Ethiopia



በጋምቤላ ክልል በኮሌራ ወረርሽን ከ15 በላይ ሰዎች ሞቱ

በጋምቤላ ክልል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተከሰተው የኮሌራ ወርረሽኝ 15 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አቤ

በምዕራብ ዩክሬን በምትገኝ አንዲት መንደር ወንዶች አይታዩም

በምዕራብ ዩክሬን የምትገኘው ማኪቭ ከተማ፣ ብዙም ወንዶች አይታዩባትም። በርካቶች ሸሽተዋል ወይም ውጊያ ላይ ናቸው አልያም የሩሲያን ወረራ ለመመከት ሲፋለሙ ሕ
የአሜሪካ ድምፅ

በምዕራብ ዩክሬን በምትገኝ አንዲት መንደር ወንዶች አይታዩም

በምዕራብ ዩክሬን የምትገኘው ማኪቭ ከተማ፣ ብዙም ወንዶች አይታዩባትም። በርካቶች ሸሽተዋል ወይም ውጊያ ላይ ናቸው አልያም የሩሲያን ወረራ ለመመከት ሲፋለሙ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ችግሩ በዩክሬን ባሉ በርካታ ከተሞች የሚታይ ነው። ጦርነቱ ወትሮውንም እየቀነሰ የመጣውን የሕዝብ ቁጥር አባብሶታል። ከጦር ሜዳ የቀሩትና ሕይወታቸውን መልሰው ለመገንባት የሚጥሩት የቀሩት ነዋሪዎች የዩክሬን የወደፊት ዕጣ ያሳስባቸዋል። በጦርነቱ ሕይወታቸውን ለሰጡ ወታደሮች መታሰቢያ በማኪቭ ዋናው አውራጎዳና ላይ ይታያል። ፎቶዎቹ መስዋቶቹ ደስተኛ በነበሩበት ጊዜ የተነሱት ነው። ከፎቷቸው በላይ “ክብር ለጀግኖች” የሚል ጽሁፍ ይታያል። ይህም ጦርነቱ የወለደው መፈክር ነው። ማኪቭ ከተማ የምትገኘው ከጦር አውድማው 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው። ጦርነት ያደረሰውን ከፍተኛ ጉዳት እንደዚህች ከተማ የሚያሳዩ ጥቂት ናቸው። በከተማዋ ዕድሜያቸው ለውትድርና የደረሱ ወንዶች የሚገኙት በፎቶ ግራፍ ላይ ብቻ ነው። ወይም ደግሞ በከተማዋ የመቃብር ሥፍራ ነው። ሌሎቹ ወንዶች ለቀው ሄደዋል። “ተመልከት፣ ሰው የት ነው ያለው? ተደብቀዋል። ስጋት አድሮባቸዋል” ይላል ሹፌሩ አሌክስ ካሞቪስኪ። ከ30 ዓመታት በላይ በጀርመን ኖሯል። ወደ ትውልድ ከተማው የተመለሰው ሰነዱን ለማደስ ነበር። ጓደኞቹ እና ዘመዶቹ በከተማው የሉም። “አሳዛኝ ነው!” ሲልም አክሏል። ካሞቪስኪ እንደሚለው ለውጊያ ዕድሜያቸው የደርሱ በርካታ ወንዶች ወደ ግንባር እንዳይላኩ ወደ ገጠር ሄደው ተደብቀዋል። በማኪቭ ከተማ መንገዶች ላይ የተዘዋወረው የቪኦኤ ዘጋቢ ያገኛቸው አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው። ወንዶች በመሄዳቸው ሕይወት ይበልጥ ከባድ እንደሆነ በርካታ ሴቶች ተናግረዋል። “እድሜዪ የገፋ ሴት ነኝ። ከሰባ ዓመቴ በላይ ነኝ። በእርግጥ ከልጆቻቸው ጋራ ለተተዉት ወጣት ሴቶች ይበልጥ ከባድ ነው። ወንድ ከቤት ካለ፣ ጠባቂ ብቻ ሳይሆን፣ ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን የሚያቀርብም ነው። በሁሉም ጉዳይ ላይ ይረዳል። በተለይም በገንዘብ ጉዳይ” ብለዋል አስተማሪ የነበሩትና አሁን ጡረታ ላይ የሚገኙት ኒዮሊና ኮቫሌንኮ። በምዕራብ ዩክሬን የሚገኙ በርካታ ከተሞች ውስጥ የወንዶች አለመኖር ትልቅ ችግር ፈጥሯል። ማኪቭ ከተማ ግን ከጦርነቱም በፊት ቢሆንም የነበረው የሕዝብ ቁጥር መቀነስ ቀውስ ማሳያ ነች፡፡ መንግሥት እንደሚለው፣ የሕዝቡ ቁጥር በእ.አ.አ 1991 ከነበረው 52 ሚሊዮን፣ በእ.አ.አ 2024 ወደ 32 ሚሊዮን አቆልቁሏል። አንጀሊና ቦንዳል የከተማዋ ነዋሪና ተማሪ ነች።“ይህ እጅግ ያስፈራኛል። በርካታ ቤተሰቦች ሃገሪቱን ለቀው በመውጣታቸው በሃገሪቱ ሁሉም ነገር ተቀይሯል። ሃገሪቱም ተቀይራለች፡፡ ብዙ ሰዎች ለቀው ስለወጡ በጣም ያሳዝናል። ምንም ጓደኛ የለኝም። ቤተሰቤ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ከሃገር ወጥቷል። ያሳዝናል” ብላለች የከተማዋ ነዋሪና ተማሪ የሆነችው አንጀሊና ቦንዳል። አንጀሊና ቦንዳር ገና 15 ዓመቷ ነው። አንድ ጎረቤቷ በጦርነቱ ሕይወቱን አጥቷል። ሌሎቹ ጎረቤቶቿ አሁንም ውጊያ ላይ ናቸው። አብዛኞቹ ጓደኞቿ ለቀው የወጡት ገና በልጅነታቸው ነው። አንድ ቀን ዩክሬንን መልሶ የመገንባት ሥራው በእርሷ ትውልድ ላይ እንደሚወድቅ አውቃለች፡፡ ያንን ሃላፊነት ለመጋፈጥ ዝግጁ ስለመሆኗ ግን እርግጠኛ አይደለችም።

እየሻከረ የመጣው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት እና ሰሞነኛ ውዝግብ

የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ ባለፈው ሰኞ፣ የኤርትራ መንግሥትን በተመለከተ በአንድ ዓለም አቀፍ ብዙኀን መገናኛ ድረ ገጽ ላይ ያወጡት
የአሜሪካ ድምፅ

እየሻከረ የመጣው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት እና ሰሞነኛ ውዝግብ

የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ ባለፈው ሰኞ፣ የኤርትራ መንግሥትን በተመለከተ በአንድ ዓለም አቀፍ ብዙኀን መገናኛ ድረ ገጽ ላይ ያወጡትን ጽሑፍ ተከትሎ ኤርትራ ምላሽ ሰጥታለች፡፡ የአሜሪካ ድምፅ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የሁለቱ ሀገራት ምሁራን በበኩላቸው፣ ኹኔታው እየሻከረ የመጣውን የተጎራባች ሀገራቱን ግንኙነት ይፋ ያደረገ እንደኾነ ገልጸዋል፤ ልዩነቱ ተባብሶ ወደ ግጭት እንዳያመራ ስጋት እንዳላቸውም አሳስበዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

ከአሜሪካ የተባበሩ ፍልሰተኞችን ኮስታሪካና ፓናማ በጊዜያዊነት እየተቀበሉ ነው

ከአሜሪካ የተባረሩትን ፍልሰተኞችን በጊዜያዊነት ለማስተናገድ ኮስታሪካና ሆንዱራስ ከፓናማ ጋራ ተቀላቀለዋል፡፡ በዐዲሱ የትረምፕ አስተዳደር የኢምግሬሽን
የአሜሪካ ድምፅ

ከአሜሪካ የተባበሩ ፍልሰተኞችን ኮስታሪካና ፓናማ በጊዜያዊነት እየተቀበሉ ነው

ከአሜሪካ የተባረሩትን ፍልሰተኞችን በጊዜያዊነት ለማስተናገድ ኮስታሪካና ሆንዱራስ ከፓናማ ጋራ ተቀላቀለዋል፡፡ በዐዲሱ የትረምፕ አስተዳደር የኢምግሬሽን ፖሊሲ ከሀገር የተባረሩና የተለያየ ሀገር ዜግነት ያላቸው 135 ስደተኞችን የጫነ አውሮፕላን ትላንት ሐሙስ ኮስታሪካ ዋና ከተማ አርፏል፡፡ 65 ህፃናት ይገኙበታል የተባሉት እነዚህ ፍልሰተኞች ከኡዝቤክስታን፣ ከቻይና ከአፍጋኒስታን ከሩሲያ እና ከሌሎች ሀገሮች የመጡ ናቸው፡፡ፍልሰተኞቹ ወደ የሀገራቸው ከመሸኘታቸው በፊት ኮስታሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ በገባችው ስምምነት መሰረት በሀገሯ ታቆያለች፡፡ ኮስትሪካ፣ ፓናማ እና ሆንዱራስ ወደ ሌሎች ሀገሮች የሚላኩ ፍልሰተኞችን ለጊዜው ተቀብለው ለማቆየት ከዩናይትድ ስቴትስት ጋራ ስምምነት የተፈራረሙ ሀገሮች ናቸው፡፡ ፓናማ በቅርቡ በመጀመሪያው ዙር የተላኩ 299 ፍልሰተኞችን የተቀበለች ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት በሆቴል ክፍሎች ውስጥ ሲቀመጡ ሌሎች ደግሞ በኮሎምቢያ ድንበር አቅራቢያ ወደሚገኝና ራቅ ወዳለ  ካምፕ ተልከዋል፡፡ ሆንዱራስ በአሜሪካና በቪንዙዌላ መካከል ቀጥተኛ በረራ ባለመኖሩ “የሰብአዊ ድልድይ” ብላ በጠራቸው የማጓጓዝ አገልግሎት 170 ቬንዙዌላውያንን ከጓንታናሞ ቤይ ወደ ቬንዙዌላ በማዛወር ረድታለች፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በቅርቡ ባደረጉት ጉብኝት ከሀገራቱ ጋራ በተደረሰው ስምምነት ዩናይትድ ስቴትስ የመጓጓዣውንና የማቆያውን ሙሉ ወጪዎች ትሸፍናለች፡፡ ፕሬዚዳንት ትረምፕ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ህገወጥ ስደተኞችን በመግታት፣ በመቀበል ወይም ሁኔታዎችን በማመቻችት እንዲተባበሩ ጫና አሳድረዋል፡፡ ከተባበረሩት ፍልሰተኞች መካከል በተለይም ከእስያ የመጡት ወደ የሀገራቸው ከመመለሳቸው በፊት እስከ ስድስት ሳምንታት ሊቆዩ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው፣ ካልሆነም በተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የፍስልተኞች ድርጅት አማካይነት፣ ወደ ሌላ ተቀባይ ሀገር የመሄድና የጥገኝነት መብታቸው ሊጠበቅ የሚችልበት አግባብ እንደሚኖር የኮስታሪካ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል መንግሥት 6 ሺሕ የአገር ውስጥ ገቢ ሠራተኞችን ከሥራ አሰናበተ

ሳግ እየተናነቃቸው የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊ፣ ቁጥራቸው 6 ሺሕ የሚጠጋ ሠራተኞች ከሥራ እንደሚባረ
የአሜሪካ ድምፅ

የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል መንግሥት 6 ሺሕ የአገር ውስጥ ገቢ ሠራተኞችን ከሥራ አሰናበተ

