ፊላደልፊያ ኤግልስ ቡድን ካንሳስ ቺፍስን ቡድን በመርታት «የሱፐር ቦል» አሸናፊ ኾነ
newsare.net
የፊላደልፊያ ኢግልስ ቡድን የካንሳስ ቺፍስ ቡድን ላይ የበላይነትን በመቀዳጀት የዘንድሮው የአሜሪካ እግር ኳስ ሊጎች የፍጻሜ ጨዋታ «ሱፐር ቦል» አሸናፊፊላደልፊያ ኤግልስ ቡድን ካንሳስ ቺፍስን ቡድን በመርታት «የሱፐር ቦል» አሸናፊ ኾነ
የፊላደልፊያ ኢግልስ ቡድን የካንሳስ ቺፍስ ቡድን ላይ የበላይነትን በመቀዳጀት የዘንድሮው የአሜሪካ እግር ኳስ ሊጎች የፍጻሜ ጨዋታ «ሱፐር ቦል» አሸናፊ ኾነ። አሸናፊው ቡድን ያለፈው ዓመት ቻምፒዮንተ ፎካካሪውን የረታው 40-22 በኾነ ውጤት ነው። የካንሳስ ቺፍ ቡድን ለሦስተኛ ተከታታይ ዓመት የአሜሪካ ብሔራዊ ሊግ አሸናፊ ይሆናል በሚል ተስፋ ከተፎካካሪው ቡድን በመጠኑ የላቀ ግምት ተሰጥቶት ነበር። ይሁንና ኒው ኦርሌየንስ ከተማ ሲዛርስ ሱፐርደም ውስጥ በተካሄደው ጨዋታ የፊላደልፊያ ኤግልስ ተጫዎቾች 34 ነጥቦችን እስካስቆጠሩበት ሦስተኛው የጨዋታው ምዕራፍ ድረስ የካንሳስ ቺፍስ ተጫዎቾች አንድም ነጥብ እንዳያስቆጥሩ ማድረግ ችለዋል። የፊላደልፊያ ኤግልስ አጥቂ መስመር ተጨዋች ጄለን ኸርትስ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተሰይሟል። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጨዋታውን በአካል ተገኝተው የተመለከቱ ሲኾን ፣ በሥልጣን ዘመኑ «ሱፐር ቦል» ጨዋታን በስፍራው ተገኝቶ የተመለከተ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነዋል። ከጨዋታው በፊት ፕሬዝደንቱ ባሰራጩት የፕሬስ መግለጫ ላይ «እግር ኳስ የአሜሪካ እጅግ ተወዳጅ ስፖርት ነው። ለዚህም መልካም ምክንያቶች አሉ። የብሔራዊ አንድነት ስሜትን ያጎለብታል፣ ቤተሰቦችን፣ ጓደኞችን እና ደጋፊዎችን አንድ ላይ በማሰባሰብ ማኅበረሰቦችን ያጠናክራል» ብለዋል። «ይህ ዓመታዊ ልማድ ልዩነቶቻችንን የሚሻገር እና ወታደራዊ አገልግሎት ጓዶቻችን፣ ሕግ አስከባሪ መኮንኖች እና ቅድሚያ ምላሽ ሰጪዎች በጀግንነት የሚጠብቁትን የቤተሰብ፣ የእምነት እና የነጻነት የጋራ አርበኛ እሴቶቻችንን ያሳያል» ሲሉም አክለዋል። «ሱፐር ቦል» በሚል የሚጠራው የአሜሪካ እግር ኳስ ሊግ የውድድር ዘመን የፍጻሜ ምሽት ከ120 ሚሊየን ሰዎች እንደተመለከቱት የተገመተ ሲሆን ፣ በዚህ ጨዋታ ወቅት የ30 ሴኮንድ ርዝመት ያለው ማስታወቂያ ለማስነገር የሚከፈለው 8 ሚሊየን ዶላር በክብረ ወሰንነት ተመዝግቧል። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት፣ በአውሮፓዊያኑ አዲስ ዓመት ኒው ኦርሊንስ በሚገኘው በርበን ጎዳና ላይ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት፣ በከባድ መኪና ተዳምጠው ለተገደሉት እና ለቆሰሉ ዜጎች እንዲሁም የመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎች የመታሰቢያ ሥነ ስርዐት ተከናውኗል። Read more