በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የድሮን ጥቃት ሲቪል ነዋሪዎች መሞታቸው ተገለጸ
newsare.net
በዐማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ «አነገሽ» ቀበሌ “ኀሙስ ገበያ” በተባለ ስፍራ፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም.በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የድሮን ጥቃት ሲቪል ነዋሪዎች መሞታቸው ተገለጸ
በዐማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ «አነገሽ» ቀበሌ “ኀሙስ ገበያ” በተባለ ስፍራ፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም. ተያይዘው በተሠሩ የንግድ ቤቶች ላይ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት፣ ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን፣ የሟች ቤተሰቦች እና የዐይን እማኞች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። በገበያው ዳር ኳስ ሲጫወት የነበረ የ15 ዓመት ልጃቸው በጥቃቱ መገደሉን የተናገሩት ወይዘሮ ታንጉት የተባሉ እናት፣ የስምንት ዓመት ልጃቸውም ቆስሎ በሆስፒታል እንደሚገኝ ገልጸዋል። የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ የኔዋ ደመቀ ግን፣ ጥቃቱ በሲቪል ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ ሳይኾን፣ “ጽንፈኛ” ሲሉ በጠሩት ቡድን ላይ የተፈጸመ እንደኾነ ገልጸው አስተባብለዋል። ጥቃቱም የተፈጸመው፣ ታጣቂው ኀይል እንደ ካምፕ እየተጠቀመበት ባለው ትምህርት ቤት ላይ እንጂ የንግድ ሱቆች ላይ አይደለም፤ ሲሉ አመልክተዋል። በአንጻሩ፣ በጥቃቱ መጎዳታቸውን የገለጹና የተጎጂዎችን አስከሬን ሰብስበናል ያሉ የስፍራው ነዋሪዎች፣ ጥቃቱ በሲቪሎች ላይ የተፈጸመ ነው፤ ብለዋል። የዐይን እማኞቹ እንደሚሉት፣ በዕለቱ ሰባት የሚደርሱ ሟቾችን ቀብር፣ በከተማው ውስጥ በሚገኝ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አከናውነዋል። አብዛኛዎቹ ተጎጂዎችም፣ ከገጠር ቀበሌዎች ቆርቆሮ ለመግዛት ተሰባስበው የመጡ ንጹሓን ናቸው፤ ብለዋል። ጥቃቱ የተፈጸመበት የአነገሽ ቀበሌ ኀሙስ ገበያ አካባቢ፣ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በፋኖ ታጣቂ ኀይሎች ቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ፣ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል። Read more