ሳግ እየተናነቃቸው የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊ፣ ቁጥራቸው 6 ሺሕ የሚጠጋ ሠራተኞች ከሥራ እንደሚባረሩ ይፋ እንዳሳወቋቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ለሮይተርስ የዜና ወኪል በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል። ይህም ሥራ በሚበዛበት የግብር መክፈያ ሰሞን የተወሰደ እርምጃ ከ6 በመቶ በላይ የሚሆነውን የድርጅቱን የሰው ኃይል የሚያሳጣ መሆኑ ተመልክቷል። የሰው ኃይል ቅነሳው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የመንግሥት ሠራተኞችን ቁጥር ለመቀነስ የያዙት ጥረት አካል ሲሆን፣ የባንኮችን ሥራ የሚቆጣጠሩ፣ የደን ጥበቃ እና እንክብካቤ ሠራተኞች፣ የሮኬት ሳይንስ አዋቂ ሳይንቲስቶች እና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ላይ የተነጣጠረ መሆኑ ታውቋል። ይህን የማስፈጸሙም ሥራ የሚመራው በፕሬዝደንት ትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ወቅት ዋነኛ ለጋሽ በነበሩት ቢሊነሩ ኢላን መስክ ነው። መስክ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት ‘ኦክሰን ሂል’ ውስጥ በሚገኘው ናሽናል ሃርበር የተባለ ሥፍራ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሪፐብሊካን የፖለቲካ ፓርቲ አቀንቃኞች እና ባለሥልጣናት የሚሳተፉበት ዓመታዊ ጉባኤ መድረክ የመንግሥታቸውን ወጪ ለመቀነስ ባራመዷቸው ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደሩ ፖሊሲዎቻቸውን ከሚታወቁት የአርጀንቲና ፕሬዝደንት ጃቪየር ሚሌ እርምጃቸውን ጥንካሬ ለማሳየት የብረት መጋዝ በስጦታ ሲቀበሉ ታይተዋል። «ይህ ቢሮክራሲ የሚቆረጥበት መጋዝ ነው» አሉ መስክ የመንግሥት ሠራተኞችን ቁጥር በከፍተኛ መጠን የቀነሱበትን እርምጃ ለማመላከት በሚመስል አኳሃን፣ መድረኩ ላይ እንደቆሙ ብርቱውን መቁረጫ ወደ ላይ ከፍ አድርገው እያሳዩ። የሠራተኛ ማኅበራት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ሠራተኞች ሥራቸውን እንደሚያጡ እየተነገራቸው ያለበትን በጅምላ ከሥራ የማስወጣት ርምጃ ለማስቆም በፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። ይሁንና አንድ ጉዳዩን ያዩ የዋሽንግተን የፌዴራል ዳኛ በትላንትናው ዕለት በሰጡት ብይን ለአሁኑ መቀጠል እንደሚችሉ የሚፈቅድ ብይን አሳልፈዋል። የአገር ውስጥ ገቢ የባለሞያዎች ቅጥር ድሬክተር ክሪስቲ አርምስትሮንግ 6ሺሕየሚጠጉ ባልደረቦቻቸው ከድርጅቱ የሰው ኃይል እንደሚቀነሱ በስልክ ባሳወቁበት ወቅት፤ ‘እምባ እየተናነቃቸው’ እንደነበር መልዕክቱ በተላለፈበት ወቅት የነበሩ አንድ ሠራተኛ ገልጸዋል። እርስ በርስ እንዲደጋገፉ ያበረታቱት ኃላፊ «በእጅጉ በስሜት ተነክተው እንደነበር» መልዕክቱን የተከታተሉት ሠራተኛ አክለው አመልክተዋል። አንድ የጉዳዩ አዋቂ እንደገለጹት፤ የአገር ውስጥ ገቢ መሥሪያ ቤቱ ቅነሳው በአጠቃላይ 6,700 ሠራተኞችን እንደሚመለከት እና በዋናነትም የባለ ጸጋ ግብር ከፋዮችን የግብር ኃላፊነት ለማስፈጸም በተያዘ ጥረት ለማጎልበት በሞከሩት በዲሞክራቱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሥራ ማስፋፊያ ዕቅድ በተቀጠሩ የድርጅት ሰራተኞች ላይ የተነጣጠረ መሆኑ ተጠቁሟል። ከሪፐብሊካን ወገን የሆኑ በተራ አሜሪካውያን ላይ አላስፈላጊ ጫና ይፈጥራል በሚል ርምጃውን ተቃውመዋል። የግብር ሰብሳቢው ድርጅት በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው 100 ሺሕ የሚጠጉ ሠራተኞች ሲኖሩት፣ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2021 ባይደን ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት የነበት ሠራተኞች ቁጥር 80 ሺሕ ነበር። ከየትኛውም ፓርቲ ወገን ያልሆኑ የበጀት ጉዳይ አዋቂዎች ባይደን እንዲያድግ ያደረጉት የሠራተኛ ኃይል የመንግስቱን ገቢ በማሳደግ፣ በትሪሊዮን ዶላር የሚሰላውን የበጀት ክፍተት ለማጥበብ ያግዛል የሚል ግምት ሰጥተው ነበር። የሠራተኛ ኃይሉን ለመቀነስ የተወሰደውን ርምጃ “ይህ እንደ እውነቱ የአገር ውስጥ ገቢ መሥሪያ ቤቱ በባለ ጸጋ ግብር ከፋዮችን ሳይሆን፤ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ላይ ትኩረት ማድረግ የመረጠ ድርጅት እዲሆን ያደርገዋል” ብለዋል፡፡ የፒትስበርግ ዩኒቨርሲቲ የግብር ጉዳዮችን የሚመለከተው ሕግ መምህሩ ፕሮፌሰር ፊሊፕ ሃክኒ። «እጅግ አሳዛኝ ድርጊት ነው» ሲሉ አክለዋል፤ ካሁን ቀደም የአገር ውስጥ ገቢ መሥሪያ ቤቱ ነገረ ፈጅ በመሆን ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሃክኒ። ከሥራ ከተባረሩት ውስጥ የግብር ክፍያ ሰብሳቢዎች፣ የደንበኛ አገልግሎት ፣ሠራተኞች፣ የግብር ክፍያ ይግባኝ የሚሰሙ ባለሞያዎች እና እንዲሁም የመረጃ ቴክኖሎጂ ሰራተኞች ይገኙባቸዋል። ርምጃው በ50ውም የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ውስጥ ባሉ ሠራተኞች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል ሲሉ ሮይተርስ ያነጋገራቸው ምንጮች አመልክተዋል። የአገር ውስጥ ገቢ መሥሪያ ቤት በበኩሉ ለቀረበለት ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። ዓመታዊው የግብር ሂሳብ የሚወራረድበት ወቅት ገና በመጋመስ ላይ በመሆኑ፤ አይርኤስ ከሌሎች የመንግስት ተቋማት የተሻለ ጥንቃቄ የታየበት አካሄድ ተከትሏል፤ ያሉት ምንጮች፣ በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ስሌት መሰረት እስከ ሚያዝያ 15 አጋማሽ በሚዘልቀው የሥራው ማጠናቀቂያ ድረስ ከ140 ሚሊዮን በላይ በግል ግብር የሚከፍሉ ሰዎችን የግብ ክፍያ ተመላሽ ማስፈጸም ስለሚጠበቅበት፣ ለዚያ ሥራ ወሳኝ ናቸው የተባሉትን በርካታ ሺሕ ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው እንደሚያቆይ አንድ ምንጭ ጠቁመዋል። የትራምፕ አስተዳደር የፌዴራል ሠራተኞችን ከሥራ የማሰናበቱ ርምጃ ለሥራ ኃላፊነቱ አዲስ በሆኑ እና ረጅም ጊዜ ካገለገሉ ሠራተኞች አንጻር ሲታይ አነስተኛ ጥበቃ ያላቸው ሰራተኞች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመልክቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የትራምፕ ዋይት ሀውስ የዩናይትድ ስቴትስ የፖስታ አገልግሎት መስሪያ ቤትን የሥራ አመራር ለመበተን እና ራሱን በራሱ የሚያስተዳድረውን ድርጅት በንግድ ጉዳዮች ሚንስቴር ሥር እንዲተዳደር ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ዋሽንግተን ፖስት ትላንት ሃሙስ ዘግቧል። በሌላ በኩል “በካንሳስ ከተማ የሚገኘው የአይአርኤስ ጽሕፈት ቤት የሙከራ ጊዜያቸውን ያላጠናቀቁ ሠራተኞች ስንብታቸውን የሚያረግጋጠውን ደብዳቤ ከሚቀበሉበት የኢሜል መልዕክት መላላኪያ በስተቀር፤ ማናቸውንም ሌሎች ተግባራት የሚያከናውኑባቸው የኮምፒውተሮቻቸው ቁልፎች በሙሉ ተዘግተው ነው የጠበቋቸው” ሲሉ የፌድራሉ የሠራተኛ ማኅበር የአካባቢው ጽሕፈት ቤት ተጠሪ ሻነን ኢሊስ ተናግረዋል። ኤሊስ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል "የአሜሪካ ሕዝብ በእውነት ሊገነዘበው የሚገባው ነገር በአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት የሚሰበሰበው ገንዘብ በኅብረተሰባችን ውስጥ በየቀኑ የምንገለገልባቸውን የተለያዩ ፕሮግራሞችን የሚደግፉ ናቸው” ብለዋል። ዋይት ሀውስ ቁጥሩ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ከሚደርሰው የመንግሥት ሠራተኛ ምን ያህሉን በከፍተኛ ቁጥር በጅምላ ከሚፈጸመው ከሥራ የማሰናበት ርምጃው እንደሚያካትት አላስታወቀም። ቁጥራቸው 75 ሺሕ የሚጠጉ ሠራተኞች ራሳቸውን በፈቃዳቸው ከሥራ እንዲያሰናብቱ የቀረበውን ዕቅድ መፈረማቸው ባለፈው ሳምንት ተዘግቧል። አስተዳደሩ የያዘው የወጪ ቅነሳ ዕቅድ ‘መንግሥት የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶች ሊጎዳ ይችላል’ በሚል አያሌ አሜሪካውያን የሚጨነቁ መሆናቸውን ሮይተርስ እና ኢፕሶስ በጋራ ያሰባሰቡት እና ትላንት ሐሙስ ይፋ የተደረገ የሕዝብ አስተያየት መረጃ ጠቁሟል።

ሐማስ የእስራኤላዊዋን አስከሬን የማይመልስ ከሆነ “ዋጋ ይከፍላል” ሲሉ ኔታንያሁ አስጠነቀቁ

ሐማስ በሰላም ስምምነቱ መሠረት ሺሪ ቢባስ የተባለችውን እስራኤላዊ እናት አስከሬን የማይመልስ ከሆነ “ዋጋ ይከፍላል” ሲሉ የእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃ
የአሜሪካ ድምፅ

ሐማስ የእስራኤላዊዋን አስከሬን የማይመልስ ከሆነ “ዋጋ ይከፍላል” ሲሉ ኔታንያሁ አስጠነቀቁ

ሐማስ በሰላም ስምምነቱ መሠረት ሺሪ ቢባስ የተባለችውን እስራኤላዊ እናት አስከሬን የማይመልስ ከሆነ “ዋጋ ይከፍላል” ሲሉ የእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ዛሬ ዓርብ አስጠንቅቀዋል። “ሺሪን ጨምሮ በሕይወት ያሉም ሆነ የሌሉ እስራኤላውያንን ለማስመለስ በቁርጠኝነት ርምጃ እንወስዳለን። ለዚህ ጨካኝና ሰይጣናዊ ለሆነ እንዲሁም ስምምነቱን ለጣሰ ተግባር ሐማስ ሙሉ ዋጋውን እንዲከፍል እናደርጋለን” ሲሉ ኔታንያሁ በቪዲዮ ባስተላልፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ሐማስ በትላንትናው ዕለት አራት ታጋቾችን የለቀቀ ሲሆን እነዚህም በታገተበት ወቅት የዘጠኝ ወር ሕፃን የነበረው ክፊር ቢባስ፣ የአራት ዓመት ወንድሙ አሪየል ቢባስ ይገኙበታል። የእናታቸው ሺሪ ቢባስ ነው ተብሎ የተመለሰው አስከሬን ግን የእርሷ እንዳልሆነ የእስራኤል ሠራዊት ዛሬ ዓርብ አስታውቋል። “ሐማስ አባትና እናትን እንዲሁም ሁለት ልጆቻቸውን ማገቱ ብቻ ሳይሆን፣ በአሳዛኝ ሁኔታ የእናቷ አስከሬን ነው በሚል የአንድ የጋዛ ነዋሪን ሴት አስከሬን ልኳል” ሲሉ አክለዋል ጠቅላይ ምኒስትሩ። ሐማስ በበኩሉ ሽሪ ቢባስ ተይዛ በነበረችበት ስፍራ እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት በፍርስራሹ ውስጥ አስከሬኗ ከሌላ አስከሬን ጋራ ተነካክቷል ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል።

በትግራይ በጸጥታ ኃይሎች እና ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 17 ሰዎች መጎዳታቸውን ተገለጸ

በትግራይ ክልል ሰሓርቲ በተባለች ወረዳ የአንድ ቀበሌ አስተዳዳሪ ማኅተም በኃይል ነጥቀዋል የተባሉ የፀጥታ አባላት ወሰዱት በተባለ ርምጃ 17 ሰዎች መጎዳታቸውን
የአሜሪካ ድምፅ

በትግራይ በጸጥታ ኃይሎች እና ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 17 ሰዎች መጎዳታቸውን ተገለጸ

በትግራይ ክልል ሰሓርቲ በተባለች ወረዳ የአንድ ቀበሌ አስተዳዳሪ ማኅተም በኃይል ነጥቀዋል የተባሉ የፀጥታ አባላት ወሰዱት በተባለ ርምጃ 17 ሰዎች መጎዳታቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ተናገሩ። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ፣ የሰራዊቱ አባላት ጣልቃ መግባታቸውን ገለፆ፣ “እንዲኽ ያለ ጣልቃ ገብነት ክልሉን ወደ ከባድ ቀውስ ያስገባዋል” ብሏል። በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በወረዳ አስተዳዳሪነት የተሾሙት፣ አቶ አታኽልቲ ግርማይ ለአሜሪካ ድምፅ “የፀጥታ አባላት ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ወግነው ወደ ሕዝብ መተኮስ ሳይኾን፣ የሥራ ድርሻቸው ሰላም እና ፀጥታ መጠበቅ ነው”ብለዋል። በድርጊት ፈጻሚነት የተወቀሰውና፣ “አርሚ 26” ተብሎ የሚጠራው የክልሉ የፀጥታ መዋቅር አዛዥ ኮሌኔል ሓጎስ ገብረ፣ የፀጥታ አባላቱ ወደ አከባቢው የገቡት በሕዝብ ጥሪ መኾኑን ገልፀው “በነዋሪዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ የለም” ብለዋል። “ክሱ የሰራዊታችን ስም ማጥፋት ነው” ሲሉም ምላሽ ሰጥተዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአሜሪካ የዋጋ ግሽበት እየጨመረ መሄዱን ኢኮኖሚስቶች እየተከታተሉት ነው

በዩናይትድ ስቴትስ የምግብ፣ የነዳጅ፣ የመኖሪያ ቤቶች እና የሌሎች ሸቀጦች ዋጋ ሲንር፣ በጥር ወር የዋጋ ግሽበቱ ጨምሯል። የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ቬሮኒካ ባልደ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ የዋጋ ግሽበት እየጨመረ መሄዱን ኢኮኖሚስቶች እየተከታተሉት ነው

በዩናይትድ ስቴትስ የምግብ፣ የነዳጅ፣ የመኖሪያ ቤቶች እና የሌሎች ሸቀጦች ዋጋ ሲንር፣ በጥር ወር የዋጋ ግሽበቱ ጨምሯል። የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ቬሮኒካ ባልደራስ ኢግሌሲያስ የትረምፕ አስተዳደር የዋጋ ንረትን ለማውረድ ምን ማድረግ እንዳለበት ኢኮኖሚስቶችን አነጋግራለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሴኔት ሪፐብሊካን ከትረምፕ በተቃራኒ የድንበር በጀቱን ለማጽደቅ እየገፉ ነው

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በአሜሪካ የሕግ አውጪው ሸንጎ (ሴኔት) ያሉ ሪፐብሊካን አባላት በስደተኞች፣ ኃይል እና መከላከያ ላይ ያተኮረውን የበጀት ረቂቃቸውን
የአሜሪካ ድምፅ

