዝ ያተ
የአሜሪካ ድምፅ

ሲ ዲ ሲ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያካሂዳቸውን ሥራዎች በአስቸኳይ እንዲያቆም ታዘዘ

የዩናይትድ ስቴትስ የጤና ባለሥልጣናት ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር የሚሠሯቸውን ሥራዎች በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል። ድንገተኛው ትዕዛዝ ያተኮረው በዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ተቋም ላይ ሲሆን የተቋሙ ባለሥልጣን የሆኑት ጆን ኒኬንጋሶንግ  ለከፍተኛ አመራሮች ዕሁድ ማታ በላኩት ማሳሰቢያ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር የሚሠሩ የተቋሙ ሠራተኞች በአስቸኳይ አቁመው ቀጣይ መመሪያ እስከሚሰጥ እንዲጠብቁ ማዘዛቸውን መመሪያውን የተመለከተው አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል። የጤና ጥበቃ አዋቂ ባለሞያዎች ድንገተኛው ትዕዛዝ አፍሪካ ውስጥ ማርበርግ ቫይረስ እና ኤምፖክስ የመሳሰሉ ወረርሽኞችን እና ሌሎችንም ዓለም አቀፍ የጤና ስጋቶችለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶች እና ምርምሮችን ያስተጓጉላል የሚል ስጋት እንዳላቸው አመልክተዋል። ትዕዛዙ የተሰጠው በዓለም ዙሪያ ያሉ የጤና ባለሥልጣናት በአሜሪካ እንስሳት ላይ የተቀሰቀሰውን የአእዋፍ ወረርሽኝ ለመከታተል ጥረት እያደረጉ ባለበት በዚህ ወቅት መሆኑ ተጠቁሟል። የተላለፈው መመሪያ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር  በትብብር የሚሠሩ ሥራዎች በሙሉ እንዲቋረጡ የሚያዝ ሲሆን የድርጅቱ መሥሪያ ቤቶች በአካል መጎብኘትም ይሁን በኢንተርኔት አማካይነት መገናኘት ይከለክላል። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስን ከዓለም የጤና ድርጅት አባልነት የማስወጣት ሂደት እንዲጀመር ባለፈው ሳምንት አስፈጻሚ ትዕዛዝ የፈረሙ ቢሆንም  ሂደቱ ወዲያውኑ አልተጀመረም። ከዓለሙ የጤና ድርጅት እንድትወጣ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት መፍቀድ አለበት። እስከዛ አሜሪካ የዓመቱን ክፍያዋን መፈጸም ያለባት ሲሆን ከድርጅቱ ለመውጣት የአንድ ዓመት ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መስጠት ይኖርባታል።

ጣሊያን 49 ፍልሰተኞችን ወደአልቤኒያ ላከች

ጣሊያን ባህር ላይ ያገኘቻቸውን 49 ፍልሰተኞች በባሕር ኃይል መርከብ አሳፍራ ወደአልቤኒያ ልካለች። ጣሊያን  ስደተኞችን በሦስተኛ ሀገር ለማስፈር ያላት ዕቅድ
የአሜሪካ ድምፅ

ጣሊያን 49 ፍልሰተኞችን ወደአልቤኒያ ላከች

ጣሊያን ባህር ላይ ያገኘቻቸውን 49 ፍልሰተኞች በባሕር ኃይል መርከብ አሳፍራ ወደአልቤኒያ ልካለች። ጣሊያን  ስደተኞችን በሦስተኛ ሀገር ለማስፈር ያላት ዕቅድ በፍርድ ቤት ክስ ቢከፈትበትም በዕቅዷ ለመግፋት  ባደረገችው ሙከራ የላከቻቸው ስደተኞች ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ አልቤኒያ  ወደብ መድረሳቸውን ሮይተርስ እማኞቹን ጠቅሶ ዘግቧል። ፍልሰተኞቹ ተመዝግበው ከወደቡ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ  ወደሚገኝ ማቆያ ካምፕ እንደሚላኩ ታውቋል። የጣሊያኑ የጆርጂያ መሎኒ መንግሥት አልቤኒያ ውስጥ ሁለት ፍልሰተኛ መቀበያ ማዕከሎችን አቋቁሟል። የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር በባህር ወደግዛቱ የሚፈልሱ ስደተኞችን ቁጥር ለመገደብ  በሚል የህብረቱ አባል ካልሆነ ሀገር ጋር እንዲህ ያለ ስምምነት በማድረግ የመጀመሪያ መሆኑ ተመልክቷል። ባለፈው ሕዳር በዕቅዱ ሕጋዊነት ዙሪያ ጥያቄ ያነሱ የሮም ፍርድ ቤት ዳኞች ወደአልቤኒያ የተላኩት ስደተኞች ትዕዛዝ መስጠታቸውን ተከትሎ በሁለቱም  የማቆያ ካምፖቹ እስካሁን ስደተኞች እለመኖራቸውን ዘገባው  ጨምሮ አውስቷል።  

በማርኮ ሩቢዮ  የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት  የአሜሪካ የአፍሪካ ፖሊሲ ምን ይመስል ይኾን? 

ማርኮ ሮቢዮ አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኾነዋል፡፡ ሩቢዮ ቻይናን በሚመለከት ጠንካራ አቋም ያላቸው ናቸው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአሜሪካ
የአሜሪካ ድምፅ

በማርኮ ሩቢዮ  የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት  የአሜሪካ የአፍሪካ ፖሊሲ ምን ይመስል ይኾን? 

ማርኮ ሮቢዮ አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኾነዋል፡፡ ሩቢዮ ቻይናን በሚመለከት ጠንካራ አቋም ያላቸው ናቸው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአሜሪካን ጥቅም በማራመድ እንደሚሠሩም ቃል ገብተዋል፡፡ ይሁን እንጂ አፍሪካን በሚመለከት የሚከተሉት ፖሊሲ እንደምን ያለ እንደሚሆን በዝርዝር አላሳወቁም፡፡ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት በበኩላቸው ሀገራቸው በአዲሱ የትረምፕ አስተዳደር ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ በሚኖራት ግንኙነት እንደሚተማመኑ ተናግረዋል፡፡ ኬት ባርትሌት ከጆሐንስበርግ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Get more results via ClueGoal