ሃማስ ከእስራኤል ጋራ የተደረሰውን ተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚያከብር ቃል ገባ
newsare.net
አክራሪው ሃማስ ከእስራኤል ጋራ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ውል እንደሚያከብር ዛሬ ሐሙስ ቃል ገብቷል፡፡ ይህ የሆነው ተኩስ አቁሙን ጥሷል በማለት አንዱ ሌላኛሃማስ ከእስራኤል ጋራ የተደረሰውን ተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚያከብር ቃል ገባ
አክራሪው ሃማስ ከእስራኤል ጋራ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ውል እንደሚያከብር ዛሬ ሐሙስ ቃል ገብቷል፡፡ ይህ የሆነው ተኩስ አቁሙን ጥሷል በማለት አንዱ ሌላኛውን ወገን እየወነጀሉ ባሉበት እና ጦርነቱ ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት በሚሰማበት በዚህ ወቅት ነው፡፡ የሃማስ ቃል አቀባይ አብደል ላቲፍ አል ካኑዋ “የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈርስ አንፈልግም፡፡ ስለዚህም አፈጻጸሙ በጥንቃቄ ሥራ ላይ እንዲውል ብርቱ ፍላጎት አለን” ያሉ ሲሆን «ወራሪዋ እስራኤልም ይሄን እንድታረጋግጥ» ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ካኑዋ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚሰነዘር “የማስፈራራት እና የዛቻ ቋንቋ” የተኩስ አቁም ስምምነቱን አፈጻጸም አያግዝም ብለዋል፡፡ ሃማስ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ እስራኤል በጋዛ የአየር ድብደባ በመፈጸም እና ርዳታ እንዳይገባ በመገደብ ስምምነቱን ጥሳለች ሲል የከሰሰ ሲሆን፤ ቡድኑ የሚለቀቁት ታጋቾች ለሌላ ጊዜ እንደሚያስተላልፍም ተናግሯል። ትላንት ረቡዕ እስራኤል ወታደራዊ ተጠባባቂዎቿን ከጠራች በኋላ፤ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የትረምፕን ማስጠንቀቂያ ደግመዋል። ካትዝ “ሃማስ ታጋቾቹን መልቀቅ ካቆመ የተኩስ አቁሙ አይኖርም፤ ጦርነት ይሆናል ማለት ነው።” ያሉ ሲሆን ጦርነቱ የበለጠ ጠንካራ እንደሚሆን እና “ትራምፕ ለጋዛ ያላቸውን ራዕይ እውን ለማድረግ የሚያስችል ይሆናል” በማለት አክለዋል። የተኩስ አቁም ስምምነቱ ባለፈው ወር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፤ በዩናይትድ ስቴትስ በአሸባሪነት የተፈረጀው ሃማስ 21 ታጋቾችን ሲለቅ በአንጻሩ እስራኤል ከ730 በላይ እስረኞችን መልቀቋ ይታወሳል። የፊታችን ቅዳሜ በሚካሄደው የታጋቾች ልውውጥ በእስራኤል በመቶዎች በሚቆጠሩ የፍልስጤም እስረኞች ለውጥ ተጨማሪ ሶስት እስራኤላውያን እንዲፈቱ ተጠይቋል። የጋዛ ጦርነት የተቀሰቀሰው በጎርጎሮሳውያኑ ጥቅምት 2023 ሃማስ በእስራኤል ላይ ባደረሰው የሽብር ጥቃት 1200 ሰዎችን ገድሎ፤ 250 ሰዎችን ማገቱን ተከትሎ ነው ። እስራኤል በፈጸመችው የአጸፋ ጥቃት ከ48 ሺህ 200 በላይ ፍልስጤማውያንን የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውን የአካባቢው የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡ እስራኤል በበኩሏ ከተገደሉት ወስጥ 17 ሺህ የሚሆኑት ታጣቂዎች ናቸው ብላለች፡፡ Read more