የሴኔት ሪፐብሊካን ከትረምፕ በተቃራኒ የድንበር በጀቱን ለማጽደቅ እየገፉ ነው

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በአሜሪካ የሕግ አውጪው ሸንጎ (ሴኔት) ያሉ ሪፐብሊካን አባላት በስደተኞች፣ ኃይል እና መከላከያ ላይ ያተኮረውን የበጀት ረቂቃቸውን ወደ ጎን ብለው፣ ከተወካዮች ምክር ቤት የሚቀርበውን ሰፋ ያለ የበጀት ሐሳብ እንዲቀበሉ ቢጠይቁም፣ የሴኔቱ የሪፐብሊካን አባላት ግን በያዙት ሐሳብ እንደሚገፉበት አስታውቀዋል። ትረምፕ በተወካዮች ምክር ቤት የቀረበውንና በትሪሊየን ዶላር የሚቆጠር የታክስ እፎይታ ጭምር የሚሰጠውን ሰፋ ያለ የበጀት ሐሳብ እንደሚመርጡ ቢያስታውቁም፣ በሴኔቱ የሚገኙ የሪፐብሊካን አባላት ግን በያዙት አቋም እንደሚገፉ በሴኔቱ አብዛኛ መቀመጫ የያዘው የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ጃን ቱን አስታውቀዋል። በሴኔቱ የቀረበው “ቀጠን ያለ” የበጀት ሐሳብ፣ ትረምፕ ያሰቡትን የታክስ ቅነሳ ለመተግበር፣ ወደፊት ሌላ በጀት በምክር ቤቱ ለማጽደቅ በሚሞክሩበት ጊዜ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት በምክር ቤቱ የሪፐብሊካን አባላት ዘንድ አድሯል። ምክንያቱ ደግሞ ፓርቲው በጠባብ ልዩነት፣ ማለትም 218 ለ215 መቀመጫዎች ብቻ የበላይነት የያዘ ስለሆነና ከሁለት ዓመታት በኋላ የም/ቤት አባላት ምርጫ ሲካሄድ የበላይነቱን ሊያጡ ይችላሉ በሚል ስጋት ነው። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ሁለቱም የሕግ አውጪ ም/ቤቶች “አንድ ትልቅ ሸጋ በጀት ረቂቅ” አጽድቀው በሃገሪቱ የዕርቅ ሂደቱን እንዲጀምሩ ጥሪ አድርገዋል። ከምክትል ፕሬዝደንት ጄዲ ቫንስ እና ከሴኔት ሪፐብሊካን ጓዶቻቸው ጋራ ስብሰባ ያደረጎት የሴኔቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ጃን ቱን፣ “ቀጠን ባለው” የበጀት ረቂቅ እንደሚገፉበት አስታውቀዋል። “በስተመጨረሻ አንድም ሆነ ሁለት የበጀት ረቂቅ አውጥተን ፕሬዝደንቱ ያሰቡትን ከዳር እናደርሳለን” ያሉት ጃን ቱን፣ ሴኔቱ ዛሬ ሐሙስ ድምጽ ይሰጣል ብለው እንደሚጠብቁ አስታውቀዋል። ትረምፕ የተቃውሞ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን ተከትሎ፣ አንዳንድ የሪፐብሊካን ዓባላት በየትኛው መንገድ መቀጠል እንዳለባቸው ግራ ተጋብተዋል ሲል የሮይተርስ ሪፖርት አመልክቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዲሞክራቶቹ ለረጅም ትግል እንደተዘጋጁ አስታውቀዋል። “የበጀት ረቂቁ የፕሬዝደንቱ ወዳጅ ለሆኑ ቢሊየነሮች የታክስ እፎይታ ለመስጠት ያለመ ነው” ሲሉ የሴኔት ዲሞክራቶች መሪው ቻክ ሹመር ክስ አሰምተዋል። ሴኔቱ ባቀረበው የበጀት ረቂቅ ውስጥ፣ ለአራት ዓመታ የ340 ቢሊዮን ዶላር፣ በየዓመቱ 85 ቢሊዮን ዶላር ድንበር ጥበቃውን ለማጥበቅና የትረምፕን ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የሚያደርጉትን ጥረት፣ የኅይል ፖሊሲን ለመቀየር  እንዲሁም የመከላከያ ወጪን ለመጨመር የሚል ተካቷል። በተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው በጀት ደግሞ፣ 4.5 ትሪሊየን የታክስ ቅነሳና፣ 2 ትሪሊየን ዶላር የወጪ ቅነሳ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት እንዲሁም ለኃይል የፖሊሲ ልውጦች የሚውል ገንዘብን ታሳቢ ያደርጋል።

ሃማስ የአራት ታጋቾች አስከሬን ለእስራኤል አስረከበ

ሃማስ በዛሬው ዕለት ደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ ውስጥ ለእስራኤል ኃይሎች ያስረከባቸው አራት እስራኤላዊ ታጋቾችን አስከሬን የያዙ ሳጥኖች በቀይ መስቀል ተሽከርካሪ
የአሜሪካ ድምፅ

ሃማስ የአራት ታጋቾች አስከሬን ለእስራኤል አስረከበ

ሃማስ በዛሬው ዕለት ደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ ውስጥ ለእስራኤል ኃይሎች ያስረከባቸው አራት እስራኤላዊ ታጋቾችን አስከሬን የያዙ ሳጥኖች በቀይ መስቀል ተሽከርካሪዎች ወደ ቴላቪቭ ተጓጉዘዋል። ባንዲራዎች እና ጹሑፎች የሰፈሩባቸው ጨርቆች በታዩበት መድረክ ሃማስ አስከሬኖቹን የተሸከሙትን አራት ጥቋቁር ሳጥኖች ባስረከበበት በዚህ ሥነ ስርዐት በብዙ መቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች ተገኝተዋል። አንዳንዶች ካነገቧቸው የተለያዩ መልዕክቶች ከሰፈረባቸው ጨርቆች አንዱ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጦር ወንጀለኝነት ይከሳል። የእስራኤል የአየር ጥቃት ለታጋቾቹ ሞት ‘ምክንያት ሆኗል’ ሲልም ይወነጅላል። ቀይ መስቀል አራቱን የሬሳ ሳጥኖች ለእስራኤል ጦር ሠራዊት ማስረከቡን እና የሟቾቹን ማንነት ለማረጋገጥ አስከሬኖቹ ቴል አቪቭ ወደሚገኘው ብሔራዊ ልዩ ምርመራ ማዕከል መወሰዳቸውን የኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ለእስራኤል ተላልፈው የተሰጡት አስከሬኖች፤ በታገቱበት ወቅት የዘጠኝ ወር ዕድሜ የነበረውን ጨቅላ ልጃቸውን እና የታላቅ ወንድሙን የአራት  ዓመቱን አርየል ቢባስን፤ የአባታቸውን የክፊር ቢባስን እና እንዲሁም የእናታቸውን ሺሪ ቢባስን ጨምሮ የአራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ይገኙበታል።  የቢባስ ቤተሰብ አባላት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ጥቅምት 7 ቀን 2023 ዓ.ም  ከኪቡትዝ ኒር ኦዝ በሃማስ ታጣቂዎች ታግተው ከተወሰዱት ውስጥ ናቸው። የእገታውን ትዕይንት የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ሺሪ ቢባስ ሁለቱን ወንዶች ልጆቻቸውን በብርድ ልብስ ሲሸፋፍኑ እና በታጣቂዎች በኃይል እየተገፉ ሲወሰዱ ያሳያል።

ዩናይትድ ስቴትስ የላከቻቸው አብዛኞቹ  ፍልሰተኞች ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማታቸውን ፓናማ ተናገረች

በቅርብ ቀናት ከዩናይትድ ስቴትስ ፓናማ ወደሚገኙ ማሸጋገሪያ ጣቢያዎች ከተላኩት ፍልሰተኞች ውስጥ ከግማሽ በላዩ በፈቃደኝነት ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ የላከቻቸው አብዛኞቹ  ፍልሰተኞች ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማታቸውን ፓናማ ተናገረች

በቅርብ ቀናት ከዩናይትድ ስቴትስ ፓናማ ወደሚገኙ ማሸጋገሪያ ጣቢያዎች ከተላኩት ፍልሰተኞች ውስጥ ከግማሽ በላዩ በፈቃደኝነት ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማታቸውን የፓናማ የደኅንነት ሚንስትር ተናገሩ፡፡ የሚበዙት የእስያ ወይም የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገር ተወላጆች መኾናቸው ተመልክቷል፡፡ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር በሕገ ወጥ ፍልሰት ላይ  እየወሰደ ባለው ርምጃ በቅርቡ ፍልሰተኞቹን  በሦስት አውሮፕላኖች አሳፍሮ ወደ ፓናማ ልኳቸዋል፡፡ ቁጥራቸው ወደ 299 የሚጠጋው ፍልሰተኞች ፓናማ ሲቲ በሚገኝ ሆቴል በሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጥበቃ ሥር ሆነው  እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) እና በመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን (ዩ ኤን ኤች ሲ አር) በኩል  የገንዘብ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን የፓናማው ሚንስትር ፍራንክ አብሬጎ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡ «171 ፍልሰተኞች ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነዋል፡፡ የተቀሩትም ተመድ መጓጓዣቸውን እንዳዘጋጀላቸው ቀስ በቀስ ይመለሳሉ» ብለዋል ሚንስትሩ፡፡ እስከዚያው በደቡባዊ ፓናማ ዳሪየን ጋፕ በሚባለው ደን አቅራቢያ  ወደሚገኝ  መጠለያ ጣቢያ  ሳይዛወሩ እንደማይቀር ተጠቁሟል፡፡ ባለፈው ወር ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋራ የተነጋገሩት የፓናማ ፕሬዝደንት ሆዜ ራኡል ሙሊኖ በሐምሌ ወር ከዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ደኅንነት ሚንስቴር ጋራ የተደረሰውን ስምምነት በማስፋት የቬንዙዌላ፣ ኢኳዶር እና ኮሎምቢያ ፍልሰተኞችንም ወደፓናማ ለመመለስ እንዲያስችል ለማድረግ እንደሚቻል ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡ 

መንግሥት: ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን እንደቻለች ማስታወቁ «ከአሜሪካ ርዳታ መቆም ጋራ በተገናኘ አይደለም፤» አለ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን እንደቻለች ይፋ ያደረገችበት መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ወራት የውጭ ርዳታ ለማቆም ካስተላለፈችው ውሳኔ ጋራ የተገናኘ አ
የአሜሪካ ድምፅ

መንግሥት: ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን እንደቻለች ማስታወቁ «ከአሜሪካ ርዳታ መቆም ጋራ በተገናኘ አይደለም፤» አለ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን እንደቻለች ይፋ ያደረገችበት መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ወራት የውጭ ርዳታ ለማቆም ካስተላለፈችው ውሳኔ ጋራ የተገናኘ አይደለም፤ ሲል መንግሥት አስታውቋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለአሜሪካ ድምፅ በጽሑፍ በሰጠው ምላሽ፣ አኹን ኢትዮጵያ ራሷን የቻለችው፣ በአንድ የምርት ዓይነት ማለትም በስንዴ እህል ምርት እንደኾነ አስታውሷል። በአገሪቱ ውስጥ፣ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች መኖራቸውም፣ በብሔራዊ ደረጃ የምግብ እጥረት ስለ መኖሩ አያሳይም፤ በማለት አብራርቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ትላንት ማክሰኞ፣ የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን ችላለች፤ ሲል አስታውቋል። ኢትዮጵያ፣ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማርካት፣ በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጪ ስንዴ ከውጭ ታስገባ እንደነበር ያወሳው መግለጫው፣ አሁን ይህን ማስቀረት መቻሉን ጠቁሟል። «ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገር ውስጥ ምርት ላይ ከፍተኛ ጭማሬ በመታየቱ ኢትዮጵያ ከውጭ በሚገባ የስንዴ ምርት ላይ ጥገኛ መኾኗ ቀርቷል፤» ሲል አመልክቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት መግለጫ የወጣው፣ ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ርዳታ ለሦስት ወራት ለማቆም የደረሰችበትን ውሳኔ ካስታወቀች ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነው። ኾኖም፣ በዚኽ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፦ ምግብ፣ መድኃኒት እና ሌሎች የአጣዳፊ ጊዜ ድጋፎች ከዕቀባው ውጪ እንዲኾኑ ትእዛዝ መተላለፉን ግልጽ አድርገዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ ሕይወት አድን መርሐ ግብሮች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ የሚያስችል “ጥቅል ማሳሰቢያ” መስጠታቸውንም ገልጸዋል። “ምግብ፣ መድኃኒት ወይም ማንኛውም ሕይወት አድን የኾነ አጣዳፊ አገልግሎት በዕቀባው አይካተትም፤« ሲሉም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ክፍል፣ በጽሕፈት ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው ምላሽ፣ አገሪቱ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን ይፋ ያደረገችበት መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ወራት የውጭ ርዳታ ለማቆም ካስተላለፈችው ውሳኔ ጋራ የተገኘ አለመኾኑን አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ይህን ስኬት በማሳየት፣ በማደግ ላይ ያሉ ሌሎች ሀገራትም፣ ራስን የመቻል መንገድ እንዲከተሉ ይነቃቃሉ ብላ ተስፋ እንደምታደርግም አመልክቷል። ጽሕፈት ቤቱ በትላንቱ መግለጫው፣ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ምርት መጠን እያደገ መሞጣቱንም ገልጿል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022/23 የምርት ዘመን፣ ኢትዮጵያ 15ነጥብ1 ሚሊየን ቶን ስንዴ እንዳመረተች ጠቁሞ፣ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ወደ 23 ሚሊየን ቶን ማደጉን ጠቅሷል። አገሪቱ በስንዴ ምርት ራሷን ቻለች ማለት፣ ስንዴ ከውጭ መግባቱ ይቆማል ማለት እንዳልኾነ ግን መግለጫው አስረድቷል። በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ ርዳታ ተቋማት፣ አኹንም ከሀገር ውስጥ ገበያ ስንዴ ከመግዛት ይልቅ ከውጭ ሀገራት ማስገባትን ሊመርጡ እንደሚችሉ ነው የጠቆመው። የሰብአዊ ርዳታ ተቋማት፣ ስንዴንና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚገዙት፦ ከመንግሥት ጋራ በመቀናጀት፣ በአገሪቱ የምግብ ድጋፍ የሚያሰፈልጋቸውን ዜጎች ለመድረስ ነው። እ.አ.አ. በመጋቢት ወር 2024 በመንግሥት እና በዓለም አቀፍ አጋሮች ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ ሰነድ፣ በተፈጥሮ እና በሰው ሠራሽ ችግሮች ምክንያት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ እንደሚጠብቁና ይህንም ለማሟላት ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ አመልክቷል። ገንዘቡ የተጠየቀው፣ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸውን 10ነጥብ4 ሚሊዮን ዜጎችን ፍላጎት ለማሟላት ጭምር እንደኾነ ሰነዱ አመልክቷል። አገሪቱ በስንዴ ራሷን መቻሏን ማስታወቋ፣ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች መኖራቸውን ከሚጠቅሰው ከዚኽ ሰነድ ጋራ እንዴት እንደሚጣጣም የተጠየቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬዝዳንት ክፍል ማብራሪያ ሰጥቷል። በአገሪቱ የተከሠቱ ድርቅ፣ ጎርፍ እና የመሬት መንቀጥቀጥን የመሳሰሉ አደጋዎች የተረጂዎችን ቁጥር እንደሚጨምሩ ጠቅሷል። ፈተናዎቹ ግን፣ አገሪቱ በምግብ ራሷን ለመቻል ያላትን ቁርጠኘነት አልቀነሱትም፤ ብሏል። ኢትዮጵያ አኹን ራሷን እንደቻለች የገለጸችው በአንድ የምርት ዓይነት ማለትም በስንዴ እንደኾነም አስታውሷል። የምግብ ዋስትና አለመረጋገጥን፣ ከአገራዊ የምግብ ዕጥረት ጋራ አለመደበላለቅ እንደሚያስፈልግም አስገንዝቧል። ከመቶ ሚሊዮን በላይ ከኾነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ »ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች አሉ« ማለት፣ »በምንም መንገድ በአገር አቀፍ ደረጃ የምግብ እጥረት መኖሩን አያሳይም፤" ብሏል የጽሕፈት ቤቱ መግለጫ። ዩናይትድ ስቴትስን በመሳሰሉ የበለጸጉ ሀገራትም፣ በምግብ ድጋፍ እና በሌሎች የርዳታ ፕሮግራሞች ላይ የሚተማመኑ ሰዎች መኖራቸውን የጠቀሰው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ክፍል፣ ያ ግን አገራዊ የምግብ እጥረትን አያመለክትም፤ ብሏል። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሞያ መሸሻ ዘውዴ፣ የመንግሥት መግለጫ የሚያመለክተው፣ ወቅታዊውን የስንዴ ምርት መጠን እንደኾነ ጠቁመዋል። ራስን ለመቻል ዋስትና የሚኾነው ግን፣ የተገለጸው የምርት መጠን ቀጣይነት እንደሚኖረው ማረጋገጥ ሲቻል እንደኾነ ሳያሳስቡ አላለፉም። መንግሥት ይፋ ያደረገው መረጃ አንድን የምርት ዓይነት ብቻ የተመለከተ እንደኾነ የጠቀሱት አቶ መሸሻ፣ በስንዴ ራስን መቻል ማለት በአጠቃላይ የምግብ እህል ምርት ራስን ከመቻል የተለየ መኾኑን አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ስንዴ ከውጭ መግዛት ያቆመችው፣ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ እንደኾነም፣ የመንግሥት መግለጫ አክሎ አውስቷል።

እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ አምስት ቦታዎች ወታደሮቿን አስቀምጣለች

የእስራኤል ወታደሮች ከታጣቂው ሄዝቦላህ ጋራ በተደረሰበት የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት፣ አካባቢውን ለቀው መውጣት በሚገባቸው የዛሬው ማክሰኞ ቀነ ገደብ 
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ አምስት ቦታዎች ወታደሮቿን አስቀምጣለች

የእስራኤል ወታደሮች ከታጣቂው ሄዝቦላህ ጋራ በተደረሰበት የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት፣ አካባቢውን ለቀው መውጣት በሚገባቸው የዛሬው ማክሰኞ ቀነ ገደብ  ከአንዳንድ የደቡብ ሊባኖስ አካባቢዎች ለቀው አለመውጣታቸው ተነገረ፡፡ እስራኤል በክልሉ ከሚገኙ አንዳንድ መንደሮች ለቃ ብትወጣም፣ የሰሜናዊ እስራኤልን የተወሰኑ ክፍሎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ናቸው ካለቻቸው አምስት ቦታዎች ኃይሏን ያላስወጣች መሆኑን ተናግራለች። የሊባኖስ ፕሬዝደንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፓርላማ አፈ-ጉባኤ ዛሬ ማክሰኞ በሰጡት የጋራ መግለጫ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል በአስቸኳይ እንድትወጣ እንዲጠይቅ ጥሪ አቅርበዋል። መግለጫው «በማንኛውም ስንዝር የሊባኖስ ግዛት ውስጥ የእስራኤል ጦር መገኘት ወረራ ነው፣ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት የሚያስከትላቸው መዘዞች አሉት» ሲል ገልጿል። የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሂዝቦላህ ከእስራኤል ድንበር ርቆ እንዲሄድ እና የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ከሊባኖስ ወታደሮች ጋራ በተለቀቀው የመከላከያ ቀጠና እንዲሰማሩ ከማድረግ ጋራ፣ እስራኤል በጥር መጨረሻ ለቃ እንድትወጣ ይጠይቃል፡፡ የተራዘመው ቀነ-ገደብ ወደ ዛሬ ማክሰኞ እንዲገፋ መደረጉም ተመልክቷል፡፡ ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሊባኖስ ተወካይ ጄኒን ሄኒስ-ፕላስቻርት እና በሊባኖስ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አሮልዶ ላዛሮ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተግባራዊ የሚደረግበት ሌላ የተራዘመ ቀን መኖሩ “እኛ ይሆናል ብለን ያሰብነው አይደለም” ብለዋል። መግለጫው አክሎም «ሁለቱም ወገኖች ግዴታቸውን እንዲወጡ እንጠይቃለን። በመንደሮቻቸው እና በከተሞቻቸው ላይ እየደረሰ ካለው መጠነ ሰፊ ውድመት ጋር የሚታገሉት የደቡብ ሊባኖስ ማህበረሰቦች፣ እንዲሁም ቤታቸውን ለቀው ለመውጣት የተገደዱት የሰሜን እስራኤል ነዋሪዎች ሁኔታ በአንድ ጀምበር የማይፈታ እና መፍትሄዎቻቸው ከወታደራዊ ዘመቻዎች ሊገኙ አይችሉም ።” ብሏል፡፡ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ሠራዊቱ »ሊባኖስ ውስጥ ከጦርነት ቀጠና ውጭ፣ በሚቆጣጠራቸው አምስት ቦታዎች እንደሚቆይ እና ማንኛውም የሂዝቦላ ጥሰት ቢኖር በኃይል እና ያለማወላወል ርምጃ ለመውሰድ መሥራቱን ይቀጥላል" ብለዋል ። በኅዳር ወር መጨረሻ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት፣ በሊባኖስ ከአንድ ዓመት በላይ የቆየውን ጦርነት አስቁሟል። ይህም የተኩስ አቁም ስምምነት ከመደረጉ በፊት በነበሩት ወራት ውስጥ የእስራኤል ወታደሮች ሊባኖስ ውስጥ የምድር ዘመቻ ሲያደርጉ እና በሂዝቦላ ላይ ተደጋጋሚ የአየር ድብደባ አጠናክረው ሲፈጽሙ ቆይተዋል። የጋዛ ሰርጥ የሃማስ ታጣቂዎች ሰሜን እስራኤል ላይ ጥቃት በመፈጸም 1 ሺሕ 200 የሚጠጉ ሰዎችን ከገደሉ እና 250 ታጋቾችን ከወሰዱ አንድ ቀን በኋላ ታጣቂዎቹ እኤአ ጥቅምት 2023 በርካታ ድንበር ተሻጋሪ ሮኬቶችን መተኮስ ጀምረዋል፡፡ እስራኤል በሃማስ ላይ ባካሄደችው አጸፋዊ ጥቃት ከ48 ሺሕ 200 በላይ ፍልስጤማውያንን ተገድለዋል ሲል የጋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል። ሚኒስቴሩ በታጣቂዎችና በሲቪሎች መካከል ያለውን የሟቾችን ቁጥር ለይቶ አላመለከተም፡፡ እስራኤል በበኩሏ ከ17 ሺሕ 000 በላይ ታጣቂዎችን መግደሏን አስታውቃለች። የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያው ምዕራፍ በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ያበቃል። እስካሁን ባለው የተኩስ አቁም ስምምነት፣ ሃማስ 24 ታጋቾችን መልቀቁን እና እስራኤል ከ1 ሺሕ በላይ የፍልስጤም እስረኞችን መፍታቷን ያካትታል።

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን ያስታወቀው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገር ውስጥ ምርት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በመታየቱ ኢትዮጵያ ከው
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን ያስታወቀው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገር ውስጥ ምርት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በመታየቱ ኢትዮጵያ ከውጪ በሚገባ የስንዴ ምርት ላይ ጥገኛ መሆኗ ቀርቷል« ሲል ተናግሯል። ኢትዮጵያ የስንዴ ምርቷ ስላደገ »ስንዴ ከውጭ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑ ቀርቷል« ብላለች።። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጽሕፈት ቤት የወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማርካት በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጪ የውጭ ሀገር የስንዴ ምርት ታስገባ ነበር። መግለጫው  አያይዞም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠ በ2022/23 የምርት ዘመን ኢትዮጵያ 15 ነጥብ 1 ሚሊየን ቶን ስንዴ እንዳመረተች ጠቁሞ የስንዴ ምርቱ መጠን በቀጠለው ዓመት ወደ 23 ሚሊየን ቶን ማደጉን አውስቷል። አያይዞም ሀገሪቱ  በስንዴ ምርት እራሷን መቻሏ  ስንዴ ከውጭ  መግባቱ  ይቆማል ማለት ግን እንዳልሆነ ያሳሰበው መግለጫው በሀገሪቱ ውስጥ የሚሠሩ የሰብአዊ ርዳታ ተቋማት አሁንም ከሀገር ውስጥ ገበያ ስንዴ ከመግዛት ይልቅ ከውጭ ሀገራት ማስገባትን ሊመርጡ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግሥቱ መግለጫ የወጣው  ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ወራት ያህል የውጭ ርዳታን እንዲቆም ባደረገችበት በአሁኑ ወቅት ቢሆንም  የአሜሪካ የውጭ ርዳታ ስለመቆሙ  አላነሳም። የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናት ምግብ፣ መድኃኒት እና ሌሎች የአጣዳፊ ጊዜ ድጋፎች ከዕቀባው ውጪ እንዲሆኑ ትዕዛዝ መተላለፉን ግልጽ አድርገዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ሕይወት አድን መርሐ ግብሮች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ  የሚያስችል “ጥቅል መሳሰቢያ” መስጠታቸውን ገልጸዋል። “ምግብ ፣ መድኃኒት ወይም ማንኛውም ሕይወት አድን  የሆነ አጣዳፊ አገልግሎት በዕቀባው አይካተትም »  ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አስታውቀዋል።

አሜሪካና ሩሲያ ግንኙነታቸውን ለማሻሻልና የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም አብረው ለመሥራት ተስማሙ

አሜሪካና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማሻሻልና የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችለውን ሥራ ለመጀመር ተስማምተዋል። ውሳኔው የመጣ
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካና ሩሲያ ግንኙነታቸውን ለማሻሻልና የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም አብረው ለመሥራት ተስማሙ

አሜሪካና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማሻሻልና የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችለውን ሥራ ለመጀመር ተስማምተዋል። ውሳኔው የመጣው የሁለቱ ወገኖች ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሳዑዲ አረቢያ ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በአሜሪካና “በሩሲያ መመሪያ ሰጪነት የሚደረግ የጦርነት ማቆም ውሳኔን” እንደማይቀበሉ ተናግረዋል። በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማቆም ሁለቱም የጦርነቱ ተሳታፊ ወገኖች በሰጥቶ መቀበል መርህ መሠረት መተው ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ ከሩሲያ ልዑክ ጋራ የተወያዩት የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ ዕለቱ የአስቸጋሪውና የረጅሙ ጉዞ አንድ ርምጃ የተወሰደበት ቀን እንደሆነ አመልክተዋል። “ዛሬ የረጅሙና አስቸጋሪው ጉዟችንን የመጀመሪያ ርምጃ የምንወስድበት ቀን ነው። ነገር ግን እጅግ አስፈላጊ ነው። ፕሬዝደንት ትረምፕ ይህንን ግጭት ለማስቆም ቆርጠዋል። በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ግጭቱ እንዲቆም እንደሚሹ አስታውቀዋል። በሁለት ወይም ሦስት ዓመታት ውስጥ መልሶ ሌላ ግጭት በማይፈጥርበት ሁኔታ ዘላቂ በሆነ መንገድ እንዲቆም ይሻሉ። ይህን መፈጸም ቀላል አይሆንም። ነገር ግን በዓለም ይህን ሂደት ሊያስጀምሩ የሚችሉት እርሳቸው ብቻ ናቸው። ዶናልድ ትረሞፕ ሂደቱን ማስጀመር የሚችሉ ብቸኛ መሪ ናቸው። እናም ዛሬ የሂደቱ  የመጀመሪያ ርምጃ የተወሰደበት ቀን ነው” ብለዋል ሩቢዮ። በንግግሩ ላይ ከተሳተፉት የአሜሪካ ባለሥልጣናት አንዱ የሆኑት የዋይት ሃውስ ብሔራዊ የፀጥታ አማካሪ ማይክ ዋልትስ በበኩላቸው፣ በፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕና በሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መካከል የሚደረገው ስብሰባ መቼ እንደሚሆን ቀን እንዳልተቆረጠለት ተናግረዋል። ድርድሩ ለዩክሬንም ሆነ ለሩሲያ የድንበርና የፀጥታ ማስተማመኛዎች በመሰጠት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ማይክ ዋልትስ አመልክተዋል። ሩሲያ በአሁኑ ወቅት አንድ አምስተኛ የሚሆነውን የዩክሬን ክፍል ትቆጣጠራለች፡፡ አሜሪካ መር የሆነው ጥረት በዩክሬን እና በአውሮፓ በሚገኙ አጋሮች ዘንድ አሳሳቢ በሆነበት በዚህ ወቅት፣ ዋናው ግባቸው “በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑት ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ያለው”  ስምምነት ላይ መድረስ እንደሆነ ማርኮ ሩቢዮ ተናግረዋል። “ዛሬ ከስብሰባው የወጣሁት፣ በምን መንገድና በምን ፍጥነት ጦርነቱ ይቋጭ በሚለው ላይ የጥረት ሂደቱን ለመጀመር ፍላጎት እንዳላቸው በመተማመን ነው። የሚፈለገው ግብ ላይ የምንደርሰው የግጭቱ ተሳታፊዎች መተው ያለባችውን ጉዳዮች ለመተው ፈቃደኛ ከሆኑ ነው። ይህን ስብሰባ ማድረጉ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ከሩሲያ ጋራ  ባለፉት ሶስት ዓመታታ ይህ ነው የሚባል ውይይት አድርገን አናውቅም” ሲሉ አክለዋል የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ። ዛሬ ማክሰኞ ከአሶስየትድ ፕሬስ ጋራ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ሪቢዮ፣ ሁለቱ ወገኖች፣ ማለትም አሜሪካ እና ሩሲያ በሶስት ጉዳዮች ላይ የተቀመጡ ግቦችን ዳር ለማድረስ እንደተስማሙ አስታውቀዋል። እነዚህም፣ በሞስኮና በዋሽንግተን በሚገኙ ኤምባሲዎቻቸው የነበረውን የሰው ኅይል ቁጥር ወደ ነበረበት መመለስ፣ የዩክሬኑን የሰላም ውይይት ለመደገፍ አንድ ከፍተኛ ቡድን ማቋቋም እንዲሁም ይበልጥ የቀረበ ግንኙነትና  የኢኮኖሚ ትብብር ማድረግ የሚሉት እንደሆኑ ሩቢዮ አመልክተዋል። የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እና ሌሎች ከፍተኛ የሩሲያ ባለሥልጣናት የተሳተፉበት ውይይት የመጀመሪያው መሆኑን እና ወዲፊት ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅም ሩቢዮ አመልክተዋል። በውይይቱ የዩክሬን ባለሥልጣናት እንዳልተገኙ የአሰኦስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ “በአሜሪካና በሩሲያ መመሪያ ሰጪነት የሚደረግን ጦርነት የማቆም ውሳኔን” እንደማይቀበሉ ተናግረዋል። ዜሌንስኪ የሃገራቸው ድንበር በእ.አ.አ 2014 ወደነበረበት እንዲመለስ ሲጠይቁ ቆይተዋል። የአሜሪካ ባለሥልጣናት ግን፣ ዩክሬን ኔቶን ለመቀላቅ እንድምታደርገው ጥረት ሁሉ፣ ድንበሩ ወደነበረበት ይመለስ የሚለው ጥያቄም ተቀባይነት ማግኘቱ አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል አስታውቀዋል። ዜሌንስኪ በዚህ ሳምንት በሳዑዲ አረቢያ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ወደ መጋቢት 1፣ 2017 አስተላልፈዋል። ምክንያቱ ደግሞ የሃገራቸው ባለሥልጣናት በውይይቱ ላይ እንዲካፈሉ ባለመጋበዛቸው እንደሆነ አመልክተዋል። በዚህ ሳምንት ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝትም ከውይይቱ ጋራ እንደሚገናኝ ተደርጎ እንዲታይ እንዳልፈለጉም አስታውቀዋል። ዜሌንስኪ በዩክሬን የአሜሪካ ልዩ ልዑክ የሆኑትን ኪት ኬሎግ ነገ ረቡዕ አግኝተው ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል።    

