Ethiopia



ትረምፕ ከፈረንሳዩ መሪ ጋር በዩክሬን ዕጣ ፈንታ ላይ ተወያዩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም፣ ከዩክሬን እና ከሩሲያ ጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸውን ተና

የዩናይትድ ስቴትስ ዳኛ ትራምፕ ኤፒ የዜና ተቋም ከዋይት ሃውስ እንዳይዘግብ የጣሉትን ገደብ አፀና

ዋሽንግተን — አሶሽየትድ ፕሬስ (ኤፒ) የዜና ተቋም በዘገባዎቹ የሜክሲኮ ባህረሰላጤ የሚለውን ስያሜ መጠቀም በመቀጠሉ በዋይት ሀውስ ተገኝቶ እንዳይዘግብ በፕሬ
የአሜሪካ ድምፅ

የዩናይትድ ስቴትስ ዳኛ ትራምፕ ኤፒ የዜና ተቋም ከዋይት ሃውስ እንዳይዘግብ የጣሉትን ገደብ አፀና

ዋሽንግተን — አሶሽየትድ ፕሬስ (ኤፒ) የዜና ተቋም በዘገባዎቹ የሜክሲኮ ባህረሰላጤ የሚለውን ስያሜ መጠቀም በመቀጠሉ በዋይት ሀውስ ተገኝቶ እንዳይዘግብ በፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የተጣለበት ገደብ እንዲነሳለት ያቀረበው ጥያቄ በአንድ ፌደራል ዳኛ ውድቅ ተደረገ። በፕሬዝደንት ትራምፕ የተሰየሙት የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት ዳኛ ትሬቨር ሚክፋደን፣ ኤፒ የፍርድ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ« ኦቫል ኦፊስ» በተሰኘው የፕሬዝደንቱ ጽሕፈት ቤት ፣ በፕሬዝደንቱ አውሮፕላን (ኤር ፎርስ ዋን) እና ሌሎች በዋይት ሀውስ የሚከናወኑ ዝግጅቶች ላይ ተገኝቶ የመዘገብ መብቱ እንዲመለስ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል። ሚክፋደን በውሳኔያቸው ፕሬዝዳንቱ «ግላዊ በኾኑ አካባቢዎች» ላይ የጣሉት ገደብ፣ ከዚህ ቀደም ፍርድቤቶች የመንግሥት ባለሥልጣናት በጋዜጠኞች ላይ የተጣሉትን ገደቦችን ካነሱባቸው ሁኔታዎች የተለየ ነው ብለዋል። በፍርድ ሂደቱ ላይም «ኤፒ ለስኬት የሚያበቃ ሁኔታ አሳይቷል ማለት አልችልም» ብለዋል። ዳኛው አክለው ዋይት ሀውስ በኤፒ የዜና ሽፋን ምክንያት አድሎ መፈፀሙን ተናግረዋል። ችግር የሚፈጥር ሁኔታ መሆኑንም ገልጸዋል። የዳኛውን ውሳኔ ተከትሎ ዋይት ሀውስ ባወጣው መግለጫ «የዩናይትድ ስቴትስን ፕሬዝደንት በቢሮዋቸው እና በአውሮፕላናቸው ተገኝቶ መጠየቅ ለጋዜጠኞች የተሰጠ ልዩ መብት እንጂ ሕጋዊ ግዴታ አይደለም» ብሏል። የኤፒ ቃል አቀባይ በበኩላቸው የዜና ተቋሙ «ለፕሬስ እና ለሕዝብ ያለመንግሥት አፀፋ በነፃነት የመናገር መብት መቆሙን እንደሚቀጥል» ገልጸዋል። ኤፒ ባለፈው ሳምንት አርብ በሦስት ከፍተኛ የትራምፕ ረዳቶች ላይ ክስ የመሰረተው፤ ዘጋቢዎቹ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ተገኝተው እንዳይዘግቡ የተላለፈው ውሳኔ በዩናይትድ ስቴትስ ሕገ መንግስት የመጀመሪያ የማሻሻያ አንቀፅ ላይ የተደነገገውን በመጣስ፣ መንግሥት በዜና ዘገባ ውስጥ የሚጠቀመውን ቋንቋ የሚያስገድድ እና የንግግር መብትን የሚገድብ ነው በማለት ነው። የኤፒ ጠበቃ ቻርስ ቶቢን በችሎት ቀርበው ባስረዱበት ወቅትም «ሕገ መንግሥቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንትም ኾኑ ሌላ የመንግሥት ባለሥልጣን ጋዜጠኞችንንም ኾነ ሌላ አካል፣ የመንግሥትን ቋንቋ በመጠቀም ዜና እንዲዘግቡ ከማድረግ ይከለክላል» ብለዋል። የትራምፕ አስተዳደር ጠበቆች በበኩላቸ ኤፒ «ፕሬዝዳንቱ ጋራ የመግባት ልዩ የሚዲያ ፈቃድ» የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል። ትራምፕ ባለፈው ወር የሜክሲኮ ባህረሰላጤ የአሜሪካ ባህረሰላጤ በሚለው ስምን እንዲተካ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ አስተላልፈው የነበረ ሲሆን፣ ኤፒ የትራምፕን ውሳኔ በመጥቀስ የባህረሰላጤውን የቆየ ስም መጠቀም እንደሚቀጥል ገልጿል። በምላሹ የኤፒ ጋዜጠኞች በዋይት ሀውስ ተገኝተው እንዳይዘግቡ እገዳ ተጥሎባቸዋል።

የመከላከያ ምኒስትሩ የኤታማዦር ሹሞቹ ሰብሳቢ ከሥራቸው የተባረሩበትን ምክንያት አስረዱ

የአሜሪካው የመከላከያ ምኒስትር ፒት ሄግሴት፣ የኤታማዦር ሹሞች ቡድን ሰብሳቢ የሆኑት ሲ ኪው ብራውን ከሥራቸው የተባረሩበትን ምክንያት ባለፈው ሳምንት መጨረ
የአሜሪካ ድምፅ

የመከላከያ ምኒስትሩ የኤታማዦር ሹሞቹ ሰብሳቢ ከሥራቸው የተባረሩበትን ምክንያት አስረዱ

የአሜሪካው የመከላከያ ምኒስትር ፒት ሄግሴት፣ የኤታማዦር ሹሞች ቡድን ሰብሳቢ የሆኑት ሲ ኪው ብራውን ከሥራቸው የተባረሩበትን ምክንያት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አስረድተዋል። ባለፈው ዓርብ ነበር ፕሬዝደንት ትረሞፕ የኤታማዦር ሹሞቹን ሰብሳቢ ከሥራቸው ማንሳታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ያስታወቁት፡፡ የቪኦኤ የፔንታገን ዘጋቢ ካርላ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የኢትዮጵያን የታዳሽ ኀይል ሀብት ወደ ዶላር የሚቀይረው የቢትኮይን አሠሣ 

በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉን የክሪፕቶ ከረንሲ መገበያያ ዓይነቶች መካከል አንዱ የኾነውን የቢትኮይን ማይኒንግ ወይም በግርድፍ ትርጉሙ በይ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያን የታዳሽ ኀይል ሀብት ወደ ዶላር የሚቀይረው የቢትኮይን አሠሣ 

በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉን የክሪፕቶ ከረንሲ መገበያያ ዓይነቶች መካከል አንዱ የኾነውን የቢትኮይን ማይኒንግ ወይም በግርድፍ ትርጉሙ በይነ መረብ አሠሣ (ፍለጋ) በመጀመር ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ኾነች።አገሪቱ፣ ባለፉት 15 ዓመታት በገነባቻቸው የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኀይል ማመንጫ ግድቦች አማካይነት ከፍተኛ የኀይል አቅርቦት ቢኖራትም፤ የኤሌክትሪክ ኀይሉን ለተጠቃሚው ሕዝብ እና ለሚፈለገው ግልጋሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ዐቅም አለመገንባቷን ባለሞያዎች ይናገራሉ። ይህን ክፍተት በመጠቀም፣ ከ22 በላይ የሚደርሱ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት፣ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኀይል አቅርቦት የሚሻውን የቢትኮይን ማይኒንግ ወይም በይነ መረባዊ አሠሣ ሥራ ጀምረዋል። ከዚኽም ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ከዘርፉ 55 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች። የያዝነው የ2017 ዓ.ም ሲጠናቀቅ ደግሞ፣ 123 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደምታገኝ፣ የዓለም አቀፍ የገበያ ትንተና ገጽ የኾነው Nasdaq ትንበያ ይጠቁማል። በኢትዮጵያ፣ በክሪፕቶ ከረንሲ ዓይነቶች ለመገበያየት፣ አኹንም ድረስ የሕግ ማሕቀፍ ስላልተበጀለት ክልክል ቢኾንም፣ ቢትኮይንን ፈልጎ የማግኘት ሥራ ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ፈቃድ መስጠት ተጀምሯል። ይኹን እንጂ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን የኀይል ፍላጎት በተፈላጊው መጠን ሟሟላት ስለመቻሉ ጥርጣሬዎች ይነሣሉ። በጎርጎርሳውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2008፣ ሳቶቺ ናካሞቶ በሚል የብዕር ስም በሚታወቅ የቴክኖሎጂ  ባለሞያ የተፈለሰፈው ቢት ኮይን፣ ሰዎች በማናቸውም ሰዓት፣ በየትኛውም የዓለም ክፍል፣ ያለባንክ እና ያለምንም የገንዘብ መተመኛ ለመገበያየት የሚያስችል ሲኾን፣ በበይነ መረብ ላይ ባለቤቱ በሚመሠርተው የምስጢር ቁልፍ ብቻ የሚንቀሳቀስ ነው። መሥራቹ ሳታቺ ናካሞቶ፣ በቁጥር የተወሰኑ ቢትኮይኖችን፣ ኮድ ባላቸው ቁልፎች በመቆለፍ ሰዎች አሥሠው በማግኘት እንዲጠቀሙባቸው ለቋል።  በኢትዮጵያ ፈቃድ አውጥተው የቢትኮይን ማይኒንግ ወይም ፍለጋ ከጀመሩ ተቋማት መካከል ቀዳሚ የሆነው፣ QRB ላብስ ተቋም መሥራች ነሞ ሥምረት፣ አገሪቱ የምታመርተውን የኤሌክትሪክ ኀይል አቅርቦት ተደራሽ የሚያደርግ መሠረተ ልማት አለመኖሩን ጠቅሶ፣ በቢትኮይን አሠሣ፥ በግድቦቹ የሚባክነውን የኤሌክትሪክ ኀይል አገሪቱ ወደ ዶላር እንድትለውጥ ያግዛል፤ ይላል። በአኹን ሰዓት አንድ ቢትኮይን፣ በዓለም ገበያ ላይ እስከ 90ሺሕ የዩናይትድ ስቴትስ ዶላር ይተመናል። ይኹን እንጂ፣ አንድን ቢትኮይን አሥሦ ለማግኘት 155 ሺሕ ኪሎዋት የሚኾን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ያስፈልጋል። ይህ አኀዝ በኢትዮጵያ 1ሺሕ33 መኖሪያ ቤቶችን ለማብራት ያስችላል። እ.ኤ.አ በ2023፣ 50ሺሕ 294 ኪሎ ቶን የኤሌክትሪክ ኀይል  መጠቀሟን፣ ኢንተር ዳታ የተሰኘ ተቋም ድረ ገጽ አመላክቷል። በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ማዕከል በኾነው ሲልከን ቫሊ ባለሞያ የኾነው ቃል ካሳ፣ በኢትዮጵያ ክርፕቶ ከረንሲ እና የቢትኮይን አሠሣ ምን እንደ ኾኑ፣ ወጣቶች እና ፖሊስ አውጭዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይሠራል። ለብዙዎች በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግተውን ፅንሰ ሐሳብ ለአሜሪካ ድምፅ አብራርቷል። ኢታን ቬራ፣ መቀመጫውን በሲያትል ዋሺንግተን ያደረገውና ኢትዮጵያን ጨምሮ በልዩ ልዩ የዓለም ክፍሎች፣ ለቢት ኮይን አምራች ተቋማት የሶፍትዌር እና የማሽን አቅርቦትን የሚያመቻቸው የሉግዘር ቴክ ባልደረባ ነው፤ በኢትዮጵያ ከሚገኙ አሣሽ ድርጅቶችም ጋራ አብሮ ይሠራል። ኢትዮጵያ በታዳሽ ኀይል ማመንጨት ኀይሏ ተመራጭ ኾናለች፤ ይላል። ኢታን ቬራ፣ ቢትኮይን፥ የአገሪቱን ሕዝብ የኀይል አቅርቦት እየተሻማ ይኾን እንደኾን፣ በአሜሪካ ድምፅ ለቀረበለት ጥያቄ፤ በኢትዮጵያ  የሚመነጨው ኀይል በተገቢው መንገድ ለማኅበረሰቡ ተደራሽ አለመኾኑን ጠቅሶ፣ በቢትኮይን ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ተቋማት የኀይል መጠኑ ሳይባክን አገሪቱ ገቢ እንድታገኝ በማስቻል እያገዙ ነው፤ ይላል። አብዛኛዎቹ በቢት ኮይን አሠሣ እና ዝላይ የተሰማሩ ተቋማት፣ ድርጅቶቻቸውንና ማሽኖቻቸውን በኀይል አመንጪ ግድቦች አቅራቢያ እንደሚተክሉ ኢታን ቬራ ይናገራል። በአንድ እና በሁለት ሰው የሚሠራውና እምብዛም የሥራ ዕድል ፈጠራ ዐቅም የሌለው የቢት ኮይን አሠሣ ሥራ፣ አገሪቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ በማድረግ ስኬታማ ኾኗል። አገሪቱ፣ ባለፈው ዓመት ብቻ 55 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ስታደርግ፤ የያዝነው የ2017 ዓ.ም ሲጠናቀቅ 123 ሚሊየን ዶላር ገቢ እንደምታገኝ፣ የዓለም አቀፍ የገበያ ትንተና ገጽ የኾነው Nasdaq ተንብይዋል። ይኹን እንጂ፣ ማሽኖችን በማስገባት እና ከተቋማት ጋራ ሥራን በማሳለጥ፣ ተግዳሮቶች እና መጓተቶች እንደነበሩ፣ የQRB ላብስ መሥራች ነሞ ሥምረት ተናግሯል። የለግዘር-ቴክ ሥራ አስፈጻሚ ኢታን ቬራም፣ አገሪቱ ሥራውን ለማሳለጥ የሚረዳ የፌደራል እና የክልል ፖሊሲዎች ማዘጋጀት እንደሚያስፈልጋት ጠቁሟል። በሌላ በኩል፣ በኢትዮጵያ ፈቃድ አውጥቶ ቢትኮይን መፈለግ የሚቻል ሲኾን፣ ቢትኮይንን ጨምሮ በሌሎች የክሪፕቶ ከረንሲ ዓይነቶች መገበያየት ግን ሕገ ወጥ እንደኾነ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር በኅዳር ወር 2017 ዓ.ም. ባረቀቀው ሰነድ ላይ አስታውቋል። ይህ ውሳኔ፣ የማኅበረሰቡን ግንዛቤ እና ክሪፕቶ ከረሲን የሚያካትት ባለመኾኑ፣ «ለኅብረተሰቡ ደኅንነት የተወሰደ ርምጃ ነው፤» የሚለው ቃል ካሳ፣ ይኹን እንጂ ማኀበረሰቡም ኾነ የመንግሥት አካላት ስለ ጉዳዩ ማወቅና ከዘመኑ ጋራ ለመራመድ ዝግጁ መኾን ይጠበቅባቸዋል፤ ይላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት፣ በገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣናት የእጅ ስልክ ላይ በመደወልና በጽሑፍ መልእክት ለቃለ መጠይቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። በተመሳሳይ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል አገልግሎት ድርጅት፣ ከቢትኮይን ገቢ የሚደረገው የውጭ ምንዛሬ(ዶላር) ፍሰት፣ ተገቢው የኀይል አቅርቦት መስመር ዝርጋታ ላይ ስለመዋሉ፣ እንዲሁም ሥራውን ለመሥራት ወደ ሀገር ለገቡ ተቋማት የማኅበረሰቡን የኀይል አቅርቦት ፍላጎት ባልተሻማ መልኩ ለማቅረብ እያደረጓቸው ስላሉ እንቅስቃሴዎች ጥያቄ ብናቀርብም፣ የኮምዩኒኬሽንስ ድሬክተር ሞገስ መኮንን፣ ከዚኽ ጉዳይ ጋራ በተያያዘ በቅርቡ ቀጣይ ሪፖርት እስኪወጣ ድረስ በጉዳዩ ላይ ቃለ መጠይቅ እንደማይሰጡ ገልጸውልናል።

