Ethiopia



ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊያ ጉብኝት አደረጉ  

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ባለፈው ታኅሣሥ ወር መጀመሪያ በቱርክ ፕሬዝደንት ረሽፕ ታይፕ ኤርዶዋን አሸማጋይነት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የኹለቱ ሀገ

በደባርቅ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ 16 ሰዎች ሞቱ

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ፣ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ በደረሰ የመኪና አደጋ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የአሜሪካ ድምፅ

በደባርቅ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ 16 ሰዎች ሞቱ

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ፣ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ በደረሰ የመኪና አደጋ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ይበልጣል መርሻ፣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ እንደገለጹት፣ በዕለቱ ተሽከርካሪው፥ ከበየዳ ወደ ደባርቅ ወረዳ ሰዎችንና እህል ጭኖ በመጓዝ ላይ እያለ፣ ከረፋዱ 3፡30 ገደማ፣ ልዩ ስሙ “አበርጊና” በተባለ ቦታ ላይ ተገልብጦ 16 ተሳፋሪዎች ሲሞቱ፣ በ35ቱ ላይ ቀላል እና ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሷል። በዐማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ሓላፊ ኢንስፔክተር ይበልጣል መርሻ፣ ዛሬ ኀሙስ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ እንደገለጹት፣ ከትላንት በስቲያ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ከረፋዱ 3:30 ገደማ፣ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት-11591 የኾነ፣ በተለምዶ ካሶኒ እየተባለ የሚጠራ የደረቅ ጭነት መኪና፣ ከበየዳ ወደ ደባርቅ ከተማ እየተጓዘ ሳለ፣ ልዩ ስሙ አበጊና በተባለው ስፍራ ላይ በመገልበጡ በተሳፋሪዎች ላይ የምት እና የመቁሰል አደጋ መድረሱን ተናግረዋል። ከ16ቱ ሟቾች መካከል አራቱ ተፈናቃዮች ናቸው፤ ያሉት ኢንስፔክተር ይበልጣል፣ የጭነት መኪናው አሽከርካሪ እስከ አኹን በቁጥጥር ሥር እንዳልዋለ ተናግረዋል። ከአደጋው ከተረፉት ተሳፋሪዎች አንዱ እንደኾነ የሚናገረው ዮሐንስ ምትኬ፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሳቢያ ከትግራይ ክልል በ2013 ዓ.ም. ተፈናቅሎ በደባርቅ ወረዳ ከማኅበረሰቡ ጋራ ተቀላቅሎ እንደሚኖር ጠቅሶ፣ ወደ በረሓ ለሥራ ፍለጋ እየተጓዘ እንደነበር ገልጿል። ለዚኽም፣ «ከአበጊና» ቀበሌ ከእርሱ ጋራ 18 ተፈናቃዮች በተሽከርካሪው መሳፈራቸውን አውስቶ፣ አንድ ኪሎ ሜትር እንኳን ሳይርቅ አደጋው መድረሱን አስረድቷል። ዮሐንስ አደጋው በእጁ ላይ ባደረሰበት ጉዳት፣ በደባርቅ ሆስፒታል በሕክምና እየተረዳ እንደሚገኝ አስታውቆ፣ አብረውት ከተሳፈሩት ውስጥ ሕይወታቸው ያለፈ እንዳሉም ገልጿል። በቅርቡ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በደባርቅ ወረዳ ከማኅበረሰቡ ጋራ ተቀላቅለው ከሚኖሩት መካከል የተፈናቃዮች ማኅበር ምክትል ሊቀ መንበር የኾኑት መሪጌታ ጠበቃው ወልደ ገብርኤል፣ ከ2015 ዓ.ም. ወዲህ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ርዳታ ስለሚሰጣቸው አብዛኛዎቹ ለቀን ሥራ ከቦታ ወደ ቦታ እንደሚንቀሳቀሱ ገልጸዋል። ከትላንት በስቲያው የመኪና አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው 18 ተፈናቃዮች ግን፣ የዓለም ባንክ በአበጊና ብር እና ምግብ ይሰጣል፤ ለሥራ ያደራጃል፤ የሚል መረጃ ሰምተው እንደተጓዙና በስፍራው ከደረሱ በኋላ ርዳታ እንደማይሰጥ ሲረዱ ለሥራ ፍለጋ ወደ በረሓ ለመሔድ ዐቅደው እየተመለሱ እንደነበር፣ የማኅበሩ ምክትል ሊቀ መንበር መሪጌታ ጠበቃው አብራርተዋል። በደባርቅ ወረዳ፣ ከሁለት ሺሕ በላይ የጦርነት ተፈናቃዮች ከማኅበረሰቡ ጋራ ተቀላቅለው ይገኛሉ።  

በምሥራቅ ኮንጎ ፍንዳታ 11 ሰዎች ሞቱ

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ክፍል የአማጺው ኤም 23 መሪዎችና ነዋሪዎች ሰልፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ በተከሰተ ፍንዳታ 11 ሰዎች ሲሞቱ 65 የሚሆኑ ተጎድተ
የአሜሪካ ድምፅ

በምሥራቅ ኮንጎ ፍንዳታ 11 ሰዎች ሞቱ

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ክፍል የአማጺው ኤም 23 መሪዎችና ነዋሪዎች ሰልፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ በተከሰተ ፍንዳታ 11 ሰዎች ሲሞቱ 65 የሚሆኑ ተጎድተዋል። በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች የተጋሩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች በርካታ ሰዎች ሲሸሹ እና በደም የተለወሱ አስከሬኖችም መንገድ ላይ ወድቀው አሳይተዋል። ፍንዳታዎቹ በተከሰቱበት ወቅት የኤም 23 መሪዎች በማዕከላዊ ቡካቩ ከተማ ከነዋሪዎች ጋራ ውይይት በማድረግ ላይ ነበሩ። ፍንዳታው “የሽብር ሥራ እና በሕገ ወጥ መንገድ በኮንጎ በሚገኝ የውጪ ጦር የተፈጸመ ነው” ሲሉ የኮንጎ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቺሴኬዲ ክስ አሰምተዋል። ኤም 23 በበኩሉ «የኮንጎ ባለሥልጣናት ፍዳታውን አቀናብረዋል» ሲል ከሷል። “የኪንሻሳው አገዛዝ ሲቪሎችን ለማጥፋት ተነስቷል” ሲልም አክሏል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በተቃዋሚዎች የቀረበውን የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ውድቅ አደረገ

ሰሞኑን በአዲሰ አበባ ከተማ ለአራት ቀናት የቆየ ውይይት ያካሄዱት ተቃዋሚዎቹ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሁሉን አካ
የአሜሪካ ድምፅ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በተቃዋሚዎች የቀረበውን የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ውድቅ አደረገ

ሰሞኑን በአዲሰ አበባ ከተማ ለአራት ቀናት የቆየ ውይይት ያካሄዱት ተቃዋሚዎቹ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሁሉን አካታች የኦሮሚያ ክልል የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት እንደሚሠሩ ገልጸዋል። “ሐሳቡ የቀረበው ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ሰላም ለማምጣት የጋራ መንግሥት ስለ ሚያሰፈልግ ነው” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር መረራ ጉዲና ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ መንግሥቱ መሠረት በምርጫ የተቋቋመ ነው” ያሉት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ ኃይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ የፓርቲዎቹ መግለጫ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ነው” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ምላሽ ሰጥተዋል።   የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ባወጣው መግለጫ፣ በኦነግና በኦፌኮ የተጠራውን ጉባኤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ አብሮ የሚሄድ ፕሮጀክት ነው በማለት አውግዟል። ተቃዋሚዎቹ የኦሮሞ ነጻነት ግንቀባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ለአራት ቀናት በተካሄደው ጉባኤ ላይ ለግጭት መነሻ የሚኾኑ የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ችግሮችንም አንስተው መነጋገራቸውን የኦፌኮ ሊቀመንበር ተናግረዋል። ይሄንኑ መነሻ አድርገው መግለጫ ያወጡት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባርና ሌሎች በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ተቃውሞ አቅርበዋል። ኦፌኮና ኦነግ፣ ድሬዳዋ እና ሞያሌን ጨምሮ በአንዳንድ ግዛቶች ላይ ይገባኛል ጥያቄ ማንሳታቸውን የጠቀሱት ፓርቲዎቹ፣ አካሔዱ የፌዴራል ሕገ መንግሥቱን እና በተለያዩ ብሔረሰቦች መካከል ያለውን በሰላም አብሮ የመኖር መርህ ይፃረራል በማለት አውግዘዋል። በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ሐሳባቸው ጥያቄዎች በድርድርና በንግግር እንዲፈቱ ማድረግ መሆኑን አብራርተዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአንጥረኛነት ፈተና በትግራይ

በትግራይ ክልል በባህላዊ የብረታብረት መገልገያ ዕቃዎች እና ጌጣጌጦች ሥራ ላይ የተሰማሩ የጥበበ እድ ሞያተኞች፣ እየደረሰብን ነው ባሉት ማኅበራዊ መገለልና ጥ
የአሜሪካ ድምፅ

የአንጥረኛነት ፈተና በትግራይ

በትግራይ ክልል በባህላዊ የብረታብረት መገልገያ ዕቃዎች እና ጌጣጌጦች ሥራ ላይ የተሰማሩ የጥበበ እድ ሞያተኞች፣ እየደረሰብን ነው ባሉት ማኅበራዊ መገለልና ጥቃት የተነሣ፣ ልጆቻቸው ከትምህርት ገበታ እየራቁ መኾናቸው በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።  በየጊዜው እየከፋ መምጣቱን በገለጹት ጥቃት ለተፈናቃይነት መዳረጋቸውን የተናገሩት የእጅ ጥበብ ሞያተኞቹ፣ «አስነዋሪ» ሲሉ በገለጹት አኳኋን ግድያ የተፈጸመባቸው የቤተሰቦቻቸው አባላት መኖራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል። መብቶቻቸውን በሕግ ለማስከበር ጥረት ቢያደርጉም «ምስክር አቅርቡ» በሚል ፍትሕ ለማግኘት አለመቻላቸውን ሞያተኞቹ አመልክተዋል። «መምህራን፣ ካህናት እና ፖሊስ አመለካከታቸው ቢስተካከል እኛም እንደ ሰው እንኖር ነበር፤” ሲሉም መፍትሔው የአመለካከት ለውጥ እንደኾነ ጠቁመዋል። የእጅ ባለሞያዎቹ ይደርስብናል ያሉትን በደል ለመከላከልና ሲበደሉም ፍትሕ ርትዕ እንዲያገኙ የሚያግዝ፦ »የትግራይ የእደ ጥበብ ባለሞያዎች ማኅበር" የተሰኘ የመብቶች ተሟጋች ማቋቋማቸውንም አክለው አስታውቀዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የካናዳ የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ለዓለም አቀፍ ተማሪዎች ስጋት ፈጥሯል

ከአውሮፓ እስከ ሰሜን አሜሪካ፣ ሀገራት የኢሚግሬሽን ፖሊሲያቸውን እያጠናከሩ ነው። ከዓለም ሀገራት ለስደተኞች መልካም አቀባበል በማድረግ የምትታወቀው ካናዳ
የአሜሪካ ድምፅ

የካናዳ የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ለዓለም አቀፍ ተማሪዎች ስጋት ፈጥሯል

ከአውሮፓ እስከ ሰሜን አሜሪካ፣ ሀገራት የኢሚግሬሽን ፖሊሲያቸውን እያጠናከሩ ነው። ከዓለም ሀገራት ለስደተኞች መልካም አቀባበል በማድረግ የምትታወቀው ካናዳም ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ላይ ተፅእኖ የሚያደርሱ ለውጦችን ይፋ አድርጋለች። ማሻሻያዎቹ ይበልጥ እየጠበቁ የሄዱትን ዓለም አቀፍ የኢሚግሬሽን ፖሊሲዎች የሚያንፀባርቁ መሆናቸውም ተመልክቷል። አርዙማ ኮምፓኦሬ ከካልጋሪ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአዲስ አበባ “የኮሪደር ልማት” አወዛጋቢ ውጤቶች የነዋሪዎች አስተያየት