የአውሮፓ መሪዎች በዩክሬንና በአህጉሩ ጸጥታዊ ጉዳዮች ላይ አስቸኳይ ጉባኤ አካሔዱ

የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት መሪዎች፣ ትላንት ሰኞ፣ ፓሪስ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ያደረጉ ሲኾን፣ በዩክሬንና በአጠቃላይ አህጉራዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ መክረ
የአሜሪካ ድምፅ

የአውሮፓ መሪዎች በዩክሬንና በአህጉሩ ጸጥታዊ ጉዳዮች ላይ አስቸኳይ ጉባኤ አካሔዱ

የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት መሪዎች፣ ትላንት ሰኞ፣ ፓሪስ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ያደረጉ ሲኾን፣ በዩክሬንና በአጠቃላይ አህጉራዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ሄንሪ ሪጅዌል ከለንደን እንደዘገበው፣ መሪዎቹ ስብሰባውን ያደረጉት፣ ሰሞኑን ዩናይትድ ስቴትስ በተከታታይ በምታካሒዳቸው የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች፣ ለአውሮፓ አህጉራዊ ጸጥታ መሠረት ለኾነው የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) ባላት ቁርጠኝነት ላይ ጥያቄ ማንሣታቸውን ተከትሎ ነው። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የኦክላሆማ ግዛት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን የኢሚግሬሽን ኹኔታ ለመመዝገብ ዐቅደዋል

በዩናይትድ ስቴትስ የኦክላሆማ ግዛት ሕግ አውጭዎች፣ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተማሪዎችንና የወላጆችን የኢሚግሬሽን ኹኔታ መረጃን የማሰባሰብ ሥራ ለመ
የአሜሪካ ድምፅ

የኦክላሆማ ግዛት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን የኢሚግሬሽን ኹኔታ ለመመዝገብ ዐቅደዋል

በዩናይትድ ስቴትስ የኦክላሆማ ግዛት ሕግ አውጭዎች፣ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተማሪዎችንና የወላጆችን የኢሚግሬሽን ኹኔታ መረጃን የማሰባሰብ ሥራ ለመጀመር የሚያስችለውን ዕቅድ እየተመለከቱ ናቸው። በአንጻሩ አንዳንድ የአካባቢ ትምህርት ቤት ሓላፊዎች፣ የቀረበውን ሕግ ተፈጻሚ ለማድረግ ፈቃደኛ እንደማይኾኑ በመናገር ላይ ናቸው። ስካት ስተርንስ ከኦክላሆማ ዳሪያ ቨርሺሌንኮ ተከታዩን ያጠናቀረውን ዘገባ  ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በአማራ ክልል በመንፈቅ ዓመቱ 89 ዳኞች ሥራ መልቀቃቸው ተገለጸ፤ የክልሉ ምክር ቤት የዳኞች ከለላ ዐዋጅን አጸደቀ

በአማራ ክልል፣ ባለፉት ስድስት ወራት 89 ዳኞች ሥራ መልቀቃቸውን፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዓለም አን
የአሜሪካ ድምፅ

በአማራ ክልል በመንፈቅ ዓመቱ 89 ዳኞች ሥራ መልቀቃቸው ተገለጸ፤ የክልሉ ምክር ቤት የዳኞች ከለላ ዐዋጅን አጸደቀ

በአማራ ክልል፣ ባለፉት ስድስት ወራት 89 ዳኞች ሥራ መልቀቃቸውን፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዓለም አንተ አግደው፣ ሰሞኑን በተካሔደው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት፣ የደኅንነት እና የጸጥታ ስጋት እንዲሁም የክፍያ ማነስ በመንፈቅ ዓመቱ በርካታ ዳኞች ከሥራ መልቀቅ ምክንያት እንደኾነ አስረድተዋል። 28 የወረዳ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎቶች አገልግሎት መቋረጡንም ፕሬዝዳንቱ አክለው ገልጸዋል። ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ሁለት የክልሉ ዳኞች፦ የሞያ ነጻነት ማጣት፣ የደመወዝ ማነስና የደኅንነት ስጋት ሥራቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቃቸው ገፊ ምክንያቶች መኾናቸውን ተናግረዋል። የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር ተወካይ ሓላፊ አቶ ብርሃኑ አሳሳ፣ ለዳኞች የሥራ መልቀቅ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት የተጠቀሰውን ምክንያት አረጋግጠው፣ የዐዋጁ መጽደቅ ማኅበሩ በተለያየ ጊዜ ሲያነሣቸው የነበሩ ችግሮችን ይቀንሳል፤ ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት፣ ለዳኞች ከለላ እና ጥበቃ ለመስጠት፣ የአማራ ብሔራዊ ክልል ፍርድ ቤቶች ማጠናከሪያ ዐዋጅን አጽድቋል። ዐዲሱ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፣ ዐዋጁን አስመልክቶ በኮሚሽኑ የፌስቡክ ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ “የዳኝነት ነጻነት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና ለሰብአዊ መብቶች መከበር መሠረት በመኾኑ፣ የዳኞች ያለመከሰስ መብት የሕግ ከለላ ማግኘቱ፦ በክልሉ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ወሳኝ ነው፤” ብለዋል።

የትረምፕ አስተዳደር የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር ሠራተኞችን ማባረር ጀምሯል 

የትራንስፖርት ሚንስቴር «ወሳኝ የበረራ ደኅንነት ሠራተኞች አልተባረሩም» ብሏል ሠራተኞቹን የማስወጣቱ ርምጃ የተጀመረው ቁጥሩ የበዛ ሰው በአውሮፕላ
የአሜሪካ ድምፅ

የትረምፕ አስተዳደር የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር ሠራተኞችን ማባረር ጀምሯል 

የትራንስፖርት ሚንስቴር «ወሳኝ የበረራ ደኅንነት ሠራተኞች አልተባረሩም» ብሏል ሠራተኞቹን የማስወጣቱ ርምጃ የተጀመረው ቁጥሩ የበዛ ሰው በአውሮፕላን በሚጓጓዝበት ያለፈው ሳምንት መጨረሻ ከመኾኑም ሌላ ባለፈው ጥር ወር በሬገን ዋሽንግተን አውሮፕላን ጣቢያ ሁለት አውሮፕላኖች አየር ላይ ተጋጭተው የበርካታ ሰዎች ህይወት ከጠፋበት አደጋ በሳምንታት ተከትሎ ነው። የአቪየሽን ደኅንነት ባለሞያዎች ማኅበር ፕሬዝደንት ዴቪድ ስፔሮ ባወጡት መግለጫ  ወደ ቋሚ ሠራተኝነት መሸጋገሪያ ክትትል ወቅት ላይ ያሉ የቅርብ ጊዜ ተቀጣሪዎች «ከሥራ ተሰናብታችኋል» የሚለው የኢሜል ደብዳቤ የደረሳቸው ባለፈው ዓርብ ማታ መሆኑን አመልክተዋል። ማንነቱ እንዳይገለጽ የጠየቀ  የበረራ ትራፊክ ተቆጣጣሪ ለአሶሲየትድ ፕሬስ በሰጠው ቃል ከተባረሩት መካከል የራዳር ክትትል ባለሞያዎች እና አብራሪዎችን አውሮፕላን በማሳረፍ እና በበረራ ሂደት የሚረዱ  ባለሞያዎች ጭምር እንዳሉባቸው ተናግሯል። የትራንስፖርት ሚንስቴር በበኩሉ ትላንት ሰኞ ማታ ለአሶሲየትድ ፕሬስ በሰጠው ቃል «በሠራተኛ ቅነሳው አንድም የአየር ትራፊክክ ተቆጣጣሪ አልተነካም። መሥሪያ ቤቱ ወሳኝ የሆኑ የበረራ ደኅንነት ሥራ ላይ ያሉ ሠራተኞች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ አድርጓል» ብሏል። በማስከተልም «የሚያርፉ አውሮፕላኖች የሚከታተሉ እንዲሁም  የበረራ  እቅድ ርዳታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች ሥራ  ወሳኝ የደኅንነት ሥራ ተብሎ ሊመደብ ይችል እንደሆነ ማጤን ይኖርብናል»  ማለቱንም አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል። የበረራ ትራፊክ ቁጥጥር ሠራተኞች ማኅበር ትላንት ሰኞ ባወጣው አጭር መግለጫ የተባለው የሠራተኞቹ መባረር በሀገሪቱ የአየር ክልል  ደኅንነት ሥርዐት እንዲሁም በማኅበሩ አባላት ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በመገምገም ላይ እንደኾነ አስታውቋል።

ቶሮንቶ ውስጥ ከወደቀው አውሮፕላን 21 መንገደኞች መካከል 19 ያህሉ ከሆስፒታል እንደወጡ ዴልታ አየር መንገድ አስታወቀ

በትናንትናው ዕለት  ቶሮንቶ ውስጥ አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ በኋላ ወደ አካባቢው ሆስፒታሎች ከተወሰዱ 21 መንገደኞች ውስጥ 19ኙ ታክመው መውጣታቸውን ዴልታ አየር መ
የአሜሪካ ድምፅ

ቶሮንቶ ውስጥ ከወደቀው አውሮፕላን 21 መንገደኞች መካከል 19 ያህሉ ከሆስፒታል እንደወጡ ዴልታ አየር መንገድ አስታወቀ

በትናንትናው ዕለት  ቶሮንቶ ውስጥ አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ በኋላ ወደ አካባቢው ሆስፒታሎች ከተወሰዱ 21 መንገደኞች ውስጥ 19ኙ ታክመው መውጣታቸውን ዴልታ አየር መንገድ ዛሬ ማክሰኞ አስታወቀ። ባለሥልጣናት በቀጠናው በረራ በመብረር ላይ የነበረው ጄት በማረፍ ሂደት ለምን እንደተገለበጠ ለማወቅ ምርመራ ቀጥለዋል። የካናዳ የትራንስፖርት ደኅንነት ቦርድ  መርማሪዎች በዴልታ አየር መንገድ ኢንዴቨር ኤር ቅርንጫፍ የሚተዳደረው ሲ አር ጄ 900 አውሮፕላን በቶሮንቶ ፒርሰን አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እንዴት በጀርባው ሊወድቅ እንደቻለ  ለማወቅ የሚደረገውን ምርመራውን እየመሩ ነው። ከሚኒሶታ ሴንት ፖል አውሮፕላን ማረፊያ በተነሳው ዲኤል 4819 አውሮፕላን ላይ ምን እንደተከሰተ እስካሁን ግልጽ አልሆነም ።የአውሮፕላን አደጋዎቸ በተለያዩ ምክንያቶች ይከሰታሉ። 90 ሰዎችን ማሳፈር  የሚችለው አውሮፕላን በካናዳው ቦምባርዲየር ኩባንያ የተሠራ ሲኾን የጄኔራል ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ያመረተውን ሞተር ይጠቀማል። አደጋው ከተከሰተ በኋላ የተቀረጹ ምስሎች ከክንፎቹ መካከል ቢያንስ አንደኛው መገንጠሉን ያሳያሉ። የቶሮንቶ ፒርሰን አውሮፕላን ማረፊያ፣ በትናንትናው ዕለት ቀደም ብሎ በስፍራው በጣለው እና ከ22 ሴ.ሜ በላይ ጥልቅት ባለው በረዶ ምክንያት የታጠፉ በረራዎችን ለማስተካከል እየጣረ እንደነበረ አስታውቋል። በአደጋው ወቅት ኃይለኛ በረዶ የቀላቀለ ነፋስ እንደነበረ የበረራ ክትትል ድረ ገጽ የሆነው ፍላይት ራዳር 24 አስታውቋል።

የአውሮፓ መሪዎች በፀጥታ ቀውስ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ

ዩናይትድ ስቴትስ በተከታታይ እየወሰደቻቸው ያለቻቸው ዲፕሎማሲያዊ ጣልቃ ገብነቶች ከአውሮፓ ሀገራት ጋራ ባላት ትብብሮች ዙሪያ ጥርጣሬ በመፍጠራቸው፣ የአውሮ
የአሜሪካ ድምፅ

የአውሮፓ መሪዎች በፀጥታ ቀውስ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ

ዩናይትድ ስቴትስ በተከታታይ እየወሰደቻቸው ያለቻቸው ዲፕሎማሲያዊ ጣልቃ ገብነቶች ከአውሮፓ ሀገራት ጋራ ባላት ትብብሮች ዙሪያ ጥርጣሬ በመፍጠራቸው፣ የአውሮፓ መሪዎች ትላንት ሰኞ ፓሪስ ላይ በፀጥታ ቀውስ ዙሪያ ስብሰባ አካሂደዋል።  በኤሊዜ ቤተመንግሥት በተካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ከተገኙት የአውሮፓ መሪዎች መካከል የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር፣ የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ፣ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዋና ጸሃፊ ማርክ ሩታ፣ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን እና ሌሎች አመራሮች ይገኙበታል።  ከስብሰባው በኋላ ለጋዜጠኞች ንግግር ያደረጉት የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር «ጥያቄ ውስጥ የገባው የዩክሬን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ብቻ አይደለም። ለአውሮፓም የህልውና ጥያቄ ነው። ስለዚህ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ጥቅም ወሳኝ ነው» ብለዋል።  «ዩናይትድ ስቴትስ ኔቶን ጥላ እንደማትወጣ ግልፅ ነው» ያሉት ስታርመር «እኛ አውሮፓውያን ግን የበለጠ ማድረግ ይጠበቅብናል። ኃላፊነትን የመጋራት ጥያቄ አዲስ ባይሆንም፣ አሁን ግን አንገብጋቢ ሆኗል። አውሮፓውያን በወጪም ኾነ ባለን አቅም የበለጠ ማድረግ አለብን» ብለዋል።  ዘላቂ የሰላም ስምምነት ካለ፣ እንግሊዝ ከሌሎች ጋራ በመሆን ጦሯን ለማስፈር ዝግጁ መሆኗን ያመለከቱት ስታርመር፣ ከጀርባ ግን ዩናይትድ ስቴትስ መኖር አለባት ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። «ምክንያቱም ሩሲያ ዩክሬንን በድጋሚ እንደማታጠቃ የመከላከያ ብቸኛ ዋስትናው የዩናይትድ ስቴትስ የጸጥታ ዋስትና ነው» ሲሉም አብራርተዋል። በዚህ ሳምንት መጨረሻ ምርጫ የሚጠብቃቸው የጀርመኑ ሾልዝ በበኩላቸው፣ አውሮፓ እና ዩክሬን የሰላም ንግግሩ አካል እንዲሆኑ ጠይቀዋል።  