 ኮንጎ ውስጥ ያልታወቀ በሽታ 50 ሰዎችን ገደለ

ሰሜን ምዕራብ ኮንጎ ውስጥ የተከሰተ ያልታወቀ ወረርሽኝ ከ50 በላይ ሰዎችን መግደሉን ከሥፍራው የሚገኙ ሃኪሞች እና የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣናት በትላንትና
የአሜሪካ ድምፅ

 ኮንጎ ውስጥ ያልታወቀ በሽታ 50 ሰዎችን ገደለ

ሰሜን ምዕራብ ኮንጎ ውስጥ የተከሰተ ያልታወቀ ወረርሽኝ ከ50 በላይ ሰዎችን መግደሉን ከሥፍራው የሚገኙ ሃኪሞች እና የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣናት በትላንትናው ዕለት አስታውቀዋል። የመጀመሪያው የበሽታው ምልክቶች በሚታዩበት እና ለሕመሙ የታጋለጠ ሰው ለሕልፈት በሚዳረግበት መካከል ያለው ጊዜ በአማካይ የ48 ሰዓታት ዕድሜ ብቻ መሆኑን ጠቅሰው፣ “በእጅጉ አሳሳቢ ያደረገውም ይህ ሁኔታ ነው” ሲሉ የክልሉ የወረርሽኞች መከታተያ ማእከል የሆነው የቢኮሮ ሆስፒታል የሕክምና ድሬክተር ሰርጅ ንጋሌባቶ ወረርሽኙን አስመልክቶ ለአሶሺየትድ ፕሬስ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል ። ባለፈው ጥር 23 ቀን  2017 ዓም የተቀሰቀሰው ወረርሽኝ ለሕልፈት የተዳረጉትን 53 ሰዎች ጨምሮ እስካሁን 419 ሰዎች ለበሽታው መጋለጣቸው ተዘግቧል። የዓለሙ ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ አክሎ እንዳመለከተው የበሽታው መከሰት የታወቀው የመጀመሪያዎቹ የወረርሽኙ ሰለባ የሆኑ ሶስት ህጻናት፣ የሌሊት ወፍ ሥጋ ከተመገቡ እና በ48 ሰዓታት ዕድሜ ከፍተኛ ትኩሳትና የደም የመፍሰስ አደጋ የሚያስከትሉ በሽታዎች ምልክቶችን አሳይተው ለሕልፈት ከተዳረጉ በኋላ ነው። የዱር እንስሳት በሥፋት ለምግብነት በሚውሉባቸው አካባቢዎች ከእንስሳት ወደ ሰው የሚዛመቱ በሽታዎች ለረጅም ጊዜ ሲያሳስቡ ቆይተዋል። የዚህን መሰል ወረርሽኞች አሃዝ ባለፉት አስርት ዓመታት ብቻ በአፍሪቃ ውስጥ ከ60 በመቶ በላይ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2022 አስታውቆ ነበር።

የዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ጠበቆች ግጭት ካየለባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ገቡ

የአይሲሲ ዐቃቤ ሕግ ካሪም ካን በምስራቃዊው የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ተባብሶ ከቀጠለባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መግባታቸውን ጽሕፈ
የአሜሪካ ድምፅ

የዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ጠበቆች ግጭት ካየለባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ገቡ

የአይሲሲ ዐቃቤ ሕግ ካሪም ካን በምስራቃዊው የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ተባብሶ ከቀጠለባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መግባታቸውን ጽሕፈት ቤታቸው ዛሬ አስታወቀ። በሩዋንዳ የሚታገዘው ኤም 23 በቅርቡ ምስራቃዊ ኮንጎ ውስጥ ሁለት ትልልቅ ከተሞችን በቁጥጥር ስር በማዋል አማጺው ቡድን ነፍጥ ካነሳበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2021 መገባደጃ ወዲህ በቀጣናው ግዙፍ ሥፍራ እንዲኖረው አድርጎታል። ካን ዋና ከተማይቱ ኪንሻሳ እንደደረሱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኮንጎ ውስጥ እየሆነ ያለው ሁኔታ፤ በተለይም በምስራቃዊው የሃገሪቱ ክፍል የሚካሄደው ግጭት በእጅጉ አሳሳቢ መኾኑን እንረዳለን” ብለዋል። “መልዕክቱ በግልፅ መተላለፍ አለበት። የትኛውም የታጠቀ ቡድን፣ የትኛውም የታጠቀ ኃይል፣ እና የትጥቅ አጋር የሆነ ወገን፤ በመካሄድ ላይ ካለው ምርመራ እና ከተጠያቂነት ነጻ አይሆንም” ብለዋል። «ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕጎችን ማክበር አለባቸው» ሲሉም አክለዋል ካን። እንደ መንግሥታቱ ድርጅት ባለሞያዎችም ገለጻም አማጺው ቡድን ኤም 23 ቁጥራቸው 4 ሺሕ  በሚጠጉ የሩዋንዳ ወታደሮች ይደገፋል።

ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ በመንግሥታቱ ድርጅት በተሰጠው ድምጽ 'ይበልጥ ሚዛናዊነትን ያንጸባረቀ' ያለችውን የዩናይትድ ስቴትስን አቋም አወደሰች

ዩናይትድ ስቴትስ «የሰላም መንገድ» በሚል ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ባቀረበችው የውሳኔ ሐሳብ ላይ የተሰጠውን ድምጽ ተከትሎ፤
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ በመንግሥታቱ ድርጅት በተሰጠው ድምጽ 'ይበልጥ ሚዛናዊነትን ያንጸባረቀ' ያለችውን የዩናይትድ ስቴትስን አቋም አወደሰች

ዩናይትድ ስቴትስ «የሰላም መንገድ» በሚል ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ባቀረበችው የውሳኔ ሐሳብ ላይ የተሰጠውን ድምጽ ተከትሎ፤ የክሬምሊን ቤተመንግሥት በዩክሬን ጉዳይ «ይበልጥ ሚዛናዊነት የተንጸባረቀበት» ያለውን የዋሽንግተንን አቋም በደስታ መቀበሉን በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የክሬምሊኑ ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ «ለጉዳዩ መቋጫ ለማበጀት (ዩናይትድ ስቴትስ) ያላትን እውነተኛ ፍላጎት» ያሳየ ብለውታል። ብሪታንያ እና ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ አጋር አውሮፓውያን በአንጻሩ ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል። ባለ አራት መስመሩ ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረበችው ጽሑፍ “በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በተፈጠረው ግጭት” በጠፋው የሰው ሕይወት ያሳደረበትን ሐዘን አስመልክቶ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ዓላማ “ዓለም አቀፍ ሰላምና ደኅንነትን ማስጠበቅ እና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት” መሆኑን ይገልጻል። በተጨማሪም «ግጭቱ በፍጥነት እንዲቆም፤ በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን አጥብቆ ይማጸናል» ይላል። «ውሳኔው የሰላም መንገድ የሚያስዘን ይሆናል» ያሉት የዩናይትድ ስቴትሷ የመንግሥታቱ ድርጅት መልዕክተኛ ዶረቲ ሺያ ለምክር ቤት አባላት ሲናገሩ “ይህ የመጀመሪያው፣ ነገር ግን ወሳኙ ርምጃ ነው” ብለዋል። “ሁላችንም ልንኮራበት ይገባል። አሁን ለዩክሬን፣ ለሩሲያ እና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሰላም እና መጭ ጊዜ ግንባታ ልንጠቀምበት ይገባል” ሲሉም አክለዋል። ውሳኔው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ ተመሳሳይ ድምፅ የሰጡትን ሩስያ እና ቻይናን ጨምሮ በ10 የድጋፍ ድምጽ ሲጸድቅ፤ ብሪታንያ እናሌሎች አራት አውሮፓውያን የምክር ቤቱ አባል አገራት ድምጽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የተቃውሞ ድምጽ ያሰማ አባል አገር ግን የለም።

በኢትዮጵያ በሬክተር መለኪያ 5.3 የተመዘገበ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሠተ

«ክሥተቱ ያዝ ለቀቅ እያደረገ መቀጠሉ መዘናጋትን በመፍጠሩ ሁልጊዜ መዘጋጀት ያስፈልጋል» - ፕር. አታላይ አየለ በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከም
የአሜሪካ ድምፅ

በኢትዮጵያ በሬክተር መለኪያ 5.3 የተመዘገበ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሠተ

«ክሥተቱ ያዝ ለቀቅ እያደረገ መቀጠሉ መዘናጋትን በመፍጠሩ ሁልጊዜ መዘጋጀት ያስፈልጋል» - ፕር. አታላይ አየለ በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከምትገኘው ጭሮ ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፣ ትላንት እሑድ፣ የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ሌሊት የተከሠተው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ በሬክተር ስኬል 5ነጥብ3 ኾኖ መመዝገቡን፣ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ተቋም አስታውቋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዲሬክተር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ አኹንም የመሬት መንቀጥቀጡ ዋና ምንጭ ፈንታሌ አካባቢ ነው። የመሬት መንቀጥቀጡ እየተፈጠረ ያለውም፣ ቅልጥ አለት እየሰረሰረ ወደ ላይ ለመውጣት በሚያደርገው ሙከራ ነው፤ ሲሉም ዳይሬክተሩ አብራርተዋል። ትላንት እሑድ፣ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 8:45 ላይ የተከሠተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት፣ አዲስ አበባ ውስጥ ጭምር መሰማቱን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል። የመሬት መንቀጥቀጡ፣ በተለይ በአንዳንድ የከተማዋ ስፍራዎች የፈጠረው ንዝረት፣ በመኖሪያ ሕንጻዎች ላይ ንቅናቄ መፍጠሩን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል። ባለፈው ጥር ወር፣ ከዘርፉ ባለሞያዎች ጋራ ውይይት ያደረጉት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ርእሰ መዲናዪቱ ካላት የመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭነት አንጻር፣ ተገቢ የጥንቃቄ ጥናቶችን የሚያደርግ የባለሞያዎች ግብረ ኀይልን በማደራጀት በጋራ ለመሥራት ከስምምነት ላይ መደረሱን መግለጻቸው ይታወሳል። ክሥተቱ ያዝ ለቀቅ እያደረገ መቀጠሉ መዘናጋት መፍጠሩን የጠቀሱት ፕሮፌሰር አታላይ፣ እስከ አኹን መሬት ላይ የወረደ ነገር አለመኖሩን አመልክተዋል። የተፈጥሮ አደጋ «አማክሮ ስለማይመጣ»፣ መደረግ ያለበትን ዝግጅት ሁልጊዜ በተጠንቀቅ ማድረግ እንደሚያስፈልግም፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዲሬክተሩ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ አሳስበዋል።  

በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የድሮን ጥቃት ሲቪል ነዋሪዎች መሞታቸው ተገለጸ

በዐማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ «አነገሽ» ቀበሌ “ኀሙስ ገበያ” በተባለ ስፍራ፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም.
የአሜሪካ ድምፅ

በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የድሮን ጥቃት ሲቪል ነዋሪዎች መሞታቸው ተገለጸ

በዐማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ «አነገሽ» ቀበሌ “ኀሙስ ገበያ” በተባለ ስፍራ፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም. ተያይዘው በተሠሩ የንግድ ቤቶች ላይ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት፣ ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን፣ የሟች ቤተሰቦች እና የዐይን እማኞች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። በገበያው ዳር ኳስ ሲጫወት የነበረ የ15 ዓመት ልጃቸው በጥቃቱ መገደሉን የተናገሩት ወይዘሮ ታንጉት የተባሉ እናት፣ የስምንት ዓመት ልጃቸውም ቆስሎ በሆስፒታል እንደሚገኝ ገልጸዋል። የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ የኔዋ ደመቀ ግን፣ ጥቃቱ በሲቪል ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ ሳይኾን፣ “ጽንፈኛ” ሲሉ በጠሩት ቡድን ላይ የተፈጸመ እንደኾነ ገልጸው አስተባብለዋል። ጥቃቱም የተፈጸመው፣ ታጣቂው ኀይል እንደ ካምፕ እየተጠቀመበት ባለው ትምህርት ቤት ላይ እንጂ የንግድ ሱቆች ላይ አይደለም፤ ሲሉ አመልክተዋል። በአንጻሩ፣ በጥቃቱ መጎዳታቸውን የገለጹና የተጎጂዎችን አስከሬን ሰብስበናል ያሉ የስፍራው ነዋሪዎች፣ ጥቃቱ በሲቪሎች ላይ የተፈጸመ ነው፤ ብለዋል። የዐይን እማኞቹ እንደሚሉት፣ በዕለቱ ሰባት የሚደርሱ ሟቾችን ቀብር፣ በከተማው ውስጥ በሚገኝ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አከናውነዋል። አብዛኛዎቹ ተጎጂዎችም፣ ከገጠር ቀበሌዎች ቆርቆሮ ለመግዛት ተሰባስበው የመጡ ንጹሓን ናቸው፤ ብለዋል። ጥቃቱ የተፈጸመበት የአነገሽ ቀበሌ ኀሙስ ገበያ አካባቢ፣ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በፋኖ ታጣቂ ኀይሎች ቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ፣ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል።

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አሜሪካና ዩክሬን በተናጥል ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ ላይ ድምፅ ይሰጣል

በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ማስቆም በተመለከተ፣ በአንድ ወገን በአሜሪካ በሌላ ወገን ደግሞ በዩክሬን ተረቀው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ
የአሜሪካ ድምፅ

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አሜሪካና ዩክሬን በተናጥል ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ ላይ ድምፅ ይሰጣል

በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ማስቆም በተመለከተ፣ በአንድ ወገን በአሜሪካ በሌላ ወገን ደግሞ በዩክሬን ተረቀው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የቀረቡ የውሳኔ ሐሳቦች ዛሬ ሰኞ ድምፅ እንደሚሰጥቸው ይጠበቃል። ጠቅላላ ጉባኤው በቅድሚያ በዩክሬን በቀረበውና በአውሮፓ ኅብረት በሚደገፈው ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምፅ እንደሚሰጥ ሲጠበቅ፣ በመቀጠል ደግሞ በአሜሪካ በቀረበው ላይ ድምፅ ይሰጣል። የድርጀቱ የፀጥታው ምክር ቤት ደግሞ በተናጥል በአሜሪካ በቀረበው ረቂቅ ላይ ድምጽ ይሰጣል ተብሏል። አሜሪካ “ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆምና በዩክሬንና በሩሲያ መካከል ዘላቂ ሠላም እንዲመጣ ጥሪ አድርጋለች” ያለው የሮይተርስ ዘገባ፣ የአሜሪካው ረቂቅ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን አያመለክትም ብሏል። የውሳኔ ሐሳቡ “ግጭቱ አሰቃቂ መሆኑን፣ ግጭቱን ለማቆም ደግሞ ተመድ ሊረዳ እንዳሚችል፣ ሠላምንም ማስፈን እንደሚችል ያሳያል” ሲሉ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ማክሮ ሩቢዮ ባለፈርው ዓርብ ተናግረዋል። ጠቅላላ ጉባኤው ያቀረበችውን የውሳኔ ሐሳብ እንዲያፀድቅ እንዲሁም በዩክሬንና በአውሮፓ አጋሮቿ የቀረበውን ሐሳብ ውድቅ እንዲያደርግ አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ መልዕክት ማስተላለፏንና ይህንኑም መመልከቱን ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል። በዩክሬን የቀረበው ረቂቅ ደግሞ ጠቅላላ ጉባኤው ከዚህ በፊት የደረሰበት የውሳኔ ሐሳብ ተግባራዊ እንዲሆን ይጠይቃል። ይህም ሩሲያ በዓለም እውቅና ከተሰጠው የዩክሬን ድንበር ሙሉ ለሙሉ እንድትወጣ የሚጠይቀውን ይጨምራል። የጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔዎች ተፈጻሚነት ሕጋዊ ግዴታ የሌለባቸው ቢሆኑም፣ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ሞራላዊ ጫና እንዲፈጠር ሊያደርጉ ግን ይችላሉ። በፀጥታው ምክር ቤት አንድ የውሳኔ ሐሳብ ለማለፍ ከ15 ዓባላት ውስጥ ቢያንስ የዘጠኙ ድጋፍ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ ከቋሚ ዓባላት ውስጥ ማለትም ከእንግሊዝ፣ ቻይና፣ ፈረንሣይ፣ ሩሲያ ወይም አሜሪካ አንዳቸው ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸን ሊጠቀሙ ይችላሉ። የአሜሪካው የውሳኔ ሐሳብ በቂ ድጋፍ ሊያገኝ እንደሚችል ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

የሱዳን ጦር የበላይነት እያገኘ መኾኑን አስታወቀ 

የሱዳን ጦር ከአንድ ዓመት በላይ በከበባ ስር የቆየውን ኦቤይድ የተሰኘ ቁልፍ ከተማ ማስለቀቁን፣ ወደ ደቡብ ማዕከላዊ ክልል መድረስ የሚያስችለው ስልታዊ  አካባ
የአሜሪካ ድምፅ

የሱዳን ጦር የበላይነት እያገኘ መኾኑን አስታወቀ 

የሱዳን ጦር ከአንድ ዓመት በላይ በከበባ ስር የቆየውን ኦቤይድ የተሰኘ ቁልፍ ከተማ ማስለቀቁን፣ ወደ ደቡብ ማዕከላዊ ክልል መድረስ የሚያስችለው ስልታዊ  አካባቢ መያዙን እና ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል ጋራ እያደረገ ላለው ጦርነት ወሳኝ የአቅርቦት መንገዶችን ማጠናከሩን አስታወቀ። የጦሩ ቃል አቀባይ ብርጋዴን ጀነራል ናቢል አብዱላህ በሰጡት መግለጫ፣ ወታደሮቹ በፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች ስር የነበረውን የነጭ አባይ ጠንካራ ይዞታ ማስለቀቅ መቻላቸውን እና ይህም የተቀናቃኙን ኃይል ያመናመነ መኾኑን ገልጸዋል። አብዱላህ አክለው አል-ሳይድ ውስጥ የሚገኘው የሀገሪቱ ጦር ወደ ኦቤይድ የሚወስደውን መንገድ መክፈቱን እና ፈጥኖ ደራሹ በሰሜናዊ ኮርዶፋን ክልል ዋና ከተማ ላይ ያካሄደው ከበባ ማብቃቱን አብራርተዋል። ከተማዋ የተንጣለለ ወታደራዊ የአየር ማረፊያ እና ሃግና ተብሎ የሚጠራው አምስተኛ ወታደራዊ የጦር ሰፈር የሚገኝበት ነው። የንግድ እና የትራንስፖርት ማዕከል የሆነችው ኦቤይድ፣ የደቡብ ዳርፉር ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን ኒያላን ከካርቱም ጋራ የሚያገናኘው የባቡር ሃዲድም የሚገኝባት ሲሆን እ.አ.አ በሚያዚያ 2023 ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ስር ቆይታለች።  የሀገሪቱ ገንዘብ ሚኒስትር ጂብሪል ኢብራሂም ጦሩ በኦቤይድ ያገኘውን ድል «ትልቅ ርምጃ» ሲሉ አወድሰዋል። 

የኮንጎ ፕሬዝዳንት 'የአንድነት መንግስት' እመሰርታለሁ አሉ

በምስራቃዊው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት እየተባባሰ በሄደበት ወቅት በቀውሱ አያያዝ ዙሪያ የሚሰነዘርባቸው ትችት እየጨመረ የሄደው የኮንጎ ፕሬዝዳንት
የአሜሪካ ድምፅ

የኮንጎ ፕሬዝዳንት 'የአንድነት መንግስት' እመሰርታለሁ አሉ

በምስራቃዊው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት እየተባባሰ በሄደበት ወቅት በቀውሱ አያያዝ ዙሪያ የሚሰነዘርባቸው ትችት እየጨመረ የሄደው የኮንጎ ፕሬዝዳንት፣ የአንድነት መንግስት እንደሚመሰርቱ አስታወቁ።  የኤም 23 አማፂያን በምስራቃዊ ኮንጎ የሚገኙ ዋና ዋና ከተሞችን ከተቆጣጠሩ በኃላ፣ ትላንት ቅዳሜ ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር ያደረጉት የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ሀገሪቱን ለሚያስተዳድረው ጥምር ፓርቲ በውስጣዊ ግጭቶች እንዳይዘናጉ አሳስበዋል።  «በትግሉ ነው እንጂ በጦርነቱ አልተሸነፍኩም » ያሉት ፕሬዳንቱ «ሁሉንም ተቃዋሚዎች ማነጋገር አለብኝ። የብሔራዊ አንድነት መንግስት ይመሰረታል» ብለዋል። ይህ ጥምር መንግስት ምን ሊመስል እንደሚችል ወይም መቼ እንደሚፈፀም ግን ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።  በምስራቅ ኮንጎ የበላነት ለማግኘት ከሚፎካከሩ ከመቶ በላይ ታጣቂ ቡድኖች መካከል ከፍተኛ ኃይል ያላቸው የኤም23 አማፂያን፣ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በመግደል ትልቁን ከተማ ጎማን ጨምሮ አብዛኛውን ምስራቃዊ ክፍል ተቆጣጥረዋል። ሺሴኬዲ ቅዳሜ እለት ባደረጉት ንግግር በጦርነቱ ህይወታቸው ላጡ ወታደሮች ምስጋና አቅርበው ጦሩን ለመደጋፍ ቃል ገብተዋል።  የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት የኤም 23 አማፂ ቡድንን በአሸባሪነት የፈረጀ ሲሆን ሩዋንዳ ለቡድኑ ድጋፍ ትሰጣለች ሲልም ይከሳል። ሩዋንዳ በበኩሏ ክሱን አትቀበልም። 

ሩሲያ በሚያንማር ወደብ እና የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት የሚያስችላት የመግባቢያ ሰነድ ፈረመች

ሚያንማር እና የቅርብ አጋሯ ሩሲያ፣ ዳዌይ በተሰነው ልዩ የኢኮኖሚ ዞን፣ የወደብ እና የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታን ያካተተ የመዋዕለ ንዋይ ትብብር መፈራረማቸውን
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ በሚያንማር ወደብ እና የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት የሚያስችላት የመግባቢያ ሰነድ ፈረመች

ሚያንማር እና የቅርብ አጋሯ ሩሲያ፣ ዳዌይ በተሰነው ልዩ የኢኮኖሚ ዞን፣ የወደብ እና የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታን ያካተተ የመዋዕለ ንዋይ ትብብር መፈራረማቸውን የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዛሬ እሁድ አስታውቋል።  የሩሲያ ሚኒስትሩ ማክሲም ሪሼንትኒኮቭ እና የሚያንማር የመዋዕለ ንዋይ እና የውጭ ኢኪኖሚ ግንኙነት ሚኒስትር ካን ዛው ስምምነቱን የተፈራረሙት፣ የሩሲያ ልዑካን ቡድን ደቡብ ምስራቃዊዋን የእስያ ሀገር በጎበኙበት ወቅት ነው።  የሩሲያው ሚኒስቴር መስሪያቤት ሪሼንትኒኮቭን ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ «ስምምነቱ በሚያንማር ከሚገኙ የሩሲያ ኩባንያዎች ጋር በጋራ የሚተገበሩ በርካታ ትላልቅ መሠረተ ልማት እና የኢነርጂ ፕሮጀክትን ያካትታል» ብሏል። ፕሮጀክቱ ወደብ፣ በድንጋይ ከሰል የሚሰራ የሙቀት ኃይል ማመንጫ እና የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካን እንደሚያካትትም በመግለጫው ተመልክቷል። እ.አ.አ በየካቲት 2021 በሚያንማር በተካሄደ መፈንቅለ መንግስት የኦንግ ሳን ሱ ኪ መንግስት ከስልጣን ከወረደ ወዲህ ሩሲያ የሚያንማር የቅርብ አጋር የሆነች ሲሆን ሞስኮ እና ኔይፒዳ፣ በኃይል ግንባታ ዙሪያ የሚያደርጉትን ትብብር ለማጠናከር ሲወያዩ መቆየታቸው ይታወሳል። 

ኢኮኖሚ፣ ስደት እና አክራሪ ኃይሎች ትኩረት የሳቡበት የጀርመን ምርጫ እየተካሄደ ነው

የጀርመን መራጮች ዛሬ እሁድ በሚካሄደው ምርጫ ድምፅ መስጠት ጀምረዋል። ምርጫው ለዓመታት የተቀዛቀዘው የአውሮፓ ኢኮኖሚ፣ ስደትን ለመግታት የሚደረገው ጫና፣
የአሜሪካ ድምፅ

ኢኮኖሚ፣ ስደት እና አክራሪ ኃይሎች ትኩረት የሳቡበት የጀርመን ምርጫ እየተካሄደ ነው

የጀርመን መራጮች ዛሬ እሁድ በሚካሄደው ምርጫ ድምፅ መስጠት ጀምረዋል። ምርጫው ለዓመታት የተቀዛቀዘው የአውሮፓ ኢኮኖሚ፣ ስደትን ለመግታት የሚደረገው ጫና፣  የዩክሬን ዕጣ ፈንታ እና ስጋት ውስጥ የወደቀው የአውሮፓ እና የዩናይትድ ስቴትስ አጋርነት ጥላ ያጠላበት ነው።  ለዘብተኛ ቀኝ ዘመም ተቃዋሚዎች ምርጫውን ሊያሸንፉ ይችላሉ የሚሉ ግምቶች ቢኖሩም፣ ከሕዝብ የተሰበሰቡ ድምፆች በበኩላቸው፣ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ባልታየ ሁኔታ ለቀኝ አክራሪ ፓርቲ ድጋፍ እንዳለ አሳይተዋል።  ጀርመን ከ27ቱ የአውሮፓ ህብረት አባላት በሕዝብ ብዛት ቀዳሚዋ ስትሆን፣ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ)ም ከፍተኛውን ድርሻ ትይዛለች።  ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥሎ ለዩክሬን ከፍተኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢ በሆነችው ጀርመን እስካሁን ከህዝብ የተሰበሰቡ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት፣ የለዘብተኛው ቀኝ ዘመም የተቃዋሚ መሪ ፍሬድሪክ ሜርዝ ፓርቲ ከ28-32 በመቶ ድጋፍ ሲያገኝ የቆየ ሲሆን ሜርዝ፤ ሾልዝን ሊተኩ ይችላሉ ተብሎም ተገምቷል።  የፀረ-ስደት አቋም የሚያራምደው ቀኝ አክራሪው ኤ ኤፍ ዲ የተሰኘው ፓርቲ በበኩሉ በ20 ከመቶ ድምፅ በሁለተኛነት ሲከተል ቆይቷል።  በዛሬው የጀርመን ምርጫ የሚፎካከሩት ፓርቲዎች በዋናነት ላለፉት ሁለት አመታት ያሽቆለቆነውን የጀርመን ኢኮኖሚ በድጋሚ እንዲያንሰራራ ያስችላል ያሉትን ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን፣ ባለፈው ወር በስደተኞች የተፈጸሙትን ጥቃቶች ተከትሎም፣ የስደት ጉዳይ የምርጫ ዘመቻው ቀዳሚ አጀንዳ መሆን ችሏል። 

ታጋቾቿ 'አሸማቃቂ' በሆነ መንገድ ተለቀዋል ያለቸው እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን የመልቀቁን ሂደት አዘገየች

እስራኤል ቀጣዮቹ ታጋቾቿ መፈታታቸው እስከሚረጋገጥ እና በጋዛ በሚካሄደው የእስረኛ ልውውጥ ወቅት ይፈፀማል ያለችው አሸማቃቂ ሥነስርዓት እስከሚነሳ ድረስ፣
የአሜሪካ ድምፅ

ታጋቾቿ 'አሸማቃቂ' በሆነ መንገድ ተለቀዋል ያለቸው እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን የመልቀቁን ሂደት አዘገየች