በአዲስ አበባ የተመረጡ አካባቢዎች፣ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ ናቸው። ፕሮጄክቶቹ፣ የተሽከርካሪ እና የእግረኛ መንገዶችን፣ ልዩ የብስክሌ
የአሜሪካ ድምፅ

የአዲስ አበባ “የኮሪደር ልማት” አወዛጋቢ ውጤቶች የነዋሪዎች አስተያየት

በአዲስ አበባ የተመረጡ አካባቢዎች፣ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ ናቸው። ፕሮጄክቶቹ፣ የተሽከርካሪ እና የእግረኛ መንገዶችን፣ ልዩ የብስክሌት መንገዶችንና ሌሎችም የመሠረተ ልማት ውጤቶችን አስገኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል፣ የርእሰ መዲናዋ የረዥም ጊዜ ነዋሪዎች መፈናቀልና በመንገዶቹ ዳር ላይ ያሉ የንግድ ተቋማት መፍረስ፣ ከፕሮጀክቶቹ አወዛጋቢ ውጤቶች መካከል ኾነው ቀጥለዋል፡፡ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችም፣ መሰል “የኮሪደር ልማት” ፕሮጀክቶች ትግበራ፣ ተመሳሳይ ውጤቶችን እያስከተሉ በመከናወን ላይ ናቸው፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በአሜሪካ የዶሮ እንፍሉዌንዛን ለመዋጋት 1 ቢሊዮን ዶላር ተመደበ

የአእዋፍ እንፍልዌንዛ ባለፉት ሦስት ዓመታት በአሜሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶሮዎችን በመግደሉና ከፍተኛ የእንቁላል እጥረት በመከሰቱ መንግሥት በሽታውን ለመዋ
የአሜሪካ ድምፅ

በአሜሪካ የዶሮ እንፍሉዌንዛን ለመዋጋት 1 ቢሊዮን ዶላር ተመደበ

የአእዋፍ እንፍልዌንዛ ባለፉት ሦስት ዓመታት በአሜሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶሮዎችን በመግደሉና ከፍተኛ የእንቁላል እጥረት በመከሰቱ መንግሥት በሽታውን ለመዋጋትና ከውጪ እንቁላል ለማስገባት 1 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን የሀገሪቱ የግብርና ምኒስትር አስታውቀዋል። ባለፉት ሦስት ዓመታት በተከሰተው የአእዋፍ እንፍሉዌንዛ 166 ሚሊዮን ዶሮዎች መሞታቸውን የአሜሪካው የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። በሽታው አንድ ሺሕ የሚሆኑ የወተት ላሞችንና 70 የሚሆኑ ሰዎችንም ማጥቃቱ ታውቋል። ባለፈው ዓመት አንድ ሰው በበሽታው ሞቷል። አምስት ሚሊዮን ዶላር ለአርቢዎች ነፃ የዶሮ ምርመራ ለማድረግ እንዲሁም 400 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ በበሽታው የተያዙ ዶሮዎቻቸውን ለመግደል ለሚሹ አርቢዎች እንደተመደበ የግብርና ምኒስትሩ ብሩክ ሮሊንድ አስታውቀዋል። ገንዘቡ በባለሀብቱ ኢላን መስክ በተመራው ቡድን በቅርቡ ከግብርና ሚኒስቴሩ ላይ ከተቀነስው በጀት ላይ እንደሚገኝም ታውቋል። ወደ ውጪ የሚላከውን እንቁላል በመቀነስና ከውጪ የሚገባውን በመጨመር በእንቁላል ገበያ ላይ የሚታየውን ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ዋጋ ለመቀነስ አስተዳደሩ ማቀዱም ተመልክቷል።

ዩክሬይን የተደቀነባት ድምጽ አልባው ትግል ፡- ውጊያ ያንገፈገፋቸው ወታደሮቿ የአዕምሮ ጤና ቀውስ

ለሦስት ዓመታት ያለማቋረጥ ጦርነት የተካሄደባት ዩክሬን የአዕምሮ ጤና ቀውስ ተደቅኖባታል፣ ሆስፒታሎቿ  በጭንቀት፣ በድብርት እና በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ በማለ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩክሬይን የተደቀነባት ድምጽ አልባው ትግል ፡- ውጊያ ያንገፈገፋቸው ወታደሮቿ የአዕምሮ ጤና ቀውስ

ለሦስት ዓመታት ያለማቋረጥ ጦርነት የተካሄደባት ዩክሬን የአዕምሮ ጤና ቀውስ ተደቅኖባታል፣ ሆስፒታሎቿ  በጭንቀት፣ በድብርት እና በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ በማለፍ በሚከሰት የአዕምሮ ቀውስ በሚሰቃዩ ወታደሮች ተጨናንቀዋል። ዶክተሮችም እነዚህ በገሃድ የማይታዩ ድብቅ  ቁስሎች ለብዙ ዐሥርት ዓመታት ተቆራኝተዋት ሊቆዩ እንደሚችሉ  ይናገራሉ። ያን ቦቻት በምዕራብ ዩክሬን ከምትገኘው ኤልቪቭ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

ደቡብ አፍሪካ ወታደሮቿን ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ አስወጣች

ደቡብ አፍሪካ 127 የሚኾኑ ወታደሮቿን ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ አስወጥታለች፡፡ አራቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው መኾኑም ታውቋል። ወታደሮቹ ከሁለት ዓመታ
የአሜሪካ ድምፅ

ደቡብ አፍሪካ ወታደሮቿን ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ አስወጣች

ደቡብ አፍሪካ 127 የሚኾኑ ወታደሮቿን ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ አስወጥታለች፡፡ አራቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው መኾኑም ታውቋል። ወታደሮቹ ከሁለት ዓመታት በፊት የ16 ሀገራት ጥምር በሆነው በደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ ወይም ሳድክ ኅይል ውስጥ ታቅፈው፣ በሩዋንዳ ከሚደገፈው ኤም 23 ጋራ በመፋለም ላይ ያለውን የኮንጎ መንግሥት ለመደገፍ የተሠማሩ ነበሩ። ሃያ አንዱ ወታደሮች ትላንት ማክሰኞ የተመለሱ ሲሆን፣ 106 የሚሆኑት ደግሞ ዛሬ ረቡዕ ተመልሰው ደቡብ አፍሪካ ወታደሮቿን በሙሉ አስወጥታ አጠናቃለች፡፡ የተጎዱት ወታደሮች ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ፣ ከተመለሱት ውስጥ አንዳንዶቹ የሥነ ልቦና ሕክምና እንደሚያስፈልጋቸውም ታውቋል። የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ባለፈው ጥር የተገደሉ 14 ወታደሮችን አስከሬን እንድታስመልስ በሃገሪቱ ውስጥ ጫና በርትቶበት ነበር። ደቡብ አፍሪካ በአጠቃላይ አንድ ሺሕ የሚሆኑ ወታደሮችን ወደ ኮንጎ እንዳሰማራች ሪፖርቶችና ትንተናዎች ቢያመለከቱም፣ ባለሥልታናት ግን ትክክለኛውን ቁጥር አልገለጹም።

በደቡብ ኦሞ ዞን አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆች ወለደች  

በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ የአይሎሀ ቀበሌ ነዋሪ የኾነችው ወይዘሮ ማርታ ታከለ  በአንድ  ጊዜ አራት ልጆችን በሰላም መገላገሏ ተገለጸ፡፡ የወይዘሮ ማርታ
የአሜሪካ ድምፅ

በደቡብ ኦሞ ዞን አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆች ወለደች  

በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ የአይሎሀ ቀበሌ ነዋሪ የኾነችው ወይዘሮ ማርታ ታከለ  በአንድ  ጊዜ አራት ልጆችን በሰላም መገላገሏ ተገለጸ፡፡ የወይዘሮ ማርታ ባለቤት አቶ አንጅሎ አዲሱ በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጸው የ29 ዓመቷ ባለቤቱ በድንገት ምጥ መጥቶባት ሆስፒታል ከገባች በኋላ ለሰዓታት በምጥ መውለድ ባለመቻሏ በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል በቀዶ ህክምና አራቱንም ልጆች ተገላግላለች።  የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ዳይሬክተር ፣ ዶክተር ቢንያም አስራት፣ ወይዘሮ ማርታ ታከለ ከፀነሰች ከሦስት ወሯ ጀምሮ በሆስፒታሉ የእርግዝና ክትትል ስታደርግ እንደነበረ አመልክተው በእርግዝናዋ ወቅት በውስጥ አካላት መመርመሪያ  በአልትራሳውንድ  የታየው የሦስት ልጆች ጽንስ ቢሆንም በቀዶ ህክምናው አራት ልጆች እንደወለደች ገልጸዋል፡፡ የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ዳይሬክተር ፣ ዶክተር ቢንያም አስራት፣ ሕጻናቱ ከተወለዱ በኋላ ያነሱትን ፎቶ አጋርተውናል።  ባለቤቱ ቋሚ ሥራ እና ገቢ የሌላት የቤት እመቤት እንደሆነች እና እርሱም ቤተሠቡን የሚያስተዳድረው  በጉልበት ሥራ በሚያገኘው የቀን ገቢ መሆኑን  የአራት ዓመት ወንድ ልጅ እንዳላቸው የገለጸው አቶ አንጀሎ አሁን ደግሞ “በአንድ ጊዜ የአራት ልጆች አባት መኾኔ ቢያስደስተኝም እንዴት እንደማሳድጋቸው ግራ ገብቶኛል” ሲል ስጋቱን አጋርቷል።  "እስካሁንም  የምንኖረው በፈጣሪ ርዳታና እና ባለቤቴ በቀን ሞያተኝነት በምታገኘው ገቢ እየተደጎምን ነው “ ሲል አክሏል። ሁለት ሴት እና ሁለት ወንድ ሕፃናቱ የተወለዱት  ዘጠኝ ወራቸውን ሞልተው እንደኾነም ሐኪሙ  አመልክተዋል። ሦስቱ ሕጻናት ክብደታቸው1 ነጥብ 8 ፣  1ነጥብ 9፣ እና  1ነጥብ 8 ኪሎ ግራም  ሲኾኑ የአራተኛው ልጅ ክብደት አንድ ኪሎ ብቻ መኾኑን የገለጹት ዶክተር ቢንያም  ለጊዜው ጨቅላ ሕጻናት በሙቀት ማቆያ ውስጥ እንዲቆይ ከተደረገ በኋላ  ዛሬ ወደ እናቱ ተመልሷል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ጨቅላ ሕጻናቱም እናታቸውም በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የሕክምና ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል፡፡   ከአሁን በፊት በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታሉ አንዲት እናት ሦስት ልጆችን መገላገሏን አስታውሰው በሆስፒታሉ  በአንድ ጊዜ አራት ልጆች ሲወለዱ የአሁኑ የመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ በሶማሊያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ ነገ ሐሙስ በሶማሊያ ጉብኝት በማድረግ ከሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ ጋራ እንደሚወያዩ ከሶማሊያ ከመንግ
የአሜሪካ ድምፅ

ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ በሶማሊያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ ነገ ሐሙስ በሶማሊያ ጉብኝት በማድረግ ከሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ ጋራ እንደሚወያዩ ከሶማሊያ ከመንግሥት ምንጮች መረጃውን ማግኘቱን ኤኤፍፒ አመልክቷል። ሁለቱ ሀገራት የሻከረውን ግንኙነታቸውን ለማደስ በመሞከር ላይ ባሉበት ወቅት የሚካሄደው ጉብኝት “በአንካራ የተፈጸመውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግና ለማጠናቀቅ ከሚደረጉ ሰፊ ጥረቶች አንዱ እንደሆነ” ዘገባው አመልክቷል። “በጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ የሚመራ ከፍተኛ የባለሥልጣኖች ቡድን ነገ ሞቃዲሹ እንደሚደርስ ይጠበቃል” ሲሉ ለፕሬዝደንታዊ ቤተ መንግሥቱ ቅርብ የሆኑና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ምንጭ መናገራቸውን ኤኤፍፒ በዘገባው አመልቷልክ። ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ተገንጥላ ራስ ገዝ ከሆነችው ሶማሊላንድ ጋራ ባለፈው ዓመት የባሕር ዳርቻ በሊዝ ለማግኘት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሉ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረት ሰፍኖ ነበር። የአንካራውን ስምምነት ተከትሎ ግን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ሙሉ ለሙሉ ወደነበረበት እንደሚመልሱ አስታውቀዋል።

የአሜሪካ ምክርቤት አፈ ጉባኤ በጀት ለማሳለፍ የሚያችል በቂ የሪፐብሊካን ድምፅ አገኙ

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን ማክሰኞ ምሽት ድምፅ የሚሰጥበትን የበጀት ረቂቅ ለማሳለፍ የሚያስችል 217 ድምፅ አሰባስበዋል። ይህም ዲሞ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ ምክርቤት አፈ ጉባኤ በጀት ለማሳለፍ የሚያችል በቂ የሪፐብሊካን ድምፅ አገኙ

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን ማክሰኞ ምሽት ድምፅ የሚሰጥበትን የበጀት ረቂቅ ለማሳለፍ የሚያስችል 217 ድምፅ አሰባስበዋል። ይህም ዲሞክራቶች «ግዴለሽነት» ሲሉ የሚጠሩትን  የሪፐብሊካን ፓርቲ የግብር እና የመንግሥት ወጪ ቅነሳ ጥረት ለማሳካት የሚያግዛቸው መሆኑም ተመልክቷል። «ከፊታችን ጠንካራ ሥራ ቢጠብቀንም፣ ቅድሚያ ለአሜሪካ የሚለውን አጀንዳችንን ግን እናሳካለን» ሲሉ ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን የሰጡት ጆንሰን «የተወሰነውን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም እናሳካለን። ይህ የሂደት ቀዳሚው ክፍል ብቻ ነው» ብለዋል። ጆንሰን እና ሌሎች የምክርቤቱ ሪፐብሊካን አመራሮች ባወጡት መግለጫ ዋና ግባቸው «ድንበር ጥበቃን የሚያጠናክር፣ ለቤተሰቦች እና ሥራ ፈጣሪዎች ታክስን የሚቀንስ፣ አሜሪካ በኃይል ምርት የነበራትን የበላይነት የሚመልስ፣ አሜሪካ በዓለም መድረክ ላይ ያላትን አቋም የሚያጠናክር እና መንግሥት ለአሜሪካውያን የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን» የሚያደርግ ሕግ ማፅደቅ እንደሆነ ገልጸዋል። የምክር ቤቱ የዲሞክራት ፓርቲ መሪ ሃኪም ጄፍሪስ በበኩላቸው ሪፐብሊካኖች ለቀድሞ ወታደሮች ይሰጡ የነበሩ ጥቅማጥቅሞችን እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች ይደረግ የነበረውን የምግብ ርዳታ እንዲሁም የጤና አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት እየሠሩ ነው ብለዋል። ጄፍሪስ አክለው «የሪፐብሊካኖቹ የበጀት እቅድ ለሀብታሞቹ፣ ደህና ኑሮ ላላቸው እና ከነሱ ጋራ ለተሳሰሩት እስከ 4.5 ትሪሊየን ዶላን የሚደርስ ግብር ቀንሶ ሠራተኛ አሜሪካውያን እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው አሜሪካውያን እንዲከፍሉ የሚያደርግ ነው» ሲሉ ለጋዜጠኞች አብራርተዋል።   ከድምፅ አሰጣጡ ሂደት በፊት በርካታ ሪፐብሊካን የምክር ቤቱ አባላት ባካሄዱት ስብሰባም፣ የግብር ቅነሳው የሚተገበርበት መንገድ እና ለአሜሪካ መራጮች ድጋፍ የሚያደርጉ የድጎማ ፕሮግራሞች ሳይነኩ የአሜሪካን ከፍተኛ ወጪ መቀነስ የሚቻልበት መንገድ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ሕግ አውጪዎቹ «ትልቅ እና ውብ» ሲሉ የጠሩትን እና የሀገር ውስጥ ፖሊሲዎቻቸው አካል የሆነውን ረቂቅ ሕግ እንዲያፀድቁ ጠይቀዋል።

የሱዳን ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ 46 ሰዎች ሞቱ

በሱዳን ዋና የመዲናዋ መንትያ ከተማ ኦምዱርማን ወታደራዊ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኝ የመኖሪያ መንደር አካባቢ፤ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ 46 ሰዎች መሞታ
የአሜሪካ ድምፅ

የሱዳን ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ 46 ሰዎች ሞቱ

በሱዳን ዋና የመዲናዋ መንትያ ከተማ ኦምዱርማን ወታደራዊ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኝ የመኖሪያ መንደር አካባቢ፤ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ 46 ሰዎች መሞታቸውን፤ የኻርቱም የመንግሥት ብዙኀን መገናኛ ቢሮ የገለጸ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል አንድ ከፍተኛ የጦር አዛዥ እንደሚገኙ የወታደራዊ ምንጮች ዘግበዋል። አደጋው የደረሰው ትላንት ማክሰኞ ማምሻውን በሰሜናዊ ኦምዱርማን በዋዲ ሲዳይና ወታደራዊ አየር ማረፊያ አቅራቢያ ነው። የሱዳን ጦር በአደጋው ብዙ ወታደራዊ አባላት እና ሲቪሎች መሞታቸውን ቢገልጽም ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በቴክኒክ ችግር ሊሆን እንደሚችል ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል። የሱዳን መገናኛ ጽሕፈት ቤትም በአደጋው ዐስር ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። ከሟቾቹ መካከል ከዚህ ቀደም በመላው ኻርቱም የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዥ ሆነው ያገለገሉት የኻርቱም ሜጀር ጄነራል ባህር አሕመድ እንደሚገኙበት የወታደራዊ ምንጮቹ አስታውቀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ዳኛ ትራምፕ ኤፒ የዜና ተቋም ከዋይት ሃውስ እንዳይዘግብ የጣሉትን ገደብ አፀና

ዋሽንግተን — አሶሽየትድ ፕሬስ (ኤፒ) የዜና ተቋም በዘገባዎቹ የሜክሲኮ ባህረሰላጤ የሚለውን ስያሜ መጠቀም በመቀጠሉ በዋይት ሀውስ ተገኝቶ እንዳይዘግብ በፕሬ
የአሜሪካ ድምፅ

የዩናይትድ ስቴትስ ዳኛ ትራምፕ ኤፒ የዜና ተቋም ከዋይት ሃውስ እንዳይዘግብ የጣሉትን ገደብ አፀና

ዋሽንግተን — አሶሽየትድ ፕሬስ (ኤፒ) የዜና ተቋም በዘገባዎቹ የሜክሲኮ ባህረሰላጤ የሚለውን ስያሜ መጠቀም በመቀጠሉ በዋይት ሀውስ ተገኝቶ እንዳይዘግብ በፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የተጣለበት ገደብ እንዲነሳለት ያቀረበው ጥያቄ በአንድ ፌደራል ዳኛ ውድቅ ተደረገ። በፕሬዝደንት ትራምፕ የተሰየሙት የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት ዳኛ ትሬቨር ሚክፋደን፣ ኤፒ የፍርድ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ« ኦቫል ኦፊስ» በተሰኘው የፕሬዝደንቱ ጽሕፈት ቤት ፣ በፕሬዝደንቱ አውሮፕላን (ኤር ፎርስ ዋን) እና ሌሎች በዋይት ሀውስ የሚከናወኑ ዝግጅቶች ላይ ተገኝቶ የመዘገብ መብቱ እንዲመለስ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል። ሚክፋደን በውሳኔያቸው ፕሬዝዳንቱ «ግላዊ በኾኑ አካባቢዎች» ላይ የጣሉት ገደብ፣ ከዚህ ቀደም ፍርድቤቶች የመንግሥት ባለሥልጣናት በጋዜጠኞች ላይ የተጣሉትን ገደቦችን ካነሱባቸው ሁኔታዎች የተለየ ነው ብለዋል። በፍርድ ሂደቱ ላይም «ኤፒ ለስኬት የሚያበቃ ሁኔታ አሳይቷል ማለት አልችልም» ብለዋል። ዳኛው አክለው ዋይት ሀውስ በኤፒ የዜና ሽፋን ምክንያት አድሎ መፈፀሙን ተናግረዋል። ችግር የሚፈጥር ሁኔታ መሆኑንም ገልጸዋል። የዳኛውን ውሳኔ ተከትሎ ዋይት ሀውስ ባወጣው መግለጫ «የዩናይትድ ስቴትስን ፕሬዝደንት በቢሮዋቸው እና በአውሮፕላናቸው ተገኝቶ መጠየቅ ለጋዜጠኞች የተሰጠ ልዩ መብት እንጂ ሕጋዊ ግዴታ አይደለም» ብሏል። የኤፒ ቃል አቀባይ በበኩላቸው የዜና ተቋሙ «ለፕሬስ እና ለሕዝብ ያለመንግሥት አፀፋ በነፃነት የመናገር መብት መቆሙን እንደሚቀጥል» ገልጸዋል። ኤፒ ባለፈው ሳምንት አርብ በሦስት ከፍተኛ የትራምፕ ረዳቶች ላይ ክስ የመሰረተው፤ ዘጋቢዎቹ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ተገኝተው እንዳይዘግቡ የተላለፈው ውሳኔ በዩናይትድ ስቴትስ ሕገ መንግስት የመጀመሪያ የማሻሻያ አንቀፅ ላይ የተደነገገውን በመጣስ፣ መንግሥት በዜና ዘገባ ውስጥ የሚጠቀመውን ቋንቋ የሚያስገድድ እና የንግግር መብትን የሚገድብ ነው በማለት ነው። የኤፒ ጠበቃ ቻርስ ቶቢን በችሎት ቀርበው ባስረዱበት ወቅትም «ሕገ መንግሥቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንትም ኾኑ ሌላ የመንግሥት ባለሥልጣን ጋዜጠኞችንንም ኾነ ሌላ አካል፣ የመንግሥትን ቋንቋ በመጠቀም ዜና እንዲዘግቡ ከማድረግ ይከለክላል» ብለዋል። የትራምፕ አስተዳደር ጠበቆች በበኩላቸ ኤፒ «ፕሬዝዳንቱ ጋራ የመግባት ልዩ የሚዲያ ፈቃድ» የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል። ትራምፕ ባለፈው ወር የሜክሲኮ ባህረሰላጤ የአሜሪካ ባህረሰላጤ በሚለው ስምን እንዲተካ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ አስተላልፈው የነበረ ሲሆን፣ ኤፒ የትራምፕን ውሳኔ በመጥቀስ የባህረሰላጤውን የቆየ ስም መጠቀም እንደሚቀጥል ገልጿል። በምላሹ የኤፒ ጋዜጠኞች በዋይት ሀውስ ተገኝተው እንዳይዘግቡ እገዳ ተጥሎባቸዋል።