የዩናይትድ ስቴትስ እና የሩሲያ ባለሥልጣናት በዩክሬን ጦርነት እና ሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ለመወያየት ተገናኙ

ከፍተኛ የአሜሪካ እና የሩሲያ ዲፕሎማቶች፣ በሀገሮቻቸው መካከል ስላለው ግንኙነት እና በዩክሬን ያለው ጦርነት ሊያቆም በሚችልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር በዛሬው
የአሜሪካ ድምፅ

የዩናይትድ ስቴትስ እና የሩሲያ ባለሥልጣናት በዩክሬን ጦርነት እና ሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ለመወያየት ተገናኙ

ከፍተኛ የአሜሪካ እና የሩሲያ ዲፕሎማቶች፣ በሀገሮቻቸው መካከል ስላለው ግንኙነት እና በዩክሬን ያለው ጦርነት ሊያቆም በሚችልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር በዛሬው ዕለት  ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ስብሰባ ጀምረዋል። ንግግሮቹ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን የፊት ለፊት  ውይይት ያደርጉ ዘንድ የሚያስችሉ የመነሻ ርምጃዎች መሆናቸውን በመግለጽ ሁለቱም ወገኖች በውይይታቸው ዙሪያ ሲሰጡ ለነበሩ መላምቶች ምላሽ ሰጥተዋል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ ማርኮ ሩቢዮ ፣የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ማይክ ዋልትዝ እና የመካከለኛው ምስራቅ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊኮፍ የሚገኙበትን ልዑክ መርተዋል። በሩሲያ በኩል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እና ከፍተኛው የፑቲን ረዳት ዩሪ ዩሻኮቭ ተገኝተዋል። የዩክሬን መሪዎች በውይይቱ ለመሳተፍ እንዳልተጋበዙ ተናግረዋል። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ፣ የዩናይትድ ስቴትስ  የዩክሬን ልዑክ ኪት ኬሎግን ዕረቡ ዕለት አግኝተው ያነጋግራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዩክሬን በራሷ ዕጣ ፋንታ ዙሪያ በሚደረጉ  ውይይቶች መሳተፍ እንዳለባት እና  በቀጠናቸው ደህንነት ዙሪያ እንደ አዲስ ለውጥ በተመለከቱት ጉዳይ ላይ የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ  በቅርቡ  ይፋ ባደረጉት የአውሮፓ መሪዎች ዘንድ አዲሱ የዩኤስ-ሩሲያ ግንኙነት ስጋት ፈጥሯል። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአውሮፓ መሪዎችን ቡድን ሰኞ ዕለት ፓሪስ ላይ ስብሰባ ጠርተው የመከላከያ ወጪን ስለማሳደግ እና ለዩክሬን ሊሰጡ በሚገቡ የጸጥታ ዋስትናዎች ዙሪያ ተወያይተዋል። የፈረንሳዩ መሪ ከፓሪሱ ውይይት በኋላ ከትረምፕ እና ዜለንስኪ ጋር መነጋገራቸውን ገልጸው አውሮፓውያን፣ አሜሪካውያን እና ዩክሬናውያን በጋራ መሥራታቸው አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። «ጠንካራ እና አስተማማኝ» የደኅንነት ዋስትናዎች እንደሚያስፈልጉ የተናገሩት ዜለንስኪ፣ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ሩሲያ ከዩክሬን ወይም ከሌሎች የአውሮፓ አገሮች ጋራ ሌላ ጦርነት እንደምትጀምር አክለው ገልጸዋል።

አባ ፍራንሲስ  ጠንከር ያለ ሕመም ስለገጠማችው ቫቲካን የሳምንት መገባደጃ መርሐ ግብራቸውን ሰረዘች 

ሐኪሞች ህመማቸው ጠንከር ያለ እንደሆነ በመግለጻቸው ምክንያት ላለፉት አምስት ቀናት ሆስፒታል ውስጥ የቆዩት የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ  ለሳምንቱ
የአሜሪካ ድምፅ

አባ ፍራንሲስ  ጠንከር ያለ ሕመም ስለገጠማችው ቫቲካን የሳምንት መገባደጃ መርሐ ግብራቸውን ሰረዘች 

ሐኪሞች ህመማቸው ጠንከር ያለ እንደሆነ በመግለጻቸው ምክንያት ላለፉት አምስት ቀናት ሆስፒታል ውስጥ የቆዩት የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ  ለሳምንቱ መገባደጃ በተያዙት መርሐ ግብሮች ላይ እንደማይገኙ ቫቲካን በዛሬው ዕለት አስታወቀች ።  የ88 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ ከአንድ ሳምንት በላይ በመተንፈሻ አካላት በሽታ ሲሰቃዩ ቆይተው አርብ ዕለት ሮም በሚገኘው  ገሚሊ  ሆስፒታል ገብተዋል።  ቅዳሜ ሊካሄድ የታቀደው የቡራኬ ሥነ ስርዐት “በቅዱስ አባታችን የጤና ሁኔታ ምክንያት ተሰርዟል” ስትል  ቫቲካን ባሰራጨችው  አጭር መግለጫ ተመላክቷል። ዘወትር እሑድ ረፋድ ላይ ለቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ምዕመንና ታዳሚ በመስኮት ሰላምታ የሚሰጡበትና የሚባርኩበት ሥርዐት በምክትል የቫቲካን ሹም በኩል እሑድ ዕለት እንደሚከናወን ተገልጿል።  ቫቲካን ሰኞ ዕለት እንዳስታወቀችው  ሐኪሞች የጳጳሱን መድኃኒት ለሁለተኛ ጊዜ ቀይረዋል። ሐኪሞች  ሊቀ ጳጳሱ የገጠማቸውን የጤና ችግር «ፖሊሚክሮቢያል ኢንፌክሽን» ብለው ገልጸውታል።  ሐኪሞቹ በሽታው በቫይረስ ፣ ባክቴሪያ እና ፈንገስ ድብልቅ ተውሳኮች ሊቀሰቀስ እንደሚችል ተናግረዋል።  ከአውሮፓዊያኑ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሊቀ ጳጳስነት መንበራቸው የቀጠሉት  ፍራንሲስ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተደጋጋሚ የኢንፍሉዌንዛ እና ሌሎች የጤና ችግሮች አጋጥሟቸዋል።  በልጅነታቸው ፕለረሲ በተባለ በሽታ በመጠቃታቸው ከአንደኛው የሳንባ ክፍል የተወሰነው በቀዶ ጥገና እንዲወገድ ተደርጓል።  በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ሊቀ ጳጳሱ  ለሳንባ መቆጣት ተጋላጭ ኾነዋል። 

በካይሮ ሕንፃ ተደርምሶ ዐሥር ሰዎች ሞቱ 

በግብፅ ዋና ከተማ  ካይሮ ውስጥ ሦስት ፎቅ ያለው የመኖሪያ ሕንፃ ተደርምሶ ዐሥር ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች ስምንት ሰዎች ቆስለዋል። ቁጥራቸው ለጊዜው ያለተለዩ ሰዎች
የአሜሪካ ድምፅ

በካይሮ ሕንፃ ተደርምሶ ዐሥር ሰዎች ሞቱ 

በግብፅ ዋና ከተማ  ካይሮ ውስጥ ሦስት ፎቅ ያለው የመኖሪያ ሕንፃ ተደርምሶ ዐሥር ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች ስምንት ሰዎች ቆስለዋል። ቁጥራቸው ለጊዜው ያለተለዩ ሰዎች ደግሞ በፍርስራሽ ውስጥ ጠፍተዋል ተብሎ እንደሚገመት የሀገሪቱ የመንግሥት ብዙኅን መገናኛ  ዘግበዋል።  በካይሮ ምዕራባዊ ክፍል በሚገኘውና ከርዳሳ በተባለው አብዛኛው የሠራተኛ መደብ በሚኖርበት አካባቢ ከተደረመሰው የሕንፃው ፍርስራሽ ውስጥ በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት የሲቪል መከላከያ ቡድኖች ፍለጋ ላይ መኾናቸውን እና አምቡላንሶች ወደ ሥፍራው መላካቸውን አል-አክባር- አል -ዮም ጋዜጣ ዘግቧል።  ለሕንፃው መደርመስ “የጋዝ ሲሊንደር ፍንዳታ” ምክኒያት መኾኑን የዐይን እማኞቹን መናገራቸውን የጠቀሰው  በመንግሥት የሚተዳደረው ብዙኅን መገናኛ ፣ ፖሊስ ምርመራ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ  ዘግቧል።  የጊዛ ግዛት አዴል አል ናጋር  ፣ ከአደጋው የተረፉት ለደኅንነታቸው ሲባል ሕንፃውን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ እና አቅራቢያ ወደሚገኙ ሕንፃዎች እንዲዛወሩ ትዕዛዝ መስጠታቸውን የግዛቲቱ አስተዳደር በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።   ከ26 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርባት በካይሮ ከተማ እየተስፋፋ በመጣው በመጣው የግንባታ ሥራዎች፣ የግንባታ ሕግና ደንቦች እምብዛም አይተገበሩም።    ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በከተማዋ የሕንፃዎች መደርመስ እየተበራከተ መጥቷል። ይኽም በግንባታ ወቅት በሚፈጠሩ ቸልተኝነትና የግንባታ ሕጎችን ባለማክበር ነው። 

አሜሪካ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 16 ነውጠኞች መገደላቸውን ሶማሊያ አስታወቀች

አሜሪካ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ከእስላማዊ መንግሥት ጋራ ግንኙነት አላቸው የተባሉ 16 ነውጠኞችን መግደሏን የሶማሊያ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በፑንትላ
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 16 ነውጠኞች መገደላቸውን ሶማሊያ አስታወቀች

አሜሪካ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ከእስላማዊ መንግሥት ጋራ ግንኙነት አላቸው የተባሉ 16 ነውጠኞችን መግደሏን የሶማሊያ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በፑንትላንድ የጸጥታ ዘመቻዎች ቃል አቀባይ የሆኑት ብርጋዴር ጄነራል ሞሃሙድ አህመድ ለቪኦኤ የሶማሊኛ ቋንቋ አገልግልግሎት እንዳስታወቁት፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት የሟቾቹን ዜግነት ለማጣራት በመሥራት ላይ ናቸው። በእሑድ የአየር ጥቃት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቁልፍ ሚና እንደተጫወተች ጀኔራሉ አስታውቀዋል። በአየር ጥቃቱ ወቅት ነውጠኞቹ በፑንትላን የፀጥታ ኅይሎች መሠረት ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸማችውን ጀኔራሉ ጨምረው አስታውቀዋል። በአፍሪካ የአሜሪካ ዕዝ ቀደም ብሎ በአወጣው መግለጫ፣ የአየር ጥቃት መከናወኑንና  ሁለት ሽብርተኞች መገደላቸውን አስታውቆ ነበር። በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ፣ የአየር ጥቃቱ ሀገራቸውና አሜሪካ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ያላቸውን ጠንካራ አጋርነት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የእሁዱ ጥቃት አሜሪካ በአንድ ወር ውስጥ የፈጸምችው ሁለተኛው የአየር ጥቃት ነው። ከበርካታ ወራቶች ዝግጅት በኋላ ፑንትላንድ በአካባቢው በሚገኙ ሽብርተኞች ላይ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ነች፡፡ ከ200 በላይ የአይሲስ ተዋጊዎችን መግደሏንና ከእነዚህም ውስጥ በርካታ የውጪ ዜጎች እንደሚገኙበት ፑንትላን አስታውቃለች፡፡

በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ከኮንጎ ወደ ቡሩንዲ ሸሹ

በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን ጥቃት እያየለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ አሥር ሺሕ የሚሆኑ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዜጎች ባለፉት ሦስት ቀናት ድንበሯ
የአሜሪካ ድምፅ

በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ከኮንጎ ወደ ቡሩንዲ ሸሹ

በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን ጥቃት እያየለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ አሥር ሺሕ የሚሆኑ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዜጎች ባለፉት ሦስት ቀናት ድንበሯን አቋርጠው መግባታቸውን ቡሩንዲ አስታውቃለች፡፡ ወታደርቶችን ከሲቪሎች ለመለየትና በተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አማካይነት መጠለያ ለመስጠት ጥረት በመደረግ ላይ መኾኑን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል። በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በምሥራቅ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሰፊ ሥፍራዎችን የተቆጣጠሩ ሲኾን፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ  በደቡብ ኪቩ ግዛት ቡካቩ የተሰኘችውን ቁልፍ ከተማ ተቆጣጥረዋል። ሥፍራው ከቡሩንዲ ድንበር 50 ኪ. ሜ. ርቀት ላይ የሚገኝ መሆኑም ታውቋል። በሺሕ የሚቆጠሩት የኮንጎ ዜጎች ወደ ቡሩንዲ የሸሹት የቡካቩ መያዝ አስደንግጧቸው እንደሆነ ታውቋል። ቡሩንዲ ባለፈው ዓርብ ፍልሰቱን ለመግታት ስትል ለተወሰኑ ሰዓታት ድንበሯን ዘግታ እንደነበር ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

አፍሪካ ኅብረት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለፕሪቶሪያው ስምምነት ተፈጻሚነት ትኩረት እንዲሰጡ ትግራይ ክልል ጥሪ አቀረበ

ትግራይ ክልል ይኽን ጥሪ ያቀረበው፣ አዲስ አበባ ላይ ሲካሔድ የቆየው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ማጠናቀቂያ ቀን፣ በፕሪቶሪያ የተደረሰው በዘላቂነ
የአሜሪካ ድምፅ

አፍሪካ ኅብረት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለፕሪቶሪያው ስምምነት ተፈጻሚነት ትኩረት እንዲሰጡ ትግራይ ክልል ጥሪ አቀረበ