እስራኤል ቀጣዮቹ ታጋቾቿ መፈታታቸው እስከሚረጋገጥ እና በጋዛ በሚካሄደው የእስረኛ ልውውጥ ወቅት ይፈፀማል ያለችው አሸማቃቂ ሥነስርዓት እስከሚነሳ ድረስ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም እስረኞችን የመልቀቁን ሂደት ማዘግየቷን አስታውቃለች።  የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት ዛሬ እሁድ ያወጣው መግለጫ ይፋ የሆነው እስረኞችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከኦፈር ማረሚያ ቤት እየወጡ ባሉበት ወቅት ሲሆን፣ መኪናዎቹ አዙረው ወደ እስርቤቱ ተመልሰዋል።  ስድስቱ የእስራኤል ታጋቾች ቅዳሜ እለት መለቀቃቸውን ተከትሎ ከእስር መፈታት የነበረባቸው 620 የፍልስጤም እስረኞች እስካሁን እንዳልተፈቱም ተገልጿል። ይህ ድንገተኛ የእስራኤል መግለጫ፣ የተኩስ ማቆሙን ስምምነት እጣፈንታ ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል።  የእስረኞቹ መፈታት መዘግየቱን የፍልስጤም አስተዳደር እስረኞች ጉዳይ ኮሚሽን ያስታወቀ ሲሆን ዌስት ባንክ ውስጥ የተቀረፀው የአሶሽዬትድ ፕሬስ ምስል፣ የእስረኛ ቤተሰቦች እጅግ በጣም በሚቀዘቅዘው አየር ውስጥ ሆነው ሲጠባበቁ እና በመጨረሻ ሲበተኑ ያሳያል።  ቅዳሜ እለት የተለቀቁት ስድስቱ ታጋቾች፣ በመጀመሪያው ዙር የተኩስ ስምምነት ይለቀቃሉ ተብለው ከተጠበቁት በህይወት ያሉ የመጨረሻዎቹ ታጋቾች ሲሆኑ፣ ይህ ዙር ከአንድ ሳምንት በኃላ ይጠናቀቃል። ለሁለተኛው ዙር የተኩስ ስምምነት የሚደረገው ድርድር ገና አለመጀመሩም ተመልክቷል። 

ወባን ከአፍሪካ ለማጥፋት በየአመቱ 5.2 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ

ወባን በሁለት አመት ውስጥ ከአፍሪካ አህጉር ለማጥፋት በየአመቱ 5 ነጥቢ 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ኅብረት አስታወቀ፡፡ በ38ኛው የአፍሪካ መሪዎ
የአሜሪካ ድምፅ

ወባን ከአፍሪካ ለማጥፋት በየአመቱ 5.2 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ

ወባን በሁለት አመት ውስጥ ከአፍሪካ አህጉር ለማጥፋት በየአመቱ 5 ነጥቢ 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ኅብረት አስታወቀ፡፡ በ38ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ኅብረቱ በሰጠው መግለጫ፣ የወባ በሽታን የመከላከል ጥረቱ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ችግር ገጥሞታል ብሏል። በቅርቡ የአሜሪካ መንግስት ርዳታን ለማቋረጥ ያሳለፈው ውሳኔ ደግሞ፣ ችግሩን ያባብሶዋል በማለት ተናግሯል። የአሜሪካ መንግስት በበኩሉ፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ሥርዐቱን ዳግም እየፈተሸ መሆኑን ገልጿል።   ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የትራምፕና ፑቲን የፊት ለፊት ውይይት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸውን ሩስያ አስታወቀች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፊት ለፊት የሚገናኙበት ስብሰባ ዝግጅት መጀመሩን የሩሲያ ምክትል የውጭ
የአሜሪካ ድምፅ

የትራምፕና ፑቲን የፊት ለፊት ውይይት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸውን ሩስያ አስታወቀች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፊት ለፊት የሚገናኙበት ስብሰባ ዝግጅት መጀመሩን የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡ ይህም በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በምዕራባውያን ለተገለለቸው ሩስያ ትልቅ ለውጥን የሚያመጣላት ነው ተብሏል፡፡ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰርጌይ ራያብኮቭ ለሃገራቸው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የፑቲንና ትራምፕ የመሪዎች ስብሰባ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይም ያተኮሩ ሰፊ ውይይትን ያካተተ ይሆናል ብለዋል፡፡ ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱን ስብሰባ ለማደራጀት ጥረቶች ገና ጅምር ላይ ናቸው ፣ እናም ይህንን ለማድረግ “በጣም የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ሥራን ይጠይቃል” ብለዋል ። ሪያብኮቭ አክለውም የዩናይትድናይትድ ስቴትስና የሩሲያ ልዑካን በከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል ለቀጣይ ንግግሮች መንገድ ለመክፈት «በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ» ሊገናኙ እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች ማክሰኞ እለት በሳኡዲ አርቢያ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆምና ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ተስማምተዋል ። በስብሰባው ላይ የዩክሬን ልዑክ ያልተሳተፈ ሲሆን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ኪየቭ ባልተሳተፈችበት የውይይቱ ምንም አይነት ውጤት ሀገራቸው እንደማትቀበል ገልጸው ባለፈው ረቡዕ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሊያደርጉ የነበረውን ጉዞም አራዝመዋል።

ቫቲካን ሊቀ ጳጳሱ ሳይኖሩ የቅዱስ ዓመቷ ክብረ በዓልን እያከናወነች ነው 

የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ከገጠማቸው የሳንባ ምች እና የተወሳሰበ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ጋር እየታገሉ ሲሆን ቫቲካን ያለ እርሳቸው የቅዱስ ዓመ
የአሜሪካ ድምፅ

ቫቲካን ሊቀ ጳጳሱ ሳይኖሩ የቅዱስ ዓመቷ ክብረ በዓልን እያከናወነች ነው 

የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ከገጠማቸው የሳንባ ምች እና የተወሳሰበ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ጋር እየታገሉ ሲሆን ቫቲካን ያለ እርሳቸው የቅዱስ ዓመት ክብረ በዓልን እያከበረች ትገኛለች፡፡  አባ ፍራንሲስ ዛሬ ሌሊት በደንብ ተኝተው ማሳለፋቸውን የቫቲካን ቃል አቀባይ ማትዮ ብሩኒ ስለላሉበት የጤና ሁኔታ በተመለከተ በሰጡት አጭር መግለጫ ተናግረዋል።  ነገር ግን ዶከተሮች የ88 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ የገጠማቸው ህመም የተወሳሰበ የሳምባ ምች ሊያስከትል የሚችል የደም 'ኢፌክሽን' ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን በመግለጥ እያሰጠነቀቁ ነው፡፡   እስከትላንት ምሽት ድረስ ግን በሽታው ይህ ስለመሆኑ ማረጋገጫ አለማግኘታቸውንና ስለሚወስዷቸው መድሃኒትቶችም ሊቀ ጳጳሱ ምላሽ እንደሚሰጡ የህክምና ቡድኑ ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ በሰጠው የመጀመርያ ማብራርያው ላይ አስታውቋል፡፡  የ88 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ ከአንድ ሳምንት በላይ በመተንፈሻ አካላት በሽታ ሲሰቃዩ ቆይተው ባለፈው ሳምንት ሮም በሚገኘው ገሚሊ ሆስፒታል ገብተዋል።  ከአውሮፓዊያኑ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሊቀ ጳጳስነት መንበራቸው የቀጠሉት ፍራንሲስ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተደጋጋሚ የኢንፍሉዌንዛ እና ሌሎች የጤና ችግሮች አጋጥሟቸዋል።  በልጅነታቸው ፕለረሲ በተባለ በሽታ በመጠቃታቸው ከአንደኛው የሳንባ ክፍል የተወሰነው በቀዶ ጥገና እንዲወገድ ተደርጓል። በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ሊቀ ጳጳሱ ለሳንባ መቆጣት ተጋላጭ ኾነዋል። 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አማፂያን ከያዟቸው የኮንጐ ከተሞች እንዲወጡ ጠየቀ 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በምስራቃዊ ኮንጎ የሚገኘው የኤም 23 አማፅያን ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም እና ከያዛቸው ግዛቶች እንዲ
የአሜሪካ ድምፅ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አማፂያን ከያዟቸው የኮንጐ ከተሞች እንዲወጡ ጠየቀ 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በምስራቃዊ ኮንጎ የሚገኘው የኤም 23 አማፅያን ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም እና ከያዛቸው ግዛቶች እንዲወጣ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ትላንት አርብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ምክር ቤቱ ግጭቱን በሚያራዝሙ አካላት ላይ ማዕቀብ እንደሚጣልባቸውም ዝቷል።  የወሳኔ ሃሳቡን ረቂቅ ያዘጋጀችው ፈረንሣይ በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ለተፈጠረው ግጭት ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ ግልጽ መልዕክት ያስተላለፈ ነው ስትል አስታውቃለች፡፡  «ቅድሚያ የሚሰጠው ውጤታማ፣ ቅድመ ሁኔታ የሌለው እና አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ነው» ሲሉ አምባሳደር ኒኮላ ዴ ሪቪየር ተናግረዋል። በቀጠናው ደረጃ የሚደረጉ የማሸማገል ጥረቶችና ውይይቶች አስፈላጊነት የገለጡት አምባሳደሩ  የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መከበር አለበት ብለዋል፡፡  የውሳኔ ሃሳቡ የሩዋንዳ መከላከያ ሰራዊት ለኤም 23 የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቆም እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግዛት በአስቸኳይ እንዲወጣ ይጠይቃል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት የሩዋንዳ መከላከያ ሰራዊት ለኤም 23 “ቀጥታ ድጋፍ” ያደርጋል ሲሉ ከሰዋል። ሩዋንዳ አማፂያኑን ትደግፋለች የሚለውን ውንጀላ ደጋግማ ስታስተባብል ቆይታለች።  የፀጥታው ምክር ቤት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሩዋንዳ «ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች በአስቸኳይ እንዲመለሱም»  አሳስቧል። 

ሃማስ ተጨማሪ እስራኤላውያን ታጋቾችን ለቀቀ 

የተኩስ አቁም ስምምነቱ አካል በሆነው የታጋቾችና እስረኞች ልውውጥ ሁለት እስራኤላውያን ታጋቾች ዛሬ አስቀድመው የተለቀቁ ሲሆን ሌሎች ሶስት ታጋቾች ደግሞ ቆይ
የአሜሪካ ድምፅ

ሃማስ ተጨማሪ እስራኤላውያን ታጋቾችን ለቀቀ 

የተኩስ አቁም ስምምነቱ አካል በሆነው የታጋቾችና እስረኞች ልውውጥ ሁለት እስራኤላውያን ታጋቾች ዛሬ አስቀድመው የተለቀቁ ሲሆን ሌሎች ሶስት ታጋቾች ደግሞ ቆይተው ተለቀዋል፡፡ በዚህ ምትክም በመቶ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞች የሚለቀቁ ይሆናል፡፡   ከጋዛ አርብ የተመለሰው አስከሬንም የታጋች ሺሪ ቢባስ መሆኑም ተረጋግጧል፡፡  አስቀድመው ከተለቀቁት ታጋቾች መካከል የ40 አመቱ ታል ሾሃም፣ እአአ ጥቅምት 7፣ 2023  ሃማስ በእስራኤል ላይ ባደረሰው ጥቃት ከኪቡትዝ ቢኤሪ ታግቶ የተወሰደ ሲሆን ሁለተኛው የ39 አመቱ አቬራ መንግስቱ ደግሞ ከአስር አመት በፊት ብቻውን ወደ ጋዛ ገብቶ የነበረ ነው፡፡   ታጋቾችን ሃማስ ዛሬ ቅዳሜ ረፋድ ላይ በጋዛ ራፋህ ከተማ ለቀይ መስቀል አስረክቧቸዋል፡፡ በርክክቡ  ወቅት አውቶማቲክ መሳሪያ የያዙ እና ወታደራዊ ልብስ የለበሱ የሃማስ ተዋጊዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዝናባማ በሆነው የአየር ሁኔታ ራፋህ አደባባይ ላይ ቁመው ታይተዋል፡፡  ሃማስ ቆይቶም የ27 ዓመቱን ኤሊያ ኮኸን፣ የ22 አመቱ ኡመር ሸህም ቶቨ እና የ23 አመቱ ኡመር ዌንከርት የተባሉ ሶስት እስራኤላውያን ታጋቾችን ለቋል፡፡  ኮኸን፣ ቶቭ እና ዌንከርት እአአ ጥቅምት 7፣ 2023 በአሜሪካ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሃማስ  በእስራኤል ላይ  ጥቃት ባደረሰበት ወቅት ከሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ አግቶ የወሰዳቸው ናቸው፡፡  በቴል አቪቭ የእስራኤልን ባንዲራ የሚያውለበልቡ እና የታጋቾቹን ምስል የያዙ ሰዎችም የታጋቾችን መለቀቅ በቪድዮ ሲከታተሉና ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል፡፡  በተለቀቁት ታጋቾች በምትኩ እስራኤል ከ600 በላይ ፍልስጤማውያንን እስረኞችን ትፈታለች።  ሌላ አንድ ታጋች ዛሬ አመሻሽ ላይ ይለቀቃ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን አጠቃላይ የተለቀቁት ስድስቱ ታጋቾችም  በመጀመሪያው ምዕራፍ የተኩስ አቁም ወቅት ነፃ የሚወጡት የመጨረሻዎቹ ታጋቾች ይሆናሉ ተብሎም ይጠበቃል። 

በምዕራብ ዩክሬን በምትገኝ አንዲት መንደር ወንዶች አይታዩም

በምዕራብ ዩክሬን የምትገኘው ማኪቭ ከተማ፣ ብዙም ወንዶች አይታዩባትም። በርካቶች ሸሽተዋል ወይም ውጊያ ላይ ናቸው አልያም የሩሲያን ወረራ ለመመከት ሲፋለሙ ሕ
የአሜሪካ ድምፅ