ትረምፕ ከፈረንሳዩ መሪ ጋር በዩክሬን ዕጣ ፈንታ ላይ ተወያዩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም፣ ከዩክሬን እና ከሩሲያ ጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸውን ተና
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ ከፈረንሳዩ መሪ ጋር በዩክሬን ዕጣ ፈንታ ላይ ተወያዩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም፣ ከዩክሬን እና ከሩሲያ ጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸውን ተናገሩ። ትራምፕ ይህን ያሉት ትላንት ከፈረንሳዩ መሪ ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በዋይት ኃውስ ተገናኝተው ስብሰባዎችን ከአካሄዱ እና አውሮፓ ትልቅ ሚና እንዲኖራት ከአሳሰቡ በኋላ ነው። ፓሪስ በበኩሏ ከሞስኮ ተጨማሪ ማረጋገጫዎችን ትፈልጋለች። የአሜሪካ ድምጿ አኒታ ፓውል ከዋይት ሀውስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የመከላከያ ምኒስትሩ የኤታማዦር ሹሞቹ ሰብሳቢ ከሥራቸው የተባረሩበትን ምክንያት አስረዱ

የአሜሪካው የመከላከያ ምኒስትር ፒት ሄግሴት፣ የኤታማዦር ሹሞች ቡድን ሰብሳቢ የሆኑት ሲ ኪው ብራውን ከሥራቸው የተባረሩበትን ምክንያት ባለፈው ሳምንት መጨረ
የአሜሪካ ድምፅ

የመከላከያ ምኒስትሩ የኤታማዦር ሹሞቹ ሰብሳቢ ከሥራቸው የተባረሩበትን ምክንያት አስረዱ

የአሜሪካው የመከላከያ ምኒስትር ፒት ሄግሴት፣ የኤታማዦር ሹሞች ቡድን ሰብሳቢ የሆኑት ሲ ኪው ብራውን ከሥራቸው የተባረሩበትን ምክንያት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አስረድተዋል። ባለፈው ዓርብ ነበር ፕሬዝደንት ትረሞፕ የኤታማዦር ሹሞቹን ሰብሳቢ ከሥራቸው ማንሳታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ያስታወቁት፡፡ የቪኦኤ የፔንታገን ዘጋቢ ካርላ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የኢትዮጵያን የታዳሽ ኀይል ሀብት ወደ ዶላር የሚቀይረው የቢትኮይን አሠሣ 

በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉን የክሪፕቶ ከረንሲ መገበያያ ዓይነቶች መካከል አንዱ የኾነውን የቢትኮይን ማይኒንግ ወይም በግርድፍ ትርጉሙ በይ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያን የታዳሽ ኀይል ሀብት ወደ ዶላር የሚቀይረው የቢትኮይን አሠሣ 

በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉን የክሪፕቶ ከረንሲ መገበያያ ዓይነቶች መካከል አንዱ የኾነውን የቢትኮይን ማይኒንግ ወይም በግርድፍ ትርጉሙ በይነ መረብ አሠሣ (ፍለጋ) በመጀመር ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ኾነች።አገሪቱ፣ ባለፉት 15 ዓመታት በገነባቻቸው የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኀይል ማመንጫ ግድቦች አማካይነት ከፍተኛ የኀይል አቅርቦት ቢኖራትም፤ የኤሌክትሪክ ኀይሉን ለተጠቃሚው ሕዝብ እና ለሚፈለገው ግልጋሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ዐቅም አለመገንባቷን ባለሞያዎች ይናገራሉ። ይህን ክፍተት በመጠቀም፣ ከ22 በላይ የሚደርሱ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት፣ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኀይል አቅርቦት የሚሻውን የቢትኮይን ማይኒንግ ወይም በይነ መረባዊ አሠሣ ሥራ ጀምረዋል። ከዚኽም ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ከዘርፉ 55 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች። የያዝነው የ2017 ዓ.ም ሲጠናቀቅ ደግሞ፣ 123 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደምታገኝ፣ የዓለም አቀፍ የገበያ ትንተና ገጽ የኾነው Nasdaq ትንበያ ይጠቁማል። በኢትዮጵያ፣ በክሪፕቶ ከረንሲ ዓይነቶች ለመገበያየት፣ አኹንም ድረስ የሕግ ማሕቀፍ ስላልተበጀለት ክልክል ቢኾንም፣ ቢትኮይንን ፈልጎ የማግኘት ሥራ ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ፈቃድ መስጠት ተጀምሯል። ይኹን እንጂ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን የኀይል ፍላጎት በተፈላጊው መጠን ሟሟላት ስለመቻሉ ጥርጣሬዎች ይነሣሉ። በጎርጎርሳውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2008፣ ሳቶቺ ናካሞቶ በሚል የብዕር ስም በሚታወቅ የቴክኖሎጂ  ባለሞያ የተፈለሰፈው ቢት ኮይን፣ ሰዎች በማናቸውም ሰዓት፣ በየትኛውም የዓለም ክፍል፣ ያለባንክ እና ያለምንም የገንዘብ መተመኛ ለመገበያየት የሚያስችል ሲኾን፣ በበይነ መረብ ላይ ባለቤቱ በሚመሠርተው የምስጢር ቁልፍ ብቻ የሚንቀሳቀስ ነው። መሥራቹ ሳታቺ ናካሞቶ፣ በቁጥር የተወሰኑ ቢትኮይኖችን፣ ኮድ ባላቸው ቁልፎች በመቆለፍ ሰዎች አሥሠው በማግኘት እንዲጠቀሙባቸው ለቋል።  በኢትዮጵያ ፈቃድ አውጥተው የቢትኮይን ማይኒንግ ወይም ፍለጋ ከጀመሩ ተቋማት መካከል ቀዳሚ የሆነው፣ QRB ላብስ ተቋም መሥራች ነሞ ሥምረት፣ አገሪቱ የምታመርተውን የኤሌክትሪክ ኀይል አቅርቦት ተደራሽ የሚያደርግ መሠረተ ልማት አለመኖሩን ጠቅሶ፣ በቢትኮይን አሠሣ፥ በግድቦቹ የሚባክነውን የኤሌክትሪክ ኀይል አገሪቱ ወደ ዶላር እንድትለውጥ ያግዛል፤ ይላል። በአኹን ሰዓት አንድ ቢትኮይን፣ በዓለም ገበያ ላይ እስከ 90ሺሕ የዩናይትድ ስቴትስ ዶላር ይተመናል። ይኹን እንጂ፣ አንድን ቢትኮይን አሥሦ ለማግኘት 155 ሺሕ ኪሎዋት የሚኾን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ያስፈልጋል። ይህ አኀዝ በኢትዮጵያ 1ሺሕ33 መኖሪያ ቤቶችን ለማብራት ያስችላል። እ.ኤ.አ በ2023፣ 50ሺሕ 294 ኪሎ ቶን የኤሌክትሪክ ኀይል  መጠቀሟን፣ ኢንተር ዳታ የተሰኘ ተቋም ድረ ገጽ አመላክቷል። በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ማዕከል በኾነው ሲልከን ቫሊ ባለሞያ የኾነው ቃል ካሳ፣ በኢትዮጵያ ክርፕቶ ከረንሲ እና የቢትኮይን አሠሣ ምን እንደ ኾኑ፣ ወጣቶች እና ፖሊስ አውጭዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይሠራል። ለብዙዎች በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግተውን ፅንሰ ሐሳብ ለአሜሪካ ድምፅ አብራርቷል። ኢታን ቬራ፣ መቀመጫውን በሲያትል ዋሺንግተን ያደረገውና ኢትዮጵያን ጨምሮ በልዩ ልዩ የዓለም ክፍሎች፣ ለቢት ኮይን አምራች ተቋማት የሶፍትዌር እና የማሽን አቅርቦትን የሚያመቻቸው የሉግዘር ቴክ ባልደረባ ነው፤ በኢትዮጵያ ከሚገኙ አሣሽ ድርጅቶችም ጋራ አብሮ ይሠራል። ኢትዮጵያ በታዳሽ ኀይል ማመንጨት ኀይሏ ተመራጭ ኾናለች፤ ይላል። ኢታን ቬራ፣ ቢትኮይን፥ የአገሪቱን ሕዝብ የኀይል አቅርቦት እየተሻማ ይኾን እንደኾን፣ በአሜሪካ ድምፅ ለቀረበለት ጥያቄ፤ በኢትዮጵያ  የሚመነጨው ኀይል በተገቢው መንገድ ለማኅበረሰቡ ተደራሽ አለመኾኑን ጠቅሶ፣ በቢትኮይን ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ተቋማት የኀይል መጠኑ ሳይባክን አገሪቱ ገቢ እንድታገኝ በማስቻል እያገዙ ነው፤ ይላል። አብዛኛዎቹ በቢት ኮይን አሠሣ እና ዝላይ የተሰማሩ ተቋማት፣ ድርጅቶቻቸውንና ማሽኖቻቸውን በኀይል አመንጪ ግድቦች አቅራቢያ እንደሚተክሉ ኢታን ቬራ ይናገራል። በአንድ እና በሁለት ሰው የሚሠራውና እምብዛም የሥራ ዕድል ፈጠራ ዐቅም የሌለው የቢት ኮይን አሠሣ ሥራ፣ አገሪቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ በማድረግ ስኬታማ ኾኗል። አገሪቱ፣ ባለፈው ዓመት ብቻ 55 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ስታደርግ፤ የያዝነው የ2017 ዓ.ም ሲጠናቀቅ 123 ሚሊየን ዶላር ገቢ እንደምታገኝ፣ የዓለም አቀፍ የገበያ ትንተና ገጽ የኾነው Nasdaq ተንብይዋል። ይኹን እንጂ፣ ማሽኖችን በማስገባት እና ከተቋማት ጋራ ሥራን በማሳለጥ፣ ተግዳሮቶች እና መጓተቶች እንደነበሩ፣ የQRB ላብስ መሥራች ነሞ ሥምረት ተናግሯል። የለግዘር-ቴክ ሥራ አስፈጻሚ ኢታን ቬራም፣ አገሪቱ ሥራውን ለማሳለጥ የሚረዳ የፌደራል እና የክልል ፖሊሲዎች ማዘጋጀት እንደሚያስፈልጋት ጠቁሟል። በሌላ በኩል፣ በኢትዮጵያ ፈቃድ አውጥቶ ቢትኮይን መፈለግ የሚቻል ሲኾን፣ ቢትኮይንን ጨምሮ በሌሎች የክሪፕቶ ከረንሲ ዓይነቶች መገበያየት ግን ሕገ ወጥ እንደኾነ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር በኅዳር ወር 2017 ዓ.ም. ባረቀቀው ሰነድ ላይ አስታውቋል። ይህ ውሳኔ፣ የማኅበረሰቡን ግንዛቤ እና ክሪፕቶ ከረሲን የሚያካትት ባለመኾኑ፣ «ለኅብረተሰቡ ደኅንነት የተወሰደ ርምጃ ነው፤» የሚለው ቃል ካሳ፣ ይኹን እንጂ ማኀበረሰቡም ኾነ የመንግሥት አካላት ስለ ጉዳዩ ማወቅና ከዘመኑ ጋራ ለመራመድ ዝግጁ መኾን ይጠበቅባቸዋል፤ ይላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት፣ በገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣናት የእጅ ስልክ ላይ በመደወልና በጽሑፍ መልእክት ለቃለ መጠይቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። በተመሳሳይ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል አገልግሎት ድርጅት፣ ከቢትኮይን ገቢ የሚደረገው የውጭ ምንዛሬ(ዶላር) ፍሰት፣ ተገቢው የኀይል አቅርቦት መስመር ዝርጋታ ላይ ስለመዋሉ፣ እንዲሁም ሥራውን ለመሥራት ወደ ሀገር ለገቡ ተቋማት የማኅበረሰቡን የኀይል አቅርቦት ፍላጎት ባልተሻማ መልኩ ለማቅረብ እያደረጓቸው ስላሉ እንቅስቃሴዎች ጥያቄ ብናቀርብም፣ የኮምዩኒኬሽንስ ድሬክተር ሞገስ መኮንን፣ ከዚኽ ጉዳይ ጋራ በተያያዘ በቅርቡ ቀጣይ ሪፖርት እስኪወጣ ድረስ በጉዳዩ ላይ ቃለ መጠይቅ እንደማይሰጡ ገልጸውልናል።