ትግራይ ክልል ይኽን ጥሪ ያቀረበው፣ አዲስ አበባ ላይ ሲካሔድ የቆየው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ማጠናቀቂያ ቀን፣ በፕሪቶሪያ የተደረሰው በዘላቂነት ተኩስ የማቆም የሰላም ስምምነት በተመለከተ ለጋዜጠኞች በተሰጠ የማብራሪያ ሪፖርት ላይ ነው። የፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ ያተኮረው ሪፖርት፣ ከመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ሲካሔድ ፣አጠቃላይ ሂደቱና ተገኝተዋል የተባሉ ትምሕርቶችን የተመለከተ ሪፖርት ይፋ ተደርጓል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌላኛውን የህወሓት ቡድንን የሚመሩት ዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ተገኝተዋል። ሁለቱ መሪዎች የእጅ ሰላምታ ተሰጣጥተውና ጎን ለጎን ተቀምጠው ተቀምጠው ማብራሪያና ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች፣ እንዲሁም ዋና አደራዳሪ የነበሩትን ኦሉሴጉን ኦባሳንጆን አና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ተገኝተዋል። በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓ መካከል ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በፕሪቶሪያ የተደረሰው በዘላቂነት ተኩስ የማቆም የሰላም ስምምነት በአፍሪካ ኅብረት መሪነት እውን የኾነ የመጀመሪያው ውጤታማ ተብሎ የሚጠቀስ የሰላም ስምምነት ነው፡፡ በሪፖርቱ ላይ መነሻውን በትግራይ ክልል አድርጎ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተስፋፋው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ ከተቀሰቀሰ ከአንድ ዓመት በኋላ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን፣ የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የኅብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ በማድረግ ለግጭቱ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ በመሾም ግጭቱን በሰላም ለማስቆም ከተለያዩ አካላት ጋራ ያደረጋቸውን ጥረቶች ተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች ቀርበዋል፡፡  በአፍሪካ ኅብረት በነበረው በዚህ ዝግጅት ላይ ንግግር ካደረጉ አካላት መካከል የሆኑት ተሰናባቹ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት፣ “ይህ ሪፖርት በመላው አፍሪካ ሰላምን ለማስፈን ለምናደርገው ጥረት መማሪያ የሚኾነን ነው” ብለዋል፡፡ የፕሪቶሪያው የሰላም ሂደት “ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” የሚለውን መርህ አጉልቶ የሚያሳይ ነው” ያሉት ዋና አደራዳሪው የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በበኩላቸው፣ “አፍሪካዊ ተቋማት በአህጉሪቱ ያሉ ግጭቶችን መፍታት እና ሰላም ማውረድ እንደሚችሉ የሚያሳይ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ህወሃትን በመወከል ስምምነቱን የፈረሙት የአሁኑ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፣ “ብዙ የስምምነቱ ይዘቶች አልተፈጸሙም” በማለት፣ የአፍሪካ ኅብረት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ “አልተፈፀሙም” ባሏቸው ነጥቦች ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ ከእነዚኽም መካከል የተፈናቃዮች ጉዳይ እና የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተን እና ወደ ማኅበረሰቡ መልሶ ማዋሃድ (ዲዲአር) እንደሚገኙበት በአጽንኦት ገልፀዋል፡፡ «ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት የሚያደርገው በትጥቅ ማስፈታት ጉዳይ ላይ ብቻ ነው» ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ነገር ግን እነዚህን ታጣቂዎች መልሶ የማቋቋም ጉዳይም አብሮ የሚሄድ ጉዳይ መሆኑ መዘንጋት የለበትም ብለዋል፡፡ አሁን እዚህ እየተናገርን ባለንበት ወቅት “በርካታ ሴቶች እና ህፃናት በመጠለያዎች በስቃይ ላይ ይገኛሉ” በማለት፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች “በሕገመንግሥቱ የትግራይ አካል ወደሆኑ ወሰኖች የመመለሳቸው ጉዳይ” በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና በአፍሪካ ኅብረት ትኩረት ሊደረግበት ይገባል ብለዋል። የኢትዮጵያን መንግሥት በመወከል በፕሪቶሪያው ድርድር ከተሳተፉት ባለሥልጣናት አንዱ የሆኑት አሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትረ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ስምምነቱን ለመፈፀም የሚያስችሉ ርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ ያልተፈፀሙ የሰምምነቱ ነጥቦች ደግሞ “በንግግር እና ሕግን ባከበረ መልኩ መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡ የሰላም ስምምነቱን በዋና አደራዳሪነት የመሩት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦባሳንጆ፣ የዲዲአር እና የአወዛጋቢ ቦታዎች ጉዳይ መፍትሔ እስኪያገኙ ድረስ በይደር መታየት እንዳለባቸው ገልፀው “የስምምነቱን ተፈጻሚነት ሊጎዱ እና ወደ ኋላ ሊመልሱት አይገባም” ብለዋል፡፡

የሩስያ ወታደሮች በምስራቅ በዩክሬን ሃይሎች ላይ ጥቃቱን አጠናክረው ቀጥለዋል  

የሩስያ ወታደሮች በምስራቃዊ ዩክሬን ጥቃታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ አጠናክረዋል ሲል የኪዬቭ ጦር አስታውቋል፡፡  አንድ የኔቶ ባለስልጣን ሞስኮ ጦርነቱን ለመጨ
የአሜሪካ ድምፅ

የሩስያ ወታደሮች በምስራቅ በዩክሬን ሃይሎች ላይ ጥቃቱን አጠናክረው ቀጥለዋል  

የሩስያ ወታደሮች በምስራቃዊ ዩክሬን ጥቃታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ አጠናክረዋል ሲል የኪዬቭ ጦር አስታውቋል፡፡  አንድ የኔቶ ባለስልጣን ሞስኮ ጦርነቱን ለመጨረስ በሚደረገው ውይይት የጥቃቱን ፍጥነት እና ጥንካሬ እንደሚጨምር ተንብየዋል።   ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰላም እንዲሰፍን ግፊት እያደረጉ ባሉበትና የአሜሪካና ሩሲያ ባለስልጣናት በሚቀጥሉት ቀናት በሳውዲ አረቢያ ይገናኛሉ ትብሎ በሚጠበቅበት በአሁኑ ወቅት የሩስያ ጦር የተከፈተው ዋናዎቹ ጥቃቶቹ ያተኮሩት በፖክሮቭስክ የሎጂስቲክስ ማእከል አቅራቢያ መሆኑ ተገልጿል፡፡  የኪየቭ ጦር ትላንት ከሩሲያ ጋር በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ 261 ውጊያዎች ማድረጉን ገልጿል፣ ይህም በዚህ አመት ከፍተኛው ቁጥር ሲሆን በቀደሙት ቀናት ከተመዘገበው በመቶ እጥፍ የሚበልጥም ነውም ብሏል፡፡   የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ እንደሚያመለክተው የሞስኮ ወታደሮች በእኤአ 2024 አጋማሽ ጀምሮ በምስራቅ በኩል መንደር በመንደር ቀስ በቀስ የገፉ መምጣታቸውን አስታውቀዋል።  ምንም እንኳን ፕሬዚደንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በምስራቅ በኩል “ ጥሩ ውጤት” ተገኝቷል ያሉ ቢሆንም፡፡  የወታደራዊ ሃይሉ ቃል አቀባይ በበኩላቸው የኪየቭ ሀይሎች የፒሽቻን መንደር መልሰው መያዛቸውን ተናግረዋል።   ፕሬዘዳንት ትራምፕ በመጀመሪያ ኪዬቭ ጋር ሳይማክሩ እና አውሮፓውያንን ሙሉ በሙሉ ለመተው ከሩሲያውያን ጋር በቀጥታ ለመገናኘት መገፋፋቸው በዩክሬን እና በአውሮፓ በኩል አስደንጋጭ ሁኗል ። የዩክሬን ባለስልጣናትም ትራምፕን ለማወደስ ጥንቃቄ አድርገዋል፡፡   ኪየቭ በሳዑዲ አረቢያ በሚደረገው ድርድር ላይ ለመሳተፍ እንዳልተጋበዘችና በማንኛውም ሁኔታ ከሩሲያ ባለስልጣናት ጋር ከመገናኘቷ በፊት ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ አጋሮቿ ጋር የጋራ ስትራቴጂ መንደፍ እንደምትፈልግ አስታውቃለች። 

በሩዋንዳ የሚደገፉት አማጽያን ሁለተኛ ከተማ ያዙ 

በሩዋንዳ የሚደገፉ አማፂያን ዛሬ ጥዋት በምስራቅ ኮንጎ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ  የሆነችውን ቡካቩን ይዘዋል፡፡  በአካባቢው ካለው የመንግስት ጦር ጥቂት መከላ
የአሜሪካ ድምፅ

በሩዋንዳ የሚደገፉት አማጽያን ሁለተኛ ከተማ ያዙ 

በሩዋንዳ የሚደገፉ አማፂያን ዛሬ ጥዋት በምስራቅ ኮንጎ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ  የሆነችውን ቡካቩን ይዘዋል፡፡  በአካባቢው ካለው የመንግስት ጦር ጥቂት መከላከል ብቻ የገጠማቸው አማጽያኑ በከተማዋ የሚገኘውን የደቡብ ኪቩ ግዛት አስተዳደር ፅህፈት ቤትን የተቆጣጠሩት  ሲሆን አብዛኞቹም የአማፂያኑን ግስጋሴ በመፍራት ሸሽተዋል።    የኤም 23 አማፂያን በ101 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘውና ባለፈው ወር ከተቆጣጠሯት የጎማ ከተማ ለቀናት ተጉዘው ዛሬ እሁድ ጥዋት ማዕከላዊ ቡካቩ  ደርሰው በከተማው ሲዘዋወሩና በርካታ ነዋሪዎች በደስታ ሲጮሁ የአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኞች ተመልክተዋል። ይሁን እንጂ በአብዛኛው የከተማው ክፍሎች የሚገኙ ቤቶች ነዋሪዎች የሌሉባቸው ባዶ ሁነዋል፡፡   የኤም 23 አማፅያን በማዕድን የበለፀገውን ምስራቃዊ የኮንጎ  ክፍል ለመቆጣጠር ከሚሞክሩ ከአንድ መቶ በላይ ታጣቂ ቡድኖች ጎልተው ለመውጣት የቻሉ  ሲሆን ከጎረቤት ሩዋንዳ በመጡ 4ሽህ ወታደሮች እንደሚደገፉም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡  አማፅያኑ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ያለባትን ከተማ ሙሉ በሙሉ ስለመቆጣጠራቸው እስካሁን ግልጽ አልሆነም፡፡ ነገር ግን አመታትን ባስቆጠረው ውጊያ በማእከላዊ ቡካቩ መገኘታቸው ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ መስፋፋት ነው። በጎርጎሪዮሳዊዉ 2012 ከብሄር ግጭት ጋር በተገናኘ በተደረገዉ ጦርነት ጎማን ብቻ ከተቆጣጠሩበት ጊዜ በተለየ በአሁኑ ወቅት አማፂያኑ የፖለቲካ ስልጣንን ለማግኘት ፍላጎት አላቸው ሲሉ ተንታኞች ይናገራሉ።  የአማጽያኑ ወደ ቡካቩ መገስገስ ተከትሎ ብዙ የኮንጐ ወታደሮች ቅዳሜ እለት ከሺህ ከሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ጋር ሲሸሹ ታይተዋል።  የኮንጎው ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ በብዙ ርቀት በምትገኘው ዋና ከተማ ኪንሻሳ የፀጥታ ስብሰባ አካሂደዋል፡  የቡካቩ ከተማ  በኤም 23 «የአጭር ጊዜ» ወረራ የተደረገባት ቢሆንም በኮንጎ ጦር ሰራዊት እና በአካባቢው ሚሊሻ አጋሮች ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ በኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል፡ ዛሬ  በአብዛኛዎቹ የቡካቩ አካባቢዎች ምንም አይነት ውጊያ እንድሌለና  የኮንጐ ሃይሎችም እንዳልታዩ የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ያስረዳል፡፡   

ደቡብ አፍሪካውያን ነጮች ትራምፕን በመደገፍ ሰልፍ አካሄዱ 

አንዳንድ ደቡብ አፍሪካውያን ነጮች ትላንት ቅዳሜ ፕሪቶሪያ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ተሰባስበው ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያላቸውን ድጋፋ  የገለጡ ሲሆን
የአሜሪካ ድምፅ

ደቡብ አፍሪካውያን ነጮች ትራምፕን በመደገፍ ሰልፍ አካሄዱ 

አንዳንድ ደቡብ አፍሪካውያን ነጮች ትላንት ቅዳሜ ፕሪቶሪያ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ተሰባስበው ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያላቸውን ድጋፋ  የገለጡ ሲሆን  በገዛ መንግሥታቸው የዘረኝነት ሰለባ መሆናቸውንም ተናግረዋል።  በመቶዎች የሚቆጠሩት ሰልፈኞቹ  “ለፕሬዚዳንት ትራምፕ ፈጣሪ ይመስገን” የሚል ፅሁፎችን የያዙ እና በደቡብ አፍሪካ መንግስት የታወጀና አናሳ ነጭዎችን ለአድሎ የሚዳርግ የዘረኝነት ህግ ነው ያሉትንም  የሚተቹ ሌሎች መፈክሮችን ይዘው ታይተዋል።  የደቡብ አፍሪካ መንግስት በበኩሉ አዲሱ ህግ ከዘር ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ፕሬዘዳንት ትራምፕ በሀገሪቱ እና በህጉ ላይ ያነሱት ጥያቄ የተሳሳተ መረጃ እና የተዛባ ነው ሲል አስተባብሏል፡፡  የትራምፕ አስተዳደር በደቡብ አፍሪካ ላይ የሰነዘረው ትችት እና ቅጣት በሀገሪቱ ለዘመናት የዘለቀው የአናሳ ነጮች አገዛዝና በጥቁሮች ላይ ያደረሱትን የጭቆና ጥፋቶችን ለመፍታት እየተወሰደ ያለውን ርምጃ አሳሳቢነት ከፍ አድርጎታል፡፡   የደቡብ አፍሪካ መንግሥት እንደሚለው፣ የመሬት ሕጉ  አብዛኛው የእርሻ መሬቶች የአገሪቱ ሕዝብ 7 በመቶው ብቻ በሆኑ ነጮች ባለቤትነት የተያዘውን በእኩልነትና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለማከፋፈል ያለመ ነው፡፡   ነጭ ሰልፈኞች ወረራ ነው ያሉትን  ህግ ጨምሮ በ1994 ከአፓርታይድ ስርዐት ማብቂያ ጀምሮ ለጥቁሮች የቅድሚያ እድሎችን ለመስጠት የተደረጉ ማሻሽያዎችን የሚያመለክቱ ባነሮችን ይዘውም ታይተዋል።  “ብላክ ኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት” በመባል የሚታወቁት እነዚህ ህጎች ለአንዳንድ ነጮች የብስጭት ምክንያት ሆነዋል። 

በኦስትርያ አንድ ሰው ስድስት መንገደኞችን በስለት በመውጋት ጉዳት አደርሰ 

በደቡባዊ ኦስትሪያ የምትገኘው ቪላች ከተማ አንድ ሰው ቀን ላይ ስድስት መንገደኞችን በስለት ወግቶ የ14 አመት ወንድ ልጅ ሲገድል አምስት ሰዎችን ደግሞ አቁስሏል
የአሜሪካ ድምፅ