በምዕራብ ዩክሬን በምትገኝ አንዲት መንደር ወንዶች አይታዩም

በምዕራብ ዩክሬን የምትገኘው ማኪቭ ከተማ፣ ብዙም ወንዶች አይታዩባትም። በርካቶች ሸሽተዋል ወይም ውጊያ ላይ ናቸው አልያም የሩሲያን ወረራ ለመመከት ሲፋለሙ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ችግሩ በዩክሬን ባሉ በርካታ ከተሞች የሚታይ ነው። ጦርነቱ ወትሮውንም እየቀነሰ የመጣውን የሕዝብ ቁጥር አባብሶታል። ከጦር ሜዳ የቀሩትና ሕይወታቸውን መልሰው ለመገንባት የሚጥሩት የቀሩት ነዋሪዎች የዩክሬን የወደፊት ዕጣ ያሳስባቸዋል። በጦርነቱ ሕይወታቸውን ለሰጡ ወታደሮች መታሰቢያ በማኪቭ ዋናው አውራጎዳና ላይ ይታያል። ፎቶዎቹ መስዋቶቹ ደስተኛ በነበሩበት ጊዜ የተነሱት ነው። ከፎቷቸው በላይ “ክብር ለጀግኖች” የሚል ጽሁፍ ይታያል። ይህም ጦርነቱ የወለደው መፈክር ነው። ማኪቭ ከተማ የምትገኘው ከጦር አውድማው 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው። ጦርነት ያደረሰውን ከፍተኛ ጉዳት እንደዚህች ከተማ የሚያሳዩ ጥቂት ናቸው። በከተማዋ ዕድሜያቸው ለውትድርና የደረሱ ወንዶች የሚገኙት በፎቶ ግራፍ ላይ ብቻ ነው። ወይም ደግሞ በከተማዋ የመቃብር ሥፍራ ነው። ሌሎቹ ወንዶች ለቀው ሄደዋል። “ተመልከት፣ ሰው የት ነው ያለው? ተደብቀዋል። ስጋት አድሮባቸዋል” ይላል ሹፌሩ አሌክስ ካሞቪስኪ። ከ30 ዓመታት በላይ በጀርመን ኖሯል። ወደ ትውልድ ከተማው የተመለሰው ሰነዱን ለማደስ ነበር። ጓደኞቹ እና ዘመዶቹ በከተማው የሉም። “አሳዛኝ ነው!” ሲልም አክሏል። ካሞቪስኪ እንደሚለው ለውጊያ ዕድሜያቸው የደርሱ በርካታ ወንዶች ወደ ግንባር እንዳይላኩ ወደ ገጠር ሄደው ተደብቀዋል። በማኪቭ ከተማ መንገዶች ላይ የተዘዋወረው የቪኦኤ ዘጋቢ ያገኛቸው አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው። ወንዶች በመሄዳቸው ሕይወት ይበልጥ ከባድ እንደሆነ በርካታ ሴቶች ተናግረዋል። “እድሜዪ የገፋ ሴት ነኝ። ከሰባ ዓመቴ በላይ ነኝ። በእርግጥ ከልጆቻቸው ጋራ ለተተዉት ወጣት ሴቶች ይበልጥ ከባድ ነው። ወንድ ከቤት ካለ፣ ጠባቂ ብቻ ሳይሆን፣ ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን የሚያቀርብም ነው። በሁሉም ጉዳይ ላይ ይረዳል። በተለይም በገንዘብ ጉዳይ” ብለዋል አስተማሪ የነበሩትና አሁን ጡረታ ላይ የሚገኙት ኒዮሊና ኮቫሌንኮ። በምዕራብ ዩክሬን የሚገኙ በርካታ ከተሞች ውስጥ የወንዶች አለመኖር ትልቅ ችግር ፈጥሯል። ማኪቭ ከተማ ግን ከጦርነቱም በፊት ቢሆንም የነበረው የሕዝብ ቁጥር መቀነስ ቀውስ ማሳያ ነች፡፡ መንግሥት እንደሚለው፣ የሕዝቡ ቁጥር በእ.አ.አ 1991 ከነበረው 52 ሚሊዮን፣ በእ.አ.አ 2024 ወደ 32 ሚሊዮን አቆልቁሏል። አንጀሊና ቦንዳል የከተማዋ ነዋሪና ተማሪ ነች።“ይህ እጅግ ያስፈራኛል። በርካታ ቤተሰቦች ሃገሪቱን ለቀው በመውጣታቸው በሃገሪቱ ሁሉም ነገር ተቀይሯል። ሃገሪቱም ተቀይራለች፡፡ ብዙ ሰዎች ለቀው ስለወጡ በጣም ያሳዝናል። ምንም ጓደኛ የለኝም። ቤተሰቤ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ከሃገር ወጥቷል። ያሳዝናል” ብላለች የከተማዋ ነዋሪና ተማሪ የሆነችው አንጀሊና ቦንዳል። አንጀሊና ቦንዳር ገና 15 ዓመቷ ነው። አንድ ጎረቤቷ በጦርነቱ ሕይወቱን አጥቷል። ሌሎቹ ጎረቤቶቿ አሁንም ውጊያ ላይ ናቸው። አብዛኞቹ ጓደኞቿ ለቀው የወጡት ገና በልጅነታቸው ነው። አንድ ቀን ዩክሬንን መልሶ የመገንባት ሥራው በእርሷ ትውልድ ላይ እንደሚወድቅ አውቃለች፡፡ ያንን ሃላፊነት ለመጋፈጥ ዝግጁ ስለመሆኗ ግን እርግጠኛ አይደለችም።

እየሻከረ የመጣው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት እና ሰሞነኛ ውዝግብ

የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ ባለፈው ሰኞ፣ የኤርትራ መንግሥትን በተመለከተ በአንድ ዓለም አቀፍ ብዙኀን መገናኛ ድረ ገጽ ላይ ያወጡት
የአሜሪካ ድምፅ

እየሻከረ የመጣው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት እና ሰሞነኛ ውዝግብ

የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ ባለፈው ሰኞ፣ የኤርትራ መንግሥትን በተመለከተ በአንድ ዓለም አቀፍ ብዙኀን መገናኛ ድረ ገጽ ላይ ያወጡትን ጽሑፍ ተከትሎ ኤርትራ ምላሽ ሰጥታለች፡፡ የአሜሪካ ድምፅ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የሁለቱ ሀገራት ምሁራን በበኩላቸው፣ ኹኔታው እየሻከረ የመጣውን የተጎራባች ሀገራቱን ግንኙነት ይፋ ያደረገ እንደኾነ ገልጸዋል፤ ልዩነቱ ተባብሶ ወደ ግጭት እንዳያመራ ስጋት እንዳላቸውም አሳስበዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

በጋምቤላ ክልል በኮሌራ ወረርሽን ከ15 በላይ ሰዎች ሞቱ

በጋምቤላ ክልል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተከሰተው የኮሌራ ወርረሽኝ 15 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አቤ
የአሜሪካ ድምፅ

በጋምቤላ ክልል በኮሌራ ወረርሽን ከ15 በላይ ሰዎች ሞቱ

በጋምቤላ ክልል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተከሰተው የኮሌራ ወርረሽኝ 15 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አቤል አሰፋ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት “ባለፈው ሳምንት በኑዌር ዞን የተከሠተው በሽታ በላቦራቶሪ ምርመራ ኮሌራ መሆኑ ተረጋግጧል” ብለዋል። እስከ ዛሬ ድረስ በተደረገው ማጣራትም 15 ሰዎች ሲሞቱ 306 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን አስታውቀዋል። በሽታው መጀመሪያ የተከሰተበት የኑዌር ዞን ጤና መምሪያ የሟቹን ቁጥር 18 አድርሶታል። የኑዌር ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጋትቤል ግርማል፣ የሟቾቹ ቁጥር መጨመሩን እና የታማሚዎቹ ቁጥር ደግሞ 270 መኾኑን ገልጸዋል። በደቡብ ሱዳን አዋሳኝ በሆነው አኮቦ ወረዳ በሽታው መከሰቱን የጠቆሙት አቶ ጋትቤል በወረዳው የስልክ አገልግሎት ችግር በመኖሩ መረጃ ከተለዋወጡ ሦስት ቀናት ማለፉን አስታውቀዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ከአሜሪካ የተባበሩ ፍልሰተኞችን ኮስታሪካና ፓናማ በጊዜያዊነት እየተቀበሉ ነው

ከአሜሪካ የተባረሩትን ፍልሰተኞችን በጊዜያዊነት ለማስተናገድ ኮስታሪካና ሆንዱራስ ከፓናማ ጋራ ተቀላቀለዋል፡፡ በዐዲሱ የትረምፕ አስተዳደር የኢምግሬሽን
የአሜሪካ ድምፅ

ከአሜሪካ የተባበሩ ፍልሰተኞችን ኮስታሪካና ፓናማ በጊዜያዊነት እየተቀበሉ ነው

ከአሜሪካ የተባረሩትን ፍልሰተኞችን በጊዜያዊነት ለማስተናገድ ኮስታሪካና ሆንዱራስ ከፓናማ ጋራ ተቀላቀለዋል፡፡ በዐዲሱ የትረምፕ አስተዳደር የኢምግሬሽን ፖሊሲ ከሀገር የተባረሩና የተለያየ ሀገር ዜግነት ያላቸው 135 ስደተኞችን የጫነ አውሮፕላን ትላንት ሐሙስ ኮስታሪካ ዋና ከተማ አርፏል፡፡ 65 ህፃናት ይገኙበታል የተባሉት እነዚህ ፍልሰተኞች ከኡዝቤክስታን፣ ከቻይና ከአፍጋኒስታን ከሩሲያ እና ከሌሎች ሀገሮች የመጡ ናቸው፡፡ፍልሰተኞቹ ወደ የሀገራቸው ከመሸኘታቸው በፊት ኮስታሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ በገባችው ስምምነት መሰረት በሀገሯ ታቆያለች፡፡ ኮስትሪካ፣ ፓናማ እና ሆንዱራስ ወደ ሌሎች ሀገሮች የሚላኩ ፍልሰተኞችን ለጊዜው ተቀብለው ለማቆየት ከዩናይትድ ስቴትስት ጋራ ስምምነት የተፈራረሙ ሀገሮች ናቸው፡፡ ፓናማ በቅርቡ በመጀመሪያው ዙር የተላኩ 299 ፍልሰተኞችን የተቀበለች ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት በሆቴል ክፍሎች ውስጥ ሲቀመጡ ሌሎች ደግሞ በኮሎምቢያ ድንበር አቅራቢያ ወደሚገኝና ራቅ ወዳለ  ካምፕ ተልከዋል፡፡ ሆንዱራስ በአሜሪካና በቪንዙዌላ መካከል ቀጥተኛ በረራ ባለመኖሩ “የሰብአዊ ድልድይ” ብላ በጠራቸው የማጓጓዝ አገልግሎት 170 ቬንዙዌላውያንን ከጓንታናሞ ቤይ ወደ ቬንዙዌላ በማዛወር ረድታለች፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በቅርቡ ባደረጉት ጉብኝት ከሀገራቱ ጋራ በተደረሰው ስምምነት ዩናይትድ ስቴትስ የመጓጓዣውንና የማቆያውን ሙሉ ወጪዎች ትሸፍናለች፡፡ ፕሬዚዳንት ትረምፕ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ህገወጥ ስደተኞችን በመግታት፣ በመቀበል ወይም ሁኔታዎችን በማመቻችት እንዲተባበሩ ጫና አሳድረዋል፡፡ ከተባበረሩት ፍልሰተኞች መካከል በተለይም ከእስያ የመጡት ወደ የሀገራቸው ከመመለሳቸው በፊት እስከ ስድስት ሳምንታት ሊቆዩ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው፣ ካልሆነም በተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የፍስልተኞች ድርጅት አማካይነት፣ ወደ ሌላ ተቀባይ ሀገር የመሄድና የጥገኝነት መብታቸው ሊጠበቅ የሚችልበት አግባብ እንደሚኖር የኮስታሪካ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል መንግሥት 6 ሺሕ የአገር ውስጥ ገቢ ሠራተኞችን ከሥራ አሰናበተ

ሳግ እየተናነቃቸው የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊ፣ ቁጥራቸው 6 ሺሕ የሚጠጋ ሠራተኞች ከሥራ እንደሚባረ
የአሜሪካ ድምፅ

የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል መንግሥት 6 ሺሕ የአገር ውስጥ ገቢ ሠራተኞችን ከሥራ አሰናበተ

