የኮንጎ ፕሬዝዳንት 'የአንድነት መንግስት' እመሰርታለሁ አሉ
newsare.net
በምስራቃዊው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት እየተባባሰ በሄደበት ወቅት በቀውሱ አያያዝ ዙሪያ የሚሰነዘርባቸው ትችት እየጨመረ የሄደው የኮንጎ ፕሬዝዳንትየኮንጎ ፕሬዝዳንት 'የአንድነት መንግስት' እመሰርታለሁ አሉ
በምስራቃዊው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት እየተባባሰ በሄደበት ወቅት በቀውሱ አያያዝ ዙሪያ የሚሰነዘርባቸው ትችት እየጨመረ የሄደው የኮንጎ ፕሬዝዳንት፣ የአንድነት መንግስት እንደሚመሰርቱ አስታወቁ። የኤም 23 አማፂያን በምስራቃዊ ኮንጎ የሚገኙ ዋና ዋና ከተሞችን ከተቆጣጠሩ በኃላ፣ ትላንት ቅዳሜ ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር ያደረጉት የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ሀገሪቱን ለሚያስተዳድረው ጥምር ፓርቲ በውስጣዊ ግጭቶች እንዳይዘናጉ አሳስበዋል። «በትግሉ ነው እንጂ በጦርነቱ አልተሸነፍኩም » ያሉት ፕሬዳንቱ «ሁሉንም ተቃዋሚዎች ማነጋገር አለብኝ። የብሔራዊ አንድነት መንግስት ይመሰረታል» ብለዋል። ይህ ጥምር መንግስት ምን ሊመስል እንደሚችል ወይም መቼ እንደሚፈፀም ግን ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። በምስራቅ ኮንጎ የበላነት ለማግኘት ከሚፎካከሩ ከመቶ በላይ ታጣቂ ቡድኖች መካከል ከፍተኛ ኃይል ያላቸው የኤም23 አማፂያን፣ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በመግደል ትልቁን ከተማ ጎማን ጨምሮ አብዛኛውን ምስራቃዊ ክፍል ተቆጣጥረዋል። ሺሴኬዲ ቅዳሜ እለት ባደረጉት ንግግር በጦርነቱ ህይወታቸው ላጡ ወታደሮች ምስጋና አቅርበው ጦሩን ለመደጋፍ ቃል ገብተዋል። የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት የኤም 23 አማፂ ቡድንን በአሸባሪነት የፈረጀ ሲሆን ሩዋንዳ ለቡድኑ ድጋፍ ትሰጣለች ሲልም ይከሳል። ሩዋንዳ በበኩሏ ክሱን አትቀበልም። Read more