 ኮንጎ ውስጥ ያልታወቀ በሽታ 50 ሰዎችን ገደለ

ሰሜን ምዕራብ ኮንጎ ውስጥ የተከሰተ ያልታወቀ ወረርሽኝ ከ50 በላይ ሰዎችን መግደሉን ከሥፍራው የሚገኙ ሃኪሞች እና የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣናት በትላንትና
የአሜሪካ ድምፅ

 ኮንጎ ውስጥ ያልታወቀ በሽታ 50 ሰዎችን ገደለ

ሰሜን ምዕራብ ኮንጎ ውስጥ የተከሰተ ያልታወቀ ወረርሽኝ ከ50 በላይ ሰዎችን መግደሉን ከሥፍራው የሚገኙ ሃኪሞች እና የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣናት በትላንትናው ዕለት አስታውቀዋል። የመጀመሪያው የበሽታው ምልክቶች በሚታዩበት እና ለሕመሙ የታጋለጠ ሰው ለሕልፈት በሚዳረግበት መካከል ያለው ጊዜ በአማካይ የ48 ሰዓታት ዕድሜ ብቻ መሆኑን ጠቅሰው፣ “በእጅጉ አሳሳቢ ያደረገውም ይህ ሁኔታ ነው” ሲሉ የክልሉ የወረርሽኞች መከታተያ ማእከል የሆነው የቢኮሮ ሆስፒታል የሕክምና ድሬክተር ሰርጅ ንጋሌባቶ ወረርሽኙን አስመልክቶ ለአሶሺየትድ ፕሬስ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል ። ባለፈው ጥር 23 ቀን  2017 ዓም የተቀሰቀሰው ወረርሽኝ ለሕልፈት የተዳረጉትን 53 ሰዎች ጨምሮ እስካሁን 419 ሰዎች ለበሽታው መጋለጣቸው ተዘግቧል። የዓለሙ ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ አክሎ እንዳመለከተው የበሽታው መከሰት የታወቀው የመጀመሪያዎቹ የወረርሽኙ ሰለባ የሆኑ ሶስት ህጻናት፣ የሌሊት ወፍ ሥጋ ከተመገቡ እና በ48 ሰዓታት ዕድሜ ከፍተኛ ትኩሳትና የደም የመፍሰስ አደጋ የሚያስከትሉ በሽታዎች ምልክቶችን አሳይተው ለሕልፈት ከተዳረጉ በኋላ ነው። የዱር እንስሳት በሥፋት ለምግብነት በሚውሉባቸው አካባቢዎች ከእንስሳት ወደ ሰው የሚዛመቱ በሽታዎች ለረጅም ጊዜ ሲያሳስቡ ቆይተዋል። የዚህን መሰል ወረርሽኞች አሃዝ ባለፉት አስርት ዓመታት ብቻ በአፍሪቃ ውስጥ ከ60 በመቶ በላይ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2022 አስታውቆ ነበር።

የዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ጠበቆች ግጭት ካየለባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ገቡ

የአይሲሲ ዐቃቤ ሕግ ካሪም ካን በምስራቃዊው የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ተባብሶ ከቀጠለባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መግባታቸውን ጽሕፈ
የአሜሪካ ድምፅ

የዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ጠበቆች ግጭት ካየለባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ገቡ

የአይሲሲ ዐቃቤ ሕግ ካሪም ካን በምስራቃዊው የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ተባብሶ ከቀጠለባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መግባታቸውን ጽሕፈት ቤታቸው ዛሬ አስታወቀ። በሩዋንዳ የሚታገዘው ኤም 23 በቅርቡ ምስራቃዊ ኮንጎ ውስጥ ሁለት ትልልቅ ከተሞችን በቁጥጥር ስር በማዋል አማጺው ቡድን ነፍጥ ካነሳበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2021 መገባደጃ ወዲህ በቀጣናው ግዙፍ ሥፍራ እንዲኖረው አድርጎታል። ካን ዋና ከተማይቱ ኪንሻሳ እንደደረሱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኮንጎ ውስጥ እየሆነ ያለው ሁኔታ፤ በተለይም በምስራቃዊው የሃገሪቱ ክፍል የሚካሄደው ግጭት በእጅጉ አሳሳቢ መኾኑን እንረዳለን” ብለዋል። “መልዕክቱ በግልፅ መተላለፍ አለበት። የትኛውም የታጠቀ ቡድን፣ የትኛውም የታጠቀ ኃይል፣ እና የትጥቅ አጋር የሆነ ወገን፤ በመካሄድ ላይ ካለው ምርመራ እና ከተጠያቂነት ነጻ አይሆንም” ብለዋል። «ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕጎችን ማክበር አለባቸው» ሲሉም አክለዋል ካን። እንደ መንግሥታቱ ድርጅት ባለሞያዎችም ገለጻም አማጺው ቡድን ኤም 23 ቁጥራቸው 4 ሺሕ  በሚጠጉ የሩዋንዳ ወታደሮች ይደገፋል።

ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ በመንግሥታቱ ድርጅት በተሰጠው ድምጽ 'ይበልጥ ሚዛናዊነትን ያንጸባረቀ' ያለችውን የዩናይትድ ስቴትስን አቋም አወደሰች

ዩናይትድ ስቴትስ «የሰላም መንገድ» በሚል ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ባቀረበችው የውሳኔ ሐሳብ ላይ የተሰጠውን ድምጽ ተከትሎ፤
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ በመንግሥታቱ ድርጅት በተሰጠው ድምጽ 'ይበልጥ ሚዛናዊነትን ያንጸባረቀ' ያለችውን የዩናይትድ ስቴትስን አቋም አወደሰች

ዩናይትድ ስቴትስ «የሰላም መንገድ» በሚል ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ባቀረበችው የውሳኔ ሐሳብ ላይ የተሰጠውን ድምጽ ተከትሎ፤ የክሬምሊን ቤተመንግሥት በዩክሬን ጉዳይ «ይበልጥ ሚዛናዊነት የተንጸባረቀበት» ያለውን የዋሽንግተንን አቋም በደስታ መቀበሉን በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የክሬምሊኑ ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ «ለጉዳዩ መቋጫ ለማበጀት (ዩናይትድ ስቴትስ) ያላትን እውነተኛ ፍላጎት» ያሳየ ብለውታል። ብሪታንያ እና ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ አጋር አውሮፓውያን በአንጻሩ ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል። ባለ አራት መስመሩ ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረበችው ጽሑፍ “በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በተፈጠረው ግጭት” በጠፋው የሰው ሕይወት ያሳደረበትን ሐዘን አስመልክቶ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ዓላማ “ዓለም አቀፍ ሰላምና ደኅንነትን ማስጠበቅ እና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት” መሆኑን ይገልጻል። በተጨማሪም «ግጭቱ በፍጥነት እንዲቆም፤ በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን አጥብቆ ይማጸናል» ይላል። «ውሳኔው የሰላም መንገድ የሚያስዘን ይሆናል» ያሉት የዩናይትድ ስቴትሷ የመንግሥታቱ ድርጅት መልዕክተኛ ዶረቲ ሺያ ለምክር ቤት አባላት ሲናገሩ “ይህ የመጀመሪያው፣ ነገር ግን ወሳኙ ርምጃ ነው” ብለዋል። “ሁላችንም ልንኮራበት ይገባል። አሁን ለዩክሬን፣ ለሩሲያ እና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሰላም እና መጭ ጊዜ ግንባታ ልንጠቀምበት ይገባል” ሲሉም አክለዋል። ውሳኔው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ ተመሳሳይ ድምፅ የሰጡትን ሩስያ እና ቻይናን ጨምሮ በ10 የድጋፍ ድምጽ ሲጸድቅ፤ ብሪታንያ እናሌሎች አራት አውሮፓውያን የምክር ቤቱ አባል አገራት ድምጽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የተቃውሞ ድምጽ ያሰማ አባል አገር ግን የለም።

በኢትዮጵያ በሬክተር መለኪያ 5.3 የተመዘገበ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሠተ

«ክሥተቱ ያዝ ለቀቅ እያደረገ መቀጠሉ መዘናጋትን በመፍጠሩ ሁልጊዜ መዘጋጀት ያስፈልጋል» - ፕር. አታላይ አየለ በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከም
የአሜሪካ ድምፅ

በኢትዮጵያ በሬክተር መለኪያ 5.3 የተመዘገበ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሠተ

«ክሥተቱ ያዝ ለቀቅ እያደረገ መቀጠሉ መዘናጋትን በመፍጠሩ ሁልጊዜ መዘጋጀት ያስፈልጋል» - ፕር. አታላይ አየለ በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከምትገኘው ጭሮ ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፣ ትላንት እሑድ፣ የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ሌሊት የተከሠተው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ በሬክተር ስኬል 5ነጥብ3 ኾኖ መመዝገቡን፣ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ተቋም አስታውቋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዲሬክተር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ አኹንም የመሬት መንቀጥቀጡ ዋና ምንጭ ፈንታሌ አካባቢ ነው። የመሬት መንቀጥቀጡ እየተፈጠረ ያለውም፣ ቅልጥ አለት እየሰረሰረ ወደ ላይ ለመውጣት በሚያደርገው ሙከራ ነው፤ ሲሉም ዳይሬክተሩ አብራርተዋል። ትላንት እሑድ፣ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 8:45 ላይ የተከሠተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት፣ አዲስ አበባ ውስጥ ጭምር መሰማቱን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል። የመሬት መንቀጥቀጡ፣ በተለይ በአንዳንድ የከተማዋ ስፍራዎች የፈጠረው ንዝረት፣ በመኖሪያ ሕንጻዎች ላይ ንቅናቄ መፍጠሩን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል። ባለፈው ጥር ወር፣ ከዘርፉ ባለሞያዎች ጋራ ውይይት ያደረጉት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ርእሰ መዲናዪቱ ካላት የመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭነት አንጻር፣ ተገቢ የጥንቃቄ ጥናቶችን የሚያደርግ የባለሞያዎች ግብረ ኀይልን በማደራጀት በጋራ ለመሥራት ከስምምነት ላይ መደረሱን መግለጻቸው ይታወሳል። ክሥተቱ ያዝ ለቀቅ እያደረገ መቀጠሉ መዘናጋት መፍጠሩን የጠቀሱት ፕሮፌሰር አታላይ፣ እስከ አኹን መሬት ላይ የወረደ ነገር አለመኖሩን አመልክተዋል። የተፈጥሮ አደጋ «አማክሮ ስለማይመጣ»፣ መደረግ ያለበትን ዝግጅት ሁልጊዜ በተጠንቀቅ ማድረግ እንደሚያስፈልግም፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዲሬክተሩ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ አሳስበዋል።  

በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የድሮን ጥቃት ሲቪል ነዋሪዎች መሞታቸው ተገለጸ

በዐማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ «አነገሽ» ቀበሌ “ኀሙስ ገበያ” በተባለ ስፍራ፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም.
የአሜሪካ ድምፅ

በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የድሮን ጥቃት ሲቪል ነዋሪዎች መሞታቸው ተገለጸ

በዐማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ «አነገሽ» ቀበሌ “ኀሙስ ገበያ” በተባለ ስፍራ፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም. ተያይዘው በተሠሩ የንግድ ቤቶች ላይ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት፣ ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን፣ የሟች ቤተሰቦች እና የዐይን እማኞች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። በገበያው ዳር ኳስ ሲጫወት የነበረ የ15 ዓመት ልጃቸው በጥቃቱ መገደሉን የተናገሩት ወይዘሮ ታንጉት የተባሉ እናት፣ የስምንት ዓመት ልጃቸውም ቆስሎ በሆስፒታል እንደሚገኝ ገልጸዋል። የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ የኔዋ ደመቀ ግን፣ ጥቃቱ በሲቪል ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ ሳይኾን፣ “ጽንፈኛ” ሲሉ በጠሩት ቡድን ላይ የተፈጸመ እንደኾነ ገልጸው አስተባብለዋል። ጥቃቱም የተፈጸመው፣ ታጣቂው ኀይል እንደ ካምፕ እየተጠቀመበት ባለው ትምህርት ቤት ላይ እንጂ የንግድ ሱቆች ላይ አይደለም፤ ሲሉ አመልክተዋል። በአንጻሩ፣ በጥቃቱ መጎዳታቸውን የገለጹና የተጎጂዎችን አስከሬን ሰብስበናል ያሉ የስፍራው ነዋሪዎች፣ ጥቃቱ በሲቪሎች ላይ የተፈጸመ ነው፤ ብለዋል። የዐይን እማኞቹ እንደሚሉት፣ በዕለቱ ሰባት የሚደርሱ ሟቾችን ቀብር፣ በከተማው ውስጥ በሚገኝ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አከናውነዋል። አብዛኛዎቹ ተጎጂዎችም፣ ከገጠር ቀበሌዎች ቆርቆሮ ለመግዛት ተሰባስበው የመጡ ንጹሓን ናቸው፤ ብለዋል። ጥቃቱ የተፈጸመበት የአነገሽ ቀበሌ ኀሙስ ገበያ አካባቢ፣ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በፋኖ ታጣቂ ኀይሎች ቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ፣ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል።

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አሜሪካና ዩክሬን በተናጥል ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ ላይ ድምፅ ይሰጣል

በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ማስቆም በተመለከተ፣ በአንድ ወገን በአሜሪካ በሌላ ወገን ደግሞ በዩክሬን ተረቀው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ
የአሜሪካ ድምፅ

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አሜሪካና ዩክሬን በተናጥል ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ ላይ ድምፅ ይሰጣል

በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ማስቆም በተመለከተ፣ በአንድ ወገን በአሜሪካ በሌላ ወገን ደግሞ በዩክሬን ተረቀው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የቀረቡ የውሳኔ ሐሳቦች ዛሬ ሰኞ ድምፅ እንደሚሰጥቸው ይጠበቃል። ጠቅላላ ጉባኤው በቅድሚያ በዩክሬን በቀረበውና በአውሮፓ ኅብረት በሚደገፈው ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምፅ እንደሚሰጥ ሲጠበቅ፣ በመቀጠል ደግሞ በአሜሪካ በቀረበው ላይ ድምፅ ይሰጣል። የድርጀቱ የፀጥታው ምክር ቤት ደግሞ በተናጥል በአሜሪካ በቀረበው ረቂቅ ላይ ድምጽ ይሰጣል ተብሏል። አሜሪካ “ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆምና በዩክሬንና በሩሲያ መካከል ዘላቂ ሠላም እንዲመጣ ጥሪ አድርጋለች” ያለው የሮይተርስ ዘገባ፣ የአሜሪካው ረቂቅ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን አያመለክትም ብሏል። የውሳኔ ሐሳቡ “ግጭቱ አሰቃቂ መሆኑን፣ ግጭቱን ለማቆም ደግሞ ተመድ ሊረዳ እንዳሚችል፣ ሠላምንም ማስፈን እንደሚችል ያሳያል” ሲሉ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ማክሮ ሩቢዮ ባለፈርው ዓርብ ተናግረዋል። ጠቅላላ ጉባኤው ያቀረበችውን የውሳኔ ሐሳብ እንዲያፀድቅ እንዲሁም በዩክሬንና በአውሮፓ አጋሮቿ የቀረበውን ሐሳብ ውድቅ እንዲያደርግ አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ መልዕክት ማስተላለፏንና ይህንኑም መመልከቱን ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል። በዩክሬን የቀረበው ረቂቅ ደግሞ ጠቅላላ ጉባኤው ከዚህ በፊት የደረሰበት የውሳኔ ሐሳብ ተግባራዊ እንዲሆን ይጠይቃል። ይህም ሩሲያ በዓለም እውቅና ከተሰጠው የዩክሬን ድንበር ሙሉ ለሙሉ እንድትወጣ የሚጠይቀውን ይጨምራል። የጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔዎች ተፈጻሚነት ሕጋዊ ግዴታ የሌለባቸው ቢሆኑም፣ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ሞራላዊ ጫና እንዲፈጠር ሊያደርጉ ግን ይችላሉ። በፀጥታው ምክር ቤት አንድ የውሳኔ ሐሳብ ለማለፍ ከ15 ዓባላት ውስጥ ቢያንስ የዘጠኙ ድጋፍ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ ከቋሚ ዓባላት ውስጥ ማለትም ከእንግሊዝ፣ ቻይና፣ ፈረንሣይ፣ ሩሲያ ወይም አሜሪካ አንዳቸው ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸን ሊጠቀሙ ይችላሉ። የአሜሪካው የውሳኔ ሐሳብ በቂ ድጋፍ ሊያገኝ እንደሚችል ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

የሱዳን ጦር የበላይነት እያገኘ መኾኑን አስታወቀ 

የሱዳን ጦር ከአንድ ዓመት በላይ በከበባ ስር የቆየውን ኦቤይድ የተሰኘ ቁልፍ ከተማ ማስለቀቁን፣ ወደ ደቡብ ማዕከላዊ ክልል መድረስ የሚያስችለው ስልታዊ  አካባ
የአሜሪካ ድምፅ

የሱዳን ጦር የበላይነት እያገኘ መኾኑን አስታወቀ 

የሱዳን ጦር ከአንድ ዓመት በላይ በከበባ ስር የቆየውን ኦቤይድ የተሰኘ ቁልፍ ከተማ ማስለቀቁን፣ ወደ ደቡብ ማዕከላዊ ክልል መድረስ የሚያስችለው ስልታዊ  አካባቢ መያዙን እና ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል ጋራ እያደረገ ላለው ጦርነት ወሳኝ የአቅርቦት መንገዶችን ማጠናከሩን አስታወቀ። የጦሩ ቃል አቀባይ ብርጋዴን ጀነራል ናቢል አብዱላህ በሰጡት መግለጫ፣ ወታደሮቹ በፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች ስር የነበረውን የነጭ አባይ ጠንካራ ይዞታ ማስለቀቅ መቻላቸውን እና ይህም የተቀናቃኙን ኃይል ያመናመነ መኾኑን ገልጸዋል። አብዱላህ አክለው አል-ሳይድ ውስጥ የሚገኘው የሀገሪቱ ጦር ወደ ኦቤይድ የሚወስደውን መንገድ መክፈቱን እና ፈጥኖ ደራሹ በሰሜናዊ ኮርዶፋን ክልል ዋና ከተማ ላይ ያካሄደው ከበባ ማብቃቱን አብራርተዋል። ከተማዋ የተንጣለለ ወታደራዊ የአየር ማረፊያ እና ሃግና ተብሎ የሚጠራው አምስተኛ ወታደራዊ የጦር ሰፈር የሚገኝበት ነው። የንግድ እና የትራንስፖርት ማዕከል የሆነችው ኦቤይድ፣ የደቡብ ዳርፉር ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን ኒያላን ከካርቱም ጋራ የሚያገናኘው የባቡር ሃዲድም የሚገኝባት ሲሆን እ.አ.አ በሚያዚያ 2023 ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ስር ቆይታለች።  የሀገሪቱ ገንዘብ ሚኒስትር ጂብሪል ኢብራሂም ጦሩ በኦቤይድ ያገኘውን ድል «ትልቅ ርምጃ» ሲሉ አወድሰዋል። 

የኮንጎ ፕሬዝዳንት 'የአንድነት መንግስት' እመሰርታለሁ አሉ

በምስራቃዊው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት እየተባባሰ በሄደበት ወቅት በቀውሱ አያያዝ ዙሪያ የሚሰነዘርባቸው ትችት እየጨመረ የሄደው የኮንጎ ፕሬዝዳንት
የአሜሪካ ድምፅ

የኮንጎ ፕሬዝዳንት 'የአንድነት መንግስት' እመሰርታለሁ አሉ

በምስራቃዊው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት እየተባባሰ በሄደበት ወቅት በቀውሱ አያያዝ ዙሪያ የሚሰነዘርባቸው ትችት እየጨመረ የሄደው የኮንጎ ፕሬዝዳንት፣ የአንድነት መንግስት እንደሚመሰርቱ አስታወቁ።  የኤም 23 አማፂያን በምስራቃዊ ኮንጎ የሚገኙ ዋና ዋና ከተሞችን ከተቆጣጠሩ በኃላ፣ ትላንት ቅዳሜ ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር ያደረጉት የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ሀገሪቱን ለሚያስተዳድረው ጥምር ፓርቲ በውስጣዊ ግጭቶች እንዳይዘናጉ አሳስበዋል።  «በትግሉ ነው እንጂ በጦርነቱ አልተሸነፍኩም » ያሉት ፕሬዳንቱ «ሁሉንም ተቃዋሚዎች ማነጋገር አለብኝ። የብሔራዊ አንድነት መንግስት ይመሰረታል» ብለዋል። ይህ ጥምር መንግስት ምን ሊመስል እንደሚችል ወይም መቼ እንደሚፈፀም ግን ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።  በምስራቅ ኮንጎ የበላነት ለማግኘት ከሚፎካከሩ ከመቶ በላይ ታጣቂ ቡድኖች መካከል ከፍተኛ ኃይል ያላቸው የኤም23 አማፂያን፣ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በመግደል ትልቁን ከተማ ጎማን ጨምሮ አብዛኛውን ምስራቃዊ ክፍል ተቆጣጥረዋል። ሺሴኬዲ ቅዳሜ እለት ባደረጉት ንግግር በጦርነቱ ህይወታቸው ላጡ ወታደሮች ምስጋና አቅርበው ጦሩን ለመደጋፍ ቃል ገብተዋል።  የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት የኤም 23 አማፂ ቡድንን በአሸባሪነት የፈረጀ ሲሆን ሩዋንዳ ለቡድኑ ድጋፍ ትሰጣለች ሲልም ይከሳል። ሩዋንዳ በበኩሏ ክሱን አትቀበልም። 

ሩሲያ በሚያንማር ወደብ እና የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት የሚያስችላት የመግባቢያ ሰነድ ፈረመች

ሚያንማር እና የቅርብ አጋሯ ሩሲያ፣ ዳዌይ በተሰነው ልዩ የኢኮኖሚ ዞን፣ የወደብ እና የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታን ያካተተ የመዋዕለ ንዋይ ትብብር መፈራረማቸውን
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ በሚያንማር ወደብ እና የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት የሚያስችላት የመግባቢያ ሰነድ ፈረመች

ሚያንማር እና የቅርብ አጋሯ ሩሲያ፣ ዳዌይ በተሰነው ልዩ የኢኮኖሚ ዞን፣ የወደብ እና የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታን ያካተተ የመዋዕለ ንዋይ ትብብር መፈራረማቸውን የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዛሬ እሁድ አስታውቋል።  የሩሲያ ሚኒስትሩ ማክሲም ሪሼንትኒኮቭ እና የሚያንማር የመዋዕለ ንዋይ እና የውጭ ኢኪኖሚ ግንኙነት ሚኒስትር ካን ዛው ስምምነቱን የተፈራረሙት፣ የሩሲያ ልዑካን ቡድን ደቡብ ምስራቃዊዋን የእስያ ሀገር በጎበኙበት ወቅት ነው።  የሩሲያው ሚኒስቴር መስሪያቤት ሪሼንትኒኮቭን ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ «ስምምነቱ በሚያንማር ከሚገኙ የሩሲያ ኩባንያዎች ጋር በጋራ የሚተገበሩ በርካታ ትላልቅ መሠረተ ልማት እና የኢነርጂ ፕሮጀክትን ያካትታል» ብሏል። ፕሮጀክቱ ወደብ፣ በድንጋይ ከሰል የሚሰራ የሙቀት ኃይል ማመንጫ እና የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካን እንደሚያካትትም በመግለጫው ተመልክቷል። እ.አ.አ በየካቲት 2021 በሚያንማር በተካሄደ መፈንቅለ መንግስት የኦንግ ሳን ሱ ኪ መንግስት ከስልጣን ከወረደ ወዲህ ሩሲያ የሚያንማር የቅርብ አጋር የሆነች ሲሆን ሞስኮ እና ኔይፒዳ፣ በኃይል ግንባታ ዙሪያ የሚያደርጉትን ትብብር ለማጠናከር ሲወያዩ መቆየታቸው ይታወሳል። 

