ፕሬዝደንት ትረምፕ የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ጀምረዋል
newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሦስት ዓመት የተጠጋውን የዩክሬን ጦርነት ለማስቆም የታለመውን የዲፕሎማሲ ዘመቻቸውን ትላንት ረቡዕ ከፍተዋል፡ፕሬዝደንት ትረምፕ የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ጀምረዋል
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሦስት ዓመት የተጠጋውን የዩክሬን ጦርነት ለማስቆም የታለመውን የዲፕሎማሲ ዘመቻቸውን ትላንት ረቡዕ ከፍተዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን ለምታደርግላት ድጋፍ በምላሹ የሚጠብቁባት የሚመስሉትን ሁኔታዎችም ዘርዝረዋል፡፡ ትረምፕ በኋይት ሃውስ ኦቫል ኦፊስ ጽሕፈት ቤታቸው እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በ2022 ሩስያ በከፈተችው ወረራ የተቀሰቀሰውን የዩክሬን ጦርነት በሚመለከት ጋዜጠኞች ላቀረቡላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ «ለምንሰጠው ገንዘብ በምላሹ ጸጥታ እንዲኖር እንፈልጋለን» ብለዋል፡፡ የቀድሞውን ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለኪቭ የሚሰጡትን ድጋፍ በሚመለከት « ገንዘባችንን ስንሰጥ በምላሹ በብድር መልክ አለያም በጸጥታ ወይም ደግሞ በነዳጃቸው ወይም በጋዛቸውም ቢሆን አንድ ነገር መጠየቅ አለብን ብያቸው ነበር» ብለዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ከ2022 ጀምሮ ለዩክሬን ወደ183 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወታደራዊ እና ወታደራዊ ያልሆነ ርዳታ መፍቀዱን ትላንት ለምክር ቤቱ የቀረበው የቁጥጥር ሪፖርት አመልክቷል፡፡ ከተፈቀደው ርዳታ እስካሁን ለዩክሬን ያልተላከው 40 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ ቀደም ሲልም ማክሰኞ ምሽት ፕሬዝደንት ትረምፕ ከሩስያ እስር ቤት የተለቀቁትን አሜሪካዊ መምህር ማርክ ፎግል በኋይት ሀውስ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ከዚያም በማስከተል ትላንት ዕኩለ ቀን ላይ ከሩስያ ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋራ በስልክ መነጋገራቸውን እና ጦርነቱን ለማስቆም በአስቸኳይ ከዩክሬን ፕሬዝደንት ዜሌንስኪ ጋራ ድርድር ለመጀመር መስማማታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ቀጥለውም ምክትል ፕሬዝደንታቸውን ጄ ዲ ቫንስን እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮን ከዜሌንስኪ ጋራ እንዲነጋገሩ ወደሚዩኒክ ልከዋቸዋል፡፡ Read more