የአሜሪካ ምክርቤት አፈ ጉባኤ በጀት ለማሳለፍ የሚያችል በቂ የሪፐብሊካን ድምፅ አገኙ
newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን ማክሰኞ ምሽት ድምፅ የሚሰጥበትን የበጀት ረቂቅ ለማሳለፍ የሚያስችል 217 ድምፅ አሰባስበዋል። ይህም ዲሞየአሜሪካ ምክርቤት አፈ ጉባኤ በጀት ለማሳለፍ የሚያችል በቂ የሪፐብሊካን ድምፅ አገኙ
የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን ማክሰኞ ምሽት ድምፅ የሚሰጥበትን የበጀት ረቂቅ ለማሳለፍ የሚያስችል 217 ድምፅ አሰባስበዋል። ይህም ዲሞክራቶች «ግዴለሽነት» ሲሉ የሚጠሩትን የሪፐብሊካን ፓርቲ የግብር እና የመንግሥት ወጪ ቅነሳ ጥረት ለማሳካት የሚያግዛቸው መሆኑም ተመልክቷል። «ከፊታችን ጠንካራ ሥራ ቢጠብቀንም፣ ቅድሚያ ለአሜሪካ የሚለውን አጀንዳችንን ግን እናሳካለን» ሲሉ ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን የሰጡት ጆንሰን «የተወሰነውን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም እናሳካለን። ይህ የሂደት ቀዳሚው ክፍል ብቻ ነው» ብለዋል። ጆንሰን እና ሌሎች የምክርቤቱ ሪፐብሊካን አመራሮች ባወጡት መግለጫ ዋና ግባቸው «ድንበር ጥበቃን የሚያጠናክር፣ ለቤተሰቦች እና ሥራ ፈጣሪዎች ታክስን የሚቀንስ፣ አሜሪካ በኃይል ምርት የነበራትን የበላይነት የሚመልስ፣ አሜሪካ በዓለም መድረክ ላይ ያላትን አቋም የሚያጠናክር እና መንግሥት ለአሜሪካውያን የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን» የሚያደርግ ሕግ ማፅደቅ እንደሆነ ገልጸዋል። የምክር ቤቱ የዲሞክራት ፓርቲ መሪ ሃኪም ጄፍሪስ በበኩላቸው ሪፐብሊካኖች ለቀድሞ ወታደሮች ይሰጡ የነበሩ ጥቅማጥቅሞችን እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች ይደረግ የነበረውን የምግብ ርዳታ እንዲሁም የጤና አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት እየሠሩ ነው ብለዋል። ጄፍሪስ አክለው «የሪፐብሊካኖቹ የበጀት እቅድ ለሀብታሞቹ፣ ደህና ኑሮ ላላቸው እና ከነሱ ጋራ ለተሳሰሩት እስከ 4.5 ትሪሊየን ዶላን የሚደርስ ግብር ቀንሶ ሠራተኛ አሜሪካውያን እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው አሜሪካውያን እንዲከፍሉ የሚያደርግ ነው» ሲሉ ለጋዜጠኞች አብራርተዋል። ከድምፅ አሰጣጡ ሂደት በፊት በርካታ ሪፐብሊካን የምክር ቤቱ አባላት ባካሄዱት ስብሰባም፣ የግብር ቅነሳው የሚተገበርበት መንገድ እና ለአሜሪካ መራጮች ድጋፍ የሚያደርጉ የድጎማ ፕሮግራሞች ሳይነኩ የአሜሪካን ከፍተኛ ወጪ መቀነስ የሚቻልበት መንገድ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ሕግ አውጪዎቹ «ትልቅ እና ውብ» ሲሉ የጠሩትን እና የሀገር ውስጥ ፖሊሲዎቻቸው አካል የሆነውን ረቂቅ ሕግ እንዲያፀድቁ ጠይቀዋል። Read more