ኢኮኖሚ፣ ስደት እና አክራሪ ኃይሎች ትኩረት የሳቡበት የጀርመን ምርጫ እየተካሄደ ነው

የጀርመን መራጮች ዛሬ እሁድ በሚካሄደው ምርጫ ድምፅ መስጠት ጀምረዋል። ምርጫው ለዓመታት የተቀዛቀዘው የአውሮፓ ኢኮኖሚ፣ ስደትን ለመግታት የሚደረገው ጫና፣
የአሜሪካ ድምፅ

ኢኮኖሚ፣ ስደት እና አክራሪ ኃይሎች ትኩረት የሳቡበት የጀርመን ምርጫ እየተካሄደ ነው

የጀርመን መራጮች ዛሬ እሁድ በሚካሄደው ምርጫ ድምፅ መስጠት ጀምረዋል። ምርጫው ለዓመታት የተቀዛቀዘው የአውሮፓ ኢኮኖሚ፣ ስደትን ለመግታት የሚደረገው ጫና፣  የዩክሬን ዕጣ ፈንታ እና ስጋት ውስጥ የወደቀው የአውሮፓ እና የዩናይትድ ስቴትስ አጋርነት ጥላ ያጠላበት ነው።  ለዘብተኛ ቀኝ ዘመም ተቃዋሚዎች ምርጫውን ሊያሸንፉ ይችላሉ የሚሉ ግምቶች ቢኖሩም፣ ከሕዝብ የተሰበሰቡ ድምፆች በበኩላቸው፣ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ባልታየ ሁኔታ ለቀኝ አክራሪ ፓርቲ ድጋፍ እንዳለ አሳይተዋል።  ጀርመን ከ27ቱ የአውሮፓ ህብረት አባላት በሕዝብ ብዛት ቀዳሚዋ ስትሆን፣ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ)ም ከፍተኛውን ድርሻ ትይዛለች።  ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥሎ ለዩክሬን ከፍተኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢ በሆነችው ጀርመን እስካሁን ከህዝብ የተሰበሰቡ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት፣ የለዘብተኛው ቀኝ ዘመም የተቃዋሚ መሪ ፍሬድሪክ ሜርዝ ፓርቲ ከ28-32 በመቶ ድጋፍ ሲያገኝ የቆየ ሲሆን ሜርዝ፤ ሾልዝን ሊተኩ ይችላሉ ተብሎም ተገምቷል።  የፀረ-ስደት አቋም የሚያራምደው ቀኝ አክራሪው ኤ ኤፍ ዲ የተሰኘው ፓርቲ በበኩሉ በ20 ከመቶ ድምፅ በሁለተኛነት ሲከተል ቆይቷል።  በዛሬው የጀርመን ምርጫ የሚፎካከሩት ፓርቲዎች በዋናነት ላለፉት ሁለት አመታት ያሽቆለቆነውን የጀርመን ኢኮኖሚ በድጋሚ እንዲያንሰራራ ያስችላል ያሉትን ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን፣ ባለፈው ወር በስደተኞች የተፈጸሙትን ጥቃቶች ተከትሎም፣ የስደት ጉዳይ የምርጫ ዘመቻው ቀዳሚ አጀንዳ መሆን ችሏል። 

ታጋቾቿ 'አሸማቃቂ' በሆነ መንገድ ተለቀዋል ያለቸው እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን የመልቀቁን ሂደት አዘገየች

እስራኤል ቀጣዮቹ ታጋቾቿ መፈታታቸው እስከሚረጋገጥ እና በጋዛ በሚካሄደው የእስረኛ ልውውጥ ወቅት ይፈፀማል ያለችው አሸማቃቂ ሥነስርዓት እስከሚነሳ ድረስ፣
የአሜሪካ ድምፅ

ታጋቾቿ 'አሸማቃቂ' በሆነ መንገድ ተለቀዋል ያለቸው እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን የመልቀቁን ሂደት አዘገየች

እስራኤል ቀጣዮቹ ታጋቾቿ መፈታታቸው እስከሚረጋገጥ እና በጋዛ በሚካሄደው የእስረኛ ልውውጥ ወቅት ይፈፀማል ያለችው አሸማቃቂ ሥነስርዓት እስከሚነሳ ድረስ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም እስረኞችን የመልቀቁን ሂደት ማዘግየቷን አስታውቃለች።  የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት ዛሬ እሁድ ያወጣው መግለጫ ይፋ የሆነው እስረኞችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከኦፈር ማረሚያ ቤት እየወጡ ባሉበት ወቅት ሲሆን፣ መኪናዎቹ አዙረው ወደ እስርቤቱ ተመልሰዋል።  ስድስቱ የእስራኤል ታጋቾች ቅዳሜ እለት መለቀቃቸውን ተከትሎ ከእስር መፈታት የነበረባቸው 620 የፍልስጤም እስረኞች እስካሁን እንዳልተፈቱም ተገልጿል። ይህ ድንገተኛ የእስራኤል መግለጫ፣ የተኩስ ማቆሙን ስምምነት እጣፈንታ ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል።  የእስረኞቹ መፈታት መዘግየቱን የፍልስጤም አስተዳደር እስረኞች ጉዳይ ኮሚሽን ያስታወቀ ሲሆን ዌስት ባንክ ውስጥ የተቀረፀው የአሶሽዬትድ ፕሬስ ምስል፣ የእስረኛ ቤተሰቦች እጅግ በጣም በሚቀዘቅዘው አየር ውስጥ ሆነው ሲጠባበቁ እና በመጨረሻ ሲበተኑ ያሳያል።  ቅዳሜ እለት የተለቀቁት ስድስቱ ታጋቾች፣ በመጀመሪያው ዙር የተኩስ ስምምነት ይለቀቃሉ ተብለው ከተጠበቁት በህይወት ያሉ የመጨረሻዎቹ ታጋቾች ሲሆኑ፣ ይህ ዙር ከአንድ ሳምንት በኃላ ይጠናቀቃል። ለሁለተኛው ዙር የተኩስ ስምምነት የሚደረገው ድርድር ገና አለመጀመሩም ተመልክቷል። 

ወባን ከአፍሪካ ለማጥፋት በየአመቱ 5.2 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ

ወባን በሁለት አመት ውስጥ ከአፍሪካ አህጉር ለማጥፋት በየአመቱ 5 ነጥቢ 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ኅብረት አስታወቀ፡፡ በ38ኛው የአፍሪካ መሪዎ
የአሜሪካ ድምፅ

ወባን ከአፍሪካ ለማጥፋት በየአመቱ 5.2 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ

ወባን በሁለት አመት ውስጥ ከአፍሪካ አህጉር ለማጥፋት በየአመቱ 5 ነጥቢ 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ኅብረት አስታወቀ፡፡ በ38ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ኅብረቱ በሰጠው መግለጫ፣ የወባ በሽታን የመከላከል ጥረቱ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ችግር ገጥሞታል ብሏል። በቅርቡ የአሜሪካ መንግስት ርዳታን ለማቋረጥ ያሳለፈው ውሳኔ ደግሞ፣ ችግሩን ያባብሶዋል በማለት ተናግሯል። የአሜሪካ መንግስት በበኩሉ፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ሥርዐቱን ዳግም እየፈተሸ መሆኑን ገልጿል።   ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የትራምፕና ፑቲን የፊት ለፊት ውይይት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸውን ሩስያ አስታወቀች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፊት ለፊት የሚገናኙበት ስብሰባ ዝግጅት መጀመሩን የሩሲያ ምክትል የውጭ
የአሜሪካ ድምፅ

የትራምፕና ፑቲን የፊት ለፊት ውይይት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸውን ሩስያ አስታወቀች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፊት ለፊት የሚገናኙበት ስብሰባ ዝግጅት መጀመሩን የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡ ይህም በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በምዕራባውያን ለተገለለቸው ሩስያ ትልቅ ለውጥን የሚያመጣላት ነው ተብሏል፡፡ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰርጌይ ራያብኮቭ ለሃገራቸው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የፑቲንና ትራምፕ የመሪዎች ስብሰባ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይም ያተኮሩ ሰፊ ውይይትን ያካተተ ይሆናል ብለዋል፡፡ ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱን ስብሰባ ለማደራጀት ጥረቶች ገና ጅምር ላይ ናቸው ፣ እናም ይህንን ለማድረግ “በጣም የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ሥራን ይጠይቃል” ብለዋል ። ሪያብኮቭ አክለውም የዩናይትድናይትድ ስቴትስና የሩሲያ ልዑካን በከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል ለቀጣይ ንግግሮች መንገድ ለመክፈት «በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ» ሊገናኙ እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች ማክሰኞ እለት በሳኡዲ አርቢያ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆምና ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ተስማምተዋል ። በስብሰባው ላይ የዩክሬን ልዑክ ያልተሳተፈ ሲሆን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ኪየቭ ባልተሳተፈችበት የውይይቱ ምንም አይነት ውጤት ሀገራቸው እንደማትቀበል ገልጸው ባለፈው ረቡዕ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሊያደርጉ የነበረውን ጉዞም አራዝመዋል።

ቫቲካን ሊቀ ጳጳሱ ሳይኖሩ የቅዱስ ዓመቷ ክብረ በዓልን እያከናወነች ነው 

የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ከገጠማቸው የሳንባ ምች እና የተወሳሰበ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ጋር እየታገሉ ሲሆን ቫቲካን ያለ እርሳቸው የቅዱስ ዓመ
የአሜሪካ ድምፅ

