የትራምፕ እና የዜለንስኪ የዋይት ሐውስ ውይይት ወደ ተጋጋለ የቃል ልውውጥ ተቀየረ
newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስኪ ጋራ በዋይት ሐውስ ያደረጉት እና አሜሪካ ከዩክሬን ልዩ ማዕድናት ማግኘየትራምፕ እና የዜለንስኪ የዋይት ሐውስ ውይይት ወደ ተጋጋለ የቃል ልውውጥ ተቀየረ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስኪ ጋራ በዋይት ሐውስ ያደረጉት እና አሜሪካ ከዩክሬን ልዩ ማዕድናት ማግኘት የሚያስችላት ስምምነት ላይ ለመድረስ ያለመችበት ውይይት ወደ ተጋጋለ ኃይለ ቃል ተቀይሮ፤ ትራምፕ «ስምምነት ላይ ትደርሳለህ አለዛ እኛ እንወጣለን» ሲሉ ለዜለንስኪን ነግረዋቸዋል። ስብሰባውን ተከትሎ ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክትም «ስምምነቱ ተዘርዟል» ሲሉ አስታውቀዋል። ትራምፕ በጹሑፋቸው «የአሜሪካ ተሳትፎ የሚቀጥል ከኾነ ፕሬዝደንት ዜለንስኪ ለሰላም ዝግጁ እንደማይሆን ወስኛለሁ። ምክንያቱም የኛ ተሳትፎ ለድርድር ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጠው ያምናል» ሲሉ ገልጸዋል። «ዩናይትድ ስቴትስን እና የፕሬዝደንቱን ኦቫል ኦፊስ' አላከበረም። ለሰላም ዝግጁ ሲኾን መመለስ ይችላል» ብለዋል ፕሬዝደንቱ። “ኦቫል ኦፊስ” በተሰኘው የፕሬዝደንቱ ጽሕፈት ቤት ውስጥ በርካታ አሜሪካውያን እና ዩክሬናውያን ጋዜጠኞች የተከታተሉት የተጋጋለ የቃላት ልውውጥ ወደ ኃይለ ቃል የተለወጠው ወደ 40ኛው ደቂቃ አካባቢ ዘለንስኪ ሩሲያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2014 ዓ.ም ክሬሚያን መውረሯን ባነሱበት ወቅት ነው። የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ጄዲ ቫንስ ወዲያውኑ ዜለንስኪን «የፕሮፓጋንዳ» ወሬዎችን መጠቀሚያ በማድረግ ተችተዋቸዋል። ቫንስ «ኦቫል ኦፊስ ውስጥ ኾኖ በአሜሪካ ሚዲያ ፊት ይህን ዐይነት ክስ ማንሳት ንቀት ነው» ነው ሲሉ ዜለንስኪን ተናግረዋቸዋል። ቫንስ እና ትራምፕ የዩክሬኑ መሪ ዋሽንግተን ለሀገራቸው ላደረገቸው ርዳታ አመስጋኝ አለመኾናቸውን ገልፀውም ወቅሰዋቸዋል። ዜለንስኪ ምላሽ ለመስጠት ቢሞክሩም ትራምፕ «ለመደራደሪያ የሚሆን አቅም እና ሥልጣን የለህም» በማለት አቋርጠዋቸው «በሚሊየን በሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ቁማር ትጫወታለህ። ከሦስተኛ ዓለም ጦርነት ጋራ ቁማር እየተጫወትክ ነው» ብለዋቸዋል። ዜለንስኪ በታቀደው መሠረት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሳይሳተፉ ቀደም ብለው ከዋይት ሐውስ ወጥተዋል። ውይይቱ በድንገት ከተጠናቀቀ በኋላ የዩክሬኑ መሪ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለአሜሪካ ሕዝብና መንግሥት መልዕት አስፍረዋል። ኤክስ በተሰኘው የማኅበራዊ ገጽ ላይ «አመሰግናለኹ አሜሪካ» ሲሉ የጻፉት ዜለንስኪ፣ « የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት፣ የምክር ቤት አባላትንና የአሜሪካን ሕዝብ እናመሰግናለን። ዩክሬን ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም ትፈልጋለች ፣ ያንን ለማግኘትም በሚገባ እየሠራን ነው» ብለዋል። የማዕድን ስምምነት ውይይቱ ከመጀመሩ በፊት ትራምፕ ከዜለንስኪ ጋራ ስምምነቱን ለመፈራረም መቃረባቸውን ገልጸው ነበር። ብዙም ምቾት እንዳልተሰማቸው ለሚያስታውቁት ዜለንስኪም «በጣም ፍትሃዊ የሆነ ስምምነት ነው ያለን፣ እናም ገብተን ለመቆፈር፣ ለመሥራት እና እነዛን ብርቅ የመሬት ማዕድናት ለማግኘት በጉጉት እንጠብቃለን » ብለዋቸው ነበር። ስምምነቱ ከጦርነቱ በኃላ ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት የሚውል የጋራ ባለቤትነት እና አስተዳደር ድንጋጌዎችን የሚያካትት ሲሆን፣ ዩክሬን ከተፈጥሮ ሀብቶቿ የምታገኘውን 50 ከመቶ የሀገሪቱን ገቢ ለዚህ ትመድባለች። ትራምፕ የማዕድን ስምምነቱን፣ ዩክሬን ከሩሲያ ጋራ የምታደርገው ጦርነት ካበቃ በኋላ በዩክሬን ውስጥ ለሚሰማሩ የአውሮፓ ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ለሚሰጡት የደህኅነት ማስተማመኛ፣ እንደ «ዋስትና» አድርገው ይገልጹታል። የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ግን ስምምነቱ እንዳልተፈረመ ገልጸዋል። Read more