ሳግ እየተናነቃቸው የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊ፣ ቁጥራቸው 6 ሺሕ የሚጠጋ ሠራተኞች ከሥራ እንደሚባረሩ ይፋ እንዳሳወቋቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ለሮይተርስ የዜና ወኪል በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል። ይህም ሥራ በሚበዛበት የግብር መክፈያ ሰሞን የተወሰደ እርምጃ ከ6 በመቶ በላይ የሚሆነውን የድርጅቱን የሰው ኃይል የሚያሳጣ መሆኑ ተመልክቷል። የሰው ኃይል ቅነሳው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የመንግሥት ሠራተኞችን ቁጥር ለመቀነስ የያዙት ጥረት አካል ሲሆን፣ የባንኮችን ሥራ የሚቆጣጠሩ፣ የደን ጥበቃ እና እንክብካቤ ሠራተኞች፣ የሮኬት ሳይንስ አዋቂ ሳይንቲስቶች እና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ላይ የተነጣጠረ መሆኑ ታውቋል። ይህን የማስፈጸሙም ሥራ የሚመራው በፕሬዝደንት ትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ወቅት ዋነኛ ለጋሽ በነበሩት ቢሊነሩ ኢላን መስክ ነው። መስክ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት ‘ኦክሰን ሂል’ ውስጥ በሚገኘው ናሽናል ሃርበር የተባለ ሥፍራ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሪፐብሊካን የፖለቲካ ፓርቲ አቀንቃኞች እና ባለሥልጣናት የሚሳተፉበት ዓመታዊ ጉባኤ መድረክ የመንግሥታቸውን ወጪ ለመቀነስ ባራመዷቸው ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደሩ ፖሊሲዎቻቸውን ከሚታወቁት የአርጀንቲና ፕሬዝደንት ጃቪየር ሚሌ እርምጃቸውን ጥንካሬ ለማሳየት የብረት መጋዝ በስጦታ ሲቀበሉ ታይተዋል። «ይህ ቢሮክራሲ የሚቆረጥበት መጋዝ ነው» አሉ መስክ የመንግሥት ሠራተኞችን ቁጥር በከፍተኛ መጠን የቀነሱበትን እርምጃ ለማመላከት በሚመስል አኳሃን፣ መድረኩ ላይ እንደቆሙ ብርቱውን መቁረጫ ወደ ላይ ከፍ አድርገው እያሳዩ። የሠራተኛ ማኅበራት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ሠራተኞች ሥራቸውን እንደሚያጡ እየተነገራቸው ያለበትን በጅምላ ከሥራ የማስወጣት ርምጃ ለማስቆም በፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። ይሁንና አንድ ጉዳዩን ያዩ የዋሽንግተን የፌዴራል ዳኛ በትላንትናው ዕለት በሰጡት ብይን ለአሁኑ መቀጠል እንደሚችሉ የሚፈቅድ ብይን አሳልፈዋል። የአገር ውስጥ ገቢ የባለሞያዎች ቅጥር ድሬክተር ክሪስቲ አርምስትሮንግ 6ሺሕየሚጠጉ ባልደረቦቻቸው ከድርጅቱ የሰው ኃይል እንደሚቀነሱ በስልክ ባሳወቁበት ወቅት፤ ‘እምባ እየተናነቃቸው’ እንደነበር መልዕክቱ በተላለፈበት ወቅት የነበሩ አንድ ሠራተኛ ገልጸዋል። እርስ በርስ እንዲደጋገፉ ያበረታቱት ኃላፊ «በእጅጉ በስሜት ተነክተው እንደነበር» መልዕክቱን የተከታተሉት ሠራተኛ አክለው አመልክተዋል። አንድ የጉዳዩ አዋቂ እንደገለጹት፤ የአገር ውስጥ ገቢ መሥሪያ ቤቱ ቅነሳው በአጠቃላይ 6,700 ሠራተኞችን እንደሚመለከት እና በዋናነትም የባለ ጸጋ ግብር ከፋዮችን የግብር ኃላፊነት ለማስፈጸም በተያዘ ጥረት ለማጎልበት በሞከሩት በዲሞክራቱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሥራ ማስፋፊያ ዕቅድ በተቀጠሩ የድርጅት ሰራተኞች ላይ የተነጣጠረ መሆኑ ተጠቁሟል። ከሪፐብሊካን ወገን የሆኑ በተራ አሜሪካውያን ላይ አላስፈላጊ ጫና ይፈጥራል በሚል ርምጃውን ተቃውመዋል። የግብር ሰብሳቢው ድርጅት በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው 100 ሺሕ የሚጠጉ ሠራተኞች ሲኖሩት፣ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2021 ባይደን ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት የነበት ሠራተኞች ቁጥር 80 ሺሕ ነበር። ከየትኛውም ፓርቲ ወገን ያልሆኑ የበጀት ጉዳይ አዋቂዎች ባይደን እንዲያድግ ያደረጉት የሠራተኛ ኃይል የመንግስቱን ገቢ በማሳደግ፣ በትሪሊዮን ዶላር የሚሰላውን የበጀት ክፍተት ለማጥበብ ያግዛል የሚል ግምት ሰጥተው ነበር። የሠራተኛ ኃይሉን ለመቀነስ የተወሰደውን ርምጃ “ይህ እንደ እውነቱ የአገር ውስጥ ገቢ መሥሪያ ቤቱ በባለ ጸጋ ግብር ከፋዮችን ሳይሆን፤ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ላይ ትኩረት ማድረግ የመረጠ ድርጅት እዲሆን ያደርገዋል” ብለዋል፡፡ የፒትስበርግ ዩኒቨርሲቲ የግብር ጉዳዮችን የሚመለከተው ሕግ መምህሩ ፕሮፌሰር ፊሊፕ ሃክኒ። «እጅግ አሳዛኝ ድርጊት ነው» ሲሉ አክለዋል፤ ካሁን ቀደም የአገር ውስጥ ገቢ መሥሪያ ቤቱ ነገረ ፈጅ በመሆን ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሃክኒ። ከሥራ ከተባረሩት ውስጥ የግብር ክፍያ ሰብሳቢዎች፣ የደንበኛ አገልግሎት ፣ሠራተኞች፣ የግብር ክፍያ ይግባኝ የሚሰሙ ባለሞያዎች እና እንዲሁም የመረጃ ቴክኖሎጂ ሰራተኞች ይገኙባቸዋል። ርምጃው በ50ውም የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ውስጥ ባሉ ሠራተኞች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል ሲሉ ሮይተርስ ያነጋገራቸው ምንጮች አመልክተዋል። የአገር ውስጥ ገቢ መሥሪያ ቤት በበኩሉ ለቀረበለት ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። ዓመታዊው የግብር ሂሳብ የሚወራረድበት ወቅት ገና በመጋመስ ላይ በመሆኑ፤ አይርኤስ ከሌሎች የመንግስት ተቋማት የተሻለ ጥንቃቄ የታየበት አካሄድ ተከትሏል፤ ያሉት ምንጮች፣ በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ስሌት መሰረት እስከ ሚያዝያ 15 አጋማሽ በሚዘልቀው የሥራው ማጠናቀቂያ ድረስ ከ140 ሚሊዮን በላይ በግል ግብር የሚከፍሉ ሰዎችን የግብ ክፍያ ተመላሽ ማስፈጸም ስለሚጠበቅበት፣ ለዚያ ሥራ ወሳኝ ናቸው የተባሉትን በርካታ ሺሕ ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው እንደሚያቆይ አንድ ምንጭ ጠቁመዋል። የትራምፕ አስተዳደር የፌዴራል ሠራተኞችን ከሥራ የማሰናበቱ ርምጃ ለሥራ ኃላፊነቱ አዲስ በሆኑ እና ረጅም ጊዜ ካገለገሉ ሠራተኞች አንጻር ሲታይ አነስተኛ ጥበቃ ያላቸው ሰራተኞች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመልክቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የትራምፕ ዋይት ሀውስ የዩናይትድ ስቴትስ የፖስታ አገልግሎት መስሪያ ቤትን የሥራ አመራር ለመበተን እና ራሱን በራሱ የሚያስተዳድረውን ድርጅት በንግድ ጉዳዮች ሚንስቴር ሥር እንዲተዳደር ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ዋሽንግተን ፖስት ትላንት ሃሙስ ዘግቧል። በሌላ በኩል “በካንሳስ ከተማ የሚገኘው የአይአርኤስ ጽሕፈት ቤት የሙከራ ጊዜያቸውን ያላጠናቀቁ ሠራተኞች ስንብታቸውን የሚያረግጋጠውን ደብዳቤ ከሚቀበሉበት የኢሜል መልዕክት መላላኪያ በስተቀር፤ ማናቸውንም ሌሎች ተግባራት የሚያከናውኑባቸው የኮምፒውተሮቻቸው ቁልፎች በሙሉ ተዘግተው ነው የጠበቋቸው” ሲሉ የፌድራሉ የሠራተኛ ማኅበር የአካባቢው ጽሕፈት ቤት ተጠሪ ሻነን ኢሊስ ተናግረዋል። ኤሊስ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል "የአሜሪካ ሕዝብ በእውነት ሊገነዘበው የሚገባው ነገር በአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት የሚሰበሰበው ገንዘብ በኅብረተሰባችን ውስጥ በየቀኑ የምንገለገልባቸውን የተለያዩ ፕሮግራሞችን የሚደግፉ ናቸው” ብለዋል። ዋይት ሀውስ ቁጥሩ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ከሚደርሰው የመንግሥት ሠራተኛ ምን ያህሉን በከፍተኛ ቁጥር በጅምላ ከሚፈጸመው ከሥራ የማሰናበት ርምጃው እንደሚያካትት አላስታወቀም። ቁጥራቸው 75 ሺሕ የሚጠጉ ሠራተኞች ራሳቸውን በፈቃዳቸው ከሥራ እንዲያሰናብቱ የቀረበውን ዕቅድ መፈረማቸው ባለፈው ሳምንት ተዘግቧል። አስተዳደሩ የያዘው የወጪ ቅነሳ ዕቅድ ‘መንግሥት የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶች ሊጎዳ ይችላል’ በሚል አያሌ አሜሪካውያን የሚጨነቁ መሆናቸውን ሮይተርስ እና ኢፕሶስ በጋራ ያሰባሰቡት እና ትላንት ሐሙስ ይፋ የተደረገ የሕዝብ አስተያየት መረጃ ጠቁሟል።

ሐማስ የእስራኤላዊዋን አስከሬን የማይመልስ ከሆነ “ዋጋ ይከፍላል” ሲሉ ኔታንያሁ አስጠነቀቁ

ሐማስ በሰላም ስምምነቱ መሠረት ሺሪ ቢባስ የተባለችውን እስራኤላዊ እናት አስከሬን የማይመልስ ከሆነ “ዋጋ ይከፍላል” ሲሉ የእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃ
የአሜሪካ ድምፅ

ሐማስ የእስራኤላዊዋን አስከሬን የማይመልስ ከሆነ “ዋጋ ይከፍላል” ሲሉ ኔታንያሁ አስጠነቀቁ

ሐማስ በሰላም ስምምነቱ መሠረት ሺሪ ቢባስ የተባለችውን እስራኤላዊ እናት አስከሬን የማይመልስ ከሆነ “ዋጋ ይከፍላል” ሲሉ የእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ዛሬ ዓርብ አስጠንቅቀዋል። “ሺሪን ጨምሮ በሕይወት ያሉም ሆነ የሌሉ እስራኤላውያንን ለማስመለስ በቁርጠኝነት ርምጃ እንወስዳለን። ለዚህ ጨካኝና ሰይጣናዊ ለሆነ እንዲሁም ስምምነቱን ለጣሰ ተግባር ሐማስ ሙሉ ዋጋውን እንዲከፍል እናደርጋለን” ሲሉ ኔታንያሁ በቪዲዮ ባስተላልፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ሐማስ በትላንትናው ዕለት አራት ታጋቾችን የለቀቀ ሲሆን እነዚህም በታገተበት ወቅት የዘጠኝ ወር ሕፃን የነበረው ክፊር ቢባስ፣ የአራት ዓመት ወንድሙ አሪየል ቢባስ ይገኙበታል። የእናታቸው ሺሪ ቢባስ ነው ተብሎ የተመለሰው አስከሬን ግን የእርሷ እንዳልሆነ የእስራኤል ሠራዊት ዛሬ ዓርብ አስታውቋል። “ሐማስ አባትና እናትን እንዲሁም ሁለት ልጆቻቸውን ማገቱ ብቻ ሳይሆን፣ በአሳዛኝ ሁኔታ የእናቷ አስከሬን ነው በሚል የአንድ የጋዛ ነዋሪን ሴት አስከሬን ልኳል” ሲሉ አክለዋል ጠቅላይ ምኒስትሩ። ሐማስ በበኩሉ ሽሪ ቢባስ ተይዛ በነበረችበት ስፍራ እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት በፍርስራሹ ውስጥ አስከሬኗ ከሌላ አስከሬን ጋራ ተነካክቷል ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል።

በትግራይ በጸጥታ ኃይሎች እና ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 17 ሰዎች መጎዳታቸውን ተገለጸ

በትግራይ ክልል ሰሓርቲ በተባለች ወረዳ የአንድ ቀበሌ አስተዳዳሪ ማኅተም በኃይል ነጥቀዋል የተባሉ የፀጥታ አባላት ወሰዱት በተባለ ርምጃ 17 ሰዎች መጎዳታቸውን
የአሜሪካ ድምፅ

በትግራይ በጸጥታ ኃይሎች እና ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 17 ሰዎች መጎዳታቸውን ተገለጸ

በትግራይ ክልል ሰሓርቲ በተባለች ወረዳ የአንድ ቀበሌ አስተዳዳሪ ማኅተም በኃይል ነጥቀዋል የተባሉ የፀጥታ አባላት ወሰዱት በተባለ ርምጃ 17 ሰዎች መጎዳታቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ተናገሩ። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ፣ የሰራዊቱ አባላት ጣልቃ መግባታቸውን ገለፆ፣ “እንዲኽ ያለ ጣልቃ ገብነት ክልሉን ወደ ከባድ ቀውስ ያስገባዋል” ብሏል። በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በወረዳ አስተዳዳሪነት የተሾሙት፣ አቶ አታኽልቲ ግርማይ ለአሜሪካ ድምፅ “የፀጥታ አባላት ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ወግነው ወደ ሕዝብ መተኮስ ሳይኾን፣ የሥራ ድርሻቸው ሰላም እና ፀጥታ መጠበቅ ነው”ብለዋል። በድርጊት ፈጻሚነት የተወቀሰውና፣ “አርሚ 26” ተብሎ የሚጠራው የክልሉ የፀጥታ መዋቅር አዛዥ ኮሌኔል ሓጎስ ገብረ፣ የፀጥታ አባላቱ ወደ አከባቢው የገቡት በሕዝብ ጥሪ መኾኑን ገልፀው “በነዋሪዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ የለም” ብለዋል። “ክሱ የሰራዊታችን ስም ማጥፋት ነው” ሲሉም ምላሽ ሰጥተዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአሜሪካ የዋጋ ግሽበት እየጨመረ መሄዱን ኢኮኖሚስቶች እየተከታተሉት ነው

በዩናይትድ ስቴትስ የምግብ፣ የነዳጅ፣ የመኖሪያ ቤቶች እና የሌሎች ሸቀጦች ዋጋ ሲንር፣ በጥር ወር የዋጋ ግሽበቱ ጨምሯል። የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ቬሮኒካ ባልደ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ የዋጋ ግሽበት እየጨመረ መሄዱን ኢኮኖሚስቶች እየተከታተሉት ነው

በዩናይትድ ስቴትስ የምግብ፣ የነዳጅ፣ የመኖሪያ ቤቶች እና የሌሎች ሸቀጦች ዋጋ ሲንር፣ በጥር ወር የዋጋ ግሽበቱ ጨምሯል። የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ቬሮኒካ ባልደራስ ኢግሌሲያስ የትረምፕ አስተዳደር የዋጋ ንረትን ለማውረድ ምን ማድረግ እንዳለበት ኢኮኖሚስቶችን አነጋግራለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሴኔት ሪፐብሊካን ከትረምፕ በተቃራኒ የድንበር በጀቱን ለማጽደቅ እየገፉ ነው

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በአሜሪካ የሕግ አውጪው ሸንጎ (ሴኔት) ያሉ ሪፐብሊካን አባላት በስደተኞች፣ ኃይል እና መከላከያ ላይ ያተኮረውን የበጀት ረቂቃቸውን
የአሜሪካ ድምፅ

የሴኔት ሪፐብሊካን ከትረምፕ በተቃራኒ የድንበር በጀቱን ለማጽደቅ እየገፉ ነው

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በአሜሪካ የሕግ አውጪው ሸንጎ (ሴኔት) ያሉ ሪፐብሊካን አባላት በስደተኞች፣ ኃይል እና መከላከያ ላይ ያተኮረውን የበጀት ረቂቃቸውን ወደ ጎን ብለው፣ ከተወካዮች ምክር ቤት የሚቀርበውን ሰፋ ያለ የበጀት ሐሳብ እንዲቀበሉ ቢጠይቁም፣ የሴኔቱ የሪፐብሊካን አባላት ግን በያዙት ሐሳብ እንደሚገፉበት አስታውቀዋል። ትረምፕ በተወካዮች ምክር ቤት የቀረበውንና በትሪሊየን ዶላር የሚቆጠር የታክስ እፎይታ ጭምር የሚሰጠውን ሰፋ ያለ የበጀት ሐሳብ እንደሚመርጡ ቢያስታውቁም፣ በሴኔቱ የሚገኙ የሪፐብሊካን አባላት ግን በያዙት አቋም እንደሚገፉ በሴኔቱ አብዛኛ መቀመጫ የያዘው የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ጃን ቱን አስታውቀዋል። በሴኔቱ የቀረበው “ቀጠን ያለ” የበጀት ሐሳብ፣ ትረምፕ ያሰቡትን የታክስ ቅነሳ ለመተግበር፣ ወደፊት ሌላ በጀት በምክር ቤቱ ለማጽደቅ በሚሞክሩበት ጊዜ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት በምክር ቤቱ የሪፐብሊካን አባላት ዘንድ አድሯል። ምክንያቱ ደግሞ ፓርቲው በጠባብ ልዩነት፣ ማለትም 218 ለ215 መቀመጫዎች ብቻ የበላይነት የያዘ ስለሆነና ከሁለት ዓመታት በኋላ የም/ቤት አባላት ምርጫ ሲካሄድ የበላይነቱን ሊያጡ ይችላሉ በሚል ስጋት ነው። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ሁለቱም የሕግ አውጪ ም/ቤቶች “አንድ ትልቅ ሸጋ በጀት ረቂቅ” አጽድቀው በሃገሪቱ የዕርቅ ሂደቱን እንዲጀምሩ ጥሪ አድርገዋል። ከምክትል ፕሬዝደንት ጄዲ ቫንስ እና ከሴኔት ሪፐብሊካን ጓዶቻቸው ጋራ ስብሰባ ያደረጎት የሴኔቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ጃን ቱን፣ “ቀጠን ባለው” የበጀት ረቂቅ እንደሚገፉበት አስታውቀዋል። “በስተመጨረሻ አንድም ሆነ ሁለት የበጀት ረቂቅ አውጥተን ፕሬዝደንቱ ያሰቡትን ከዳር እናደርሳለን” ያሉት ጃን ቱን፣ ሴኔቱ ዛሬ ሐሙስ ድምጽ ይሰጣል ብለው እንደሚጠብቁ አስታውቀዋል። ትረምፕ የተቃውሞ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን ተከትሎ፣ አንዳንድ የሪፐብሊካን ዓባላት በየትኛው መንገድ መቀጠል እንዳለባቸው ግራ ተጋብተዋል ሲል የሮይተርስ ሪፖርት አመልክቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዲሞክራቶቹ ለረጅም ትግል እንደተዘጋጁ አስታውቀዋል። “የበጀት ረቂቁ የፕሬዝደንቱ ወዳጅ ለሆኑ ቢሊየነሮች የታክስ እፎይታ ለመስጠት ያለመ ነው” ሲሉ የሴኔት ዲሞክራቶች መሪው ቻክ ሹመር ክስ አሰምተዋል። ሴኔቱ ባቀረበው የበጀት ረቂቅ ውስጥ፣ ለአራት ዓመታ የ340 ቢሊዮን ዶላር፣ በየዓመቱ 85 ቢሊዮን ዶላር ድንበር ጥበቃውን ለማጥበቅና የትረምፕን ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የሚያደርጉትን ጥረት፣ የኅይል ፖሊሲን ለመቀየር  እንዲሁም የመከላከያ ወጪን ለመጨመር የሚል ተካቷል። በተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው በጀት ደግሞ፣ 4.5 ትሪሊየን የታክስ ቅነሳና፣ 2 ትሪሊየን ዶላር የወጪ ቅነሳ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት እንዲሁም ለኃይል የፖሊሲ ልውጦች የሚውል ገንዘብን ታሳቢ ያደርጋል።