ቫቲካን ሊቀ ጳጳሱ ሳይኖሩ የቅዱስ ዓመቷ ክብረ በዓልን እያከናወነች ነው 

የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ከገጠማቸው የሳንባ ምች እና የተወሳሰበ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ጋር እየታገሉ ሲሆን ቫቲካን ያለ እርሳቸው የቅዱስ ዓመት ክብረ በዓልን እያከበረች ትገኛለች፡፡  አባ ፍራንሲስ ዛሬ ሌሊት በደንብ ተኝተው ማሳለፋቸውን የቫቲካን ቃል አቀባይ ማትዮ ብሩኒ ስለላሉበት የጤና ሁኔታ በተመለከተ በሰጡት አጭር መግለጫ ተናግረዋል።  ነገር ግን ዶከተሮች የ88 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ የገጠማቸው ህመም የተወሳሰበ የሳምባ ምች ሊያስከትል የሚችል የደም 'ኢፌክሽን' ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን በመግለጥ እያሰጠነቀቁ ነው፡፡   እስከትላንት ምሽት ድረስ ግን በሽታው ይህ ስለመሆኑ ማረጋገጫ አለማግኘታቸውንና ስለሚወስዷቸው መድሃኒትቶችም ሊቀ ጳጳሱ ምላሽ እንደሚሰጡ የህክምና ቡድኑ ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ በሰጠው የመጀመርያ ማብራርያው ላይ አስታውቋል፡፡  የ88 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ ከአንድ ሳምንት በላይ በመተንፈሻ አካላት በሽታ ሲሰቃዩ ቆይተው ባለፈው ሳምንት ሮም በሚገኘው ገሚሊ ሆስፒታል ገብተዋል።  ከአውሮፓዊያኑ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሊቀ ጳጳስነት መንበራቸው የቀጠሉት ፍራንሲስ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተደጋጋሚ የኢንፍሉዌንዛ እና ሌሎች የጤና ችግሮች አጋጥሟቸዋል።  በልጅነታቸው ፕለረሲ በተባለ በሽታ በመጠቃታቸው ከአንደኛው የሳንባ ክፍል የተወሰነው በቀዶ ጥገና እንዲወገድ ተደርጓል። በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ሊቀ ጳጳሱ ለሳንባ መቆጣት ተጋላጭ ኾነዋል። 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አማፂያን ከያዟቸው የኮንጐ ከተሞች እንዲወጡ ጠየቀ 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በምስራቃዊ ኮንጎ የሚገኘው የኤም 23 አማፅያን ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም እና ከያዛቸው ግዛቶች እንዲ
የአሜሪካ ድምፅ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አማፂያን ከያዟቸው የኮንጐ ከተሞች እንዲወጡ ጠየቀ 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በምስራቃዊ ኮንጎ የሚገኘው የኤም 23 አማፅያን ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም እና ከያዛቸው ግዛቶች እንዲወጣ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ትላንት አርብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ምክር ቤቱ ግጭቱን በሚያራዝሙ አካላት ላይ ማዕቀብ እንደሚጣልባቸውም ዝቷል።  የወሳኔ ሃሳቡን ረቂቅ ያዘጋጀችው ፈረንሣይ በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ለተፈጠረው ግጭት ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ ግልጽ መልዕክት ያስተላለፈ ነው ስትል አስታውቃለች፡፡  «ቅድሚያ የሚሰጠው ውጤታማ፣ ቅድመ ሁኔታ የሌለው እና አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ነው» ሲሉ አምባሳደር ኒኮላ ዴ ሪቪየር ተናግረዋል። በቀጠናው ደረጃ የሚደረጉ የማሸማገል ጥረቶችና ውይይቶች አስፈላጊነት የገለጡት አምባሳደሩ  የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መከበር አለበት ብለዋል፡፡  የውሳኔ ሃሳቡ የሩዋንዳ መከላከያ ሰራዊት ለኤም 23 የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቆም እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግዛት በአስቸኳይ እንዲወጣ ይጠይቃል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት የሩዋንዳ መከላከያ ሰራዊት ለኤም 23 “ቀጥታ ድጋፍ” ያደርጋል ሲሉ ከሰዋል። ሩዋንዳ አማፂያኑን ትደግፋለች የሚለውን ውንጀላ ደጋግማ ስታስተባብል ቆይታለች።  የፀጥታው ምክር ቤት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሩዋንዳ «ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች በአስቸኳይ እንዲመለሱም»  አሳስቧል። 

ሃማስ ተጨማሪ እስራኤላውያን ታጋቾችን ለቀቀ 

የተኩስ አቁም ስምምነቱ አካል በሆነው የታጋቾችና እስረኞች ልውውጥ ሁለት እስራኤላውያን ታጋቾች ዛሬ አስቀድመው የተለቀቁ ሲሆን ሌሎች ሶስት ታጋቾች ደግሞ ቆይ
የአሜሪካ ድምፅ

ሃማስ ተጨማሪ እስራኤላውያን ታጋቾችን ለቀቀ 

የተኩስ አቁም ስምምነቱ አካል በሆነው የታጋቾችና እስረኞች ልውውጥ ሁለት እስራኤላውያን ታጋቾች ዛሬ አስቀድመው የተለቀቁ ሲሆን ሌሎች ሶስት ታጋቾች ደግሞ ቆይተው ተለቀዋል፡፡ በዚህ ምትክም በመቶ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞች የሚለቀቁ ይሆናል፡፡   ከጋዛ አርብ የተመለሰው አስከሬንም የታጋች ሺሪ ቢባስ መሆኑም ተረጋግጧል፡፡  አስቀድመው ከተለቀቁት ታጋቾች መካከል የ40 አመቱ ታል ሾሃም፣ እአአ ጥቅምት 7፣ 2023  ሃማስ በእስራኤል ላይ ባደረሰው ጥቃት ከኪቡትዝ ቢኤሪ ታግቶ የተወሰደ ሲሆን ሁለተኛው የ39 አመቱ አቬራ መንግስቱ ደግሞ ከአስር አመት በፊት ብቻውን ወደ ጋዛ ገብቶ የነበረ ነው፡፡   ታጋቾችን ሃማስ ዛሬ ቅዳሜ ረፋድ ላይ በጋዛ ራፋህ ከተማ ለቀይ መስቀል አስረክቧቸዋል፡፡ በርክክቡ  ወቅት አውቶማቲክ መሳሪያ የያዙ እና ወታደራዊ ልብስ የለበሱ የሃማስ ተዋጊዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዝናባማ በሆነው የአየር ሁኔታ ራፋህ አደባባይ ላይ ቁመው ታይተዋል፡፡  ሃማስ ቆይቶም የ27 ዓመቱን ኤሊያ ኮኸን፣ የ22 አመቱ ኡመር ሸህም ቶቨ እና የ23 አመቱ ኡመር ዌንከርት የተባሉ ሶስት እስራኤላውያን ታጋቾችን ለቋል፡፡  ኮኸን፣ ቶቭ እና ዌንከርት እአአ ጥቅምት 7፣ 2023 በአሜሪካ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሃማስ  በእስራኤል ላይ  ጥቃት ባደረሰበት ወቅት ከሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ አግቶ የወሰዳቸው ናቸው፡፡  በቴል አቪቭ የእስራኤልን ባንዲራ የሚያውለበልቡ እና የታጋቾቹን ምስል የያዙ ሰዎችም የታጋቾችን መለቀቅ በቪድዮ ሲከታተሉና ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል፡፡  በተለቀቁት ታጋቾች በምትኩ እስራኤል ከ600 በላይ ፍልስጤማውያንን እስረኞችን ትፈታለች።  ሌላ አንድ ታጋች ዛሬ አመሻሽ ላይ ይለቀቃ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን አጠቃላይ የተለቀቁት ስድስቱ ታጋቾችም  በመጀመሪያው ምዕራፍ የተኩስ አቁም ወቅት ነፃ የሚወጡት የመጨረሻዎቹ ታጋቾች ይሆናሉ ተብሎም ይጠበቃል። 

በምዕራብ ዩክሬን በምትገኝ አንዲት መንደር ወንዶች አይታዩም

በምዕራብ ዩክሬን የምትገኘው ማኪቭ ከተማ፣ ብዙም ወንዶች አይታዩባትም። በርካቶች ሸሽተዋል ወይም ውጊያ ላይ ናቸው አልያም የሩሲያን ወረራ ለመመከት ሲፋለሙ ሕ
የአሜሪካ ድምፅ

በምዕራብ ዩክሬን በምትገኝ አንዲት መንደር ወንዶች አይታዩም

በምዕራብ ዩክሬን የምትገኘው ማኪቭ ከተማ፣ ብዙም ወንዶች አይታዩባትም። በርካቶች ሸሽተዋል ወይም ውጊያ ላይ ናቸው አልያም የሩሲያን ወረራ ለመመከት ሲፋለሙ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ችግሩ በዩክሬን ባሉ በርካታ ከተሞች የሚታይ ነው። ጦርነቱ ወትሮውንም እየቀነሰ የመጣውን የሕዝብ ቁጥር አባብሶታል። ከጦር ሜዳ የቀሩትና ሕይወታቸውን መልሰው ለመገንባት የሚጥሩት የቀሩት ነዋሪዎች የዩክሬን የወደፊት ዕጣ ያሳስባቸዋል። በጦርነቱ ሕይወታቸውን ለሰጡ ወታደሮች መታሰቢያ በማኪቭ ዋናው አውራጎዳና ላይ ይታያል። ፎቶዎቹ መስዋቶቹ ደስተኛ በነበሩበት ጊዜ የተነሱት ነው። ከፎቷቸው በላይ “ክብር ለጀግኖች” የሚል ጽሁፍ ይታያል። ይህም ጦርነቱ የወለደው መፈክር ነው። ማኪቭ ከተማ የምትገኘው ከጦር አውድማው 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው። ጦርነት ያደረሰውን ከፍተኛ ጉዳት እንደዚህች ከተማ የሚያሳዩ ጥቂት ናቸው። በከተማዋ ዕድሜያቸው ለውትድርና የደረሱ ወንዶች የሚገኙት በፎቶ ግራፍ ላይ ብቻ ነው። ወይም ደግሞ በከተማዋ የመቃብር ሥፍራ ነው። ሌሎቹ ወንዶች ለቀው ሄደዋል። “ተመልከት፣ ሰው የት ነው ያለው? ተደብቀዋል። ስጋት አድሮባቸዋል” ይላል ሹፌሩ አሌክስ ካሞቪስኪ። ከ30 ዓመታት በላይ በጀርመን ኖሯል። ወደ ትውልድ ከተማው የተመለሰው ሰነዱን ለማደስ ነበር። ጓደኞቹ እና ዘመዶቹ በከተማው የሉም። “አሳዛኝ ነው!” ሲልም አክሏል። ካሞቪስኪ እንደሚለው ለውጊያ ዕድሜያቸው የደርሱ በርካታ ወንዶች ወደ ግንባር እንዳይላኩ ወደ ገጠር ሄደው ተደብቀዋል። በማኪቭ ከተማ መንገዶች ላይ የተዘዋወረው የቪኦኤ ዘጋቢ ያገኛቸው አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው። ወንዶች በመሄዳቸው ሕይወት ይበልጥ ከባድ እንደሆነ በርካታ ሴቶች ተናግረዋል። “እድሜዪ የገፋ ሴት ነኝ። ከሰባ ዓመቴ በላይ ነኝ። በእርግጥ ከልጆቻቸው ጋራ ለተተዉት ወጣት ሴቶች ይበልጥ ከባድ ነው። ወንድ ከቤት ካለ፣ ጠባቂ ብቻ ሳይሆን፣ ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን የሚያቀርብም ነው። በሁሉም ጉዳይ ላይ ይረዳል። በተለይም በገንዘብ ጉዳይ” ብለዋል አስተማሪ የነበሩትና አሁን ጡረታ ላይ የሚገኙት ኒዮሊና ኮቫሌንኮ። በምዕራብ ዩክሬን የሚገኙ በርካታ ከተሞች ውስጥ የወንዶች አለመኖር ትልቅ ችግር ፈጥሯል። ማኪቭ ከተማ ግን ከጦርነቱም በፊት ቢሆንም የነበረው የሕዝብ ቁጥር መቀነስ ቀውስ ማሳያ ነች፡፡ መንግሥት እንደሚለው፣ የሕዝቡ ቁጥር በእ.አ.አ 1991 ከነበረው 52 ሚሊዮን፣ በእ.አ.አ 2024 ወደ 32 ሚሊዮን አቆልቁሏል። አንጀሊና ቦንዳል የከተማዋ ነዋሪና ተማሪ ነች።“ይህ እጅግ ያስፈራኛል። በርካታ ቤተሰቦች ሃገሪቱን ለቀው በመውጣታቸው በሃገሪቱ ሁሉም ነገር ተቀይሯል። ሃገሪቱም ተቀይራለች፡፡ ብዙ ሰዎች ለቀው ስለወጡ በጣም ያሳዝናል። ምንም ጓደኛ የለኝም። ቤተሰቤ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ከሃገር ወጥቷል። ያሳዝናል” ብላለች የከተማዋ ነዋሪና ተማሪ የሆነችው አንጀሊና ቦንዳል። አንጀሊና ቦንዳር ገና 15 ዓመቷ ነው። አንድ ጎረቤቷ በጦርነቱ ሕይወቱን አጥቷል። ሌሎቹ ጎረቤቶቿ አሁንም ውጊያ ላይ ናቸው። አብዛኞቹ ጓደኞቿ ለቀው የወጡት ገና በልጅነታቸው ነው። አንድ ቀን ዩክሬንን መልሶ የመገንባት ሥራው በእርሷ ትውልድ ላይ እንደሚወድቅ አውቃለች፡፡ ያንን ሃላፊነት ለመጋፈጥ ዝግጁ ስለመሆኗ ግን እርግጠኛ አይደለችም።

Get more results via ClueGoal