ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በትግራዩ ውጥረት ዙሪያ የሰጡት አስተያየት
newsare.net
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል የፖለቲካ ኃይሎች መካከል በቀጠለው የፖለቲካ ልዩነት ዙሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት ሰጡ። በዛጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በትግራዩ ውጥረት ዙሪያ የሰጡት አስተያየት
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል የፖለቲካ ኃይሎች መካከል በቀጠለው የፖለቲካ ልዩነት ዙሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት ሰጡ። በዛሬው ዕለት በፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ "የትግራይ የፖለቲካ መሪዎች እና ልሂቃን የውስጥ ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ’ ሲሉ ጥሪ ያሰሙት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ፣ ከሌሎች ክልሎች ይሁን ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር የሚነሱ ማናቸውም ልዩነቶች የሃገሪቱ ሕገ መንግሥት በሚያዘው መሠረት ሊፈቱ ይገባል’ ብለዋል። የትግራዩ የፖለቲካ አለመግባባት በቅርቡ አንዳንድ የክልሉ የጦር አዛዦች ድጋፋቸውን ለሕወሐት ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከገለጹ በኋላ ከክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ጋራ የገቡት ብርቱ የፖለቲካ ውዝግብ ተባብሶ መቀጠሉ ተዘግቧል። የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ የክልሉ ምክር ቤት ከተበተነ ከዓመታት በኋላ በትላንትናው ዕለት አማካሪ ምክር ቤት ተመስርቷል። የአማካሪው ምክር ቤት ፕሬዝዳንቱን ከመሰየም በመለስ የክልል ምክር ቤቱን ሥራ እንደሚሠራ ተገልጿል። እርምጃውን የተቃወሙት የሕወሐት መሪ አማካሪ ጉባኤውን ድርጅታቸውን ለመበተን የታለመ ሲሉ ተከራክረዋል። ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ የትግራይ ሕዝብ “የትላንት ቁስሉ ሳይጠግ፣ አሁንም በፍርሃት እና በተሸበረ ሥሜት እንዳለ ነው” ብለዋል። Read more