ሃማስ የአራት ታጋቾች አስከሬን ለእስራኤል አስረከበ

ሃማስ በዛሬው ዕለት ደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ ውስጥ ለእስራኤል ኃይሎች ያስረከባቸው አራት እስራኤላዊ ታጋቾችን አስከሬን የያዙ ሳጥኖች በቀይ መስቀል ተሽከርካሪ
የአሜሪካ ድምፅ

ሃማስ የአራት ታጋቾች አስከሬን ለእስራኤል አስረከበ

ሃማስ በዛሬው ዕለት ደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ ውስጥ ለእስራኤል ኃይሎች ያስረከባቸው አራት እስራኤላዊ ታጋቾችን አስከሬን የያዙ ሳጥኖች በቀይ መስቀል ተሽከርካሪዎች ወደ ቴላቪቭ ተጓጉዘዋል። ባንዲራዎች እና ጹሑፎች የሰፈሩባቸው ጨርቆች በታዩበት መድረክ ሃማስ አስከሬኖቹን የተሸከሙትን አራት ጥቋቁር ሳጥኖች ባስረከበበት በዚህ ሥነ ስርዐት በብዙ መቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች ተገኝተዋል። አንዳንዶች ካነገቧቸው የተለያዩ መልዕክቶች ከሰፈረባቸው ጨርቆች አንዱ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጦር ወንጀለኝነት ይከሳል። የእስራኤል የአየር ጥቃት ለታጋቾቹ ሞት ‘ምክንያት ሆኗል’ ሲልም ይወነጅላል። ቀይ መስቀል አራቱን የሬሳ ሳጥኖች ለእስራኤል ጦር ሠራዊት ማስረከቡን እና የሟቾቹን ማንነት ለማረጋገጥ አስከሬኖቹ ቴል አቪቭ ወደሚገኘው ብሔራዊ ልዩ ምርመራ ማዕከል መወሰዳቸውን የኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ለእስራኤል ተላልፈው የተሰጡት አስከሬኖች፤ በታገቱበት ወቅት የዘጠኝ ወር ዕድሜ የነበረውን ጨቅላ ልጃቸውን እና የታላቅ ወንድሙን የአራት  ዓመቱን አርየል ቢባስን፤ የአባታቸውን የክፊር ቢባስን እና እንዲሁም የእናታቸውን ሺሪ ቢባስን ጨምሮ የአራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ይገኙበታል።  የቢባስ ቤተሰብ አባላት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ጥቅምት 7 ቀን 2023 ዓ.ም  ከኪቡትዝ ኒር ኦዝ በሃማስ ታጣቂዎች ታግተው ከተወሰዱት ውስጥ ናቸው። የእገታውን ትዕይንት የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ሺሪ ቢባስ ሁለቱን ወንዶች ልጆቻቸውን በብርድ ልብስ ሲሸፋፍኑ እና በታጣቂዎች በኃይል እየተገፉ ሲወሰዱ ያሳያል።

ዩናይትድ ስቴትስ የላከቻቸው አብዛኞቹ  ፍልሰተኞች ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማታቸውን ፓናማ ተናገረች

በቅርብ ቀናት ከዩናይትድ ስቴትስ ፓናማ ወደሚገኙ ማሸጋገሪያ ጣቢያዎች ከተላኩት ፍልሰተኞች ውስጥ ከግማሽ በላዩ በፈቃደኝነት ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ የላከቻቸው አብዛኞቹ  ፍልሰተኞች ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማታቸውን ፓናማ ተናገረች

በቅርብ ቀናት ከዩናይትድ ስቴትስ ፓናማ ወደሚገኙ ማሸጋገሪያ ጣቢያዎች ከተላኩት ፍልሰተኞች ውስጥ ከግማሽ በላዩ በፈቃደኝነት ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማታቸውን የፓናማ የደኅንነት ሚንስትር ተናገሩ፡፡ የሚበዙት የእስያ ወይም የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገር ተወላጆች መኾናቸው ተመልክቷል፡፡ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር በሕገ ወጥ ፍልሰት ላይ  እየወሰደ ባለው ርምጃ በቅርቡ ፍልሰተኞቹን  በሦስት አውሮፕላኖች አሳፍሮ ወደ ፓናማ ልኳቸዋል፡፡ ቁጥራቸው ወደ 299 የሚጠጋው ፍልሰተኞች ፓናማ ሲቲ በሚገኝ ሆቴል በሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጥበቃ ሥር ሆነው  እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) እና በመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን (ዩ ኤን ኤች ሲ አር) በኩል  የገንዘብ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን የፓናማው ሚንስትር ፍራንክ አብሬጎ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡ «171 ፍልሰተኞች ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነዋል፡፡ የተቀሩትም ተመድ መጓጓዣቸውን እንዳዘጋጀላቸው ቀስ በቀስ ይመለሳሉ» ብለዋል ሚንስትሩ፡፡ እስከዚያው በደቡባዊ ፓናማ ዳሪየን ጋፕ በሚባለው ደን አቅራቢያ  ወደሚገኝ  መጠለያ ጣቢያ  ሳይዛወሩ እንደማይቀር ተጠቁሟል፡፡ ባለፈው ወር ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋራ የተነጋገሩት የፓናማ ፕሬዝደንት ሆዜ ራኡል ሙሊኖ በሐምሌ ወር ከዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ደኅንነት ሚንስቴር ጋራ የተደረሰውን ስምምነት በማስፋት የቬንዙዌላ፣ ኢኳዶር እና ኮሎምቢያ ፍልሰተኞችንም ወደፓናማ ለመመለስ እንዲያስችል ለማድረግ እንደሚቻል ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡ 

መንግሥት: ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን እንደቻለች ማስታወቁ «ከአሜሪካ ርዳታ መቆም ጋራ በተገናኘ አይደለም፤» አለ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን እንደቻለች ይፋ ያደረገችበት መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ወራት የውጭ ርዳታ ለማቆም ካስተላለፈችው ውሳኔ ጋራ የተገናኘ አ
የአሜሪካ ድምፅ

መንግሥት: ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን እንደቻለች ማስታወቁ «ከአሜሪካ ርዳታ መቆም ጋራ በተገናኘ አይደለም፤» አለ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን እንደቻለች ይፋ ያደረገችበት መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ወራት የውጭ ርዳታ ለማቆም ካስተላለፈችው ውሳኔ ጋራ የተገናኘ አይደለም፤ ሲል መንግሥት አስታውቋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለአሜሪካ ድምፅ በጽሑፍ በሰጠው ምላሽ፣ አኹን ኢትዮጵያ ራሷን የቻለችው፣ በአንድ የምርት ዓይነት ማለትም በስንዴ እህል ምርት እንደኾነ አስታውሷል። በአገሪቱ ውስጥ፣ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች መኖራቸውም፣ በብሔራዊ ደረጃ የምግብ እጥረት ስለ መኖሩ አያሳይም፤ በማለት አብራርቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ትላንት ማክሰኞ፣ የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን ችላለች፤ ሲል አስታውቋል። ኢትዮጵያ፣ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማርካት፣ በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጪ ስንዴ ከውጭ ታስገባ እንደነበር ያወሳው መግለጫው፣ አሁን ይህን ማስቀረት መቻሉን ጠቁሟል። «ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገር ውስጥ ምርት ላይ ከፍተኛ ጭማሬ በመታየቱ ኢትዮጵያ ከውጭ በሚገባ የስንዴ ምርት ላይ ጥገኛ መኾኗ ቀርቷል፤» ሲል አመልክቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት መግለጫ የወጣው፣ ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ርዳታ ለሦስት ወራት ለማቆም የደረሰችበትን ውሳኔ ካስታወቀች ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነው። ኾኖም፣ በዚኽ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፦ ምግብ፣ መድኃኒት እና ሌሎች የአጣዳፊ ጊዜ ድጋፎች ከዕቀባው ውጪ እንዲኾኑ ትእዛዝ መተላለፉን ግልጽ አድርገዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ ሕይወት አድን መርሐ ግብሮች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ የሚያስችል “ጥቅል ማሳሰቢያ” መስጠታቸውንም ገልጸዋል። “ምግብ፣ መድኃኒት ወይም ማንኛውም ሕይወት አድን የኾነ አጣዳፊ አገልግሎት በዕቀባው አይካተትም፤« ሲሉም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ክፍል፣ በጽሕፈት ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው ምላሽ፣ አገሪቱ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን ይፋ ያደረገችበት መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ወራት የውጭ ርዳታ ለማቆም ካስተላለፈችው ውሳኔ ጋራ የተገኘ አለመኾኑን አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ይህን ስኬት በማሳየት፣ በማደግ ላይ ያሉ ሌሎች ሀገራትም፣ ራስን የመቻል መንገድ እንዲከተሉ ይነቃቃሉ ብላ ተስፋ እንደምታደርግም አመልክቷል። ጽሕፈት ቤቱ በትላንቱ መግለጫው፣ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ምርት መጠን እያደገ መሞጣቱንም ገልጿል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022/23 የምርት ዘመን፣ ኢትዮጵያ 15ነጥብ1 ሚሊየን ቶን ስንዴ እንዳመረተች ጠቁሞ፣ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ወደ 23 ሚሊየን ቶን ማደጉን ጠቅሷል። አገሪቱ በስንዴ ምርት ራሷን ቻለች ማለት፣ ስንዴ ከውጭ መግባቱ ይቆማል ማለት እንዳልኾነ ግን መግለጫው አስረድቷል። በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ ርዳታ ተቋማት፣ አኹንም ከሀገር ውስጥ ገበያ ስንዴ ከመግዛት ይልቅ ከውጭ ሀገራት ማስገባትን ሊመርጡ እንደሚችሉ ነው የጠቆመው። የሰብአዊ ርዳታ ተቋማት፣ ስንዴንና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚገዙት፦ ከመንግሥት ጋራ በመቀናጀት፣ በአገሪቱ የምግብ ድጋፍ የሚያሰፈልጋቸውን ዜጎች ለመድረስ ነው። እ.አ.አ. በመጋቢት ወር 2024 በመንግሥት እና በዓለም አቀፍ አጋሮች ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ ሰነድ፣ በተፈጥሮ እና በሰው ሠራሽ ችግሮች ምክንያት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ እንደሚጠብቁና ይህንም ለማሟላት ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ አመልክቷል። ገንዘቡ የተጠየቀው፣ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸውን 10ነጥብ4 ሚሊዮን ዜጎችን ፍላጎት ለማሟላት ጭምር እንደኾነ ሰነዱ አመልክቷል። አገሪቱ በስንዴ ራሷን መቻሏን ማስታወቋ፣ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች መኖራቸውን ከሚጠቅሰው ከዚኽ ሰነድ ጋራ እንዴት እንደሚጣጣም የተጠየቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬዝዳንት ክፍል ማብራሪያ ሰጥቷል። በአገሪቱ የተከሠቱ ድርቅ፣ ጎርፍ እና የመሬት መንቀጥቀጥን የመሳሰሉ አደጋዎች የተረጂዎችን ቁጥር እንደሚጨምሩ ጠቅሷል። ፈተናዎቹ ግን፣ አገሪቱ በምግብ ራሷን ለመቻል ያላትን ቁርጠኘነት አልቀነሱትም፤ ብሏል። ኢትዮጵያ አኹን ራሷን እንደቻለች የገለጸችው በአንድ የምርት ዓይነት ማለትም በስንዴ እንደኾነም አስታውሷል። የምግብ ዋስትና አለመረጋገጥን፣ ከአገራዊ የምግብ ዕጥረት ጋራ አለመደበላለቅ እንደሚያስፈልግም አስገንዝቧል። ከመቶ ሚሊዮን በላይ ከኾነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ »ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች አሉ« ማለት፣ »በምንም መንገድ በአገር አቀፍ ደረጃ የምግብ እጥረት መኖሩን አያሳይም፤" ብሏል የጽሕፈት ቤቱ መግለጫ። ዩናይትድ ስቴትስን በመሳሰሉ የበለጸጉ ሀገራትም፣ በምግብ ድጋፍ እና በሌሎች የርዳታ ፕሮግራሞች ላይ የሚተማመኑ ሰዎች መኖራቸውን የጠቀሰው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ክፍል፣ ያ ግን አገራዊ የምግብ እጥረትን አያመለክትም፤ ብሏል። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሞያ መሸሻ ዘውዴ፣ የመንግሥት መግለጫ የሚያመለክተው፣ ወቅታዊውን የስንዴ ምርት መጠን እንደኾነ ጠቁመዋል። ራስን ለመቻል ዋስትና የሚኾነው ግን፣ የተገለጸው የምርት መጠን ቀጣይነት እንደሚኖረው ማረጋገጥ ሲቻል እንደኾነ ሳያሳስቡ አላለፉም። መንግሥት ይፋ ያደረገው መረጃ አንድን የምርት ዓይነት ብቻ የተመለከተ እንደኾነ የጠቀሱት አቶ መሸሻ፣ በስንዴ ራስን መቻል ማለት በአጠቃላይ የምግብ እህል ምርት ራስን ከመቻል የተለየ መኾኑን አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ስንዴ ከውጭ መግዛት ያቆመችው፣ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ እንደኾነም፣ የመንግሥት መግለጫ አክሎ አውስቷል።

እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ አምስት ቦታዎች ወታደሮቿን አስቀምጣለች

የእስራኤል ወታደሮች ከታጣቂው ሄዝቦላህ ጋራ በተደረሰበት የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት፣ አካባቢውን ለቀው መውጣት በሚገባቸው የዛሬው ማክሰኞ ቀነ ገደብ 
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ አምስት ቦታዎች ወታደሮቿን አስቀምጣለች

የእስራኤል ወታደሮች ከታጣቂው ሄዝቦላህ ጋራ በተደረሰበት የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት፣ አካባቢውን ለቀው መውጣት በሚገባቸው የዛሬው ማክሰኞ ቀነ ገደብ  ከአንዳንድ የደቡብ ሊባኖስ አካባቢዎች ለቀው አለመውጣታቸው ተነገረ፡፡ እስራኤል በክልሉ ከሚገኙ አንዳንድ መንደሮች ለቃ ብትወጣም፣ የሰሜናዊ እስራኤልን የተወሰኑ ክፍሎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ናቸው ካለቻቸው አምስት ቦታዎች ኃይሏን ያላስወጣች መሆኑን ተናግራለች። የሊባኖስ ፕሬዝደንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፓርላማ አፈ-ጉባኤ ዛሬ ማክሰኞ በሰጡት የጋራ መግለጫ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል በአስቸኳይ እንድትወጣ እንዲጠይቅ ጥሪ አቅርበዋል። መግለጫው «በማንኛውም ስንዝር የሊባኖስ ግዛት ውስጥ የእስራኤል ጦር መገኘት ወረራ ነው፣ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት የሚያስከትላቸው መዘዞች አሉት» ሲል ገልጿል። የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሂዝቦላህ ከእስራኤል ድንበር ርቆ እንዲሄድ እና የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ከሊባኖስ ወታደሮች ጋራ በተለቀቀው የመከላከያ ቀጠና እንዲሰማሩ ከማድረግ ጋራ፣ እስራኤል በጥር መጨረሻ ለቃ እንድትወጣ ይጠይቃል፡፡ የተራዘመው ቀነ-ገደብ ወደ ዛሬ ማክሰኞ እንዲገፋ መደረጉም ተመልክቷል፡፡ ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሊባኖስ ተወካይ ጄኒን ሄኒስ-ፕላስቻርት እና በሊባኖስ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አሮልዶ ላዛሮ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተግባራዊ የሚደረግበት ሌላ የተራዘመ ቀን መኖሩ “እኛ ይሆናል ብለን ያሰብነው አይደለም” ብለዋል። መግለጫው አክሎም «ሁለቱም ወገኖች ግዴታቸውን እንዲወጡ እንጠይቃለን። በመንደሮቻቸው እና በከተሞቻቸው ላይ እየደረሰ ካለው መጠነ ሰፊ ውድመት ጋር የሚታገሉት የደቡብ ሊባኖስ ማህበረሰቦች፣ እንዲሁም ቤታቸውን ለቀው ለመውጣት የተገደዱት የሰሜን እስራኤል ነዋሪዎች ሁኔታ በአንድ ጀምበር የማይፈታ እና መፍትሄዎቻቸው ከወታደራዊ ዘመቻዎች ሊገኙ አይችሉም ።” ብሏል፡፡ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ሠራዊቱ »ሊባኖስ ውስጥ ከጦርነት ቀጠና ውጭ፣ በሚቆጣጠራቸው አምስት ቦታዎች እንደሚቆይ እና ማንኛውም የሂዝቦላ ጥሰት ቢኖር በኃይል እና ያለማወላወል ርምጃ ለመውሰድ መሥራቱን ይቀጥላል" ብለዋል ። በኅዳር ወር መጨረሻ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት፣ በሊባኖስ ከአንድ ዓመት በላይ የቆየውን ጦርነት አስቁሟል። ይህም የተኩስ አቁም ስምምነት ከመደረጉ በፊት በነበሩት ወራት ውስጥ የእስራኤል ወታደሮች ሊባኖስ ውስጥ የምድር ዘመቻ ሲያደርጉ እና በሂዝቦላ ላይ ተደጋጋሚ የአየር ድብደባ አጠናክረው ሲፈጽሙ ቆይተዋል። የጋዛ ሰርጥ የሃማስ ታጣቂዎች ሰሜን እስራኤል ላይ ጥቃት በመፈጸም 1 ሺሕ 200 የሚጠጉ ሰዎችን ከገደሉ እና 250 ታጋቾችን ከወሰዱ አንድ ቀን በኋላ ታጣቂዎቹ እኤአ ጥቅምት 2023 በርካታ ድንበር ተሻጋሪ ሮኬቶችን መተኮስ ጀምረዋል፡፡ እስራኤል በሃማስ ላይ ባካሄደችው አጸፋዊ ጥቃት ከ48 ሺሕ 200 በላይ ፍልስጤማውያንን ተገድለዋል ሲል የጋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል። ሚኒስቴሩ በታጣቂዎችና በሲቪሎች መካከል ያለውን የሟቾችን ቁጥር ለይቶ አላመለከተም፡፡ እስራኤል በበኩሏ ከ17 ሺሕ 000 በላይ ታጣቂዎችን መግደሏን አስታውቃለች። የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያው ምዕራፍ በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ያበቃል። እስካሁን ባለው የተኩስ አቁም ስምምነት፣ ሃማስ 24 ታጋቾችን መልቀቁን እና እስራኤል ከ1 ሺሕ በላይ የፍልስጤም እስረኞችን መፍታቷን ያካትታል።

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን ያስታወቀው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገር ውስጥ ምርት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በመታየቱ ኢትዮጵያ ከው
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን ያስታወቀው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገር ውስጥ ምርት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በመታየቱ ኢትዮጵያ ከውጪ በሚገባ የስንዴ ምርት ላይ ጥገኛ መሆኗ ቀርቷል« ሲል ተናግሯል። ኢትዮጵያ የስንዴ ምርቷ ስላደገ »ስንዴ ከውጭ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑ ቀርቷል« ብላለች።። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጽሕፈት ቤት የወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማርካት በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጪ የውጭ ሀገር የስንዴ ምርት ታስገባ ነበር። መግለጫው  አያይዞም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠ በ2022/23 የምርት ዘመን ኢትዮጵያ 15 ነጥብ 1 ሚሊየን ቶን ስንዴ እንዳመረተች ጠቁሞ የስንዴ ምርቱ መጠን በቀጠለው ዓመት ወደ 23 ሚሊየን ቶን ማደጉን አውስቷል። አያይዞም ሀገሪቱ  በስንዴ ምርት እራሷን መቻሏ  ስንዴ ከውጭ  መግባቱ  ይቆማል ማለት ግን እንዳልሆነ ያሳሰበው መግለጫው በሀገሪቱ ውስጥ የሚሠሩ የሰብአዊ ርዳታ ተቋማት አሁንም ከሀገር ውስጥ ገበያ ስንዴ ከመግዛት ይልቅ ከውጭ ሀገራት ማስገባትን ሊመርጡ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግሥቱ መግለጫ የወጣው  ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ወራት ያህል የውጭ ርዳታን እንዲቆም ባደረገችበት በአሁኑ ወቅት ቢሆንም  የአሜሪካ የውጭ ርዳታ ስለመቆሙ  አላነሳም። የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናት ምግብ፣ መድኃኒት እና ሌሎች የአጣዳፊ ጊዜ ድጋፎች ከዕቀባው ውጪ እንዲሆኑ ትዕዛዝ መተላለፉን ግልጽ አድርገዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ሕይወት አድን መርሐ ግብሮች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ  የሚያስችል “ጥቅል መሳሰቢያ” መስጠታቸውን ገልጸዋል። “ምግብ ፣ መድኃኒት ወይም ማንኛውም ሕይወት አድን  የሆነ አጣዳፊ አገልግሎት በዕቀባው አይካተትም »  ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አስታውቀዋል።

አሜሪካና ሩሲያ ግንኙነታቸውን ለማሻሻልና የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም አብረው ለመሥራት ተስማሙ

አሜሪካና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማሻሻልና የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችለውን ሥራ ለመጀመር ተስማምተዋል። ውሳኔው የመጣ
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካና ሩሲያ ግንኙነታቸውን ለማሻሻልና የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም አብረው ለመሥራት ተስማሙ

አሜሪካና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማሻሻልና የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችለውን ሥራ ለመጀመር ተስማምተዋል። ውሳኔው የመጣው የሁለቱ ወገኖች ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሳዑዲ አረቢያ ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በአሜሪካና “በሩሲያ መመሪያ ሰጪነት የሚደረግ የጦርነት ማቆም ውሳኔን” እንደማይቀበሉ ተናግረዋል። በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማቆም ሁለቱም የጦርነቱ ተሳታፊ ወገኖች በሰጥቶ መቀበል መርህ መሠረት መተው ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ ከሩሲያ ልዑክ ጋራ የተወያዩት የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ ዕለቱ የአስቸጋሪውና የረጅሙ ጉዞ አንድ ርምጃ የተወሰደበት ቀን እንደሆነ አመልክተዋል። “ዛሬ የረጅሙና አስቸጋሪው ጉዟችንን የመጀመሪያ ርምጃ የምንወስድበት ቀን ነው። ነገር ግን እጅግ አስፈላጊ ነው። ፕሬዝደንት ትረምፕ ይህንን ግጭት ለማስቆም ቆርጠዋል። በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ግጭቱ እንዲቆም እንደሚሹ አስታውቀዋል። በሁለት ወይም ሦስት ዓመታት ውስጥ መልሶ ሌላ ግጭት በማይፈጥርበት ሁኔታ ዘላቂ በሆነ መንገድ እንዲቆም ይሻሉ። ይህን መፈጸም ቀላል አይሆንም። ነገር ግን በዓለም ይህን ሂደት ሊያስጀምሩ የሚችሉት እርሳቸው ብቻ ናቸው። ዶናልድ ትረሞፕ ሂደቱን ማስጀመር የሚችሉ ብቸኛ መሪ ናቸው። እናም ዛሬ የሂደቱ  የመጀመሪያ ርምጃ የተወሰደበት ቀን ነው” ብለዋል ሩቢዮ። በንግግሩ ላይ ከተሳተፉት የአሜሪካ ባለሥልጣናት አንዱ የሆኑት የዋይት ሃውስ ብሔራዊ የፀጥታ አማካሪ ማይክ ዋልትስ በበኩላቸው፣ በፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕና በሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መካከል የሚደረገው ስብሰባ መቼ እንደሚሆን ቀን እንዳልተቆረጠለት ተናግረዋል። ድርድሩ ለዩክሬንም ሆነ ለሩሲያ የድንበርና የፀጥታ ማስተማመኛዎች በመሰጠት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ማይክ ዋልትስ አመልክተዋል። ሩሲያ በአሁኑ ወቅት አንድ አምስተኛ የሚሆነውን የዩክሬን ክፍል ትቆጣጠራለች፡፡ አሜሪካ መር የሆነው ጥረት በዩክሬን እና በአውሮፓ በሚገኙ አጋሮች ዘንድ አሳሳቢ በሆነበት በዚህ ወቅት፣ ዋናው ግባቸው “በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑት ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ያለው”  ስምምነት ላይ መድረስ እንደሆነ ማርኮ ሩቢዮ ተናግረዋል። “ዛሬ ከስብሰባው የወጣሁት፣ በምን መንገድና በምን ፍጥነት ጦርነቱ ይቋጭ በሚለው ላይ የጥረት ሂደቱን ለመጀመር ፍላጎት እንዳላቸው በመተማመን ነው። የሚፈለገው ግብ ላይ የምንደርሰው የግጭቱ ተሳታፊዎች መተው ያለባችውን ጉዳዮች ለመተው ፈቃደኛ ከሆኑ ነው። ይህን ስብሰባ ማድረጉ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ከሩሲያ ጋራ  ባለፉት ሶስት ዓመታታ ይህ ነው የሚባል ውይይት አድርገን አናውቅም” ሲሉ አክለዋል የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ። ዛሬ ማክሰኞ ከአሶስየትድ ፕሬስ ጋራ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ሪቢዮ፣ ሁለቱ ወገኖች፣ ማለትም አሜሪካ እና ሩሲያ በሶስት ጉዳዮች ላይ የተቀመጡ ግቦችን ዳር ለማድረስ እንደተስማሙ አስታውቀዋል። እነዚህም፣ በሞስኮና በዋሽንግተን በሚገኙ ኤምባሲዎቻቸው የነበረውን የሰው ኅይል ቁጥር ወደ ነበረበት መመለስ፣ የዩክሬኑን የሰላም ውይይት ለመደገፍ አንድ ከፍተኛ ቡድን ማቋቋም እንዲሁም ይበልጥ የቀረበ ግንኙነትና  የኢኮኖሚ ትብብር ማድረግ የሚሉት እንደሆኑ ሩቢዮ አመልክተዋል። የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እና ሌሎች ከፍተኛ የሩሲያ ባለሥልጣናት የተሳተፉበት ውይይት የመጀመሪያው መሆኑን እና ወዲፊት ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅም ሩቢዮ አመልክተዋል። በውይይቱ የዩክሬን ባለሥልጣናት እንዳልተገኙ የአሰኦስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ “በአሜሪካና በሩሲያ መመሪያ ሰጪነት የሚደረግን ጦርነት የማቆም ውሳኔን” እንደማይቀበሉ ተናግረዋል። ዜሌንስኪ የሃገራቸው ድንበር በእ.አ.አ 2014 ወደነበረበት እንዲመለስ ሲጠይቁ ቆይተዋል። የአሜሪካ ባለሥልጣናት ግን፣ ዩክሬን ኔቶን ለመቀላቅ እንድምታደርገው ጥረት ሁሉ፣ ድንበሩ ወደነበረበት ይመለስ የሚለው ጥያቄም ተቀባይነት ማግኘቱ አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል አስታውቀዋል። ዜሌንስኪ በዚህ ሳምንት በሳዑዲ አረቢያ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ወደ መጋቢት 1፣ 2017 አስተላልፈዋል። ምክንያቱ ደግሞ የሃገራቸው ባለሥልጣናት በውይይቱ ላይ እንዲካፈሉ ባለመጋበዛቸው እንደሆነ አመልክተዋል። በዚህ ሳምንት ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝትም ከውይይቱ ጋራ እንደሚገናኝ ተደርጎ እንዲታይ እንዳልፈለጉም አስታውቀዋል። ዜሌንስኪ በዩክሬን የአሜሪካ ልዩ ልዑክ የሆኑትን ኪት ኬሎግ ነገ ረቡዕ አግኝተው ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል።    

Get more results via ClueGoal