በኦስትርያ አንድ ሰው ስድስት መንገደኞችን በስለት በመውጋት ጉዳት አደርሰ 

በደቡባዊ ኦስትሪያ የምትገኘው ቪላች ከተማ አንድ ሰው ቀን ላይ ስድስት መንገደኞችን በስለት ወግቶ የ14 አመት ወንድ ልጅ ሲገድል አምስት ሰዎችን ደግሞ አቁስሏል፡፡  ጥቃቱን ያደርሰው የ23 ዓመቱ ተጠርጣሪ ብዙም ሳይቆይ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በኦስትሪያ የመኖሪያ ፍቃድ ያለው ሶሪያዊ እንደሆነ ተገልጿል።   በምግብ አቅራቢ ድርጅት ውስጥ የሚሠራ ሌላ ሶሪያዊ መኪናውን ወደ ተጠርጣሪው በመንዳት ጉዳቱን ለማስቆምና እንዳይባባስ ረድቷል ሲልም ፖሊስ አስታውቋል። የኦስትሪያ ነፃ የሶሪያ ማህበረሰብ ከጥቃቱ ራሱን ያገለለ መግለጫ አውጥቷል።  60ሽህ የሚጠጉ ነዋሪዎች በሚኖሩባት ከተማ ነዋሪዎቹ ጥቃቱ በተፈፀመበት ቦታ ላይ ሻማ አብርተዋል። የኦስትሪያው ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ቫን ደር ቤለን ጥቃቱን “አሰቃቂ” ሲሉ ገልጸውታል፡፡ የኦስትሪያ ነፃ የሶሪያ ማህበረሰብ  በፌስቡክ በጥቃቱ እንደሌለበት በማሳወቅ ለተጎጂ ቤተሰቦች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።  የኦስትሪያ ባለስልጣናት የስለት ጥቃቱን «እስላማዊ የሽብር ክስተት» በማለት ፈርጀውታል። የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጌርሃርድ ካርነር ዛሬ እንደተናገሩት «በዚህ ከተማ ውስጥ ንፁሃን ዜጎችን ያለ ልዩነት በጩቤ በገደለው እስላማዊ ጥቃት አድራሽ  ቁጣ ተሰምቶኛል» ብለዋል።  ካርነር በቪላች ውስጥ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ጥቃት አድራሹ ከእስላማዊ መንግስት ቡድን ጋር ግንኙነት እንደነበረውና እራሱን  በአጭር ጊዜ ውስጥ አክራሪ አድርጎ በቀጥታ ድህረገጾች ሲያቀርብ ነበር ብለዋል፡፡  ይህ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኦስትሪያ ውስጥ ሁለተኛው ገዳይ ጥቃት ነው። እ.ኤ.አ. በህዳር 2020፣ ከዚህ ቀደም እስላማዊ መንግስት ቡድንን ለመቀላቀል የሞከረ አንድ ሰው በቪየና ውስጥ ጥቃት አድርሶ እንደነበረ አሶሼትድ ፕሬስ አስታውሷል፡፡ 

 ታዳጊዎችን የሚያግዘው ማኅበር

በሐረር  ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በቁሳቁስና የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚያግዘው ድንበር የለሽ የሐረር ልጆች ማኅበር ሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ የከተማዋ ተወ
የአሜሪካ ድምፅ

 ታዳጊዎችን የሚያግዘው ማኅበር

በሐረር  ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በቁሳቁስና የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚያግዘው ድንበር የለሽ የሐረር ልጆች ማኅበር ሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ የከተማዋ ተወላጆች የተመሰረተ ነው፡፡ ደግሞ በትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ምገባ ለመጀመር የገንዘብ ድጋፍን እያፈላለገ እንደሚገኝ የማኅበሩ ፕሬዝደንት  ዶክተር ማሾ አብርሃ ተናግረዋል፡፡ ነዋሪነታቸውን በዩናይትድ ስቴትት ጆርጅያ ግዛት ካደረጉት የማኅበሩ ፕሬዝደንት  ዶክተር ማሾ ጋራ ያደረግነውን ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።   

የቡና ዲፕሎማሲ

ኢትዮጵያውያን አንኳር ባህል እና የማኅበራዊ ሕይወት ማድመቂያ የኾነው የቡና አፈላል ሥነ ሥርዐት በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ መሰብሰቢያ አዳራሽ
የአሜሪካ ድምፅ

የቡና ዲፕሎማሲ

ኢትዮጵያውያን አንኳር ባህል እና የማኅበራዊ ሕይወት ማድመቂያ የኾነው የቡና አፈላል ሥነ ሥርዐት በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ መሰብሰቢያ አዳራሽ ለእንግዶች መስተናገጃ ቀርቧል። ከጉባኤው ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ባህል እና ቱሪዝም ሀብቶችን ለተሳታፊዎች የማስተዋወቅ ሥራ እየተከናወነ መኾኑንም የቱሪዝም ሚኒስትር ድኤታ ዶር. እንደገና አበበ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

አፍሪካ ኅብረት በአህጉሪቱ ተፈጽመዋል ላላቸው ቀደምት በደሎች የካሳ ጥያቄ አነሳ

ዛሬ በአዲስ አበባ በተጀመረው 38ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ «የማካካሻ ፍትሕ» ጥያቄ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኗል፡፡ በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያው
የአሜሪካ ድምፅ

አፍሪካ ኅብረት በአህጉሪቱ ተፈጽመዋል ላላቸው ቀደምት በደሎች የካሳ ጥያቄ አነሳ

ዛሬ በአዲስ አበባ በተጀመረው 38ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ «የማካካሻ ፍትሕ» ጥያቄ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኗል፡፡ በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የማካካሻ ጥያቄው “የርዳታ ሳሆን የፍትሕ ጥያቄ ነው” ብለዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ደግሞ “ለማካካሻ ፍትሕ ማዕቀፎች ጊዜው አሁን ነው” ሲሉ ጥያቄው መልስ እንዲያገኝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 8 ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የኅብረቱ ዋና አዳራሽ ሲጀመር፣ እንደ የባሪያ ፍንገላ፣ ቅኝ ግዛት እና አፓርታይድ ላሉ በአህጉሪቱ ለተፈጸሙ ቀደምት ኢ-ፍትሐዊ ተግባራት የማካካሻ ፍትሕ ጥያቄ ማቅረብን ዋነኛ አጀንዳው አድርጓል፡፡ «የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ቃል በተጀመረው በዚህ ጉባኤ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ጥያቄው ፍትሕን የመሻት ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ “የማካካሻ ጥያቄው የበጎ አድራጎት ወይም የገንዘብ ርዳታ ጥያቄ አይደለም» ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ «ስለ ፍትሕ ነው። የሚሊዮኖችን ክብር የመመለስ እና ጥልቅ የሆነ የድህነት፣ የመበላለጥ እና የአድሎ ጠባሳን መፈወስን የሚጠይቅ ነው። በሀብቶቻችን እና ዕድሎቻችን ላይ የሚፈጸመው ስልታዊ ብዝበዛን እንዲቆም ይጠይቃል። በተጨማሪም በአህጉሪቱ ውስጥ ባሉ ማኅበረሰቦች ላይ የተፈጠሩ በደሎችን ለማረም ድፍረት የተሞላበት ርምጃ የሚወሰድበት የለውጥ ሂደት እንዲኖር የሚጠይቅ ነው። ከሁሉም በላይ፣ የማካካሻ ጥሪው የእያንዳንዱን ሰው እኩልነት ለማረጋገጥ ቃላትን ብቻ ሳይሆን ተጨባጭ ድርጊቶችን ይጠይቃል።” ብለዋል። በኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥም፣ የኅብረቱ የካሳ ጥያቄ አግባብ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ “አፍሪካ የሁለት ከባድ እና የተወሳሰቡ ኢፍትሃዊ ድርጊቶች ሰለባ መሆኗን ዓለም መዘንጋት የለበትም።እነዚህም፣ የቅኝ ግዛት እና የአትላንቲክ የባሪያ ንግድ ከፍተኛ ተጽዕኖዎች ናቸው። የእነዚህ ድርጊቶች ሥረ መሰረት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓመታትን ያስቆጠረ ነው፡፡ መራራ ፍሬው ግን አፍሪካውያንን እና ዘርዓ-አፍሪካውያንን እስከ ዛሬ ድረስ እየጎዳ ነው፡፡ ከቅኝ ግዛት መላቀቅ በራሱ መድኃኒት አይደለም። የፖለቲካ ነፃነት፣ ሀገሮችን በብዝበዛ ላይ ከተመሠረቱ መዋቅሮች እና ለበርካታ ዐስርት ዓመታት ከዘለቀው የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና ተቋማዊ የኢንቨስትመንት እጥረት ነፃ አላደረገም። ለማካካሻ ፍትህ ማዕቀፎች ጊዜው አሁን ነው።” ብለዋል። የኅብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በሁለት ቀናት በሚያደርጉት ውይይት በዚሁ የማካካሻ ፍትኅ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚያደርጉ፣ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነት ስፍራን ከሞሪታኒያው ፕሬዝደንት ዛሬ የተረከቡት የአንጎላው አቻቸው ዡዋ ሎሬንሶ ተናግረዋል፡፡ “በዚህ ጉባኤ በብዙ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል» ያሉት ዡዋ ሎሬንሶ "ነገር ግን ለአህጉራችን በጣም አስፈላጊ የሆኑት የአፍሪካ ህብረት የስራ ማዕቀፍ እና ለዚህ ዓመት በመሪ ሃሳብነት የተመረጠውን፣ ለአፍሪካ እና ለትውልደ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትህን ተግባራዊ እንዲሆን የማድረግ ጉዳይ ዋናዎቹ ናቸው” ብለዋል። የማካካሻ ፍትሕ ጥያቄውን በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡን የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪና የፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ሄኖክ ጌታቸው፣ ጠያቄው አሁን ዋና አጀንዳ ቢሆንም ከከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲነሳ የነበረ ነው ብለዋል፡፡ ከማካካሻ ፍትሕ በተጨማሪ፣ የአኅጉሪቱ ፈተና ኾኖ የቀጠለውን የሰላምና ፀጥታ እጦት ጨምሮ፣ የወጣቶች ጥያቄ፣ ትምህርትና ጤናን የመሳሰሉ ጉዳዮችም የውይይት አጀንዳዎች እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡ ተሰናባቹ የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት፣ በአኅጉሪቱ የቀጠሉ ግጭቶች ከሌሎች ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ቀውሶች ጋር ተዳምረው በአብዛኛው የኅብረቱ አባል አገራት ወትሮውንም የነበረውን የደኅንነት ምግብ የጤና እና መሰል ችግሮች እያባባሰ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

የተማሪዎችን የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ግንዛቤ የሚያዳብረው መርሐ ግብር

«ሞዴል ዩኤን» ወይም «አምሳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት»፦ ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ዲፕሎማሲን እንዲማሩ፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የትኩረ
የአሜሪካ ድምፅ

የተማሪዎችን የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ግንዛቤ የሚያዳብረው መርሐ ግብር

«ሞዴል ዩኤን» ወይም «አምሳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት»፦ ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ዲፕሎማሲን እንዲማሩ፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የትኩረት አቅጣጫ በኾኑ የልማት ግቦች ላይ ግንዛቤን እንዲያዳብሩ የሚደረግ የውይይት እና የክርከር መርሐ ግብር ነው፡፡  መርሐ ግብሩ፣ ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ በብዙ ሀገራት የተዘረጋ መድረክ ነው። በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ የኾነው ጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ፣ በየዓመቱ ከልዩ ልዩ የዓለም ክፍሎች ለመጡ ተማሪዎች መርሐ ግብሩን ያዘጋጃል፡፡በዘንድሮው መርሐ ግብር፣ 45 ኢትዮጵያውያን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከባላፈው ቅዳሜ የካቲት አንድ 2017 ዓ.ም አንስቶ ሁለት ሳምንት በሚዘልቀው መርሃግብር ላይ ለሁለተኛ ጊዜ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ የመርሐ ግብሩ አስተባባሪ፣ በትምህርት ላይ የሚሠራው «ኦል ፋውንዴሽን» ሲኾን፣ የተቋሙ መሥራች እና የቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ ኑርሑሴን ሐሰን ሑሴን፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርገዋል፡:

የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾኑ

ጅቡቲን ለብዙ ዓመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ ቀጣዩ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾነው ተመረጡ። ‘ አዲስ አበባ ውስ
የአሜሪካ ድምፅ

የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾኑ

ጅቡቲን ለብዙ ዓመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ ቀጣዩ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾነው ተመረጡ። ‘ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጽሕፈት ቤት እየተካሔደ ባለው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ፣ መሪዎቹ በሚስጥር በሰጡት ድምጽ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ኮሚሽኑን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ ተመርጠዋል። ኮሚሽኑን እንዲመሩ በሊቀመንበርነት የተመረጡት የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በተካሔደውና ብርቱ ፉክክር በታየበት፣ እንዲኹም እስከ ሰባተኛ ዙር ድረስ በዘለቀ ምርጫ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ አግኝተው ነው። ከሳምንት በፊት 60ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ያከበሩት ዩሱፍ፣ በምርጫው አሸናፊ የኾኑት የኬንያውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን በማሸነፍ ነው። ዩሱፍ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዙሮች በ18 እና በ19 ድምፅ አግኝተው ከራኢላ ጋራ በተቀራረበ ሁኔታ ሁለተኛ ዙር ላይ ነበሩ። ከሦስተኛው ዙር ጀምሮ በተካሔዱት የድምጽ አሰጣቶች ግን ዩሱፍ በመሪነት ቀጥለዋል። በመጨረሻም ለአሸናፊት የሚያበቃው 33 ድምጽ በማግኘት የመሪነቱ ቦታ ተረክበዋል። አዲሱ የኅብረቱ ተመራጭ ኮሚሽነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር፣ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኾነው አገልግለዋል። በአፍሪካ አህጉር ረዥም ጊዜ ያገለገሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ናቸው።  ከኅብረቱ ከታገዱት ስድስት ሀገራት በስተቀር 55ቱም የአባል ሀገራት በ38ኛው የኅብረቱ መሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጭ ለቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት እንደተናገሩት፣ 29 ፕሬዝዳንቶች ፣ ሦስት ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ አራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች እና አንድ ንጉስ በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል። ከአፍሪካ ኅብረት አባልነት የታገዱት ስድስቱ ሀገራት ቡርኪናፋሶ፣ጋቦን፣ጊኒ፣ማሊ፣ኒጀር እና ሱዳን ናቸው። የዘንድሮው የመሪዎች ጉባኤ በመካሔድ ላይ የሚገኘው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት እየተባባሰ ባለበት ወቅት አማጽያን በምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍሎች እየገሰገሱ ባሉበት ወቅት ነው። የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች አስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል። መሪዎቹ ሊወያዩበት ያቀዱት ሌላው የግጭቱ ዋና ማዕከል ሱዳን ናት። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ ተፋላሚ ወገኖች ጦርነቱን እንዲያቆሙ እና የሰብአዊ አገልግሎት ሠራተኞች እና ሲቪሎችን ደኅንነት እንዲጠብዙ ጥሪ አቅርበዋል። ጉቴሬዥ 26 ሚሊዮን ለሚጠጉ አስቸኳይ ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሱዳናውያን ዜጎች 6 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ጠይቀዋል።

Get more results via ClueGoal