በኢትዮጵያ በሬክተር መለኪያ 5.3 የተመዘገበ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሠተ
newsare.net
«ክሥተቱ ያዝ ለቀቅ እያደረገ መቀጠሉ መዘናጋትን በመፍጠሩ ሁልጊዜ መዘጋጀት ያስፈልጋል» - ፕር. አታላይ አየለ በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከምበኢትዮጵያ በሬክተር መለኪያ 5.3 የተመዘገበ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሠተ
«ክሥተቱ ያዝ ለቀቅ እያደረገ መቀጠሉ መዘናጋትን በመፍጠሩ ሁልጊዜ መዘጋጀት ያስፈልጋል» - ፕር. አታላይ አየለ በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከምትገኘው ጭሮ ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፣ ትላንት እሑድ፣ የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ሌሊት የተከሠተው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ በሬክተር ስኬል 5ነጥብ3 ኾኖ መመዝገቡን፣ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ተቋም አስታውቋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዲሬክተር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ አኹንም የመሬት መንቀጥቀጡ ዋና ምንጭ ፈንታሌ አካባቢ ነው። የመሬት መንቀጥቀጡ እየተፈጠረ ያለውም፣ ቅልጥ አለት እየሰረሰረ ወደ ላይ ለመውጣት በሚያደርገው ሙከራ ነው፤ ሲሉም ዳይሬክተሩ አብራርተዋል። ትላንት እሑድ፣ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 8:45 ላይ የተከሠተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት፣ አዲስ አበባ ውስጥ ጭምር መሰማቱን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል። የመሬት መንቀጥቀጡ፣ በተለይ በአንዳንድ የከተማዋ ስፍራዎች የፈጠረው ንዝረት፣ በመኖሪያ ሕንጻዎች ላይ ንቅናቄ መፍጠሩን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል። ባለፈው ጥር ወር፣ ከዘርፉ ባለሞያዎች ጋራ ውይይት ያደረጉት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ርእሰ መዲናዪቱ ካላት የመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭነት አንጻር፣ ተገቢ የጥንቃቄ ጥናቶችን የሚያደርግ የባለሞያዎች ግብረ ኀይልን በማደራጀት በጋራ ለመሥራት ከስምምነት ላይ መደረሱን መግለጻቸው ይታወሳል። ክሥተቱ ያዝ ለቀቅ እያደረገ መቀጠሉ መዘናጋት መፍጠሩን የጠቀሱት ፕሮፌሰር አታላይ፣ እስከ አኹን መሬት ላይ የወረደ ነገር አለመኖሩን አመልክተዋል። የተፈጥሮ አደጋ «አማክሮ ስለማይመጣ»፣ መደረግ ያለበትን ዝግጅት ሁልጊዜ በተጠንቀቅ ማድረግ እንደሚያስፈልግም፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዲሬክተሩ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ አሳስበዋል። Read more