የሱዳን ጦር የበላይነት እያገኘ መኾኑን አስታወቀ
newsare.net
የሱዳን ጦር ከአንድ ዓመት በላይ በከበባ ስር የቆየውን ኦቤይድ የተሰኘ ቁልፍ ከተማ ማስለቀቁን፣ ወደ ደቡብ ማዕከላዊ ክልል መድረስ የሚያስችለው ስልታዊ አካባየሱዳን ጦር የበላይነት እያገኘ መኾኑን አስታወቀ
የሱዳን ጦር ከአንድ ዓመት በላይ በከበባ ስር የቆየውን ኦቤይድ የተሰኘ ቁልፍ ከተማ ማስለቀቁን፣ ወደ ደቡብ ማዕከላዊ ክልል መድረስ የሚያስችለው ስልታዊ አካባቢ መያዙን እና ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል ጋራ እያደረገ ላለው ጦርነት ወሳኝ የአቅርቦት መንገዶችን ማጠናከሩን አስታወቀ። የጦሩ ቃል አቀባይ ብርጋዴን ጀነራል ናቢል አብዱላህ በሰጡት መግለጫ፣ ወታደሮቹ በፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች ስር የነበረውን የነጭ አባይ ጠንካራ ይዞታ ማስለቀቅ መቻላቸውን እና ይህም የተቀናቃኙን ኃይል ያመናመነ መኾኑን ገልጸዋል። አብዱላህ አክለው አል-ሳይድ ውስጥ የሚገኘው የሀገሪቱ ጦር ወደ ኦቤይድ የሚወስደውን መንገድ መክፈቱን እና ፈጥኖ ደራሹ በሰሜናዊ ኮርዶፋን ክልል ዋና ከተማ ላይ ያካሄደው ከበባ ማብቃቱን አብራርተዋል። ከተማዋ የተንጣለለ ወታደራዊ የአየር ማረፊያ እና ሃግና ተብሎ የሚጠራው አምስተኛ ወታደራዊ የጦር ሰፈር የሚገኝበት ነው። የንግድ እና የትራንስፖርት ማዕከል የሆነችው ኦቤይድ፣ የደቡብ ዳርፉር ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን ኒያላን ከካርቱም ጋራ የሚያገናኘው የባቡር ሃዲድም የሚገኝባት ሲሆን እ.አ.አ በሚያዚያ 2023 ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ስር ቆይታለች። የሀገሪቱ ገንዘብ ሚኒስትር ጂብሪል ኢብራሂም ጦሩ በኦቤይድ ያገኘውን ድል «ትልቅ ርምጃ» ሲሉ አወድሰዋል። Read more