የዩናይትድ ስቴትስ ዳኛ ትራምፕ ኤፒ የዜና ተቋም ከዋይት ሃውስ እንዳይዘግብ የጣሉትን ገደብ አፀና
newsare.net
ዋሽንግተን — አሶሽየትድ ፕሬስ (ኤፒ) የዜና ተቋም በዘገባዎቹ የሜክሲኮ ባህረሰላጤ የሚለውን ስያሜ መጠቀም በመቀጠሉ በዋይት ሀውስ ተገኝቶ እንዳይዘግብ በፕሬየዩናይትድ ስቴትስ ዳኛ ትራምፕ ኤፒ የዜና ተቋም ከዋይት ሃውስ እንዳይዘግብ የጣሉትን ገደብ አፀና
ዋሽንግተን — አሶሽየትድ ፕሬስ (ኤፒ) የዜና ተቋም በዘገባዎቹ የሜክሲኮ ባህረሰላጤ የሚለውን ስያሜ መጠቀም በመቀጠሉ በዋይት ሀውስ ተገኝቶ እንዳይዘግብ በፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የተጣለበት ገደብ እንዲነሳለት ያቀረበው ጥያቄ በአንድ ፌደራል ዳኛ ውድቅ ተደረገ። በፕሬዝደንት ትራምፕ የተሰየሙት የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት ዳኛ ትሬቨር ሚክፋደን፣ ኤፒ የፍርድ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ« ኦቫል ኦፊስ» በተሰኘው የፕሬዝደንቱ ጽሕፈት ቤት ፣ በፕሬዝደንቱ አውሮፕላን (ኤር ፎርስ ዋን) እና ሌሎች በዋይት ሀውስ የሚከናወኑ ዝግጅቶች ላይ ተገኝቶ የመዘገብ መብቱ እንዲመለስ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል። ሚክፋደን በውሳኔያቸው ፕሬዝዳንቱ «ግላዊ በኾኑ አካባቢዎች» ላይ የጣሉት ገደብ፣ ከዚህ ቀደም ፍርድቤቶች የመንግሥት ባለሥልጣናት በጋዜጠኞች ላይ የተጣሉትን ገደቦችን ካነሱባቸው ሁኔታዎች የተለየ ነው ብለዋል። በፍርድ ሂደቱ ላይም «ኤፒ ለስኬት የሚያበቃ ሁኔታ አሳይቷል ማለት አልችልም» ብለዋል። ዳኛው አክለው ዋይት ሀውስ በኤፒ የዜና ሽፋን ምክንያት አድሎ መፈፀሙን ተናግረዋል። ችግር የሚፈጥር ሁኔታ መሆኑንም ገልጸዋል። የዳኛውን ውሳኔ ተከትሎ ዋይት ሀውስ ባወጣው መግለጫ «የዩናይትድ ስቴትስን ፕሬዝደንት በቢሮዋቸው እና በአውሮፕላናቸው ተገኝቶ መጠየቅ ለጋዜጠኞች የተሰጠ ልዩ መብት እንጂ ሕጋዊ ግዴታ አይደለም» ብሏል። የኤፒ ቃል አቀባይ በበኩላቸው የዜና ተቋሙ «ለፕሬስ እና ለሕዝብ ያለመንግሥት አፀፋ በነፃነት የመናገር መብት መቆሙን እንደሚቀጥል» ገልጸዋል። ኤፒ ባለፈው ሳምንት አርብ በሦስት ከፍተኛ የትራምፕ ረዳቶች ላይ ክስ የመሰረተው፤ ዘጋቢዎቹ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ተገኝተው እንዳይዘግቡ የተላለፈው ውሳኔ በዩናይትድ ስቴትስ ሕገ መንግስት የመጀመሪያ የማሻሻያ አንቀፅ ላይ የተደነገገውን በመጣስ፣ መንግሥት በዜና ዘገባ ውስጥ የሚጠቀመውን ቋንቋ የሚያስገድድ እና የንግግር መብትን የሚገድብ ነው በማለት ነው። የኤፒ ጠበቃ ቻርስ ቶቢን በችሎት ቀርበው ባስረዱበት ወቅትም «ሕገ መንግሥቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንትም ኾኑ ሌላ የመንግሥት ባለሥልጣን ጋዜጠኞችንንም ኾነ ሌላ አካል፣ የመንግሥትን ቋንቋ በመጠቀም ዜና እንዲዘግቡ ከማድረግ ይከለክላል» ብለዋል። የትራምፕ አስተዳደር ጠበቆች በበኩላቸ ኤፒ «ፕሬዝዳንቱ ጋራ የመግባት ልዩ የሚዲያ ፈቃድ» የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል። ትራምፕ ባለፈው ወር የሜክሲኮ ባህረሰላጤ የአሜሪካ ባህረሰላጤ በሚለው ስምን እንዲተካ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ አስተላልፈው የነበረ ሲሆን፣ ኤፒ የትራምፕን ውሳኔ በመጥቀስ የባህረሰላጤውን የቆየ ስም መጠቀም እንደሚቀጥል ገልጿል። በምላሹ የኤፒ ጋዜጠኞች በዋይት ሀውስ ተገኝተው እንዳይዘግቡ እገዳ ተጥሎባቸዋል። Read more