የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አማፂያን ከያዟቸው የኮንጐ ከተሞች እንዲወጡ ጠየቀ
newsare.net
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በምስራቃዊ ኮንጎ የሚገኘው የኤም 23 አማፅያን ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም እና ከያዛቸው ግዛቶች እንዲየተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አማፂያን ከያዟቸው የኮንጐ ከተሞች እንዲወጡ ጠየቀ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በምስራቃዊ ኮንጎ የሚገኘው የኤም 23 አማፅያን ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም እና ከያዛቸው ግዛቶች እንዲወጣ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ትላንት አርብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ምክር ቤቱ ግጭቱን በሚያራዝሙ አካላት ላይ ማዕቀብ እንደሚጣልባቸውም ዝቷል። የወሳኔ ሃሳቡን ረቂቅ ያዘጋጀችው ፈረንሣይ በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ለተፈጠረው ግጭት ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ ግልጽ መልዕክት ያስተላለፈ ነው ስትል አስታውቃለች፡፡ «ቅድሚያ የሚሰጠው ውጤታማ፣ ቅድመ ሁኔታ የሌለው እና አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ነው» ሲሉ አምባሳደር ኒኮላ ዴ ሪቪየር ተናግረዋል። በቀጠናው ደረጃ የሚደረጉ የማሸማገል ጥረቶችና ውይይቶች አስፈላጊነት የገለጡት አምባሳደሩ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መከበር አለበት ብለዋል፡፡ የውሳኔ ሃሳቡ የሩዋንዳ መከላከያ ሰራዊት ለኤም 23 የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቆም እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግዛት በአስቸኳይ እንዲወጣ ይጠይቃል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት የሩዋንዳ መከላከያ ሰራዊት ለኤም 23 “ቀጥታ ድጋፍ” ያደርጋል ሲሉ ከሰዋል። ሩዋንዳ አማፂያኑን ትደግፋለች የሚለውን ውንጀላ ደጋግማ ስታስተባብል ቆይታለች። የፀጥታው ምክር ቤት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሩዋንዳ «ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች በአስቸኳይ እንዲመለሱም» አሳስቧል። Read more