የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አሜሪካና ዩክሬን በተናጥል ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ ላይ ድምፅ ይሰጣል
newsare.net
በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ማስቆም በተመለከተ፣ በአንድ ወገን በአሜሪካ በሌላ ወገን ደግሞ በዩክሬን ተረቀው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤየተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አሜሪካና ዩክሬን በተናጥል ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ ላይ ድምፅ ይሰጣል
በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ማስቆም በተመለከተ፣ በአንድ ወገን በአሜሪካ በሌላ ወገን ደግሞ በዩክሬን ተረቀው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የቀረቡ የውሳኔ ሐሳቦች ዛሬ ሰኞ ድምፅ እንደሚሰጥቸው ይጠበቃል። ጠቅላላ ጉባኤው በቅድሚያ በዩክሬን በቀረበውና በአውሮፓ ኅብረት በሚደገፈው ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምፅ እንደሚሰጥ ሲጠበቅ፣ በመቀጠል ደግሞ በአሜሪካ በቀረበው ላይ ድምፅ ይሰጣል። የድርጀቱ የፀጥታው ምክር ቤት ደግሞ በተናጥል በአሜሪካ በቀረበው ረቂቅ ላይ ድምጽ ይሰጣል ተብሏል። አሜሪካ “ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆምና በዩክሬንና በሩሲያ መካከል ዘላቂ ሠላም እንዲመጣ ጥሪ አድርጋለች” ያለው የሮይተርስ ዘገባ፣ የአሜሪካው ረቂቅ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን አያመለክትም ብሏል። የውሳኔ ሐሳቡ “ግጭቱ አሰቃቂ መሆኑን፣ ግጭቱን ለማቆም ደግሞ ተመድ ሊረዳ እንዳሚችል፣ ሠላምንም ማስፈን እንደሚችል ያሳያል” ሲሉ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ማክሮ ሩቢዮ ባለፈርው ዓርብ ተናግረዋል። ጠቅላላ ጉባኤው ያቀረበችውን የውሳኔ ሐሳብ እንዲያፀድቅ እንዲሁም በዩክሬንና በአውሮፓ አጋሮቿ የቀረበውን ሐሳብ ውድቅ እንዲያደርግ አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ መልዕክት ማስተላለፏንና ይህንኑም መመልከቱን ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል። በዩክሬን የቀረበው ረቂቅ ደግሞ ጠቅላላ ጉባኤው ከዚህ በፊት የደረሰበት የውሳኔ ሐሳብ ተግባራዊ እንዲሆን ይጠይቃል። ይህም ሩሲያ በዓለም እውቅና ከተሰጠው የዩክሬን ድንበር ሙሉ ለሙሉ እንድትወጣ የሚጠይቀውን ይጨምራል። የጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔዎች ተፈጻሚነት ሕጋዊ ግዴታ የሌለባቸው ቢሆኑም፣ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ሞራላዊ ጫና እንዲፈጠር ሊያደርጉ ግን ይችላሉ። በፀጥታው ምክር ቤት አንድ የውሳኔ ሐሳብ ለማለፍ ከ15 ዓባላት ውስጥ ቢያንስ የዘጠኙ ድጋፍ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ ከቋሚ ዓባላት ውስጥ ማለትም ከእንግሊዝ፣ ቻይና፣ ፈረንሣይ፣ ሩሲያ ወይም አሜሪካ አንዳቸው ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸን ሊጠቀሙ ይችላሉ። የአሜሪካው የውሳኔ ሐሳብ በቂ ድጋፍ ሊያገኝ እንደሚችል ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል። Read more