ሃማስ ተጨማሪ እስራኤላውያን ታጋቾችን ለቀቀ
newsare.net
የተኩስ አቁም ስምምነቱ አካል በሆነው የታጋቾችና እስረኞች ልውውጥ ሁለት እስራኤላውያን ታጋቾች ዛሬ አስቀድመው የተለቀቁ ሲሆን ሌሎች ሶስት ታጋቾች ደግሞ ቆይሃማስ ተጨማሪ እስራኤላውያን ታጋቾችን ለቀቀ
የተኩስ አቁም ስምምነቱ አካል በሆነው የታጋቾችና እስረኞች ልውውጥ ሁለት እስራኤላውያን ታጋቾች ዛሬ አስቀድመው የተለቀቁ ሲሆን ሌሎች ሶስት ታጋቾች ደግሞ ቆይተው ተለቀዋል፡፡ በዚህ ምትክም በመቶ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞች የሚለቀቁ ይሆናል፡፡ ከጋዛ አርብ የተመለሰው አስከሬንም የታጋች ሺሪ ቢባስ መሆኑም ተረጋግጧል፡፡ አስቀድመው ከተለቀቁት ታጋቾች መካከል የ40 አመቱ ታል ሾሃም፣ እአአ ጥቅምት 7፣ 2023 ሃማስ በእስራኤል ላይ ባደረሰው ጥቃት ከኪቡትዝ ቢኤሪ ታግቶ የተወሰደ ሲሆን ሁለተኛው የ39 አመቱ አቬራ መንግስቱ ደግሞ ከአስር አመት በፊት ብቻውን ወደ ጋዛ ገብቶ የነበረ ነው፡፡ ታጋቾችን ሃማስ ዛሬ ቅዳሜ ረፋድ ላይ በጋዛ ራፋህ ከተማ ለቀይ መስቀል አስረክቧቸዋል፡፡ በርክክቡ ወቅት አውቶማቲክ መሳሪያ የያዙ እና ወታደራዊ ልብስ የለበሱ የሃማስ ተዋጊዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዝናባማ በሆነው የአየር ሁኔታ ራፋህ አደባባይ ላይ ቁመው ታይተዋል፡፡ ሃማስ ቆይቶም የ27 ዓመቱን ኤሊያ ኮኸን፣ የ22 አመቱ ኡመር ሸህም ቶቨ እና የ23 አመቱ ኡመር ዌንከርት የተባሉ ሶስት እስራኤላውያን ታጋቾችን ለቋል፡፡ ኮኸን፣ ቶቭ እና ዌንከርት እአአ ጥቅምት 7፣ 2023 በአሜሪካ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ባደረሰበት ወቅት ከሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ አግቶ የወሰዳቸው ናቸው፡፡ በቴል አቪቭ የእስራኤልን ባንዲራ የሚያውለበልቡ እና የታጋቾቹን ምስል የያዙ ሰዎችም የታጋቾችን መለቀቅ በቪድዮ ሲከታተሉና ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል፡፡ በተለቀቁት ታጋቾች በምትኩ እስራኤል ከ600 በላይ ፍልስጤማውያንን እስረኞችን ትፈታለች። ሌላ አንድ ታጋች ዛሬ አመሻሽ ላይ ይለቀቃ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን አጠቃላይ የተለቀቁት ስድስቱ ታጋቾችም በመጀመሪያው ምዕራፍ የተኩስ አቁም ወቅት ነፃ የሚወጡት የመጨረሻዎቹ ታጋቾች ይሆናሉ ተብሎም ይጠበቃል። Read more